27/08/2026
ከካንሰር ህመሟ ድና የመኖር ህልሟ እንዲቀጥል በሰፊው እርዳታዎች ቢሰሩም ጨካኙ ሞት ወጣቷን ነጥቆናል!
ይቺ የምታሳሳ ወጣት ኤል ሮኢን ትባላለች ። ከወራቶች በፊት ለማትረፍ ያልተረባረበ አልነበረም ከካንሰር ህመሟ ድና የመኖር ህልሟ እንዲቀጥል በሰፊው እርዳታዎች ቢሰሩም ጨካኙ ሞት ወጣቷን ነጥቆናል ኤልሮኢ አርፋለች።
በጣም ያሳዝናል በዚህ እድሜ ህይወቷ ማለፉ ለወዳጆቿ ለቤተሰቦቿ ትልቅ ህመም ነው። ግን መኖር አልተፈቀዳላትም ህይወቷ አልፏል ።
አሁን ላይ ካንሰር ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እየነጠቀን ነው ካንሰር በርትቷል ። እባካችሁ የካንሰር ህመም መነሻ ከሆነ ተግባራት ተቆጠቡ ጥንቃቄ አይለያችሁ ።ለቤተሰቦቿ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን እንመኛለን ። ነብሷን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን
ግዮን ማለዳ