
07/05/2025
የኢብራሂም ትራኦሬ ጠባቂ እንዲህ ይላል፦
ኢብራሂም ትራኦሬ ለአምላኩ ተንበርክኮ በሚጸልይበት ወቅት እንድመታው አምስት ሚሊዮን ዶላር አቀረቡልኝ። ከዚህም በላይ ለእኔና ለቤተሰቤ የዚያን ሀገር ዜግነት እንደሚሰጡን ቃል ገቡልኝ። ይህን ጥያቄ እንዴት እንደምቀበል ሳስብ ተገረምኩ። ለእነርሱ ገንዘብ ከሰው ልጅ ክብር በላይ ነው ማለት ነው።
ራሴን ጠየቅሁ… አምስት ሚሊዮን ዶላር የጥፋተኝነት ስሜቴን እስከ ዘላለም ድረስ ሊሸፍንልኝ ይችላል? ይህ ገንዘብ በባዕድ ሀገር ንጉሥ ያደርገኛል ወይስ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻቸው የሚሳለቁበት ሞኝ? በከተማቸው እንደ ውሻ ከመኖር በገዛ ምድሬ እንደ አንበሳ መኖር እመርጣለሁ!