14/08/2021
#ኢትዮጵያ
ወቶ-አደሩ ወገኔ
መርፌ ይመስል፣ጠጠር አሸዋው ከሚዋጋ፣
ያኔ በጀግንነትህ ከዚያ ዱር ስትጠጋ፣
ለሀገርህ በጦር አውድማ ስትዋጋ፣
ጋሻ በግራ ፣ጦር በቀኝ ይዘህ
በአውላላ ሜዳ ክፉኛ ተደፍተህ፣
እንዳሸለበህ ውለህ ያደርክ፣
እንዴት አድርክ፣
እንዴት ዋልክ፣
እንዴት ሰነበትክ፣
እንዴትስ ከረምክ፣
ዥጉርጉር ልብስህ በለይህ አልቆ፣
እጀጠባቡ ሰፊው ጥብቆ፣
ከጊዜ ብዛት ተበጫጭቆ፣
እርቃን የቀረህ ከዚያ ከጥሻ፣
ጀግናው ወቶ-አደር ጥቁር ሀበሻ፣
ስጋህ ብቻ ከጎድኑ ተቦጥቡጦ፣
በጭልፊትና በጆፌ ተውጦ፣
አፅምህ ብቻውን ተጋድሟል
በስተግራ ጋሻህ ወድቋል፣
በስተቀኝ ጦርህ ይታያል፣
ማንም አላየው፣
ከዚያው ዱር ከዚያው ከጥሻ ተረስቷል ፣
ለጀግንነትህ ለውድነትህ ብቻ አርማ ሆኗል።
"ክብር ለሚገባቸው ክብር መስጠት የታላቅነት ነው"
ረቂቅ መስፍን