Jara Travelers

Jara Travelers Welcome to Jara Travelers, an adventurous and culturally immersive traveling group based in Ethiopia'

  Itti aanaan Komishinara Komishinii Tuurizimii Oromiyaa Obbo Dawud Mumee Alii ganama har'aa balaa konkolaataatiin du'aa...
31/07/2025



Itti aanaan Komishinara Komishinii Tuurizimii Oromiyaa Obbo Dawud Mumee Alii ganama har'aa balaa konkolaataatiin du'aan addunyaa kanarraa boqotan.

Abbaa ijoollee afur kan ta'an Obbo Dawud Mume, Hoggansa kutannoo qabuu fi guddina damee ikootuurizimii naannichaa keessatti nama adda duree ijoo turan. dhaabbilee kunuunsaa qabbeenyaa umamaa fi turizimii waliin walqabatan waliin hojjachudhan ogeessa muuxannoo waggoota dheeraa qaban keessa tuuran. Hojiiwwan guddina damee ikootuurizimii fi kunuunsa qabbeenya uumamaa Oromiyaa irrati hojjetaniin dhiibbaa waaraa taasiisan.

Miseensoonni imaltoota Jaarraa (Jara Travelers) du'a tasa Obo Dawud Mumeen gadda guddaa nutti dhaga'ame ibsachaa; Maati isaaniif, hiriyoota fi waahillan isaanif, akkasumaas qooda fudhattoota turizimii Oromiyaa hundaaf Rabbiin obsa fi jajjabiina akka kennuf haawwiina.

Lubbuun isaani nagaan haa boqottu!

#የሐዘንመግለጫ
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ኦቦ ዳውድ ሙሜ አሊ ዛሬ ጠዋት ባገጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

የአራት ልጆች አባት የሆኑት ኦቦ ዳውድ ሙሜ ከተፈጥሮ ጥበቃና ቱሪዝም ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ተቋማት ጋር ለረጅም አመት የሰሩ አንጋፋ ባለሙያ ሲሆኑ፤ በክልሉ ውስጥ የኢኮቱሪዝም ዘርፉን በማሳደግ ረገድ ቁርጠኛ ባለሙያ እና ቁልፍ መሪም ነበሩ። በኦሮሚያ ኢኮ-ቱሪዝም ዘርፍ እድገት እና በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ በሠሯቸው ያላሰለሰ ሥራዎች በዘርፉ ዘላቂ ተፅዕኖን መፍጠር ችለዋል።

የJara Travelers አባላት በኦቦ ዳውዱ ሙሜ ድንገተኛ ህልፈት የተሠማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን፤ ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሙያ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው ቱሪዝም ባለ ድርሻ አካላት ፈጣሪ የልብ መፅናናትን እንዲሠጣቸው እንመኛለን።

ነፍሳቸው በዘላለማዊ ሠላም ትረፍ!

ዝነኛው  #የአርሲ ሴቶች ሙዚቃ  #አሾአሺላ  ይህ የሙዚቃ አይነት  #ሴቶች ብቻ የሚታደሙበት ረጋ ያለና ሁለት አይነት ዜማዎችን ያቀፈ ሙዚቃ ሲሆን ሴቶች ያለ እድሜ ገደብ ይሳተፉበታል። በእዚ...
16/07/2025

ዝነኛው #የአርሲ ሴቶች ሙዚቃ #አሾአሺላ

ይህ የሙዚቃ አይነት #ሴቶች ብቻ የሚታደሙበት ረጋ ያለና ሁለት አይነት ዜማዎችን ያቀፈ ሙዚቃ ሲሆን ሴቶች ያለ እድሜ ገደብ ይሳተፉበታል። በእዚህ ሙዚቃ ወቅት ሴቶቹ በቡድን በመሆን ወደ ፊት እና ወደ ኋላ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ ረጋ በማለት እየተንቀሳቀሱ የሚዘፍኑ ሲሆን ሌላ ሰውነታቸውን መነቅነቅ እና መዝለል የሙዚቃው ህግ አይፈቅድም።

በእዚህ ሙዚቃ የተለያዩ ማህበራዊ ሁኔታዎች ይዳሰሳሉ። በተለይ ከቤት ውስጥ ስራ በተጨማሪ ከቤት ወጥተውም ወንዱንም በጉልበት ስራ ስለሚያግዙ የውስጡንም የውጭውንም የህይወት ውጣ ውረድ በእዚህ ሙዚቃ ይዳስሱበታል። ስለ ከብቶች እና ስለ አካባቢው ደንብ እና ስርዓቶች በሰፊው የሚዳሰስ ሲሆን በይበልጥ ደግሞ #ሰርግ ላይ የወንዱ ቤተሰቦች ሙሽራውን የሚያወዱሱበት ሁኔታ ሰፊ ቦታ ይይዛል።

Hin fuutu jettee o'odeessitee
Hamattuun garaa nu bobeessitee
Hamattuun sunuu eda duutehoo
Aamme Aayyiyyoo baga fuutehoo.

የአርሲ ሴቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ #ከብቶቻቸው መዝፈን የሚወዱ ሲሆን #የአሾአሺላ #ግጥሞች ውስጥም ከብቶቻቸውን የሚያወድሱበት ስንኞች እናገኛለን።

Ganamaa subii ganamaatii hoo
Uunshiyyoo fardoo falakaatii hoo
Warra faradoolleen maqaa qabduu
Dhangalaasi waanyoon si haa dhabduu...

ታድያ በእዚህ ሙዚቃ ውስጥ #የፍቅር እና ሌሎች ፆታዊ ጉዳዮች የማይነሱ ቢሆንም በአንድ ወቅት #የአርሲ #ወንዶች ዘፈኑ #ፆታዊ #ስሜቶችን የሚያነሳሳ ስለሆነ ይታገድልን ብለው ታዋቂ #የአርሲ #ሼህ ጋር ሄዱ ይባላል። እኚህ ታዋቂ የአርሲ ሼኽም ሴቶቹን አስመጥተው የዘፈኑን ግጥም ከመረመሩ በኋላ የሙዚቃው ግጥሞች ውስጥ ምንም #መጥፎ ነገር ባለማግኘታቸው እንዲዘፍኑ ፈቀዱላቸው ይባላል። ለእዛ ነው የአሾአሺላ ዘፈን ውስጥ ይሄን ግጥም ደጋግመን የምንሰማው

Ashoo ashilaa jette beerilleen
Haa jedhan dhiisaa jedhan sheeknilleen...

Intala warra ee marroolee hoo
Si eegdoo algaan ala ooleehoo
Algaan ala oole sun boonumaa
Ka fardaan duchiisan sun loonumaa

.


#አርሲ ❤

Jara Travelers

 #ሲኮ እና  #መንዶዎቹ የአርሲ ልጆች  #ላንጋኖ  #አርዳ  #ጂላ  #ጉታ ላይ ተገናኝተው  #ጊንር   ላይ ለሚያደርጉት ለዋናው የገዳ ስልጣን ሽግግር ቅደመ ሁኔታዎችን እያመቻቹ ይገኛሉ። ይ...
15/07/2025

#ሲኮ እና #መንዶዎቹ የአርሲ ልጆች #ላንጋኖ #አርዳ #ጂላ #ጉታ ላይ ተገናኝተው #ጊንር ላይ ለሚያደርጉት ለዋናው የገዳ ስልጣን ሽግግር ቅደመ ሁኔታዎችን እያመቻቹ ይገኛሉ። ይህ ቅድመ ዝግጅት yaa'ii (yaa'a) ተብሎ የሚጠራና በ 8 አመት አንዴ የሚደረግ ሲሆን #የአርሲ ጎሳ ሁሉ ቦታው ላይ ተገናኝቶ የሚተያይበት፣ መኖሩን የሚያሳውቅበት እና 'ራሱን የሚያስተዋውቅበት፣ የዋናውን ስልጣን ርክክብ ቀን እና ሁኔታ የሚወስንበት፣ የተበላሹ ህግ እና ስርዓቶች የሚስተካከሉበት አዳዲስ ህግጋቶች የሚፀድቁበት፣ የጋብቻ እና #ጉማ ስርዓቱን የሚፈትሽበት፣ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት የሚያስጠብቅበት፣ የተጣላ እና የተበዳደለ ይቅር የሚባባልበት ትልቅ ባህላዊ ፕሮግራም ሲሆን ይሄ ሁሉ የሚደረገው #አርሲ ውስጥ በስፋት በሚታወቀው በ (አንተም ና እኔም ልምጣ) #ስርዓት ነው።

Jara Travelers

26/06/2025



ባለውብ ቀለማት ወፎች የሚወጡበት እና ፈገግ ያለ የመሬት ገፅታ የሚታይበት ስፍራ!አቢጃታ-ሻላ ሃይቆች ብሄራዊ ፓርክ - በኦሮሚያ ምዕራብ አርሲ ዞን ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 200 ኪሎ ሜትር ...
25/06/2025

ባለውብ ቀለማት ወፎች የሚወጡበት እና ፈገግ ያለ የመሬት ገፅታ የሚታይበት ስፍራ!

አቢጃታ-ሻላ ሃይቆች ብሄራዊ ፓርክ - በኦሮሚያ ምዕራብ አርሲ ዞን ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያለ አስደናቂ ቦታ ነው። ከ400 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች መኖሪያ፣ከአፍሪካ ምርጥ የአእዋፍ መዳረሻዎች መሃል አንዱ ነው።

የአእዋፋቱና የሐይቆቹ ጥምረት ሰማዩንም ዳርቻዎቹንም በቀለማት ደምቀው እንዲታዩ ያደርጋቸዋል። እሳተ ገሞራ የፈጠራቸው ኮረብታዎች፣ ነጫጭ ጨዋማ የባህር ዳርቻዎች፣ የፍልውሃና የእንፋሎት ፍልቅልቅ ምንጮች እና ሶስቱ አስማታዊ ሀይቆች በአንድነት ፖርኩን የተፈጥሮ ውበቶች መሰባሠቢያ ስፍራ ያደርጉታል።

🦩 አቢጃታ እና ሻላ ሀይቆች ፦አንደኛው ጥልቀት የሌለውና ሮዝ ፍላሚንጎዎችን የሚመግብ፣ ሌላኛው ደሞ ጥልቀት ያለው እና የተቀደሰ ከፔሊካኖች መኖሪያ ደሴቶች ጋር። በ3ኪ.ሜ ርቀት አንድ ላይ ሲሆኑ የፓርኩን ውበት ህይወት ይዘሩበታል።

🪶 የአእዋፍ ህይወት እና የዱር አራዊት ፦ እንደ ጥቁር ክንፍ ያላቸው የፍቅር ወፎች፣ Cliff Chat ወፎች፣ Barbets፣ Herons እና የStarling ያሉ ብርቅዬ እና እንግዳ የሆኑ የአዕዋፍ ዝርያዎች ተደባልቀው ይገኛሉ። በፓርኩ የሚገኙ እንደ ከርከሮዎች፣ የቆላ አጋዘን፣ ዱኩላዎች፣ የሜዳ ፍየሎች፣ ዝንጀሮዎች፣ ኮሎበስ ጦጣዎች እና የማይረብሹ የሰጎን እርምጃዎች የፓርኩን ውበት እጥፍ ድርብ ያደርጉታል።

⚠️ በአሁኑ ወቅት ለፓርኩ የህልውና አደጋ የሆኑ ድርጊቶች : የደን ጭፍጨፋ፣ ከሰል ማክሠል እና በህገ ወጥ መንገድ የጨው ማውጣት ሲሆኑ
የአእዋፉም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ በመሆኑ ዝምታው እየጨመረ ነው።
መፍትሄ: የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ለአካባቢው ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠርና በማሳተፍ እና አሁን ካለው በተጨማሪ ጥብቅ የጥበቃ እና የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት፤ የዚህን ድንቅ ፣ያልተነካ የቱሪዝም ሃብት ህልውና መጠበቅ ይገባል።
Jara Travelers

24/06/2025

Tourism and Technology Forum

𝐓𝐡𝐞 𝐃𝐮𝐛𝐛𝐞 𝐚𝐧𝐝 𝐐𝐨𝐫𝐨𝐬𝐨 𝐨𝐟 𝐁𝐚𝐭𝐮The town of Batu is blessed with a fresh supply of tasty fish from its backyard Lake Dambal....
22/06/2025

𝐓𝐡𝐞 𝐃𝐮𝐛𝐛𝐞 𝐚𝐧𝐝 𝐐𝐨𝐫𝐨𝐬𝐨 𝐨𝐟 𝐁𝐚𝐭𝐮
The town of Batu is blessed with a fresh supply of tasty fish from its backyard Lake Dambal. Batu also boasts a slew of artisan cooks who have perfected the art of frying the Qoroso and Dubbe fish types to crisp perfection. It is the coming together of this artisanal knowledge and the fresh ingredients that makes for a seriously mouth watering experience. Add in the fact that the fish are caught sustainably and the prices they go for is very reasonable and you have an experience you should not skip if you're ever in Batu
✍️ Meti Sorecha



Jara Travelers

    IJA Developers Jara Travelers
22/06/2025




IJA Developers
Jara Travelers

22/06/2025

Lake Langano

Imala Shaallaa fi Abijaataa      IJA Developers Jara Travelers
21/06/2025

Imala Shaallaa fi Abijaataa




IJA Developers
Jara Travelers

Hiriyoota kudha jaha, miidiyaa hawaasaa irratti wal beekan walitti qabamanii gara Salaalee imaluudhaan: riqicha seena qa...
20/06/2025

Hiriyoota kudha jaha, miidiyaa hawaasaa irratti wal beekan walitti qabamanii gara Salaalee imaluudhaan: riqicha seena qabeessa Salaalee fi aannan Salaalee waliin wal nu barsiisan, suuraawwan babbareedoo nutti agarsiisan imalli isaanii fudhatamummaa waan argateef, waan kana cimsuuf imala biraa gochuuf karoorfatan
Jaarraa Tiraavilars haala kanaan karoorfame.

Ji'a lama booda, hiriyoota biroo fedhii seenaa qorachuu, aadaa isaanii baruu fi barsiisuu, uumama dinqisiifachuu qaban dabalanii, Finfinnee naannoo Meeksiikootti walitti qabamanii imala lammaffaa gara haroo wanciitti godhan.
Waggaa lamaan har'a imala lammaffaa gara ganda tuurizimii Wanciitti godhamee irratti
Jaarraa Tiraavilars dhalate✨

Sana booda dabaree dabreedhaan Oromiyaa bahaa, kaabaa, kibbaa, dhihaan naanna'uudhaan aadaa, seenaa fi duudhaalee ummata Oromoo fi qabeenya uumamaa fi namtolchee Oromiyaan qabdu baruu fi qorachuun adduunyaatti barruuwwan keenyaan beeksiisaa, waggaa lama lakkoofsiisne. Waggaa lama keessatti ayyaanotaa fi taateewwan aadaa, afuuraa, seenaa, akkasumas daawwannaa hawwata uumamaa 25 ol ta'an irratti hirmaatanii jiru;
Kana boodas, aadaa fi duudhaalee Oromiyaa fi kutaalee biyyattii garaagaraatti imaluudhaan iddoowwan haawwata tuurizimiis wal barsiisaa itti fufna.

Maatii Jaarraa
Baga hundeeffama waggaa 2ffaa Jaarraa Tiraavilars geenye.
Jara Travelers

Address

Addis Ababa

Telephone

+251976004444

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jara Travelers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Jara Travelers:

Share

Category