Visit Tora

Visit Tora Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit Tora, Tourist Information Center, Torra, Addis Ababa.

ተጨባጭ ለውጥ እያየን ስለሆነ እናመሰግናለን ክቡር ከንቲባውና አመራራቸው የተጀመሩ ለውጦችን አጠናክረው ማስቀጠል አለባቸው ህዝቡም ከጎን መደገፍ ይኖርበታል።
12/06/2026

ተጨባጭ ለውጥ እያየን ስለሆነ እናመሰግናለን ክቡር ከንቲባውና አመራራቸው የተጀመሩ ለውጦችን አጠናክረው ማስቀጠል አለባቸው ህዝቡም ከጎን መደገፍ ይኖርበታል።

የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሂደት ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የምስጋና መርሃ ግብር እንዲሁም በሂደቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ጉድለቶች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጦራ ከተማ አስተዳ...
05/06/2026

የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሂደት ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የምስጋና መርሃ ግብር እንዲሁም በሂደቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ጉድለቶች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጦራ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ !

ግንቦት 28/2018 [ ጦራ ኮሙዩኒኬሽን ]

በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ሲካሄድ የቆየው የ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን ተከትሎ የምስጋና ፣ በሂደቱ ላይ የታዩ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች የግምገማ እና ቀጣይ በሚከናወኑ የልማት ተግባራት ላይ የዉይይት መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩን የጦራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ካሚል አማን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት ሲሆን የክልል ፣ የዞን ደጋፊ አመራሮች የከተማው፣ የቀበሌዎች አመራሮች እና ማህበረሰቡ በቅንጅት ፣ በመናበብ የሰሩት የቅድመ ዝግጅትና የክትትል ስራ ለምርጫው ስኬታማነት ጉልህ ሚና ማበርከቱን ተናግረዋል።

ምርጫዉ በስኬት እንዲጠናቀቅ አጋዥ ለነበሩ ታዛቢዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የከተማችን ነጋዴዎች ፣ወጣቶችና ሴቶች ፣የሃይማኖት አባቶች ና የሀገር ሽማግሌዎች፣ መምህራን ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ የሲቪል ሰርቪስ ባለሙያዎች ፣ ለሁላዘር የባህል ቡድን ፣ የሚድያ ባለሙያዎች ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ብርድና ፀሀይ ሳይበግረዉ በድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ የማህበረሰብ ክፍሎች አቶ ካሚል አማን በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

ከንቲባው አክለውም በምርጫ ስራ ወቅት የነበረንን ቁርጠኝነት ይዘን ፊታችንን ወደ ልማት በማቅናት
ጦራ ከተማን ለነዋሪዎቿ ፅዱ ፣ ውብ ፣ ተስማሚ ፣ ንፁህ በማድረግ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለቅመን ለመፍታት ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል ።

የጦራ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ደኑር ኮሪ በበኩላቸው እያንዳንዱ ዜጋ ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ምርጫዉን በስኬት ማጠናቀቁን በመግለጽ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የዲሞክራሲ ባህልን አንድ እርምጃ ወደፊት ያሻገረ መሆኑን አብራርተዋል።

ምርጫዉ የአመራር መናበብና ቅንጅት የታየበት እንደነበር የገለጹት አቶ ደኑር ኮሪ ለጋራ ዓላማ በጽናት ከቆምን የማይሳካ ጉዳይ እንደሌለ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

የስልጤ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ ፈቱ ኪምባዶ በበኩላቸው የከተማው ማህበረሰብ ያሳየው ከፍተኛ የነቃ ተሳትፎና የጸጥታው አስተማማኝነት ትልቅ ስኬት እንደሆነ የገለፁ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ሊደገም እንደሚገባ አመላክተው መላው ህብረተሰብ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የቡናና ቅመማ ቅመም ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተውፊቅ ጁኃር በበኩላቸው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱ ታሪካዊ እንደነበር በመጥቀስ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተደረገው የተቀናጀ ስራ በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ትልቅ አቅምና ጠንካራ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን አንስተው ፣ በቀጣይም ሌሎች የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ለይቶ በትጋት መስራት እንዳለብን አንስተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ህዝቡ በምርጫው ወቅት ያሳየውን ህብረትና መነሳሳት ወደ ልማት በመቀየር የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ግብርና ቢሮ የቡናና ቅመማ ቅመም ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተውፊቅ ጁኃር ፣ የስልጤ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ ፈቱ ኢምባዶ ፣የጦራ ከተማ አስተዳደር

ይነይ ፈረዝ ደነክ ምን ኢሉያን?
14/04/2026

ይነይ ፈረዝ ደነክ ምን ኢሉያን?

በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ትልቁ መስጊድ (አቡበከር መስጂድ)
08/04/2026

በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ትልቁ መስጊድ (አቡበከር መስጂድ)

በጦራ ከተማ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች መርቶ ለገበያ የቀረበው አዱካሌ አጃክስ ሳሙና በተጠቃሚዎች ዘንድ እጅግ ተፈላጊ መሆን ችሏል።በከተማችን መፍጠር የሚችሉ ኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ መሆኗ የተ...
06/04/2026

በጦራ ከተማ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች መርቶ ለገበያ የቀረበው አዱካሌ አጃክስ ሳሙና በተጠቃሚዎች ዘንድ እጅግ ተፈላጊ መሆን ችሏል።

በከተማችን መፍጠር የሚችሉ ኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ መሆኗ የተረጋገጠበት በመሆኑ ይህም የጦራ ከተማ ልዩ መገለጫ እየሆነ ነው!!

Address

Torra
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Tora posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share