Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም

Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም, Historical Tour Agency, Ethiopia, Addis Ababa.
(2)

☸️የጉራጌና የከንባታ ባላባቶች አቤቱታ🔯►►►►►►►►►►►►►►►►►►► #በዚያ ወራት የሹም ሽሩ ሥራ ሁሉ ካለቀ በኋላ አንድ ቀን ወደ ምኒስትሮች ክፍል የምክር ቤት ስለተጠራሁ ሄድሁ፤ እንደኔ...
11/01/2026

☸️የጉራጌና የከንባታ ባላባቶች አቤቱታ🔯
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#በዚያ ወራት የሹም ሽሩ ሥራ ሁሉ ካለቀ በኋላ አንድ ቀን ወደ ምኒስትሮች ክፍል የምክር ቤት ስለተጠራሁ ሄድሁ፤ እንደኔውም ምኒስትሮች ያልሆኑ ሌሎችም ጥቂቶች
መኳንንት ነበሩ ፤ ከምኒስትሮቹም ጋር ወደ አስራምስቱ እንሆን ነበር፡፡ ወደ እተዘጋጀውም ስፍራ ገብተን እንደተቀመጥን ጸሐፌ ትዕዛዝ ወልደ መስቀል የተጠራንበትንና የተሰበሰብንበትን ጉዳይ በዝርዝሩ አመለከቱ፡፡

#ነገሩም #በጉራጌና #በከንባታ ወገን ያለው አገር ባላባቶች ባንድነት ሆነው አቤቱታ ላስታወቁት ጉዳይ ነበረ፡፡ቃሉም ‹‹እንደመሬቱ መጠን ለመልከኛውና ለሻለቃው የሚከፍለው የገባሩ ግብር ጥንት #ትንሽ ነበር፡፡ በየጊዜው የሚለዋወጠው የሻለቃ ሁሉ ግን አንዳንድ ነገር እየጨመረ ግብሩን ሁሉ #አሳድጐብን አሁን ብዙው ገባር #መገበር አቅቶት መሬቱን እየተወ #ተሰደደ፡፡ የዚያንም የተሰደደውን ገባር ግብር፣ እኛን #ባላባቶቹን #የግድ ገብሩ ብለው ያዙን፡፡የተሰደደው ገባር እየመኳንንቱ #የወላስማና #የጉልት መሬት ነው የገባው፡፡ይኸውም የወላስማና የጉልት መሬት የመንግሥት ግብር ብዙ ስለሌለበት እየተስማማ እየሄደ እርቦ አራሽ ሆነ፡፡ ለሄደውና ለሚሄደው ሁሉ #የስንቱን ገባር #ጠፍ መሬት ገብረን እንዘልቀዋለን፡፡ የሄደውንም ገባር ከሄደበት ተከታትለን እያወጣን በግድ ለመመለስ አንችልም፤ ባለጉልቱም ይከለክለናል፡፡ ስለዚህ አጥብቀን ተቸግረናልና፤ጠፉን መሬት ቢፈልጉ ገባሩ ጥሎት የሄደውን እናስረክባለን፡፡ በሄደው ገብሩ ተብለን እንዳንያዝ ደግሞም አሁን ያለውም ጨርሶ እንዳይጠፋ በየጊዜው የሻለቃና መልከኛ ያሳደገውና የጨመረው ግብር እንዲፋቅልን እናመለክታለን፤» ብለው በየጊዜው የተጨመረውንም ግብር በዝርዝሩ አጽፈው የሰጡትን ደጋግመው አንበው «ይኸን እንድታስቡበትና እንድትመክሩበት! ስለዚሁም የወሰናችሁትን እንዳውቀው ብለዋል ጃንሆይ» ብለው አመለከቱን፡፡

#ነገሩን ሰምተን ጥቂት ዝምታ ከሆነ በኋላ አንዳንዶች መኳንንት መናገር ጀመሩ፡፡ እነሱም የበላተኛውን ወገን፣ የመልከኛና የሺአለቃውን አበል ለመንካት የተጨመረውንም ግብር ዝቅ ለማድረግ እጅግ ፈርተው መልከኛው ደግሞ
አበላችንን ከለከላችሁ ብሎ ይነሳብናል! የሚያስቸግር ነገር ነው» እያሉ ተናገሩ፡፡ደግሞ ጥቂቶቹም፣ «መሬቱን እየለቀቀ የሚሄደውን ገባር ያው መልከኛው እየፈለገ እየተከታተለ እየያዘ ይመልሰውና ያስገብረው! በያንዳንዱ አገርስ እንደዚሁ ያለ ደንብ አለ የለሞይ፡፡ በንደዚህ ያለው ባላባት መያዙ ይቅር» አሉ፡፡

#እኔም በተራዬ ሁሉንም ካዳመጥኩ በኋላ ነገሬን ስጀምር ሁሉም ዝም ብለው አዳመጡኝ፡፡ የተናገርኩትም #በሐረርጌ ወገን ያለው ገባር አስተዳደሩ ከዚህ ከተነገረው ልዩነት ስላለው መጀመሪያ የዚያን አኳሆን ነበር፡፡ ‹‹በሐረርጌ ገባር መሬቱን ጥሎ ቢሄድ መልከኛው እራሱ መሬቱን ቢያርሰው ወይም ለሌላም አራሽ አጋዝቶም ቢሆን የሚገኘውን (ይበላል) ይወስዳል እንጂ ገባር አልችልም ካለ እንኳን ተሰዶና እዚያውም አገር ላገር አስታውቆ ለቆ ቢቀመጥ የሚነካው የለም፡፡ የተወሰነውም ዓመት ሳይደርስ እንኳን ወደ መሬቱ ለመመለስ ፈልጐ በፈቃዱ ቢመለስ ገብቶ አለችግር መያዝ
ይችላል፡፡ስለዚህ ሰው የሚገብረው ለኑሮውና ለትዳሩ ሲል መሬት ይዞ፣ ቤት ሰርቶ፣ሚስት አግብቶ፣ ልጅ ወልዶ፣ ለተቀመጠበት እንጂ! የማይችለውን ዕዳ ሊከፍልበት
አደለም፡፡ ደግሞስ ይኸንኑ መሬቱን ዕዳውን አልችልም ብሎ ደህይቶ ቢሰደድ የግድ እየተፈለገ የሚያዘው ምን ባደረገ ነው? እስኪ እራሳችን እናስበው፡፡ ሰው የሚወደውን
ቤቱን፣ እኖርበታለሁ ያለውን እርስቱን፣ እንዲኖር የሚረዳውና የሚደግፈው ዳኛ በማጣት ይኸው በየጊዜው የተጨመረበትንና ያደገበትን ጽፎ አቅርቦልን እናያለን፡፡ይኸን ያለ መንግሥት ፈቃድ የተጨመረውን ለመቀነስና ለማሻሻል መከራ መስሎ ይታያችኋል፡፡ በላተኛውን በመፍራት ከዚህ ለማዳን የማይቻል ሲመስላችሁ ድኃውን ከተሰደደበት አብርሮ መያዝና የግድ ገብር ማለት ትልቅ የግፍ ግፍ ነው» ብዬ «ይልቅስ እኔ አሳቤን ላመለክታችሁ የምሻው ከተናገርኩ በስተኋላ ቀጥዬ፣ እውነተኛው ነገር፣ ለመንግሥቱም ሆነ ለባላገሩ ታላቅ እንቅፋት ሆነን ለማሻሻል፤ያስቸገርነው፣ እኛና እኛን የመሰለው ሹማምንት ሁሉ ነን፡፡ ምክንያቱም ከመንግሥት ደሞዝ እንቀበላለን፡፡ አገርም እየገዛን የገባሩን ግብር እንወስዳለን፡፡ ደግሞም በዚሁ ላይ ብዙ ሰፋፊ መሬት እርስት እያልን እየያዝን መቶውን ጋሻ ባምስት ሸማ፣ አምሳውን
ጋሻ በሦስት ጉንዶ ማር፣ እየሆነ ብዙውን ሰፋፊ መሬት ሁሉ ያለ ግብር ይዘን እያወክን ባንድ ወገን በዚህ አኳሆን የመሬቱ ግብር ሁሉ እየጐደለ፣ በሌላው ወገን ደግሞ በገባሩ ላይ በመጨመሩ ሊኖር አቃተው፡፡በሌላው መፍረድ እንድንችል እስቲ መጀመሪያ በራሳችን እንፍረድ፡፡ ሌላው ነገር እንኳን ለጊዜው ቢቆይ እርስት ብለን ያለ ደንበኛው ግብር የያዝነውን መሬት እንደድኃው ገባር ልክ በያንዳንዱ ጋሻ ግብሩን ተካክለን እንገብር፡፡ ይኸንኑም ብናደርግ ከባላገሩ ላይ የከበደውን ታላቅ የግብር ሸክም መቀነስና ማቅለል ይቻላል፡፡ ገባሩም ግብሩ ከቀለለለት በመሬቱ መኖር ይችላል፡፡ ደግሞ በየጊዜው በየሻለቃው ምክንያት እንዳይጨመር መንግሥቱ የሚጠበቅበትን ደንብ ከሰራለት መሬቱን ለቆ የሚሄድ ገባር
ምንም ያህል አይገኝም፡፡ ግብሩም በሚሄድበት ስፍራ ሁሉ ተመሳሳይ ስለሆነ ይኸ የቀረበልን ነገር ትልቅ ነው፡፡ ዳር አገር በተባለው አገር ሁሉ ባላገሩ አቅም እያነሰው ነው እንጂ በዚህ በቀረበው አቤቱታ አይነት ወሬውን እንደምንሰማው ያልደኸየና
ያልተቸገረ አገር አይገኝም፡፡ ይኸውም በብርታት ቶሎ የሚድንበት ነገር ካልተሰራ፣ይኸ አሁን የተፈራው በላተኛ አገሩን ፈጽሞ ካደኸየ በኋላ የሚበላው ሲያጣ እንደገና
መንግሥቱን እያስቸገረ የከፋ ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ አሁን እንኳን የተመቻቸው ሹማምንት አገር ሲለምኑ፤ 'ይኸ ያልተበላ አገር ነውና ስጡን' ይላሉ ይባላል››፡፡ ብዬ ነገሬን ጨረስኩ፡፡

#እዚያም ከነበሩት አንዳንድ ትልልቆች መኳንንት አዎ «ያዳሜን እርስት ሁሉ ልትነቅል፤ የማይሆነውን ነገር» እያሉ አንድ ጊዜ ነገራቸውን አወረዱብኝ፡፡ከልጅ እግሮቹ ወገን ግን አንዳንዶቹ ምንም ቢያንሱ፤ የኔኑ አይነት አሳብ የመሰለውን ተናገሩ፡፡ በዚሁ ስንጨቃጨቅ ያንለት ሰዓቱ ደርሶ ተለያየን፡፡ ሁለተኛም በዚህ ነገር የተነጋገርንበትንና የተፈጸመ እኔ የማውቀው የለም፡፡ እንደመሰለኝም ላቤት ባዮቹ መልስ ያህል ምንአልባት ጥቂት ነገር ያደረጉላቸው ይኖር ይሆናል፡፡

📌ካየሁትናከማስታውሰው፤ራስእምሩኃይለሥላሴ፤180-2
****

►ከዚህ ክስተት መገንዘብ እንደሚቻለው የኢትዮጵያ ገባሮች በምን ደረጃ ይጨቆኑና ይበዘበዙ እንደነበረ ነው። ትላልቆቹ መሣፍንት እና መኳንንቶች ለገባሮቻቸው ያላቸው ሀዘኔታ በእጅጉ ያነሰ እንደሆነ በወቅቱ ከፍተኛ መሣፍንት የነበሩትና የግርማዊ ጃንሆይ የቅርብ ዘመድ ከሆኑት ራስ እምሩ በላይ ምስክር የለም።ልዑል ራስ እምሩ ከመሣፍንቶች በሙሉ በተራማጅነታቸው የሚጠቀሱበትና ከደርግ ጅምላ ግድያ የተረፉበት ዋነኛ ምክንያት ይኸው ማንነታቸው ነው።

 #የሀላባ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ  #ሴራ በዓል በአዲሱ  🏟️ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡📸HalabaTv
11/01/2026

#የሀላባ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ #ሴራ በዓል በአዲሱ 🏟️ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡

📸HalabaTv

 #የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች፦►ኮ/ል ስምረት መድኃኔ(ቀኝ)፤የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና ስራ አስኪያጅ►አቶ ግርማ ዋቄ(ግራ)፤ካሁኑና ከዚህ ቀደም ከነበሩት አቶ ተወልደ በፊት የነበሩ ...
11/01/2026

#የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች፦

►ኮ/ል ስምረት መድኃኔ(ቀኝ)፤የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና ስራ አስኪያጅ
►አቶ ግርማ ዋቄ(ግራ)፤ካሁኑና ከዚህ ቀደም ከነበሩት አቶ ተወልደ በፊት የነበሩ ስራ አስኪያጅ፤
►አቶ መስፍን ጣሰው(መሃል)፤ያሁኑ ስራ አስኪያጅ

📸2-ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ ከጀኔራል መርዕድ መንገሻ ጀርባ በቀኝ የቆሙት ናቸው።

☸️አሰብ ሰላምና ልማት፣ የቀይ ባህር አፋሮች ኢትዮጵያዊነት►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► #የልማት ሊቃውንት ለአንድ አገር መበልጸግ በአገሩ ሰረጅምዓመታት የሰላም መስፈን አስፈላጊ...
11/01/2026

☸️አሰብ ሰላምና ልማት፣ የቀይ ባህር አፋሮች ኢትዮጵያዊነት
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#የልማት ሊቃውንት ለአንድ አገር መበልጸግ በአገሩ ሰረጅም
ዓመታት የሰላም መስፈን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን
ይገልጻሉ። ለልማት ሊውሉ የሚችሉ ግብዓቶች እንደልብ ቢገኙ ሰላምና መረጋጋት ከሌለ ልማትና ብልጽግና ሊኖር እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሳያቋርጥ ተያይዞ ለረጅም ዓመታት ይቅርና ለአምሳ ዓመታት እንኳን ሰላም አጣጥማ እንደማታውቅና ለዚህ ኢትዮጵያ ለተጫናት ድህነት ከዋናዎቹ ምክንያቶች አንዱ ከጦርነት አዙሪት መውጣት አለመቻሏ መሆኑን የታሪክ ምሁራን ይነግሩናል፡፡

#የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ሌሎችም በኢትዮጵያ
ለሰላም መደፍረስና ለግጭት መንስኤዎች የአባይ ወንዝ ውሀ
ፍትሐዊ አጠቃቀምና የኢትዮጵያ የባህር በር በተለይም የአሰብ
ባለቤትነት ጉዳይ እንደሚሆን ሳያመነቱ ይናገራሉ፡፡ በኘሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እይታ ኢትዮጵያ በራስዋ ወደብ አድርጋ ወደ ባህር የመዝለቅ መብት በሰላም መፍትሔ ካልተሰጠው ወደ ፊት ብሔራዊ ስሜት ያለው መንግሥት መንበሩን ሲይዝ አሰብ ለጦርነት መንስኤ እንደምትሆን አያጠራጥርም ይላሉ፡፡ይህንን አደገኛ ሁኔታ ለማስቀረት ለጋስ አገሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ድርድር መደረግ እንዳለበት ኘሮፌሰር ጌታቸው ያሳስባሉ።

#የድርድሩም ውጤት መሆን የሚገባውን አስብን አሰምንም
ቅድመ ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ሲሆን ይህም ወደፊት
ሊመጣ የሚችለውን የጦርነት መዓት ያስቀራል ይላሉ ኘሮፌሰር ጌታቸው፡፡ አያድርገውና ለወደፊቱ በኤርትራና በኢትዮጵያ መሃከል ግጭት ቢፈጠር መንስኤው የወሰን መከላከል ጉዳይ ሳይሆን በአሰብ ባለቤትነትና በአፋር ህዝብ አንድነት ላይ ያጠነጠነ እንደሚሆን የተለያዩ ምሁራን ያስገነዝባሉ፡፡ ኣቶ ኃይለ ሚካኤል ገብረአናንያ የፕሮፌሰር ጌታቸው አቋም በማጠናከር የሚከተለውን ብለዋል።

“የአሰብ ጉዳይ የተደፈነ እሳት ማለት ነው፡፡ አማራጭ እያለህ ዝም ብለህ የምታካሄደው ጦርነት (War of Choice) የምርጫ ጦርነት ሲሆን አሁን ያጋጠመን ግን ልንሸሽው የማንችል አስገዳጅ ጦርነት (War of necessity) ነው፡፡ ምርጫ የሌላት አገር አስገዳጅ ጦርነት ለማካሄድ ትገደዳለች፡፡"

#የኢትዮጵያና የኤርትራ ችግር አሁን የድምበር ብቻ
አይደለም፣ የመሬትም ጉዳይም አይደለም፤ ዋናው አንኳሩ የባህር ወዳብ ጉዳይ ነው፡፡ ሁላችንም ቁጭ ብለን ችግራችንን መፍታት ያለብን በተለይም ደግሞ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ይሄ ችግር መኖሩን አውቀው ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጋር በግልጽ መነጋገር አለባቸው።ምክንያቱም እነርሱም ወደ ሥልጣና የመ እንደሆነ ከእነርሱም ጋር
ጦርነት መግጠማችን አይቀርም፡፡ ኢሕአዴግ ካላደረገው ቀጥሎ የሚመጣው መንግሥት ይሄንን ጥያቄ እንደሚነሳና ኢሕአዴግንም እንደሚወቀስ አምናለሁ።

#አሰብ ጥንትም አሁንም የአንድ ብሔረሰብ የአንድ ኃይማኖት
ተከታይ የሆነውን ከጥንታዊቷ ከሉሲ (ድንቅነሽ) ብንጀምር
ምናልባት የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን መሬት ነች፡፡ በአፋሮች ዘንድ የኢትዮጵያ የኤርትራ አፋር የሚባል ነገር የለም፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል የተፈጠረው ክፍፍል አፋሮች በጽኑ ይቃወሙታል፡፡ የሃይማኖትና የዓለማዊ ጉዳዮች አላፊ የአሳይታው ሱልጣን ሲሆኑ እኚህ ሰው የአፋሮች ሁሉ አባትና መሪ ተደርገው የሚቆጠሩ ከቅርብ ሳምንታት በፊት ያረፋትና የጅቡቲው ጠቅላይ ሚኒስትር በክብር የቀበሩአቸው ቢትወዳድ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፋሬ ናቸው።

#ክቡር ቢትወደድ በአፄ ኃይለ ሥላሴ የአገዛዝ ዘመን የአውሳ (አሰብ) አውራጃ አስተዳደሪ ቢሆኑም ከሌሎች የኢትዮጵያ አውራጃ አስተዳዳሪዎች የተለየ ሥልጣንና ለንጉሠ ነገሥቱ ቀረቤታ ነበራቸው። የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥትም በአፋር ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም ነበር።አሰብ ምን ጊዜም በታሪካም ጭምር ከኤርትራ የተለየች ብትሆንም ጣልያኖች ከኤርትራ አካል በግድ ቢቀላቅልዋትም ምን ጊዜም ቢሆን ሕዝቡ የኤርትራ አካል መሆኑን አልተቀበለውም፡፡በኤርትራ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ የኤርትራዊነት ብሔራዊ ስሜት በአፋሮች ዘንድ አይታይም።

#ክቡር ቢትወደድ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሌሎችም የአፋር መሪዋች በተለያዩ ወቅቶች እንደገለፁት ኢትዮጵያዊነታቸውን አጥብቀው የያዙ ሕዝቦች ናቸው።ክቡር ቢትወደድ አሊ ሚራህ ለዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ በሰጡአቸው ቃለ ምልልስ እንዲህ ብለው ነበር፡፡

“የአፋር ሕዝብ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሩን ወዳድ ነው በታሪኩና በባህሉም ይኮራል። ኢትዮጵያዊነታችንም ማንም ሊነፍገን አይችልም የአፋር ሕዝብ ጠላቶች ብቻ ናቸው አፋርን የተለየች አድርገው የሚቆጥሩት፡፡ እነኚህ ጸረ ሕዝቦችን እናጋልጣቸዋለን።ይኸም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲባል መደረግ አለበት”፡፡

#እንዲሁም ክቡር ቢትወደድ አሊ ሚራህ በሐምሌ ወር 1983 ዓ.ም ኢሕአዴግ የሽግግር መንግሥት ለማደራጀት በጠራው ጉባዔ ላይ ተገኝተው አቶ መለስና አቶ ኢሣያስ ባሉበት “የአፋር ሕዝብ ወሰን ቀይ ባህር ነው፡፡ ግመሎቻችን እንኳን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቁአታል” ብለው ነበር”። እንዲሁም በሽግግሩ ቻርተር ስብሰባ ላይ ለቀድሞው ቺፍ አቭ ስታፍ ሌተና ጀኔራል ጻድቃን ገብር ትንሣኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ የቀይ ባህር አፋሮች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወሰኑ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው እንደ ነበር ጀኔራል አበበ በጽሁፋቸው ገልጸውታል፡፡

#የራሴን ዕድል በእራሴ እወስናለሁ በማለት ለብዙ ዓመታት ተዋግታ ይህንኑ ያስከበረችው ኤርትራ የቀይ ባህር አፋሮችን የግድ በኤርትራ ስር ትሆናላችሁ በማለትዋ እንደማንኛውም ለመብቱ ተቆርቋሪ ሕዝብ የአፋር ሕዝብም ነፃ ለመውጣትና ከእናት አገሩ ከኢትዮጵያ ጋር ለመቀላቀል ያለው መብት ማንም ሊገድበው አይችልም፡፡

#ከላይ በተለያዩ ምሁራን እንደተገለጸው ወደፊት በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል ግጭት ቢነሳ መንስኤው ኤርትራ እዚህ አንድ ኪሎ ሜትር እዚያ ሌላ አንድ ኪሎ ሜትር
የኢትዮጵያን ወሰን ጥሳ ገባች በሚል ሳይሆን (ያም የማይፈቀድ ቢሆንም) ኢትዮጵያ የባህር በር ተዘግቶባት ልማቷ፤ ደህንነትዋና ሉዓላዊነትዋ አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ ነው፡፡

#ኢትዮጵያ ለ40 ዓመታት በከፍተኛ ወጪ የገነባቻችው የባህር በሮች አንድ የነበረ አገር ለሁለት ተከፍሎ አንዱ ሁለቱንም የባህር በሮች ጠቅልሎ ሲይዝ ሌላው ደግሞ ባዶውን ይቅር ማለት · ፍትሕና መልካም ጉርብትና የማይቀበለው ጉዳይ ስለሆነ የኤርትራና የኢትዮጵያ
ሰላም አሰብን ወደ ኢትዮጵያ በማካለል ላይ መንጠልጠሉ ያለ ማመንታት መተንበይ ይቻላል።

#በመጨረሻም ኤርትራውያንስ የኢትዮጵያ የባህር በር
መብትን በተላይ አሰብን አስመልክቶ ምን ይላሉ የሚለው ጥያቄ መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ነው፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሰብ
የኢትዮጵያ ሉዐላዊ ግዛት ነች እያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው
ጽሁፎች ሲያወጡ በየአጋጣሚው ሲከራከሩ ኤርትራውያን ለዚህ ለኢትዮጵያውያን አቋም መልስ ሲሰጡበት ብዙ ጊዜም
አልተደመጠም፡፡ ይህ ጽሐፊ አሰብ የኢትዮጵያ ሉዐላዊ ግዛት ነች በማለት ለጻፈው ወሎ ተወልደው ያደጉትና የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሉጂ መምህር የነበሩት በአሁኑ ጊዜ የሻቢያ አባልና የአሥመራ ዩኒቨርሲቲ መምህርጰየሆኑት ፕሮፌሰር አሥመሮም ለገሠ መልስ ሲጸፉ የሚከተለው ብለው ነበር፡፡

“አሰብ ወደብ የኢትዮጵያ ነው ብለው በአሁኑ ጊዜ የሚከራከሩት ትምህርት የማይለውጣቸው ጊዜ የማያስተምራቸው የአማራ ባለሥልጣናት የነበሩ ናቸው፡፡ አሰብ የኢትዮጵያ ነው እያሉ የሚከራከሩ ነፍጠኞች አንዳንድ የወያኔ መሪዋችን በመስበክ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆኑና የትግራይ ልጆች እርስ በርሳቸው ተናንቀው ተላልቀው ሲያበቁ የአመራር ክፍተት ስለሚፈጥር ምንም ሳይዋጉ ወደ ሥልጣናቸው የመመለስ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ናቸው"

#ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ ችግሮች በሙሉ በአማራ ላይ ማላከክ
ልማድ ሆኖባቸው ነው እንጂ ጸሐፊው ኢትዮጵያዊ እንጂ የአማራ ነፍጠኛ የሚባል ነገር ካለ “የአማራ ነፍጠኛ” እንደልሆነ በተገነዝቡ ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ ሉዐላዊ ግዛት መከራከር ነፍጠኛ የሚያሰኝ ከሆነ በ1997 ዓ.ም በኢሕአዴግና በተቀዋሚዎች በተደረገው ክርክር ነፍጠኛነቱን እንደገለጸ ሁሉ ይህ ጸሐፊ አሁንም ነፍጠኛ ነው።

#ይህ አቋም የፕሮፌሰሩ የግላቸው ሲሆን በአቶ ኢሣያስ
ተቃዋሚዎች በኩል ምንም የተደመጠ ነገር የለም፡፡ ሆኖም የአቶ ኢሣያስ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ መንግሥት እንደ መደገፋቸው ወደብን አስመልክቶ ከኢሕአዴግ ጋር አንድ መግባቢያ እንደቀየሱ መገመት ይቻለል።

📌አሰብየማናት፤ያዕቆብኃይለማርያም፤179-83

☸️የአዲስ አበባ ሕዝብ ተሳትፎ ለኮሎኔል መንግሥቱ የእናት ሀገር ጥሪ►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► #የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ ለጥሪው የሰጠው...
11/01/2026

☸️የአዲስ አበባ ሕዝብ ተሳትፎ ለኮሎኔል መንግሥቱ የእናት ሀገር ጥሪ
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ ለጥሪው የሰጠው ምላሽ በጣም አስገራሚ ነበር። አገራችን በሶማሊያ መወረሯን እንደሰማ ተበሳጨ፣ቁጭትም አደረበት። በዚህ የተነሳ ሕዝባዊ ሠራዊት ለማሰልጠን ዝግጅት መጀመሩን እንዳወቀ በሚጠየቀው መንገድ ሁሉ ለመርዳት ፈቃደኛ ሆኖ ተነሳ።

#በቅድሚያ የዕድሮችን ድንኳኖች በሙሉ አስረከበ። ከግለሰቦችና ከድርጅቶች የተለያዩ ቁሳቁሶችን ሰብስቦ በስጦታ መልክ አበረከተ። በዚህ ብቻ ሳይወሰን በርከት ያሉ ሰዎችን ተራ አስገብቶ በየቀኑ ወደ ታጠቅ ጦር ሠፈር በመላክ ድንኳኖችን አስተከለ። የጉልበት ሠራተኛ የሚጠይቁ ሥራዎችን ማለትም ጉድጓድ መቆፈር፣ እንጨት መፍለጥ፣ ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ዕቃዎችን ማመላለስ፣ ከመኪና ማውረድ ወይም መጫን የመሳሰሉትን ሥራዎች ሊሠሩ የሚችሉ ሰዎችን በፈቃደኝነት እያሰባሰበ ቦታው ድረስ በማጓጓዝ አድርሷል።እነዚህ ሥራዎች እንዲከናወኑ ያስተባበሩትና አመራር የሰጡት የቀበሌ ማህበራት ነበሩ።

#ከሁሉ ይበልጥ የአዲስ አበባ ሴቶች የተጫወቱት ሚና በእጅጉ የሚያስገርም ነበር።ከከፍለ ሃገራት እየተመለመሉ ታጠቅ ጦር ሠፈር የመጡትን ምልምሎች እንደእናት
እየተቀበሉ አስተናግደዋል፣ መግበዋል፣ ተንከባክበዋል። ቋሚ ሠራተኛ በሌለበት ወቅት የአዲስ አበባ ሴቶች በየቀኑ ታጠቅ ጦር ሠፈር በመገኘት የሥራ ክፍፍል እያደረጉ
እህል ይለቅማሉ፣ ያስፈጫሉ፣ ሊጥ ያቦካሉ፣ ይጋግራሉ፣ ወጥ ይሠራሉ። ይህን ሥራ የሚያከናውኑት ተራ ገብተው ነው። በተራቸው ቀን በአንድ በተወሰነ ቦታ ይሰባሰባሉ።
ከዚያ በአውቶቡስ ተሳፍረው ወደ ታጠቅ ጦር ሠፈር ይሄዳሉ። ሙሉ ቀን ምግብ ሲያዘጋጁና ሠራዊቱን ሲመግቡ ውለው ማታ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። በማግስቱ ደግሞ ባለተራዎቹ በተመሳሳይ ሥራ ላይ ይውላሉ። ይህን ተግባር የሚያከናውኑት እንደብሔራዊ ግዴታ ስለሆነ አንዳቸውም ቅር የመሰኘት ወይም የመከፋት ምልክት አያሳዩም። እንዲያውም በሥራ ላይ እያሉ ይፎክሩና ጉሮ ወሸባዬ በማለት ይዘምሩ ነበር።

#ይህን የመሰለው የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ድርጊት ያበሳጨውና ዕኩይ ዓላማውን ለማስፈጸም እንደእንቅፋት አርጎ የተመለከተው #ኢሕአፓ በአገር ፍቅር ስሜት የተቃጠሉት ሴቶች ለእናት አገር ጥሪው ድጋፍ እንዳይሰጡ ለማድረግ የግድያ ሙከራና የማስፈራሪያ ዘመቻ ከፍቶባቸው ነበር። ይሁን እንጅ የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው ሴቶች መካከል በኢሕአፓ ድርጊት ደማቸው የተቆጣው
“ማን ይፈራል ሞት ማን ይፈራል! ለእናት ሃገር ሲባል” የሚለውን ሕዝባዊ ዜማ ፈጥረው ወደ ታጠቅ በሚያደርጉት ጉዞና በታጠቅ በሥራ ላይ በተሠማሩባቸው ጊዜያት ሁሉ በኅብረት ያዜሙት ነበር።

#በአገራችን ላይ የተሰነዘረው ወረራ ሙሉ በሙሉ አስኪገታና ደህንነታችን እስኪረጋገጥ ድረስ ሠራዊት የማሰልጠን እንቅስቃሴ መቀጠል እንዳለበት በመታመኑ ምግብ የሚያበስሉና የሚመግቡ ቋሚ ሠራተኞች ሥራውን እስኪረከቡ ድረስ የአዲስ አበባ ሴቶች አገልግሎት ቀጥሎ ቆይቷል። የአዲስ አበባ ሕዝብ በሁሉም የሥራ መስክ በታጠቅ ጦር ሠፈር እየተገኘ ተሳትፎ አድርጓል።የተለየ ሙያ ያላቸው ጥሪውን ተቀብለው ነጻ አገልግሎት ሰጥተዋል። እዚህ ላይ በወቅቱ በአዲስ አበባ የፀጉር አስተካካይ የነበሩ ወገኖቻችን ያበረከቱትን ተግባር መጥቀስ ይቻላል።

#ከሁሉም አገሪቱ ክፍሎች የመጡት ምልምሎች እንደ አካባቢያቸው ባህልና የአኗኗር ዘይቤ የተሠራው ፀጉራቸው ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት ከሚፈቅደው ውጭ ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ፀጉር አስተካካዮች ታጠቅ ጦር ሠፈር ድረስ መጥተው የሕዝባዊ ሠራዊቱን ፀጉር እንዲያስተካክሉ በሠራተኛ ማህበር በኩል ጥሪ ተደረገላቸው። ለጥሪው
መልስ ለመስጠት አላመነቱም። ወዲያው አባሎቻቸውን ተራ አስገብተው በዘመቻ መልክ ለማስተካከል ወሰኑ። ጊዜ አላባከኑም ማስተካከያ መሣሪያቸውን ይዘው ታጠቅ ጦር ሠፈር በመገኘት ጊዜያዊ የፀጉር ማስተካከያ ቦታ አዘጋጅተው ማስተካከል ጀመሩ። የማስተካከሉ ሥራ ስልጠናው አስኪጠናቀቅ ድረስ ቀጥሏል። ፀጉር አስተካካዮች በሙያቸው ላገራቸው ያበረከቱት አኩሪ ተግባር የመንፈስ ደስታ ሰጥቷቸዋል።

#በታጠቅ ጦር ሠፈር አዲስ በተተከለው ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ለሠራዊቱ የሚበቃ ዳቦ ማምረት እስኪቻል ድረስ ሠራዊቱን ለመመገብ ከግል ዳቦ መጋገሪያ ቤቶች
በየቀኑ ዳቦ እየገዛን መውሰድ ነበረብን። በዚህ የተነሳ ዳቦ ጋጋሪዎች የአዲስ አበባ ሕዝብንና የታጠቅ ጦር ሠፈርን የዳቦ ፍላጎት ማሟላት ስላቃታቸው መንግሥት የሚፈልጉትን ያህል
የዳቦ ዱቄት በመስጠት ሌት ከቀን ዳቦ እንዲጋግሩ ተደረገ። በዚህ አኳኋን ጋጋሪዎቹ ብርቱ ጥረት አድርገው በወቅቱ የገጠመንን ችግር አስወገዱ።

#በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአውቶቡሶችና የተሽከርካሪ ባለቤቶች የእናት አገር ጥሪውን ተቀብለው ሕዝባዊ ሠራዊቱን በማጓጓዝ ረገድ ያበረከቱት አስተዋጽዖም በጣም አስመስጋኝ
ነበር። የእነሱ ትብብርና ፈቃደኝነት ባይታከልበት ኖሮ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝባዊ ሠራዊትን ከጠረፍም ሳይቀር አጓጉዘን አዲስ አበባ ማድረስ አይቻለንም ነበር። “አገር
ከሌለ እኛም ሀብት ሊኖረን አይችልም። ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የምንሰጠው ለአገራችን ጉዳይ ነው” ብለው ይሰበርብናል ወይም ይበላሽብናል የሚል ስጋት ሳያድርባቸው ያላቸውን ተሽከርካሪ በሙሉ ሠራዊቱን እንዲያጓጉዝ በፈቃደኝነት አሰማሩ። ከባለቤቶቹ ባልተናነሰ ሁኔታ ሹፌሮችም ሙሉ ፈቃደኛና ተባባሪ በመሆናቸው አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ወጥተውና ወርደው በመጓዝ ያለምንም እንከን ምልምሎችን ታጠቅ ጦር ሠፈር አድርሰዋል።

📌እኛናአብዮቱ፤ፍቅረሥላሴወግደረስ፤376-7

🔯በሸዋ ፡ ያለ ፡ መልከኝነት ፡ ከነዜጋው ፡ እንደተቆጠረ ።—በዲርማ ፡ ደብረ ፡ ነጐድጓድ ፡ እንደተቆፈረ ።►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► #በዚህም ፡ ጊዜ ፡ በመላ ፡ ሸዋ ፡ ...
11/01/2026

🔯በሸዋ ፡ ያለ ፡ መልከኝነት ፡ ከነዜጋው ፡ እንደተቆጠረ ።—በዲርማ ፡ ደብረ ፡ ነጐድጓድ ፡ እንደተቆፈረ ።
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#በዚህም ፡ ጊዜ ፡ በመላ ፡ ሸዋ ፡ ያለ ፡ መልከኝነት ፡ ግንደበሉም ፡ገባሩም ፡ ሰሞነኛውም ፡ ጢሰኛውም ፡ በወገን ፡ በወገኑ ፡ ይጻፍ ፡ ዘንድ፡በጸሐፌ ፡ ትእዛዝ ፡ አለቃ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ እጅ ፡ ትእዛዝ ፡ ወጣ ።ወበውእቱ ፡ መዋዕል ፡ ወጽአ ፡ ትእዛዝ ፡ እምኀበ ፡ ቄሣር ፡ ንጉሥ ፡ከመ ፡ ይጸሐፍ ፡ ኵሉ ፡ ዓለም ፡ እንዳለ ፡ ይህም ፡ የሆነ ፡ በዘመነ ፡ ዮሐንስ ፡ በ፲፰፻፸፪ ፡ ዓመተ ፡ ምሕረት ፡ ነው ።

#ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በ፲፰፻፸፫ ፡ ዓመተ ፡ ምሕረት ፡ በዘመነ ፡ ማቴዎስ ወደ ፡ ደብረ ፡ ብርሃን ፡ ወጡ። በዚህም ፡ ጊዜ ፡ የጥሙጋ ፡ ዲና ፡ ወደ አዳል ፡ እየወረደ ፡ ነጋዴ ፡ ቢቀማ ፡ ግብሩን ፡ አስቀርቶ ፡ ነበርና ፡ ወደ ጥሙጋ ፡ ገሥግሠው ፡ አዘሎ ፡ ድረስ ፡ ያለውን ፡ አገር ፡ አስገብረው ተመልሰው ፡ እከተማዎ ፡ ወረይሉ ፡ ከረሙ ።

#ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በ፲፰፻፸፬ ፡ ዓመተ ፡ ምሕረት ፡ በዲርማ ፡ ደብረ ነጐድጓድን ፡ በለገሒዳ ፡ አትሮንሰ ፡ ማርያምንና ፡ ታዕካ ፡ ነገሥትን በለገጐራ ፡ መካነ ፡ ሥላሴን ፡ ጥንት ፡ በኖራ ፡ የተሠሩ ፡ አብያተ ፡ ክርስቲያናት ፡ በግራኝ ፡ ጊዜ ፡የተቃጠሉትን ፡ እያስቆፈሩ ፡ ግምቡን ፡ አወጡት ። የግምቡም ፡ ቁመት ፡ ሰባትም ፡ ስምንትም ፡ ክንድ ፡ ሆነ ፡ነገር ፡ ግን ፡ ከቀን ፡ ብዛት ፡ የተነሣ ፡ መሬቱ ፡ አጥብቆ ፡ ውጦታልና እስከ ፡ መሠረቱ ፡ ለመቆፈር ፡ አልተቻለም ። ሥራውም ፡ ድንጋዩ አራት ፡ ማዕዘን ፡ የተጸረበ ፡ የተቀረጸ ፡ እጅግ ፡ የሚያስደንቅ ፡ ነው ፡ከዚያውም ፡ ብዙ ፡ ንዋየ ፡ ቅድሳት ፡ ወጣ ። የወሎም ፡ ሰው ፡ ይህን ሁሉ ፡ ባየ ፡ ጊዜ ፡ እውነት ፡ የክርስቲያን ፡ አገር ፡ መሆኑን ፡ ተረዳው።

📌ዳግማዊአጤምኒልክ፤ጸሓፌትዕዛዝገብረሥላሴ፥99-100

☸️መንግሥት በተዛወረበት ቀን ስለ ሆነው ነገር፤የልጅ እያሱ ሽረትና በዝርዝር የቀረበባቸው ከእስልምና ጋር የተያያዙ ክሶች►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► #መስከረም 17 ቀን 190...
11/01/2026

☸️መንግሥት በተዛወረበት ቀን ስለ ሆነው ነገር፤የልጅ እያሱ ሽረትና በዝርዝር የቀረበባቸው ከእስልምና ጋር የተያያዙ ክሶች
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#መስከረም 17 ቀን 1909 ዓ.ም ረቡዕ በ3 ሰዓት አቡነ ማቴዎስና እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ በሊጋባው ተጠርተው ወደ ግቢ መጡ፡፡ እንዲሁም ሚኒስትሮችና በአዲስ አበባ ያሉ መኳንንት ሻለቆችና ሻምበሎች ሁሉ ሠራዊታቸውን እያስለፉ መጥተው በቤተ መንግሥቱ ግቢ ተሰበሰቡ፡፡ ከሚኒስትሮች ደጃዝማች አብርሃ ብቻ በቤታቸው ቀርተው ነበር።እነዚህ ሁሉ በግቢው ውስጥ በአዳራሹ አጠገብ በአደባባዩ ላይ ወደ ተተከለው አጅባር ድንኳን ገብተው አቡኑና እጨጌ በመካከል፤ ሚኒስትሮችና መኳንንት ሻለቆችና ሻምበሎች በቀኝና በግራ በየማዕርጋቸው ከተቀመጡ በኋላ ልጅ ኢያሱን ለመሻርና አዲስ መንግሥት ለማቋቋም የተፈለገበትን ምክንያት ለሕዝብ ለማስረዳት በጉባኤው መሪዎች ተዘጋጅቶ የተጻፈውን ቃል ከንቲባ ወልደ ጻድት ጐሹ አነበቡ፣ ቃሉም ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው።

#ጃንሆይ አጼ ምኒልክ ለሃይማኖትዎና ለመንግሥትም እጅግ ተጨናቂ ነበሩና እንዳለፉት ነገሥታት ጊዜ ሠራዊትዎ እርስ በርሱ እንዳይተላሉቅብዎ በመንግሥትዎ ነፋስ እንዳይገባበት አስበው ፈጽመው አቤት ሳይውሉ በ1901 ዓ.ም. ሊቀ ጳጳሱና እጨጌው ቆማችሁ መኳንንቱንና ሕዝቡን ሰብስበው ልጅ ኢያሱን ሰጥቻችኋለሁና ከሱ ፈቃድ የወጣ ሰው ርጉም ይሁን ጥቁር ውሻ ይውለድ ብለው ሰጡን:: እሱም እናንተን ያለ አግባብ የበደለ እንደ ሆነ ርጉም ይሁን ጥቁር ውሻ ይውለድ ብለው ሰጡን አባታችንም እጨጌም በዚሁ ቃል አውግዛችሁ ሰጣችሁን:: እኛም ደስ ብሎን ተቀበልን:: የግዝትም ቃል
እንዳይናወጥብን ተጠንቅቀን በእያለንበት አገር ሁሉ በትሕትና ራሳችንን ደፍተን በተቻለን በሙሉ ልባችን መንግሥታችንን እየረዳን እስካሁን ቄየን ከግዝትም ቃል የወጣ ሥራ እንዳልሠራን አባታችንም መላ ኢትዮጵያም ያውቃል፡፡ የምናስታውቀውም ቃል ይህ ነው፤

►መጀመሪያ

#ጃንሆይ ማረፋቸውን ሰው ሁሉ በልቡ እያወቀው ባረፉበት ዘመን በልጅ ኢያሱ ትእዛዝ ሰው ሁሉ ፈረሱን እየጫነ ጉግሥ ሲጫወት ሰነበተ የቀረው ቢቀር በዚያው ሰሞን ማዘን
መተከዝ ይገባ ነበር፡፡ መኳንንቱና ሕዝቡም ለጌታው ሳያለቅስ ዕንባውን እንዳረገዘ ቀረ።ምኒልክን የመሰለ የድኻ አባት እናት የነጋው ንጉሣችን መላ ኢትዮጵያን እንድ አድርገው
አስማምተው አሕዛብን አቅንተው ባጸኑት መንግሥት ባሠሩት አብያተ ክርስቲያናት ጥዋፍ ዕጣን ሳይባል ቀረ።ዐፅምዎም የወደቀበትን ቦታ አባታችን ያውቁታል:: በጃንሆይ ማረፍ ሕዝቡ በግልጥ እንዳያለቅስ ማድረጋቸውና ፍታት አለማስፈታታቸው መንግሥት እንዳይነቃነቅባቸው ይሆናል ተዛሬ ነፃ ፍታት አስፈቱ ምጽዋት አድርጉላቸው ይሉናል እያልን ስንጠብቅ ይህንን ያህል ቀን ቈየን:: ያባታቸውን ማረፍ ከምንም ሳይቆጥሩት የቀሩት ለካስ ሃይማኖታቸውን ከለወጡ ብዙ ጊዜያቸው ኑሮዋል::

►ሁለተኛ

#ሃይማኖታቸውን መለወጣቸውንና ከክርስቲያን መንገድ መውጣታቸውን መግለጥ ከወጠኑበት ቀን ጀምሮ የሠሩትን ያልተገባ ሥራ ሁሉ ጽፈን ለመጨረስ አይቻልምና ዋና
ዋናውን ብቻ ባጭር ቃል እናመለክታለን::ጌታችን ጃንሆይ እኔው ተሽቀዳድሜ በቶሎ ባገሬ የአውሮጳን ሥራት ካላስገባሁና በሁሉም ነገር እነሱን ካልመሰልኋቸው አይሆንም ብለው የአውርጳን ሥራት ማስለመጃ ይሁን ብለው
የሌሊት ዘበኛ ቢያቆሙ ልጅ ኢያሱ አሽከሮቻቸውን እያስከተሉ ሌሊት እየዞሩ ዘበኞቹን እየገደሉ በከንቱ ደማቸውን እያፈሰሱ የቆመውን ደንብ ስለ ማይረባ ነገር በገዛ እጃቸው አፈረሱት::

►ሦስተኛ

#የእስላም ቃልቾች እየሰበሰቡ የመሐመድንና የግራኝን ታሪከ ነገሥት እያስነበቡ የአያቶቻቸውን ዘር እያስቈጠሩ የይማሞች ዘር ከመሐመድ ዘር የወረደ ነው አሰኝተው እስላምነታቸውን ካደላደሉ በኋላ የእስላም ቤት እየፈለጉ የጅማ አባ ጅፋርን ልጅ የእኅቱንም ልጅ የአሚር አብዱ ዚጋ ልጅ የደራ መድን ልጅ የአዳልንም የባላባት ልጅ ያሰን እንጃሞንም ልጅ እነዚህን ሁሉ እያስፈለጉ አግብተው ቁባት ቀበቱ።የቀሩትማ የእስላም ሴቶች ስንቱ ተጽፈው ያልቃሉ እንኳንስ ያልተጠመቀችውንና
ክርስቲያንም ብትሆን በመጽሐፋችን የታዘዘው አንድ ወንድ ላንዲት ሴት ነው።

►አራተኛ

#አባታችንም እጨጌም ይህን ሁሉ ሥራ ሲሠሩ አያወቁና እየሰሙ መክረው ለመመለስ ተሸነፉ:: አባታችሁም ንጉሥ ሚካኤል ልጃቸውን መክረው ከዚህ ክፉ መንገዳቸው
ይመልሱልናል ብለን ተስፋ ስናደርግ አሸንፈዋቸው ኖሩ፡
አምና ዘፍልሰታ የእስላም ጦም ገጥሞ ነበር፣ በአባታቸው ከተማ በደሴ ላይ የሠሩት የክህደት ሥራ በጅሌና በጥሙጋ ዘጨና ዘላሌ ሲያደርጉት የከረሙት ሥራ ሁሉ ቢጽፉትም አያልቅ። ለመስማትም ደስ አያሰኝ ይህን ሁሉ ሥራ ሲሠሩ መኳንንቱም ሠራዊቱም እያየ እየሰማ ሕፃን ቢሆን ነው እያለ ትዕግሥት ቢያበዛ ልጅ ኢያሱ ዘውዳቸውን ጭነው በክርስትና ጸንተው መንግሥታቸውን ጠብቀው መያዝና ማጥናት ጠልተው ዕድሜያቸው ለዕውቀት ሲደርስ ሐያ ዓመት ሲሞላቸው የቃልቻ ቃል እየሰሙ የክርስቲያን መንግሥት አልቋል ከመሐመድና ከግራኝ በር የወረዱት የይማሞች መንግሥት መነሻ ደርስዋል እያሉ በሐሰት ቢያታልላቸው እውነት መስሎዋቸው ልጅ ኢያሱ አምና ሐረርጌ የወረዱ ጊዜ አራቱ አድባራት ቤተ ክርስቲያን ገብተው እንድ ጊዜ እጅ ሳይነ
ቀሩ። ከዚያም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ላንዱ እንኳ ገንዘብ ሳይሰጡ የመላ ሐረርጌ እየተሰበበ ከሚሰግድበት መስጊድ ሂደው አብረው ሰገዱ። በአምስቱ በር ዙሪያ ላሉት መስጂዶችና ቃልቾች አትርሱኝ እያሉ ብዙ ገንዘብ ሰጡ

►አምስተኛ

#ጃንሆይ ሐረርጌን የሰበሩ ጊዜ ክርስቲያን ሲዋጋ ጃንሆይ በፈቃድዎ ለመንግሥት ርስት ይሁን ብለው ለካህናትና ለከተማው ዘበኛ ከከተማ ለማይለይ ሰው ሰጥተው ይህን ያህል ዘመን ይዞት የኖረውን ቤትና ቦታ ለእስላሙ ስጡት ብለው አስለቀቁት: ካህናቱም ከታቦት ተለይተው እያዘኑ ወደ ውጪ ወጡ።ድኻውም እያለቀሰ ለቀቀ::

►ስድስተኛ

#ያሩሲ ኦሮሞ ሸፍቶ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስና ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ሽፍታውን ለማረጋጋት ሰው ቢልኩ ይኸው ከጥፋት ተቆጥሮባቸው ተነቀፉበት:: ይህም እስላም
እንዳይነካ በማድላት ነው:: እንደዚሁም በደጃዝማች ቆራሪ ግዛት በውጋዴን 45ቱን የክርስቲያን ወታደሮች ሱማሌ አርዶዋቸው ሥራይ ሳይደረግላቸው ቀረ።ከቶውንም ሶማሌዎች አዲስአበባ ቢመጡ ተሸልመው እንደገና ወደ ውጋዴን ሄዱ።የክርስቲያኑም ደም እንደ ውሻ ደም ሆኖ ቀረ።
ተረ: በዚህም ነገር እስላሙ በክርስቲያን ደም መቀባቱ በሳቸው ዘንድ የተመሰገነ እንደ ሆነ በስራቸው ተገለጠ።

►ሰባተኛ

#በአዲሱ ከተማ በድሬዳዋ ላይ ቀድሞ ያለነበረው መስጊድ ተሠርቶ አሁን ከዚህ የወራዱ ጊዜ የእስላም ዓሊሞች ልብስ ለብሰው የእስላም አጠማጠም ጠምጥመው ግልድም አገልድመው ፈጽመው የክህደት ሥራ ሠርተው እመስጊድ ገብተው አብረው ሰገዱ። ለመስጊዱም ብዙ ገንዘብ ሰጡ።የኛ ታቦት ግን አስቀድሞ በዚያ ተቈርቁሮ ተተክሎ የነበረውን በመቃኞ የኖረውን ካህናቱም መኳንንቱም ቢያስታውቁ እምቢ ብለው እስካሁን ሳይሠራ ቀርቶ የመስጊዱ ሥራ በልጦ ቀደመው::

►ስምንተኛ

#ጅጅጋ ላይ ዳርቻ አገር ነውና በዘያ ውስጥ የሚቀመጥ ክርስቲያን መቅደስ ካልተተከለለት ሰውነቱን ያረክሳል ያማግጣል ብለን የተከልነውን ታቦት ይህ ለመስጊድ የሚሆን ቦታ ነውና ታቦቱ ከሌላ ቦታ ሄዶ ይደረብ ብለው ካህናቱም ታቦቱን ይዘው ጊሪ ከሚባል ቦታ ተዳብለው ተቀምጠዋል። ይህስ እስላም ነኝ የእስላም ሃይማኖትን አጽኚ ነኝ
ማለት አይደለምን፣ አሁን መጠቅለያውን ደግሞ የሐረርጌ መድኃኔ ዓለም ቦታ ቀድሞ መስጊድ ነበርና ታቦቱ ይውጣና
እንደ ጥንቱ መስጊድ ይሁን ብለው ነበር:: ነገር ግን በቅርብ ቀን ነገር የሚነሣባቸው ቢሆን ለጊዜው ተዉት በኋላ ግን ያሰቡትን ሳይፈጽሙት አይቀሩም ነበር።

►ዘጠነኛ

#ከዚህ ሁሉ የሚከፋ ሥራ ሲሠሩ እስካሁን ድረስ ከእስላም ጋር እየተጋደለ በክርስትና ጸንቶ በዓለሙ ሁሉ ታውቆ ራሱን ችሎ የኖረውን የኢትዮጵያን መንግሥት ስሙን ከምድር
አጥፍተው ሃይማኖቱን አስለውጠው የመንግሥታችን ስም የክብር መጠሪያ በሆነው በሰንደቅ ዓላማችን ላይ ላኢላህ ኢላላህ መሐመድ ረሱል አላህ ብለው አስጥፈው ወስደው ለቱርክ መንግሥት ቆንስል አስረከቡት።

#ሰንደቅ ዓላማ ማለት ትርጓሜው በመንግሥት ፈንታ ሆኖ ለዓለም ሁሉ የሚታይና የሚታወቅ ምልክት ማለት ነው:: ለዚሁም ምስክር መንግሥት ሲባል ሰንደቅ ዓላማ የሌለው
መንግሥት የለም::የቱርክ መንግሥት ቆንስልም ይህንን ሰንደቅ ዓላማ ተቀብሎ ብዙ ደስታ ኣድርጎ ሻምፓኝ እያጠጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የእስላም ሃይማኖት ከዓለም ሁሉ ሃይማኖት የተመረጠ መሆኑን ተረድቶ ዛሬ አመነ ለዚህም ምስክር ሰንደቅ ዓላማውን ለእስላሞች ጠቅላይ ለቱርክ
መንግሥት ሰጠ እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ የቱርክና የኢትዮጵያ መንግሥት አንድ መሆኑን የሚጠራጠር ሰው ቢገኝ ወንጀል ይሆንበታል ብሎ በጉባኤ መካከል ቆሞ መረቀ።የውጪ መንግሥት እንደራሴዎች ይህን ሰምተው ሰንደቅ ዓላማችሁን አስመልሱ እያሉ ቢመሩ የሚሰማቸው ጠፍቶ ሰንደቅ ዓላማው አሁንም በቱርክ መንግሥት ቆንስል እጅ እንዳለ ነው::

►ዓሥረኛ

#በፍጹም መስለማቸውን የሚያስታውቅ እስከ ፵ የእስላም ትውልዳቸውን ቈጥረው በጠርቡሽ ላይ አስጥፈው እኔ ወገናችሁ ነኝና እስላምነቴን ዕውቄ ብለው ለሐረርጌ እስላምና ለሱማሌ ሽልማት ሰጡ፡፡ ይህም ያልተሰወረ በግልጥ የሆነ ሕዝብ ሁሉ ያየው ነገር ነው::ይህስ የክርስቲያንን ሃይማኖት መካድና ክርስቲያንን መጥላት በእስላም ሃይማኖት ማመን
እስላምን መውደድ አይደለምን?!

►ዓሥራ አንደኛ

#ሐረርጌ የእስላሙን ቃዲ ጠላና ጠጅ ትጠጣለህ አሉ ስለምን የእስላም መጽሐፍ የማያዘውን ሥራ ትሠራለህ ብለው ከሳሽ ሰው ሳይነሣበት በአደባባይ በግድ ፍረዱ ብለው
ክርስቲያኑንም እስላሙንም አስፈርደው አሰሩት:: እስላሙስ ይፍረድ ክርስቲያኑን በማያውቀው ሕግ ቀላቅለው በፍርሃት ማስፈረዳቸው የምን ማድረግ ይመስላል::

►ዓሥራ ሁለተኛ

#አሁን ጅጅጋ ከወረዱ የሱማሌውን ውጋዝና ባላገር ሰብስበው ሙሉ የጦር ልብስ ሸልመው የኢትዮጵያን መንግሥት ባለግርማ ሰንደቅ ዓላማችንን እዚህ አዲስ አበባ ለቱርክ መንግሥት ቆንስል የሰጡት አንሶ ዓሥራ ሁለት ሰንደቅ ዓላማ ላይ ላኢላህ ኢላላህ መሐመድ ረሱል አላህ የሚል ተጽፎበት ምሳሌ የሚሆን ቀይ ክር ከሰንደቅ ዓላማው ላይ ተንጠልጥሎ ይህንኑ ክር የሚበጥስ ፋስ የያዘ ጠርቡሽ ያደረገ የእስላም ሰው ሥዕል ተሥሎበት ለሱማሌዎች ሰጥተዋቸው ባደባባይ ይዘውት ወጥተው ፎከሩበት᎓᎓ ይህስ በክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የመነሣት ምልክት አይደለምን

►ዓሥራ ሦስተኛ

#የኢትዮጵያ መኳንንትና ሕዝብ ወደ ጥፋት መሄዱን እያየና እያወቀ ዝም ብሎ ትዕግሥት ቢያበዛ ፈረንጆች የልጅ ኢያሱን ሥራ ሁሉ ተመልክተው ይህ ነገር ጀሃድ የማሰኘትና የኢትዮጵያን ክርስቲያን አጥፍቶ በመጨረሻው ገና ላይ የሚከፋ ነገር ለማምጣት ነውና ይህን ነገር ለመንግሥት እናመልክትና ለራሱ ብልሃት ቢያዝ ያብጅ በተቀረ እኛ
የምንሠራውን እናውቃለን ብለው አንድነት ሆነው በግልጥ አስታውቁን:: ይህንን ነገር አስቀድመው ለመንግሥት ማስታወቃቸው ብናውቅበትማ ለኛ እጅግ መልካም ነገር ነው :
ክፋት አስበው ቢሆን ግን ዝም ብለው ነው እዚ ኢያሱ እሳቸውን ከፈጸሙ በኋላ ባገራችን ላይ በክፉ ለመነሣት ይመቻቸው ነበር::ጃንሆይ የመሠረቱትን ውል ጠብቀን ተጠንቅቀን ከኖርን ግን ኢትዮጵያን የሚነካት ሰው የለም:: ባንድ በልጅ ኢያሱ ብቻ ውል ማፍረስ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይጠሉ እንዴት ለምለም አገራችንን እንዴት እናስወስዳታለን ሃይማኖትስ ሲፈርስ ዝም ብለን ምን
እናስተውላለን፡አሁን ደግሞ ጀሃድ እያሉ የጃንሆይን አሽከሮችና የክርስቲያንን ደም ያፈሰሱትን እስላሞች
ሼኽ ጦልሃን ያሰን እንጃምም ልጅ ያባ ጅፋርን ልጅ ደግሞ ሌሎችን እንደነዚህ ያሉትን ይዘው እዋናው እስላም አገር ጅጅጋ ተቀምጠው ውጋዴን ውስጥ ሽፍታ ሆኖ እያስቸገረ ከሚኖረው ጅጅጋም ድረስ መጥቶ ክርስቲያንን ሲፈጅ ከነበረው ከከቢራ ጋር እየተላላኩ ብዙ ጠበንጃና ጥይት መትረየስም ሰደዱለት
ደግሞም የእንግሊዝንና የኢጣልያንን ዜጎች ጠርተው እየሰበሰቡ ጀሃድ እንበል እያሉ መክረዋል።

#ጅጅጋ ወርደው ይሀን መምክራቸው የእስላም መሃከለኛ አገር ነውና ጀሃድ በሚሉበት ጊዜ ኃይላቸው እንዲበረታ ነው::
እርሳቸው ግን እስላም ያረደውን እየበሉ እኔ ይህን ማድረጌ አገር ለማስፋፋትና ሰው ለማባበል ነው እንጂ ስለ ሌላ ነገር አይደለም እያሉ የሚያታልሉት ይህ ሱማሌና እስላም ከዚህም በፊት አሁንም ለጃንሆይ የገበረ የቀቀለ ዜጋቸው ነው:: ልጅ ኢያሱ ግን ከእስላም ጋር አብረው መብላታቸው የራሳቸውን እስልምና ለማጽናት ነው እንጂ በማባበላቸውስ ፊት ከቀናው ከገበረው አገር በቀር ሌላ አንድ ስንዝር መሬት የጨመሩት የለም::ይህንም እስልምናቸውን ለማጽናት እንዳደረጉት በጣም የሚገልጥና የሚያስረዳ ከሁሉ በፊት አስቀድመው የእስልምና ምልክትን ሲያሳዩ ሐነፊ ለሚባል እስላም ሚስት ስምዋ ነፍሳት ለተባለች ልጄን አንቺ አሳድጊልኝ ብለው ልጃቸውን ሰጡዋት::

#ልጅ ኢያሱ ያደረጉት ይህ ነገር ምንድር ነው እንዴት የንጉሠ ነገሥት ክርስቲያን ልጅ የእስላም ምግብ እየተመገበች የእስላም ልማድ እየተማረች በእስላሞች አፍ የእስላም
ሃይማኖት ሲከበርና ሲመሰገን የክርስቲያን ሃይማኖት ሲሰደብና ሲነቀፍ ሁልጊዜ ጥዋት ማታ እየሰማች ከእስላሞች ጋር አድን የክርስቲያንን ሃይማኖት መጻሕፍትን ሳትሰማ
በመስማትም ክፉን ከመልካም ለይታ ሳታውቅ ሥጋ ወደሙን ሳትቀበል ከእስላም ጋር እንዲህ ሆና አድጋ በኋላ እንዴት ክርስቲያን ልትሆን ትችላለች ብለን ልባችንን እያመመን
ይህ ነገር ምንድር ነው የምን ምልክት ነው እያልን በሆዳችን ሲክፋን ከዚህ ጋር ደግሞ በጣም ይድነቃችሁና ይውጣላችሁ ብለው ምንስ የፊቱም ሽሽግ ባይሆን በግልጥ ሐረርጌ
ከእስላም አገር አውርደው ከፉቅራ ቤት የአስላም ሃይማኖት እንድታጠና ቁርአንን አስተምራት ብለው አኖሩዋት.. እነሆ ሌላው ሁሉ ቀርቶ ይህ የተገለጠ ነገር ነውና አስተዋይ
ልቡና መርማሪ ሕሊና ላለው ይህ ብርቱ የእስልምና ምልክት እንደ ሆነ ፈጽሞ ይታያል::

#ዳግመኛም የእስልምና ምልክትን ሲያሳዩ ልጅ ኢያሱ የደጃዝማች ጆቴን ልጅ አስካለ ማርያም የምትባለውን ዳዊት ደጋሚቱን ሐረርጌ ወስደው ስምዋን ለውጠው በእስላሞች ሴቶች ስም ሞሚና አሉዋት ምቅና የሚባል የተለየ የእስላም ሴቶች መሸፈኛ አለበሷት። ይህም ወርቁን በነሐስ ንጽሑን በርኩስ እንደ መለወጥ ያለ ነውና ክፉ ምልክት ነው: እርሳቸውም የእስላም ልብስ ለብሰው እመስጊድ ገብተው መስገዳቸው በነበረው በኢትዮጵያ መንግሥት ስንደቅ ዓላማ የመስቀል ምልክት ባለበትና ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ተብሎ በሚጻፍበት ላይ የጨረቃ ግማሽ ሥዕልና የቱርክ እስላም መንግሥት ምልክት ላኢላህ ኢላላህ መሐመድ
ረሱል አላህ ተብሎ ሲያጽፉበት ይህ የእስልምና ክፉ ምልክት አይደለምን፡፡

#ልጅ ኢያሱ ይህን ሁሉ ጥፋት የሚሠሩት ልብ ነሥቷቸው አእምሮ ጐድሏቸው አይደለም፡፡የሰውን ምክር ባለመስማት ምን አለብኝ በማለት ወደው ለምደው ያደረጉት ሥራ ነው እንጂ
አብደው እንደ ናቡከደነፆር ልብ አጥተው የልብ ማጣት ቢሆንስ ያሳዝነን ያስለቅሰን ነበር እንጂ ባልፈረድንባቸውም ነበር። ይልቁንም አስረን በስውር ቦታ አኑረን ስለ ጤናቸው
መድኃኒት እንፈልግላቸው ብዙም እንደክምላቸው ዘንድ ይገባን ነበረ። ነገር ግን አበዱ ብሎ የማያስሩዋቸው ጨመቱ ብሎ የማያከብሩዋቸው ሆነው አጉል ሥራ እየሠሩ እዚህ ሁሉ
ነገር በገዛ እጃቸው ደረሱ፤ እኛንም በማይገባ ክፉ ሥራቸው ለሁከት እንቀሳቀሱን፣አሁንም ጃንሆይ ያሽከሮቻቸውን ደም አፍስሰው ያቀኑት አገር የእስላም ሰንደቅ ዓላማ ሲሳቃልበት ክርስቲያኖችም የሠሩዋቸው አብያተ ክርስቲያናት የእስላም መስገጃ ሊሆኑ ነውና ሃይማኖት መፍረሱን መንግሥት መጥፋቱን አስበን እንቻልህ እንታገሥህ ብንለው የማይቻለን ሆነ።

#ስለዚህ ከአውሮጳ በፊት በወንጌል ተሰብኮ በክርስትና ጸንቶ እስካሁን ድረስ የኖረውን መንግሥት አሁን የእስላሞች ዋና ገዥ የቱርክ መንግሥት ሊወድቅ በደረስበት ሰዓት ወደ
እስላምነት ሲመለስና የክርስቲያን ደም ብዙ ጊዜ ከእስላም ጋር በመዋጋት እንደ ጎርፍ የፈስስበት አገር ኢትዮጵያ የእስላም ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቀልበት ከማየት አስቀድሞ የሃይማኖት ኣምላክ ይርዳን ብለን ለሃይማኖትና ለመንግሥት ደማችንን ለማፍስስ ቈርጠናል::እንግዲህ መንግሥት ያለ ሃይማኖት ሃይማኖትም ያለ መንግሥት እንዳይጸና የታወቀ ነውና
ለዚሁም ሃይማኖትና መንግሥት ጃንሆይ አልጋ ላይ ከዋሉ ጀምረው እስካሁን የደከሙበት አባታችን ነዎ:: ሃይማኖት ይጥና መንግሥታችን ይርጋ ያሉ እንደ ሆነ የማርቆስ ሃይማኖት
አምላክ ለዳዊት እርዳታ ያወረደ መንፈስ ቅዱስ አይለያችሁ ብለው አባታችን መስቀልዎን እፊታችን ይዘው ሃይማኖታችንን ያጥኑልን፣ በጸሎትዎም ይባርኩን፣እስላም ጀሃድ ካለ በኋላ የስደድ (የቋያ) እሳት ከተቃጠለ ለማጥፋት እንዲያስቸግር እንደዚሁ ያስቸግራልና በቶሎ ካልነቃንበትና ካላጠፋነው ሥር ክሰደደ በኋላ ይልቁንም የክርስቲያን ደም ብዙ ይፈስብናል።

#ይህም የተነሣንበት ሁሉ በሹመት በሽረት በማግኘት በማጣት አይደለም፣፣ ለሃይማኖታችንና ለመንግሥታችን ለሀገራችንና ለሕዝባችንም ስንል ነው እንጂ። ምክንያቱ ይህ እንደ ሆነ ሌላ ነገር እንዳይደለ የኢትዮጵያ አምላክ ይመስክርብን::

#መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ
የሚል ተነበበ፡፡

#ደግሞ አሁን የምናስታውቃችሁም የአጼ ምኒልክን ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱ ንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ ብለን በአባታቸው በንድፍ መወሰናችንንና የሣህለ ሥላሴን ዘር የራስ መኰንንን ልጅ ደጃዝማች ተፈሪን ስም እና ስራሽ ማድረጋችን ነው የሚል ቃል ተነገረ።

#ንባቡ ተነቦ ካለቀ በኋላ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ “ልጆቼ ሆይ ጥቂት ቀን ስጡኝና እኔ ራሴ ወደ ሐረርጌ ወርጄ ልምከረው፣ የተበደላችሁትን ነገር ሁሉ አይቼ አስክሼ ላስታርቃችሁ
ብለው አጭር ቃል ተናገሩ፡፡ በዚህ ጊዜ እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ የጳጳሱን ንግግር በመቃወም እንዲህ አሉ!

“አሁን ነገር ካለቀ በኋላ ልምከረው የሚሉት ከዚህ ቀደም ሁለት ሦስት ጊዜ ይምከሩልን ብለን አስታውቀንዎት አልነበረም ወይ፣ መቼ መከሩዋቸው፤ ደግሞስ ልጅ ኢያሱ
የእስላሙን የአባ ጅፋርን ልጅና ከቤትዎ በታች ያለውን የእስላሙን የነጋድራስ አቡበክርን ልጅ ማግባቱን አልሰሙም ኖሮአል ወይ ብለው በቊጣ ቃል ተናገሩና እንግዲህ ልጄ
ኢያሱን የተከተልህ ለልጅ ኢያሱ የተገዛህ ገዝቻለሁ አሉ፡፡

#አቡነ ማቴዎስም ጥያቄአቸውን ትተው ልጅ ኢያሱን የተከተለና የተቀበለ ውጉዝ ይሁን ብለው ተናገሩ፡፡በዚህ ንግግር መካከል ቀኛዝማች ተሰማ ከተማ የተባለ ሰው “ጳጳሱ ልምከር ላስታርቅ ያላት ቃል ስለምን ተጠላ ብሎ ንግግር ጀምሮ ሳለ ገና ነገሩን ሳይጨርሰው፣ ሊጋባ በየነወንድማገኘሁ ጐራዴ መዘዙና የእስላም ወገን የሆንክ ሰው እንግዲህ ተለይ ብለው በፉከራ አኳኋን ተናገሩ። ቀኛዝማች ተሰማም ደንግጦ እርሱን ከመሰሉት ሰዎች ጋራ ሸሽቶ አመለጠ። ወዲያው አንድ ጥይት ቢተኩስ ተሸበረና ሌላው ሁሉ ተኵስ ጀመረ፡፡

#አብዛኛው ሰው ወደ ሰማይ ይተኵስ ነበር፡፡ በተኲሱም ምክንያት አጋፋሪው ባሻ ዳመናና ባሻ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ቀኛዝማች ሀብተ ማርያም የተባለ የሐረርጌ ሰው ሌሎችም አምስት ከልካዮች በተባራሪ ጥይት ሞቱ፡፡ አምስት ሰዎች ቈሰለ፣ ሽብሩ እኩል ሰዓት ያህል እንደ ቈየ ሊጋባ በየነ ወደ ዓዋጅ መንገሪያው ስፍራ ወደ አላማጣ በር ብቅ ብለው “አሁን
የተተኰሰው የደስታ ምልክት ነው እንጂ ለክፋት አይደለምና ባለህ እርጋ ብለው ተናግረው ሰዉን አረጋጉት፡፡

#ከዚህ በኋላ እኩለ ቀን ሲሆን ጳጳሱና እጨጌው ሚኒስትሮቹና መኳንንቱ ወደ እልፍኝ አዳራሽ ገብተው ምክር አደረጉና ወይዘሮ ዘውዲቱ ለጊዜው ባይኖሩም ዓዋጁ ተነግሮ
ይቈይ፣ ዓዋጅ ሲነገር አገር ይረጋል በሚል ሐሳብ ተስማሙ፡፡ ከዚህ በኋላ ደጃዝማች ተፈሪ መኰንን ራስ ወርቅ አስረውና ትልቁን የሰሎሞን ኮርዶን ኒሻን አድርገው በወርቅ
ወምበር ተቀምጠው ለሕዝብ ተገለጹና ቀጥሎ ያለው ዓዋጅ በነጋሪት ታወጀ፡

►ዓዋጅ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ
ስማ ስማ መስማሚያ አይንህ

ልጅ ኢያሱ ሃይማኖታችንን ስለ ለወጡ እሳቸውን ሽረን ያጼ ምኒልክን ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ብለን አንግሠናል:: ደጃዝማች ተፈሪንም ራስ ብለን አልጋ ወራሽ አድርገናልና ገበሬም እረስ ነጋዴም ነግድ የጥዋቱም ተኵስ በአንድነት ሆነን በምክር ስለ ተስማማን ለሃይማኖታችንና ለመንግሥታችን የደስታ ምልክት ነው እንጂ የክፉ ነገር
አይደለምና አትስጋ:: እንግዲህ ግን ጠበንጃ ተኵስ የተገኘህ ብርቱ ቅጣት ትቀጣለህ፡

#ይህ ሁሉ ሲሆን ወይዘሮ ዘውዲቱ ፋሌ ላይ ነበሩና በቶሎ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተብሎ በጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስና በጦር ሚኒስትሩ በፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ማኅተም የታተመ ደብዳቤ ተላከላቸው፡፡ ቃሉም የሸዋ መኳንንት በአንድነት መክሮ የአባትዎን አልጋ ሰጥቶዎታልና ይህ ደብዳቤ እንደ ደረስዎ በቶሎ እንዲመጡልን ይሁን የሚል ነበር፣ ወረቀቱን ለመስጠትና አጅቦ ለማምጣት የተላኩትም መኳንንት አዛዥ ሽብሩ ኢብሳና ልጅ መኰንን ዋልቴ፣ ባላምባራስ ጐርፉ ናቸው፡፡ ሌሎችም ሻምበሎች
ተጨምረው ሄደው ነበር፡፡

#የልጅ ኢያሱን ሽረትና የአዲሱን መንግሥት መቆም በያገሩ ያሉት መሳፍንትና መኳንንት እንዲያውቁት መስከረም 18 ቀን ለሁሉም በስልክ ተነገረ፡፡ በጽሑፍም ተላለፈ:: ለንጉሥ
ሚካኤልም የዚሁ ዓይነት ቃል በስልክ ተላለፈላቸው᎓᎓ የልጅ ኢያሱ ሽረት ወሎ ላይ እንዴት እንደ ተለማ የነገሩን ሁናቴ ወደፊት እገልጣለሁ፡፡ደግሞም በዚሁ ቀን ሚኒስትሮችና መኳንንት ስብሰባ አድርገው በየዳር አገር ለሚገኙ መኳንንትና ለሠራዊት የሚላክ ጽሑፍ አሰናዱ፡፡ ጽሑፉ የልጅ ኢያሱን ሽረትና በምክር የተደረገውን የመንግሥት ለውጥ በዝርዝር ለማስረዳት እንደሚያገለግል ሆኖ በሁለት ዓይነት ተሰናዳ፡፡ አንደኛው በጳጳሱና በእጨጌው ማኅተም የሚታተም የግዝት ቃል ያለበት መልእክት ሲሆን ሁለተኛው በሚኒስትሮችና በመኳንንት ስም የሚላክ መልእክት ነው:: የተላከውም በየጊዜው ስለ ሆነ ወደፊት ጽሑፉን እገልጣለሁ።

📌የሐያኛውክፍዘመባቻ፤መርስዔኅዘንወልደቂርቆስ፤143-9

☸️ሻምበል ለማ ጉያ ገመዳ  በመጫና ቱለማ ማህበር ►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►► #የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር በተለያዩ አካባቢዎች ካደረገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በሰኔ ወር 1958 ...
11/01/2026

☸️ሻምበል ለማ ጉያ ገመዳ በመጫና ቱለማ ማህበር
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር በተለያዩ አካባቢዎች ካደረገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በሰኔ ወር 1958 ዓ/ም #በአድአ ውስጥ የአንዳንዴ ፣ የሣሌ ቅዱስ ጊዮርጊስና የቢሾፍቱ ከተማ ህዝብ በጋራ አዘጋጅቶት በነበረው የልማት ስብሰባ ላይ የማህበሩ መሪዎች እንዲገኙለት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የማህበሩ መሪዎች በዚሁ ስብሰባ ላይ ተገኙ። ይህንን ስብሰባ በማስተባበርም ሆነ በኋላ በክልሉ የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ቅርንጫፍ ለማቋቋም የተደረጉትን ጥረቶች #በግንባር ቀደምትነት የመሩት እውቁ የስነ ጥበብ ሰው #ሻምበል ለማ ጉያ ናቸው ። ሻምበል ለማ ጉያ ይህንን ስብሰባ አስተባብረው ለዚህ በማብቃታቸው ወዲያውኑ በመስሪያ ቤታቸው በኩል ወደ አስመራ እንዲዛወሩ ከመደረጋቸውም በላይ ለእሥራትም ተዳርገዋል።

#በዚህ ስብሰባ ላይ ማህበሩ የአስተባበረውን የስነ ጥበብ ሰውነት በመገመት ይመስል ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሮሚኛ ቋንቋ የተዘጋጀና የትምህርት ጥቅም የሚያስረዳ ድራማ አቀረበ ። ይህንኑ ድራማ የጻፉትና ያዘጋጁት የማኅበሩ ሁለገብ ካድሬ የነበሩት #መቶ አለቃ ማሞ መዘምርና አቶ ቡሽራ ወርቁ ናቸው። ይህ ድራማ ቀደም ሲል ማህበሩ በተሳተፈባቸው ስብሰባዎች ላይ እንደተደረገው ሁሉ የሕዝቡን ራስን በራስ የመርዳት ስሜት ከመቀስቀሱም በላይ እንደ ቀድሞዎቹ ስብሰባዎች ውጤቶች ሁሉ በዚህም አካባቢ ለማህበሩ ታዋቂነትን አስገኘ።

#የነበረው መንግስት በማህበሩ ላይ የማጥቃት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት በአድአው ስብሰባ አስተባባሪ በነበሩት #በሻምበል ለማ ጉያ ላይ የተወሰደው እርምጃ ይህው የማህበሩ ዝና ወደ አየር ኃይሉ ግቢ ዘልቆ እንዳይገባ ለመከላከል ሲል የወሰደው እርምጃ ይመስላል ። ይሁንና በዚህ ጊዜ ከሻምበል ለማ ጉያ ጋር በክልሉ ስራ ላይ የነበሩት አቶ አብዬ ገለታና ሻምበል ደምሴ ዴሬሣ ከአየር ወለድ የሚገኙበት የክልሉ የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር አስኳል ተመስርቶ ነበር ።

#ማህበሩ በአድአም ያደረገውን ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ካገባደደ በኃላ በሐምሌ ወር ላይ ለማድረግ ወደ ወጠነው የአቤቤ ቄረንሳ ስብሰባ ከመሄዱ በፊት ሁለት ዋና ዋና የክፍለሃገር ቅርንጫፎችን ለማዋቀር የሚያስችል እርምጃዎችን በመውሰድ ድሩን በመላው የኦሮሞ አካባቢዎች ባልተጠበቀ ፍጥነት ዘረጋ። በዚህም መሰረት በዚሁ በሰኔ ወር ውስጥ የወለጋና የሐረርጌ ቅርንጫፎች ለማቋቋም የሚያስችለውን እርምጃ ወሰደ።

#ሻምበል ለማ ጉያ በዚህ የሰኔ 1958 ዓ/ም የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ንቁ ተሳትፎና በቢሾፍቱ ግምባር ቀደም አስተባባሪነቱ ምክንያት በመንግስት በግዞት መልክ ከአካባቢው ከዘመድ አዝማድ ርቆ ወደ አስመራ እንዲዛወር ከመደረጉም በላይ በስራው ላይ የማዕረግ እድገት እንዳይኖረው በሻምበል ማዕረግ ብቻ ተወስኖ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ጉዳዩን የሚያውቁ የቅርብ ጓደኞቹ ይች የሻምበል ማዕረግህ #የክርስትና ስም ነች እያሉ ይተርቡት ነበር። ሻምበል ለማ ጉያ ከጄኔራል ታደሰ ብሩና ከመቶ አለቃ ማሞ መዘምር ጋርም የቅርብ ወዳጅነት ነበራቸው።

📌ግዝትና ግዞት በኦላና ዞጋ፤ 59-60

📌የብ/ ጀኔራል ታደሰ ብሩ የእጅ ጽሁፍና ፊርማ►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►"Just Friends and Brave Enemies" የሚለውን በፕሬዝዳንት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ወንድም ሴናተር ሮበርት...
11/01/2026

📌የብ/ ጀኔራል ታደሰ ብሩ የእጅ ጽሁፍና ፊርማ
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
"Just Friends and Brave Enemies" የሚለውን በፕሬዝዳንት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ወንድም ሴናተር ሮበርት ኬኔዲ የተፃፈ መጽሃፍን #ብ/ጀኔራል ታደሰ ብሩ በስጦታ መልክ ለሎሬት #ሻምበል ለማ ጉያ በስጦታ መልክ ሲሰጣቸው የሚከተለውን መልዕክት ጽፈው ነበር።

❝ሰው ትልቅ የሚያሰኝ በትልቅ ስራ እራስን በመውልድና ለአገርና ለወገን ትልቅ ሙያ በመፈጸም መሆኑ እርግጥ ነው❞

►መ/አለቃ ለማ ጉያ

«እራሱን በትልቅነት ለማስጠራት ሳይሆን ርሑርሁረቱና ሰብአዊው ህሊናው ስላስገደደው መሆኑ ምስክሩ ስራው ብቻ ነው ። ስለ መልካም ስራውና ተግባሩ በፊደል ሰራዊት ማህበር ስም ሁኘ ይህንን መጽሃፍ ሳበረክት ከፍ ያለ ደስታ እየተሰማኝ ፣ድንቁርና ከአገራችን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ተካፋይ መሆንህን ለታሪክ መዝገብ እንድትሆን በማመን ነው።»

ብ/ጄኔራል ታደሰ ብሩ
የብሄራዊ ፊደል ሰራዊት የስራ ሰብሳቢ ሊቀመንበር

📸Negash Qemant

►ምስሎቹ፤የሮበርት ኬኔዲ፤የብ/ጀነራል ታደሰ ብሩና የሻምበል ለማ ጉያ ናቸው።

11/01/2026

#የክብር ዘበኛ ማርሽ ባንድ(የሼህ ሆጀሌ ልጆች) መሪ ሻለቃ በልሁ አባ ቆሮ፤

#በስዊዝ ማስተር ሙሴ ኒኮ የሰለጠኑት አባላት የሚመሩት 2.8 ሜ በሚረዝመው አባ ቆሮ ነበር።

11/01/2026

 #ይህ ጎዳና አዲስአበባ የት ነው?!-1924 ዓ.ም
11/01/2026

#ይህ ጎዳና አዲስአበባ የት ነው?!-1924 ዓ.ም

Address

Ethiopia
Addis Ababa
+251

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም:

Share