Yod Abyssinia Tour & Travel -Ye'Janderebaw Guzo

Yod Abyssinia Tour & Travel -Ye'Janderebaw Guzo An Inbound & Outbound Tour Operator Based in Addis Ababa Ethiopia Bole Medhaniyalem area next to Brass Hospital,
Addis Ababa, Ethiopia.

Phone: +251-1-(0) 116 612154
For Ye'Janderebaw Guzo to Jerusalem call at +251-1-(0)927 356 654 or 51
For flight tickets call at +251-1-(0)927 356 654
e-mail:
for general inquiry - [email protected]
for flight tickets inquiry - [email protected]
website http://www.yodabyssiniatour.com

10/09/2026

መልካም አዲስ አመት
ዮድ አቢሲኒያ የኢትዮጵያ የባህልና የቱሪዝም አምባሳደር #

ስምንተኛ ቀን፦ ማክሰኞ ነሃሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ኢየሩሳሌም - አላዛር - ቴላቪቭ - አዲስ አበባ ጠዋት በተያዘላቸው ሆቴል ቁርስ ከተመገቡ በኋላ የሆቴል ክፍሎቻቸውን አስረክበው ወደ አይ...
26/08/2026

ስምንተኛ ቀን፦ ማክሰኞ ነሃሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
ኢየሩሳሌም - አላዛር - ቴላቪቭ - አዲስ አበባ
ጠዋት በተያዘላቸው ሆቴል ቁርስ ከተመገቡ በኋላ የሆቴል ክፍሎቻቸውን አስረክበው ወደ አይነከርም እንሄድና እመቤታችን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት የሄደችበትን፣የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ፅንስ የእመቤታችንን ድምፅ በሰማ ግዜ የዘለለበትን እና የተወለደበትን አይነከርምን ተሳልመን ወደ አላዛር ከተማ በማቅናት በዚያ የሚገኘውን የአቡነ ተ/ሃይማኖት ገዳም ጎብኝተን ምሳ በሳቫቫ ሬስቶራንት ቤተልሄም ተመግበን ወደ ቴላቪቭ በመጓዝ ራት ቅዱስጊዮርጊስ ሬስቶራንት ያፎ ተመግበን ምሽት ላይ ወደ ቤንጎሪዮን የአውሮፕላን ማረፊያ ይሄዳሉ፣ንጋት 11:00 ላይ ተጓዦች በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ እና የጉዞው ፍፃሜ ይሆናል፡፡

☎️ 0985 27 28 29
0913 27 44 11
📍 ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዮድ አቢሲኒያ
የባህል ምግብ አዳራሽ ጊቢ ውስጥ

ሰባተኛቀን፡ ሰኞ  ነሃሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም እየሩሳሌም - ቤተልሔም - አእየሩሳሌም ጠዋት እንግዶቻችን በተዘጋጀላቸው አውቶቡስ ወደ ቤተልሔም በማምራት በቤተልሔም ከተማ የኢትዮጵያ ደብረ ...
26/08/2026

ሰባተኛቀን፡ ሰኞ ነሃሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
እየሩሳሌም - ቤተልሔም - አእየሩሳሌም
ጠዋት እንግዶቻችን በተዘጋጀላቸው አውቶቡስ ወደ ቤተልሔም በማምራት በቤተልሔም ከተማ የኢትዮጵያ ደብረ ሰላም ኢየሱስ ገዳምን ተሳልመንና ጸበል ተረጭተን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባትን በረት፣በመቀጠልም የእረኞቹን መንደር (The Shepherds Fields) አይተን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደተወለደ መላዕክት ምሥራቹን ያበሰሩበትን ‘ኖሎት’ ተብሎ ወደሚጠራው ሥፍራ እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደት የጀመርችበትን የወተት ዋሻ መጀመሪያ መዳረሻችን አድርገን ምሳ በቴንት ሬስቶራንት ተመግበን ወደ ሆቴላችን በማምራት እቃችንን ለነገ ጉዞ ዝግጁ በማድረግ ራትና አዳር በእየሩሳሌም ከተማ በሆቴላችን ይሆናል፡፡

🛂 0985 27 28 29
0913 27 44 11
📍 ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዮድ አቢሲኒያ
የባህል ምግብ አዳራሽ ጊቢ ውስጥ

ስድስተኛ ቀን፡እሁድ ነሃሴ17 ቀን2018 ዓ.ም ኢየሩሳሌም - ባህረ ዮርዳኖስ(ኢያሪኮ) - ኢየሩሳሌም  ጠዋት ቁርሳችንን በቴካወይ ይዘን ወደ ባህረ ዮርዳኖስ ወንዝ በመሄድ የዕለቱን ጉብኝት እ...
26/08/2026

ስድስተኛ ቀን፡እሁድ ነሃሴ17 ቀን2018 ዓ.ም
ኢየሩሳሌም - ባህረ ዮርዳኖስ(ኢያሪኮ) - ኢየሩሳሌም

ጠዋት ቁርሳችንን በቴካወይ ይዘን ወደ ባህረ ዮርዳኖስ ወንዝ በመሄድ የዕለቱን ጉብኝት እንጀምራለን፣በባህረ ዮርዳኖስ ከተጠመቅን በኋላ ቁርሳችንን ተመግበን ወደ ኢያሪኮ በማቅናት ገዳመ ቆሮንቶስንና የኤልሳዕ ምንጭን ጎብኝተንምሳ በቴምፕቴሽን ሬስቶራንት ተጠቅመን የዘኬዎስን ዛፍ፣የኢትዮጵያ ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን ጎብኚተን፣የሙት ባሕርን ጨምሮ ቁምራንን (የሙት ባህርጥቅሎች የተገኙበት) አካባቢውን ተመልክተን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ እራትና አዳር በኢየሩሳሌምሆቴል ይሆናል፡፡

🛂 0985 27 28 29
0913 27 44 11
📍 ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዮድ አቢሲኒያ
የባህል ምግብ አዳራሽ ጊቢ ውስጥ

አምስተኛ ቀን፡ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ኢየሩሳሌምበእለቱ ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት የሚመነኩሱትን 10:00 ሰዓት ቀሪውን በመያዝ እየሩሳሌም ደ/ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያ...
26/08/2026

አምስተኛ ቀን፡ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ኢየሩሳሌም
በእለቱ ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት የሚመነኩሱትን 10:00 ሰዓት ቀሪውን በመያዝ እየሩሳሌም ደ/ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ተገኝተን አስመንኩሰን አስቆርበንና አስቀድሰን በነበረው ትልቅ በዓል ላይ ተሳትፈን ቁርስ በልተን ወደ ጌቴሰማno ሄደን የእመቤታችንን መቃብር ተሳልመን ወደ ደብረ ዘይት ተራራ በመውጣት በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ጌታችን ያረገበትን ቦታ ተሳልመን የኤልዮን ዋሻን አይተን እየሩሳሌምን ከከፍታ ቦታ ተመልክተን ወደ ፅዮን ተራራ በመውጣት የቅዱስ ዳዊትን መቃብር የእመቤችንን የግንዘት ቦታ ተሳልመን ምሳ በልተን ወደ ሆቴላችን ተመልሰን ረፍት ራትና አዳር በሆቴላችን ሆኗል ፡፡

🛂 0985 27 28 29
0913 27 44 11
📍 ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዮድ አቢሲኒያ
የባህል ምግብ አዳራሽ ጊቢ ውስጥ

አራተኛቀን፡አርብ ነሃሴ15 ቀን2018 ዓ.ም                    ኢየሩሳሌምበጠዋት በመነሳት  ወደጥንታዊው የኢየሩሳሌም ከተማ በማቅናት ከቤተሳይዳ፣የጌታችን ፍኖተ መስቀል የመጀመሪያ ...
22/08/2026

አራተኛቀን፡አርብ ነሃሴ15 ቀን2018 ዓ.ም
ኢየሩሳሌም
በጠዋት በመነሳት ወደጥንታዊው የኢየሩሳሌም ከተማ በማቅናት ከቤተሳይዳ፣የጌታችን ፍኖተ መስቀል የመጀመሪያ ምዕራፍ ከሆነው የጲላጦስ አደባባይ በመጀመር 14ቱን ምዕራፎች እያዩና ገለጻ እየተደረገላቸው፣ጌታችን የተሰቀለበትን ቀራኒዮን /ጎለጎታ/፣ቅዱስ ሥጋው የተቀበረበትንና ሞትና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሳበትን ቅዱስ ስፍራዎች ጎብኚተን ምሳ በልተን የግብይት ጊዜ እንዲኖረን ተደርጎ ወደ ሆቴላችን ተመልሰን ራትና አዳር በሆቴል በኢየሩሳሌም ከተማ ይሆናል፡፡

🛂 0985 27 28 29
0913 44 27 11
📍 ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዮድ አቢሲኒያ
የባህል ምግብ አዳራሽ ጊቢ ውስጥ

መስቀልን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያክብሩ             ዮድ አቢሲኒያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ጋር 📅  የመነሻ ቀን ፡- መስከረም 13 - 20 🛂  0985 27 28 29         ...
21/08/2026

መስቀልን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያክብሩ
ዮድ አቢሲኒያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ጋር

📅 የመነሻ ቀን ፡- መስከረም 13 - 20
🛂 0985 27 28 29
0913 44 27 11
📍 ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዮድ አቢሲኒያ
የባህል ምግብ አዳራሽ ጊቢ ውስጥ

ሶስተኛቀን፡ሐሙስ ነሃሴ14 ቀን2018 ዓ.ም                ጥብርያዶስ - ሃይፋ - ያፎ - ኢየሩሳሌምጠዋት የሆቴል ቁልፍ አስረክበን ወደ ሃይፋ የወደብ ከተማ በማቅናት የሚስብ ማራኪ ...
20/08/2026

ሶስተኛቀን፡ሐሙስ ነሃሴ14 ቀን2018 ዓ.ም
ጥብርያዶስ - ሃይፋ - ያፎ - ኢየሩሳሌም
ጠዋት የሆቴል ቁልፍ አስረክበን ወደ ሃይፋ የወደብ ከተማ በማቅናት የሚስብ ማራኪ እይታ ያለበትን የሜዲትራንያን የባህር ዳርቻ እያየን ወደ ቀርሜሎስ ተራራ እንወጣለን በዚህም የነብዩ ኤሊያስን ዋሻ ተሳልመን ለተወሰነ ሰዓት በአካባቢው እይታ ተዝናንተን የሃይፋ ከተማን ስናቋርጥ ውቡን የባሃኢ የአትክልት ስፍራ እና የሜዲትራንያንን የባህር ዳርቻ በዓይናችን እየጎበኘን ወደ ያፎ (የቴላቪቭ ጥንታዊ ከተማ) እናመራለን። በዚህም ጥንታዊውን የወደብ ከትማ፣ ነብዩ ዮናስ ጀልባውን ያሳረፈበትን ቦታ እንዲሁም ቅዱስ ጴጥሮስ ራእይ ያየበትንና በስሙ ቤተክርስቲያን የታነጸበትን የሰማኦን ቀሬናዊውን ቤት እንጎበኛለን። ምሳ ሩት ሬስቶራንት ተመግበን ልዳ ጊዮርጊስን ተሳልመን ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ሆቴላችንን እንይዛለን። አዳር ኢየሩሳሌም በሆቴል፡፡

ሁለተኛ ቀን፡ እረቡ ነሃሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም  ደ/ታቦር - ገሊላ ባህር ዙሪያ ጠዋት ተነስተን ወደ ደ/ታቦር ተራራ በማቅናት ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበትን ቦታ ተሳልመንና የእለቱን ክብረ...
20/08/2026

ሁለተኛ ቀን፡ እረቡ ነሃሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም
ደ/ታቦር - ገሊላ ባህር ዙሪያ

ጠዋት ተነስተን ወደ ደ/ታቦር ተራራ በማቅናት ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበትን ቦታ ተሳልመንና የእለቱን ክብረ በዓል አስበን የአካባቢውን መልካዓ ምድርና የጌዲዮን ጦር የተዋጋበትን መጸሐፍ ቅዱሳዊ ታሪካዊ ቦታን አይተን ወደ ገሊላ ባህር ዳርቻ አምርተን ቅፍርናሆምን፣የአንቀጸ ብፁዓን ስብከት ተራራ እና በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ሌሎች ቅዱሳት ቦታዎችን እንጎበኛለን፣ ለመታሰቢያነት የሚሆን በሚግዳል ሬስቶራንት ምሳ ከተመገብን በኋላ የጀልባ ጉዞ በገሊላ ባሕር ላይ እናደርግና ወደ ዘይት ፋብሪካ በማምራት ዘይት ገዝተን ወደ ሆቴል እናመራለን፡፡አዳር በሆቴል ጥብርያዶስ/ናዝሬት፡፡

የደብረታቦር ተጓዦቻችን በሰላም ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገብተዋል                                  አዲስ አበባ - ቴልአቪቭተጓዦች  ጉዞአችውን ከለሊቱ 8፡00 ሰዓት ከቦሌ...
18/08/2026

የደብረታቦር ተጓዦቻችን በሰላም ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገብተዋል
አዲስ አበባ - ቴልአቪቭ
ተጓዦች ጉዞአችውን ከለሊቱ 8፡00 ሰዓት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተን ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ቴልአቪቭ ቤንጎርዮን አየር ማረፊያ ደርሰናል ከዚያም አስፈላጊውን የኢሚግሬሽን ስርዓት ፈፅመን ስንጨርስ የTWT የኤጀንሲው ባልደረቦች ተቀብለውናል እቃችንን በተዘጋጀልን አውቶቡስ ጭነን ወደ ናዝሬት ከተማ ተጉዘን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብሥራት የተቀበለችበትን፣ከምንጭ ውሃ ትቀዳበት የነበረበትን ፣ በጫማዋ ለውሻ ውሀ ያጠጣችበትንና ቤተ ዮሴፍ የተባለውን ቅዱሳት ሥፍራዎች ተሳልመን ምሳ በናዝሬት ተመግበን አዳር ናዝሬት በፕላዛ ሆቴል ፡፡

Address

Near Bole International Airport
Addis Ababa
503CODE1250

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yod Abyssinia Tour & Travel -Ye'Janderebaw Guzo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category