
20/03/2025
!!
ከወራቶች ሁሉ አሏህ የመረጠው፡
ፀጋና ደረጃን አግዝፎ የሰጠው፡
ረመዷናችን ተጉዞ እዚህ ደርሷል፡
አልሀምዱ ሊላሒ ብዙ ቀልብ ርሷል፡
ብዙወች ነበሩ ከእውነት የራቁ፡
በረመዷን ሰበብ ተውሒድን አወቁ፡
ከቢዲዐ ፀድተው በሱና ደመቁ፡
በሰላም በደስታ በፍቅር አዳርሶን፡
በፍትህ በፀጋ በእዝነት ደባብሶን፡
ከክብር ማማ ላይ በአምልኮ አድርሶን፡
መሔጃው ደረሰ ብዙ ፀጋ አቅምሶን፡
ለይለተል ቀድርን ነቅተን እንጠብቃት፡
ለይሉን ሳንተኛ በአምልኮ እናድምቃት፡
እንቅልፍ ሳንተኛ በሞራል በንቃት፡
መስፈርቷን ጠብቀን በደስታ በብቃት፡
በላጭ የሆነችው ከአንድ ሽ ወራት፡
ያች የድል ጭራ የአማኞች ብስራት፡
አላህ በቁርአን የተናገረላት፡
ነብዩ በሀዲስ ብዙ ያወሩላት፡
ቀደምቶች በጉጉት የሚጠባበቋት፡
እርሷን በመናፈቅ በክብር ያላቋት፡
የለይለተል-ቀድር ታላቅ ነው ሚስጥሩ፡
ሚንዳው በርካታ ነው አያልቅም በቁጥሩ፡
በዚህች ቀን ብዙ ነው የሚሰራው ነገር፡
የአሏህ ቃል በቂ ነው እኔ ምን ልናገር፡
ኸይሩን ሚን አልፊ ሸህር ብሎ ያደመቃት፡
ከቀናቶች መርጦ ለብቻ ያላቃት፡
አማኙ በጉጉት የሚጠባበቃት፡
አሏህ ይወፍቀን እኛም እናግኛት፡
ናፍቃን እንዳትቀር እንድህ ስንመኛት፡
እርሷን በመገጠም ጌታችን ያግራልን፡
ዱአችንን ሰምቶ በኛ ላይ ያምጣልን፡
የአርሹ ባለቤት አዛኙ ጌታችን፡
ኸይሩን ሚን አልፊ ሸህር ይገጠም ህዝባችን፡
ቀሪወቹን ቀናት እንበል ሽርሽር፡
በተሀጁድ ታጥቀን የተቅዋን ሚኒሽር፡
በኢባዳ እንበርታ ሙስሊሙ ያዝ አብሽር፡
በአስሮቹ ቀናት አሽረል አዋኺር፡
!! ☎️+251947999990 /+251933444400
📍 ቦሌ ፍሬንድሺፕ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304/4
አልረያን ሀጅና ኡምራ አገልግሎት