AWULA TOUR and Travel

AWULA TOUR and Travel አውላ የጉዞ ወኪል

04/11/2025

ከቦታው
ምሽት 3 ሰዓት። ከአውላ የጉዞ ወኪል ጋር በመተባበር በመጀመሪያው ዙር የዑምራ ጉዞ ከተሳተፍን ጥቂት ተጓዦች ጋር፣ ከመስጂደል ሐራም በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የኮንትራት ታክሲ ይዘን ወጣን። በግምት አምስት ኪሎ ሜትር ያህል ከተጓዝን በኋላ፣ በግርማ ሞገስ ወደቆመው ጀበለ ኑር (የብርሃን ተራራ) ግርጌ ደረስን። ይህ ሰማይ ጠቀስ ተራራ ከባሕር ወለል በላይ 642 ሜትር ገደማ ከፍታ እንዳለው የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ።

በዚህ ተራራ አናት ላይ የሚገኝ አንድ ታሪካዊ ጎድጓዳ ስፍራ አለ። የሒራእ ዋሻ ይሰኛል። ከስሩ ሽቅብ ወደ ተራራው ጫፍ ሲመለከቱ፣ አቀበቱ ወደ ሰማይ የሚወጣ ግዙፍ መሰላል የመሰለ አስፈሪ ገጽታ መላበሱን ያስተውላሉ። ይህን ፈታኝ አቀበት ከሦስት ዓመታት በፊት የመውጣት ዕድል አጋጥሞኝ ነበር። በወቅቱ፣ ተራራውን ከእግር እስከ አናቱ ለመጨረስ የፈጀብኝ 38 ደቂቃዎች ብቻ ነበር።

ዘንድሮ ደግሞ፣ በምሽቱ የመካ ነፋሻማ አየር ታግዘን፣ በጋራ በጀመዓ አቀበቱን መውጣት ጀመርን። በመንገዳችን ላይ በተደጋጋሚ የምናገኛቸው የደቡብ፣ የደቡብ-ምሥራቅ እና የመካከለኛው ኤዥያ አገራት ዜጎች ናቸው። ጀርባቸው ላይ መቀነት አስረው መሬቱን ላፍ ላፍ እያሉ የሚወጡ የቱርክ አረጋውያንንም አስተውለናል። በተለይም ከደቡብ ኤዥያ የመጡት ዜጎች፣ ተራራውን በተደጋጋሚ የመውጣት ልምድ ያካበቱ ይመስል፣ እንደ አትሌት በቅልጥፍና ሲያልፉን ነበር።

​የእኛ ጉዞ ቀስ ያለ ነበር፤ እንዲያውም ከኤሊ ትንሽ የፈጠነ እንጂ የሚያስደንቅ ፍጥነት አልነበረንም። የጋራው ጉዞ በደካማው ተጓዥ ፍጥነት መጓዝ ስለነበረበት፣ የተወሰነ ወደ ኋላ ቀርተናል። የልባችን ምት ካኒቴራችንን ማራገብ ሲጀምር ልብ ስራዋን ለማቆም የዳዳት ይመስላል። አልፎ አልፎ መንገድ ላይ ውሃ የሚሸጡ ሰዎች ባይኖሩ ኖሮ፣ ምላሳችን ከላንቃችን ተጣብቆ ድምጻችን ይሰወር ነበር።

እንደምንም ብለን፣ ከ55 ደቂቃዎች ፈታኝ ጉዞ በኋላ፣ የተራራው ጫፍ ላይ ደረስን። በብርሃን ያሸበረቀችውን መካ ቁልቁል ስንመለከት፣ ከ14 ክፍለዘመናት በፊት ጭል ጭል በሚል የቀንዲል ብርሃን የምትታወቀው መካ፣ በዓይነ-ሕሊናችን ታየችን። በኡስታዝ ዐብዱረሕማን ሙሐመድ የሚመራው የምሽት ቅፍለትም ቁርኣን ለመጀመሪያ ጊዜ በወረደበት የተራራው ክፍል ሰፈረ። ጋሩ ሒራእ እያለም በቦታው እንዲህ ዘመረ።

«ጉዞዎ በአደራችን»
​አውላ የጉዞ ወኪል፣ ቀጣይ ከታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ል እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ል ለሚያደርገው ሁለተኛ ዙር የዑምራ ጉዞ፣ እንግዳ ሆናችሁ ከኛ ጋር ያማረና ምቹ ቆይታ እንድታደርጉ በሩን ከፍቶ ይጠብቃችኋል።

13/08/2025

ለመሄድ የምንዘጋጀው ፣ ታሪክ በራሱ አንደበት ያለፉ ክስተቶችን ወደሚተርክበት የምድር ክፍል ነው። የእስልምና ዓለም የልብ ትርታ ማዕከል ወደሆነችው ቅዱስ ስፍራ። በረቂቅ ጥበብ የተሰራውና በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊ ሕንፃዎች መካከል አንዱ ወደሆነው ካዕባ። በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ከምንጩ ሳይደርቅ የቢሊዮኖችን ጥም እየቆረጠ ዘላለማዊ ተዓምር ወደሆነው የዘምዘም ውሃ። ወደ ታላቁ ሰው የትውልድ መናገሻ ከተማ - መካ።

ሌላው የጉዟችን አቅጣጫ ​መዲና ናት። ከሌሎች ከተሞች ትለያለች። የብርሃን እና የሰላም ከተማ። ኢስላማዊ መንግስትን ለመመስረት ታላቁ ስደት የተፈፀመባት ምድር። የነብዩ መሐመድ (ﷺ) ክቡር አካል ያረፈበትን መስጂድ አል-ነበዊይ በእቅፏ የያዘች ከተማ። ነፍስ ንጽህናዋን ለመመለስ ዕድል የምታገኝበት ቀዬ። ልብ እምነቷን ለማደስ ዕጣ የምትጎናጸፍበት ምድር።

​ከኛ ጋር የምታደርጉት ጉዞ ፣ ከራስ ጋር ለመገናኘትና የማይረሳ መንፈሳዊ ተሞክሮ ለመላበስ ነው። ኢንሻአላህ።

゚viralシ

10/08/2025

Check out AWLA TOUR & TRAVEL’s video.

ታላቁ ወርሃ ረመዷን ሲገባ በኛ አካባቢ ሁሌም አንድ ተወዳጅ ስብዕና ይታወሳሉ። ረመዷንን ተከትሎ የእሳቸውን ወደ ባቲ መምጣት የሚሰማ የከተማው ነዋሪ እንደ ንብ መንጋ ወደ ታላቁ የባቲ ጃሚዕ ...
03/08/2025

ታላቁ ወርሃ ረመዷን ሲገባ በኛ አካባቢ ሁሌም አንድ ተወዳጅ ስብዕና ይታወሳሉ። ረመዷንን ተከትሎ የእሳቸውን ወደ ባቲ መምጣት የሚሰማ የከተማው ነዋሪ እንደ ንብ መንጋ ወደ ታላቁ የባቲ ጃሚዕ መስጂድ ይተማል። መስጂዱ በምዕመናን ብዛት ከአፍ እስከ ገደፉ ይሞላል። ጠጠር መጣያ ቦታ ይቅርና ነፋስ ማስገቢያ ስንጥቅ ይጠፋል።

ሸይኽ ያሲን ጀማል ይባላሉ። ወረባቦ ያፈራቻቸው አንደበተ ርቱዕ ዳዒየህ ናቸው። ከሰውነታቸው ላይ ቀላል መጎናጸፊያቸውን ጣል አድርገው ማይኩን ሲጨብጡ ፣ ከሰማይ አንዳች ነገር ያረበበ ይመስል ታዳሚው በጸጥታ ይዋጣል። ከጣፋጭ አንደበታቸው በሚወጡት የቁርኣን አናቅጽ የልጅ አዋቂውን ልብ ይቆጣጠሩታል። አንዱን የቁርኣን አንቀጽ ካብራሩ በኋላ ወደሌላው አንቀጽ የሚሻገሩበት ፍጥነት እጅን በአፍ ያስጭናል። ንግግራቸው ኮለል ብሎ እንደሚፈስ የምንጭ ውኃ የደረቀን ልብ ያረሰርሳል። ከአላህ ጋር እርቅ የፈለገን ፍጡር ቆራጥ ያደርጋል። ሸይኽ ያሲን ጀማል በመንፈሳዊነት ድርቅ የተመታውን ምዕመናን ለማከም ከአገሪቱ ርዕሰ መዲና እስከ ክልል ከተሞች የሚዘልቁ ተንቀሳቃሽ ዳዒየህ በመሆናቸው ለብዙኋን እንግዳ ይሆናሉ ብለን አንጠብቅም።

አውላ የጉዞ ወኪል፣ ከሸይኽ ያሲን ጀማል ጋር በእኔ አስተባባሪነት ከመስከረም 7/2018 ዓ.ል እስከ መስከረም 18/2018 ዓ.ል ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር የዑምራ ጉዞ ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ያበስራል። ይህ ፓኬጅ በመካ 7 ቀናት እና በመዲና 4 ቀናትን ያካትታል።

ምግብ በቅመም እንደሚጣፍጥ፣ ዑምራንም ከሸይኽ ያሲን ጀማል ጋር ማሳለፍ በህይወት ውስጥ የማይረሳ ጣፋጭ ትዝታ እንደማኖር ነው።

ለመመዝገብ በዚህ ይደውሉ

📞 + 251943989999
+ 251911955887

በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ለማናገር
+251921555158 ወይም

አድራሻ 👉 ቤተል ፊውቸር ሞል ሶስተኛ ፎቅ - ቢሮ ቁጥር 305

゚viralシ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AWULA TOUR and Travel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share