05/06/2026
✝️ ኤረር በዓታን በጸሎት ሰሚነቷ ሲመሰከርላት ጠዋት ነግረዋት ለማታ ናት ሲሏት እኔስ መቼ ይሆን ተራዬ ደርሶ ከደጇ ደርሼ ጸሎቴን ሰምታ እንደሌሎቹ የምመሰክረው እያልኩኝ ደጇን ለመርገጥ ብዙ ፈተናዎች ሲገጥሙኝ ነገ ስል ዛሬ ብቻ ተፈቀደልኝ እና ደጇ ደረስኩኝ የእውነት የሄዳቹህ ሰዎች መቼም ትረዱኛላቹህ የቦታውን ሰላም እና የሚሰጠውንን መረጋጋት አውደ ምህረቱ ላይ በምስክርነት ተጨናንቋል ከ 11 አመት በኋላ በልጅ የተባረኩ እና ከዲስክ መንሸራተት የተፈወሱ ብቻ ብዙ ምስክርነቶች ተነገሩ አሁን እኔም ተስፋዬ ለመለመ እመቤታችን ያረፈችበትን ቅዱሳን አባቶች የተሰወሩበትን ዋሻ ለመጎብኘት ተራራውን ስንወጣ እንደ እብድ እየለፈለፍኩ እና እያለቀስኩ እመቤቴ ሆይ የኔንም ጸሎት መልሺ እያልኩ ከቦታው ደረስን ጸሎትና ልመናዬ ብሰራ ብሰራ አልለወጥ ያለውን ስራዬን እንድትባርክልኝ እና አታገቢም እንድ እድሜሽ ሄደ እኮ የሚለውንን የሰቀቀን ጥያቄ እንድታስቆምልኝ ነበር ለካ የጥያቄዬ መልስ ሁሉ ከደጇ ነበር የቅዱሳኑን አጽም አይተን ይዘውት በነበረው መስቀል ተባርከን ስንወጣ እንባዬን እንድጠርገው ሶፍት ያቀበለኝ አንድ ወጣት ዛሬ የትዳር አጋሬ እና የሁለት ልጆቼ አባት ሆኗል የኔ ጸሎት እስከ ማታም አልቆየም ስራዬንም ባርካልኝ እዳዬን ከፍዬ ለሰው ተርፊያለው በደጇ ጋብቻችንን አለመፈጸማችን ቢቆጨንም ልጆቻችንን ለሷ ሰተን ክርስትና አስነስተናል የኤረሯ እናቴ ዛሬም ድረስ ጸሎቴን አታሳድርብኝም እኔን የሰማች እናቴ የእናንተንም ጸሎት አታሳድርባችሁ🙏 ወደዚህ ልዩ #የምስክርነት፣ #የበረከት፣ #የቃልኪዳን ስፍራ ።
የመነሻ ቦታ:➛
አብረውን ለመጓዝ በስልክ ቁጥር
📱
📱
ትኬቱንም በአካል
ማግኘት ይችላሉ።
#ይደርስዎታል
ይህን ቁጥር:➛⓪❾-➌⓪-➋➏-➊➏-➊➏ ይጠቀሙ።