ZAD Tour & Travel Agent / ዛድ ትራቭል

ZAD Tour & Travel Agent / ዛድ ትራቭል Your trusted companion on the sacred journey of Umrah. Provision for the soul, peace for the heart.

ስለ አዲሱ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ እውነታው‼============================(ከዛድ ቱር & ትራቭል የተሰጠ ማብራሪያ)||✍️ እንደሚታወቀው የሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስ...
14/08/2026

ስለ አዲሱ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ እውነታው‼
============================
(ከዛድ ቱር & ትራቭል የተሰጠ ማብራሪያ)
||
✍️ እንደሚታወቀው የሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ከሐምሌ 13/2018 E.C. (July 20, 2026) ጀምሮ አዲስ የዑምራ ቪዛ ህግ በይፋ ሥራ ላይ አውሏል። በዚህም መሠረት በ13ኛው ዙር (ከሐምሌ 23 እስከ ነሐሴ 03) የተጓዙ ተጓዦቻችን
ያወረድንላቸው ቪዛ የ1 ዓመት ቪዛ ነበር።

⚠️ ትክክለኛው እውነታ እና ህዝቡ ሊያውቀው የሚገባው ማብራሪያ፦

✅ አንዳንድ ኤጀንሲዎች “እኛ የምንሰጠው የ1 ዓመት ቪዛ ስለሆነ ዋጋው ይጨምራል” ወይም “ልዩ የ1 ዓመት ቪዛ አዘጋጅተናል” በማለት ተጓዦችን ሲያደናግሩ ይስተዋላል።

▫️ እውነታው ግን ይህ ነው፦
ይህ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ የሳዑዲ መንግሥት በሲስተም ደረጃ ለሁሉም ተጓዦች በይፋ የደነገገው አዲስ አሰራር እንጂ፣ የትኛውም የጉዞ ወኪል (ኤጀንሲ) በራሱ ጥረት የሚያስጀምረው ወይም የሚቀይረው ልዩ ቪዛ አይደለም! በአሁኑ ሰዓት የሚወጡ የዑምራ ቪዛዎች
በሙሉ በሳዑዲ ህግ መሠረት የ1 ዓመት ቪዛ ናቸው። የተለመደውን የ3 ወሩን እናውርድ ቢሉ ራሱ አይችሉም። By default ቫሊዲቲው 1 አመት ነው። ከታች ያያዝነውን የኡስታዝ ሳሊምን የባለፈ ቪዛ ተመልከቱት።

💎 በዚህ ከተስማማን አዲሱ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ እንዴት ይሠራል? እስከዛሬ የ1 አመት ሲባል ደጋግሞ ለቪዛ ተብሎ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ መግባትና መውጣት የሚቻልበት multiple entry ነው ወይንስ የሚለይ ነገር አለው?

እውነታው፦

1️⃣ የቪዛው ቆይታ (Validity)፦ ቪዛው ከተቆረጠበት ቀን ጀምሮ ለ365 ቀናት (ለ1 ሙሉ ዓመት) ያገለግላል።

2️⃣ ተደጋግሞ መግባት (Multiple-Entry)፦
በዓመቱ ውስጥ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በተደጋጋሚ መግባት እና መውጣት ይቻላል።

3️⃣ የመቆያ ጊዜ (Duration of Stay)፦
በነዚህ 365 ቀናት ውስጥ አጠቃላይ በሳዑዲ የሚያሳልፉት ድምር ጊዜ ከ90 ቀናት (3 ወራት) መብለጥ የለበትም። (ለምሳሌ፦ ለመጀመሪያ ጉዟችሁ 30 ቀን ብትቆዩ፣ በቀሪው የዓመቱ ጊዜያት ውስጥ የቀሩትን 60 ቀናት ተከፋፍለው መጠቀም ትችላላችሁ)። ከፈለጋችሁ በ1 ጉዛችሁ 10 ቀናት ብቻ ከሆነ የምትቆዩት፤ 9 ጊዜ መመላለስ ትችላላችሁ። 9*10= 90።

4️⃣ ነገር ግን ለቀጣይ ጉዞዎች የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፦

➡️ በቪዛው ድጋሚ ለመጓዝ ስትፈልጉ፣ ከመጓዛችሁ በፊት በNusuk (ኑሱክ) ፕላትፎርም (መጀመሪያ ባወጣላችሁ ኤጀንት) በኩል የአገልግሎት ፓኬጅ መግዛት አለባችሁ።

➡️በNusuk መተግበሪያ በኩል የዑምራ ፈቃድ (Permit) ማውጣት ግዴታ ነው።

ይህ እስከዛሬ ከተለመደው የ1 አመት ቪዛ የሚለየው ነጥብ ነው። ይህ የአገልግሎት ፓኬጅ ደግሞ አሁን ላይ ክፍያው 5000 ሪያል አካባቢ ነው። በኢትዮ ሲመነዘር፤ ለ1 ሙሉ ፓኬጅ ከሚከፈለው ይበልጣል። ምናልባት ቀስ በቀስ ሥራው ሲለመደው ሳዑዲዎች ይህን ዋጋ ካላሻሻሉት በስተቀር፤ አሁን ባለው ተጨባጭ የ1 አመት መሆኑ በ1 ጉዞ 3 ወር ሙሉ ለሚቆይ እንጂ ለሚመላለስ ፋይዳ የለውም ማለት ይቻላል።

5️⃣ ይህ ቪዛ በሐጅ ወቅት (ከዙልቂዕዳ 1 እስከ ዙልሒጃ 13) አገልግሎት አይሰጥም፤ ለሐጅ መግቢያነትም አይሆንም።

🔸 እኛ ሁልጊዜም ለደንበኞቻችን ግልጽ፣ ታማኝ እና ከማንኛውም የተሳሳተ ማስታወቂያ (Fake Marketing) የጸዳ አገልግሎት መስጠትን መርሃችን ነው።

የዑምራ ጉዟችሁን በዘመናዊ፣ አስተማማኝ እና ምቹ በሆነ መልኩ ለማካሄድ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ለማግኘት
በራችን ክፍት ነው!

አግኙን፦

📞 ስልክ ቁጥር፦ 0985222666/0986111333

📱 ቴሌግራም/ዋትስአፕ፦

🌐 www.zadtravelagency.com
🔸 [email protected]

09/08/2026

የዛድ የክረምት ልዩ የዑምራ የጉዞ ፓኬጆች!🕋

▫️ የአላህን ቤት ለመዘየር ለምትፈልጉ በሙሉ፤ የዛድ የጉዞ ኤጀንሲ ቀጣይ የጉዞ ፓኬጆችን ምዝገባ ለውስን ቦታዎች ክፍት አድርጓል።

የበረራ ቀኖቻችን (Rounds)፦

- 🛫 14ኛ ዙር፦ ከነሐሴ 14 – 24 (August 20-30)

- 🛫 15ኛ ዙር፦ ከነሐሴ 28 – መስከረም 03 (September 03-13)

- 🛫 16ኛ ዙር፦ ከመስከረም 07 – 17 (September 17-27)

💎 የፓኬጅ ዓይነቶችና ዋጋዎች፦

▫️ መደበኛ ፓኬጅ (Standard)፦ ሙሉ ፓኬጅ 150,000 ብር ብቻ! (7 ቀን መካ፣ 3 ቀን መዲና - በድምሩ 10 ቀናት)

▫️ ቪአይፒ ፓኬጅ (VIP)፦ 177,500 ብር (ተመሳሳይ ሆቴል ሆኖ ለ2 ቤተሰቦች ወይም ለባለ ትዳሮች ለብቻ የተዘጋጀ)

▫️ VVIP፦
220 ሺህ ብር (ለሐረም በጣም ቅርብ የሆኑ ሆቴሎች ለቤተሰብ የተዘጋጀ)

▫️ VVIP Premium፦
285 ሺህ ብር (ለሐረም በጣም ቅርብ የሆኑ ሆቴሎች፣ ለባለ ትዳሮች የተዘጋጀ)

የፓኬጃችን አገልግሎቶች፦

1️⃣ የደርሶ መልስ ትኬት እና ቪዛ

2️⃣ ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብና ጥራት ያላቸው ሆቴሎች (መዲና፦ ዲያረ ጦይባና ዲያረል ሐቢብ ሆቴል / መካ፦ አብራጀ ተይሲር)

Map location: https://zadtravelagency.com/emergency-address

3️⃣ ሙሉ የትራንስፖርት ወጪና የታሪካዊ ቦታዎች ዚያራ (ጉብኝት)

4️⃣ ልምድ ያላቸው አስጎብኚዎችና ከጉዞ በፊት የዑምራ አደራረግ ስልጠና

⚠️ ማሳሰቢያ፦ ባለፈው ዙር እንደተከሰተው ቦታው ከሞላ በኋላ ተጨማሪ ምዝገባ የማናደርግ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን።

📞 ለመመዝገብ እና ለበለጠ መረጃ፦

- 💬 በቴሌግራም፦

- 📱 በዋትስአፕ፦ 0986111333

- 📞 በስልክ መስመር፦ 0985222666

- 🌐 የቴሌግራም ቻናላችን፦ t.me/ZadTravelAgency

- 🌎 ድረ-ገጽ፦ www.zadtravelagency.com

Your trusted companion on the sacred journey of Umrah. Provision for the soul, peace for the heart.

ከሰኔ 18–28 (June 25– July 05) ያዘጋጀነው የዑምራ ፓኬጃችን የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ በትናንትናው ዕለት ተጠናቋል።እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ 3 ቀናት ሁለተኛ ዙር ምዝገባ በማይታ...
18/06/2026

ከሰኔ 18–28 (June 25– July 05) ያዘጋጀነው የዑምራ ፓኬጃችን የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ በትናንትናው ዕለት ተጠናቋል።

እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ 3 ቀናት ሁለተኛ ዙር ምዝገባ በማይታመን ልዩ ቅናሽ ለጥቂት ሰዎች ብቻ ጀምረናል።

ለመመዝገብ፦ በዋትስ አፕ 0985 111 333 ወይም በቴሌግራም ላይ ያናግሩን።

ለመደወል ስልክ፦
09 85 222 666

📍በአካል ቢሮ መጥታችሁ ለመመዝገብ፦ ቤተል ፋሚሊ ታወር 3ኛ ፎቅ: 310

ቀጣይ ዙር ከነ ቤተሰባችሁና ልጆቻችሁ የምትጓዙበት ከሐምሌ 23– ነሐሴ 03, ከነሐሴ 28– መስከረም 3 ልዩ የክረምት ፓኬጆችንም ስላዘጋጀን ከወዲሁ በመመዝገብ ቦታችሁን ያዙ።

[email protected]

www.zadtravelagency com

ልዩ የክረምት የዑምራ ፓኬጃችን በይፋ ተጀምሯል‼===========================✍️ ውድ የዛድ ትራቭል ቤተሰቦች፤ እነሆ የዑምራ ፓኬጅት መሰናዷችን በአዲሱ የዑምራ ሲዝን ምዝገባ ጀ...
01/06/2026

ልዩ የክረምት የዑምራ ፓኬጃችን በይፋ ተጀምሯል‼
===========================
✍️ ውድ የዛድ ትራቭል ቤተሰቦች፤ እነሆ የዑምራ ፓኬጅት መሰናዷችን በአዲሱ የዑምራ ሲዝን ምዝገባ ጀምረናል።

ባለፈ አመት መሃል ላይ መጀመራችን፣ በቀጥታ የሆቴልና የቪዛ አቅርቦትን በራሳችን አለመስጠታችን፣ ለሥራውም አዲስ መሆናችን ጥቂት ለማይባሉ ክፍተቶች ቢዳርገንም፤ እነሆ ዘንድሮ በአዲስ አመት፣ በአዲስና ዘመናዊ አሠራር ሙሉ በሙሉ በራሳችን ጀምረናል።

ከሐጅ በኋላ ከሰኔ 18–28, 2018 E.C. (June 25– July 05, 2026) ሁለት ጁሙዓህ ሐረም ላይ የምትሰግዱበትን ልዩ የክረምት የዑምራ ፓኬጅ ምዝገባ በይፋ መጀመራችንን ስናበስራችሁ በደስታ ነው።

የዑምራህ ፓኬጃችን የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያካትታል፦

1️⃣ የደርሶ መልስ ትኬት፣
2️⃣ ቪዛ፣
3️⃣ መካና መዲና ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብ የሆኑና ጥራታቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣
4️⃣ ሙሉ የትራንስፖርት ወጪ፣
5️⃣ የታሪካዊ ቦታዎች ዚያራ/ጉብኝት፣
6️⃣ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አብረው ሆነው ዑምራህ የሚያስደርጉ ልምድ ያላቸው አስተባባሪዎች፣
7️⃣ ከዑምራህ በፊት ስለ ዑምራህ አደራረግና ቅድመ ዝግጅት ስልጠና።

ለመመዝገብ፦ በዋትስ አፕ 098 611 1333 ወይም በቴሌግራም ላይ ያናግሩን።

ለመደወል ስልክ፦
09 85 222 666

📍በአካል ቢሮ መጥታችሁ ለመመዝገብ፦ ቤተል ፋሚሊ ታወር 3ኛ ፎቅ: 310

💰ክፍያ ለጥቂት ቀናት የሚቆይ ቅናሽ ስላዘጋጀን:

➡️ ለ1 ወይም 2 ሰው ሙሉ ፓኬጅ 165 ሺህ ብር፣

➡️ 3 እና 4 ሆነው ለሚመጡ የ1ሰው ሙሉ ፓኬጅ 164 ሺህ ብር፣

➡️ 5 እና 6 ሆነው ለሚመጡ የ1ሰው ሙሉ ፓኬጅ 163, 500 ብር፣

➡️ ከ7–10 ሆነው ለሚመጡ የ1 ሰው ሙሉ ፓኬጅ 163 ሺህ ብር፣

➡️ ከ10 በላይ እስከ 20 ሆነው ለሚመጡ የ1 ሰው ሙሉ ፓኬጅ 162 ሺህ ብር፣

▫️ ከ20 በላይ ሆነው ለሚመጡ ለየት ያለ ፓኬጅ አዘጋጅተናል።

ብዙ ጊዜ መሄጃ ቀኑ ሲደርስ መመዝገብ የተለመደ ስለሆነ፤ ቀድሞ ሳይሞላባችሁ ከወዲሁ እንድትመዘገቡ እንመክራለን።

🛫 ቻነላችን፦ t.me/ZadTravelAgency

🌐 ድረ ገፅ፦ www.zadtravelagency.com

💼 [email protected]
✍️ [email protected]

ልዩ የክረምት የዑምራ ፓኬጃችን በይፋ ተጀምሯል‼===========================✍️ ውድ የዛድ ትራቭል ቤተሰቦች፤ እነሆ የዑምራ ፓኬጅት መሰናዷችን በአዲሱ የዑምራ ሲዝን ምዝገባ ጀ...
21/05/2026

ልዩ የክረምት የዑምራ ፓኬጃችን በይፋ ተጀምሯል‼
===========================
✍️ ውድ የዛድ ትራቭል ቤተሰቦች፤ እነሆ የዑምራ ፓኬጅት መሰናዷችን በአዲሱ የዑምራ ሲዝን ምዝገባ ጀምረናል።

ባለፈ አመት መሃል ላይ መጀመራችን፣ በቀጥታ የሆቴልና የቪዛ አቅርቦትን በራሳችን አለመስጠታችን፣ ለሥራውም አዲስ መሆናችን ጥቂት ለማይባሉ ክፍተቶች ቢዳርገንም፤ እነሆ ዘንድሮ በአዲስ አመት፣ በአዲስና ዘመናዊ አሠራር ሙሉ በሙሉ በራሳችን ጀምረናል።

ከሐጅ በኋላ ከሰኔ 18–28, 2018 E.C. (June 25– July 05, 2026) ሁለት ጁሙዓህ ሐረም ላይ የምትሰግዱበትን ልዩ የክረምት የዑምራ ፓኬጅ ምዝገባ በይፋ መጀመራችንን ስናበስራችሁ በደስታ ነው።

የዑምራህ ፓኬጃችን የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያካትታል፦

1️⃣ የደርሶ መልስ ትኬት፣
2️⃣ ቪዛ፣
3️⃣ መካና መዲና ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብ የሆኑና ጥራታቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣
4️⃣ ሙሉ የትራንስፖርት ወጪ፣
5️⃣ የታሪካዊ ቦታዎች ዚያራ/ጉብኝት፣
6️⃣ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አብረው ሆነው ዑምራህ የሚያስደርጉ ልምድ ያላቸው አስተባባሪዎች፣
7️⃣ ከዑምራህ በፊት ስለ ዑምራህ አደራረግና ቅድመ ዝግጅት ስልጠና።

ለመመዝገብ፦ በዋትስ አፕ 098 611 1333 ወይም በቴሌግራም ላይ ያናግሩን።

ለመደወል ስልክ፦
09 85 222 666

📍በአካል ቢሮ መጥታችሁ ለመመዝገብ፦ ቤተል ፋሚሊ ታወር 3ኛ ፎቅ: 310

💰ክፍያ ለጥቂት ቀናት የሚቆይ ቅናሽ ስላዘጋጀን:

➡️ ለ1 ወይም 2 ሰው ሙሉ ፓኬጅ 165 ሺህ ብር፣

➡️ 3 እና 4 ሆነው ለሚመጡ የ1ሰው ሙሉ ፓኬጅ 164 ሺህ ብር፣

➡️ 5 እና 6 ሆነው ለሚመጡ የ1ሰው ሙሉ ፓኬጅ 163, 500 ብር፣

➡️ ከ7–10 ሆነው ለሚመጡ የ1 ሰው ሙሉ ፓኬጅ 163 ሺህ ብር፣

➡️ ከ10 በላይ እስከ 20 ሆነው ለሚመጡ የ1 ሰው ሙሉ ፓኬጅ 162 ሺህ ብር፣

▫️ ከ20 በላይ ሆነው ለሚመጡ ለየት ያለ ፓኬጅ አዘጋጅተናል።

ብዙ ጊዜ መሄጃ ቀኑ ሲደርስ መመዝገብ የተለመደ ስለሆነ፤ ቀድሞ ሳይሞላባችሁ ከወዲሁ እንድትመዘገቡ እንመክራለን።

🛫 ቻነላችን፦ t.me/ZadTravelAgency

🌐 ድረ ገፅ፦ www.zadtravelagency.com

💼 [email protected]
✍️ [email protected]

አዲሱ የዑምራ ጉዞ ዘመን በዛድ ትራቭል‼==========================✍️ የአር-ረሕማን እንግዶችን በተቻለ መጠን በከፍተኛ ክብር ማገልገል የጀመረው ዛድ ትራቭል ኤጀንሲ (Zad T...
09/04/2026

አዲሱ የዑምራ ጉዞ ዘመን በዛድ ትራቭል‼
==========================

✍️ የአር-ረሕማን እንግዶችን በተቻለ መጠን በከፍተኛ ክብር ማገልገል የጀመረው ዛድ ትራቭል ኤጀንሲ (Zad Travel Agency)፣ ከተመሰረተ ገና አንድ ዓመት እንኳ ሳይሞላው በኢትዮጵያ የዑምራ ጉዞ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 500 የሚጠጉ ተጓዦችን በተሳካ ሁኔታ በማስተናገድ፣ በርካታ የአር'ረሕማን እንግዶችን ወደ ሐረም በመውሰድ ግንባር ቀደም መሆን መቻላችን የአላህ ፈቃድና የናንተ የደንበኞቻችን እምነት ውጤት ነው። አል-ሐምዱ ሊላህ!

አዲስ እንደመሆናችን መጠን፣ የቪዛ፣ የሆቴል እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በቀጥታ (B2B) ከሳዑዲ ዓረቢያ ኩባንያዎች ያለማግኘታችን ክፍተትና የሦስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት በስራችን ላይ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይህን መሰረታዊ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍና ለሙዕተሚሮቻችን እንግልት-አልባ አገልግሎት ለመስጠት፣ በመዲና ከተማ በተካሄደው ግዙፉ የዑምራና ዚያራ ፎረም (Umrah and Ziyarah Forum) ላይ በአካል ተገኝተናል።

የዛድ ትራቭል ልዩ ስኬት በፎረሙ ላይ፦
☑ በፎረሙ ላይ ከተሳተፉት በመቶዎች ከሚቆጠሩ የሳዑዲ ካምፓኒዎች መካከል፣ በጥብቅ መስፈርቶችና በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅም መመዘኛ በማወዳደር ከ 5 ግዙፍ እና ምርጥ የዑምራ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር ታሪካዊ የትብብር ስምምነቶችን (Agreements) በይፋ ተፈራርመናል።

ይህ ድል፣ ዛድ ትራቭልን ከበርካታ የሳዑዲ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በአንድ ጊዜ በመፈራረም በኢትዮጵያ ብቸኛው እና ቀዳሚው ኤጀንሲ ያደርገዋል!

ከመደበኛው የዑምራ አገልግሎት ስምምነት ባሻገር፣ እነዚህን ተቋማት የመረጥንበት ዋነኛው ምክንያት፦
1⃣) ብዙዎቹ ከ45 ዓመታት በላይ የዘርፉ ልምድ ያላቸው አንጋፋ ተቋማት በመሆናቸው።

2⃣) የቴክኖሎጂ ውህደት (API Integration)፡ የዑምራ አገልግሎት አሰጣጡን ሙሉ በሙሉ ዘመናዊና (Automated) ለማድረግ፣ የእነሱን ሲስተም በቀጥታ ከዛድ ትራቭል ድረ-ገጽ (Portal) ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል አቅም ያላቸው በመሆናቸው ነው።

ይህ ለናንተ ለተጓዦች ምን ማለት ነው?

⬇️ ቀጥተኛ እና ተወዳዳሪ ዋጋ፡ ደላላን እና የሦስተኛ ወገን ወጪን በማስቀረት፣ ጥራት ያለው የዑምራ ፓኬጅን በተመጣጣኝና ርካሽ በሚባል ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላል።

⬇️ ፈጣን እና አስተማማኝ ሲስተም፡ የቪዛ፣ የሆቴል እና የትራንስፖርት ምዝገባዎን በተቀላጠፈ የቴክኖሎጂ አሰራር ያለ ምንም መጉላላት ያጠናቅቃሉ።

⬇️ የተሟላ ዋስትና፡ በመካና መዲና ጠንካራ መሠረት ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በቀጥታ በመስራታችን፣ ቆይታዎ የተረጋጋ እና ምቹ ይሆናል።

🎀 ዛድ ትራቭል የዑምራን ጉዞ ከባህላዊ አሰራር አውጥቶ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ሐቅና አማናን የጠበቀ፣ ዘመናዊ አገልግሎት ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። ለቀጣዩ ዓመት የዑምራ ጉዞ፣ የነበሩ ክፍተቶችን በመቅረፍና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጥራቱን የጠበቀ እና የተቀናጀ አገልግሎት ለመስጠት መንገዱን ጠርገን፣ ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀን እየጠበቅንዎት ነው!

የተቀደሰውን ጉዞዎን፣ ዘመናዊና አስተማማኝ በሆነው ዛድ ትራቭል ያድርጉ!

ዛድ ትራቭል ኤጀንሲ (የቴክኖሎጂ እና የመንፈሳዊነት ጥምረት!)

🌐 www.zadtravelagency.com
📱 t.me/ZadTravelAgency

የስልጠና ጥሪ‼===========✍️ ከረመዿን 16–29፣ 19–29፣ 19– ሸዋል 04 በኤጀንሲያችን የተመዘገባችሁ የ Zad Travel Agency / ዛድ ቤተሰቦች በሙሉ፤ ልዩ የዑምራ ስልጠና...
01/03/2026

የስልጠና ጥሪ‼
===========
✍️ ከረመዿን 16–29፣ 19–29፣ 19– ሸዋል 04 በኤጀንሲያችን የተመዘገባችሁ የ Zad Travel Agency / ዛድ ቤተሰቦች በሙሉ፤ ልዩ የዑምራ ስልጠና ከልዩ የኢፍጣር መሰናዶ ጋር የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 24, 2018 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በወዳጅነት ፓርክ (ቤተ መንግስቱ አጠገብ – ሸራተን ፊት ለፊት) ስለተዘጋጀላችሁ፤ ሁላችሁም ቀድማችሁ በቦታው እንድትገኙ።

ስልጠናው በሸይኽ ዐብዱ-ስ'ሰላም አንዋር፣ ኡስታዝ ሸሃቡድን ሸኑራ እና ኡስታዝ ወ ኢንጂነር ጂብሪል አክመል ይሰጣል።

አሁንም መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁለተኛ ዙር ስለጀመርን ከፈጠናችሁ ትችላላችሁ።

መመዝገብ የምትፈልጉ ወይም በዋትስአፕ 09 85 222 666 አናግሩን።

ከረመዿን፦

➡️ 16–29 (2ኛ ዙር) ⬅️ 280 ሺህ ብር፣
➡️ 19–29 (1ኛ ዙር) ⬅️ 270 ሺህ ብር፣
➡️ 19– ሸዋል 04 ⬅️ (ይህ ሞልቷል፣ ሁለተኛ ዙር አንጨምርም በዚህ!)

የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ።

ከረመዿን ፓኬጅ ውጭ ሁለት ጁሙዓህ የምታገኙበት ከሸዋል 06–16 ስላዘጋጀን፤ የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ።

ይህን ወንድማችንን አስታወሳችሁት⁉️ይህ ወንድማችን በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ600ው 592 አካባቢ በማምጣት በሃገር አቀፍ ደረጃ 1ኛ ወጥቶ ነበር። በወቅቱ ወንድማችንን እና 590 አካ...
19/02/2026

ይህን ወንድማችንን አስታወሳችሁት⁉️

ይህ ወንድማችን በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ600ው 592 አካባቢ በማምጣት በሃገር አቀፍ ደረጃ 1ኛ ወጥቶ ነበር። በወቅቱ ወንድማችንን እና 590 አካባቢ ያመጣውን ሁለተኛ ደረጃ የወጣውን ጎሳን ለማበረታታት ብለን ሁለቱንም በናንተ ደጋጎች ቀና ትብብር የዑምራህ ሽልማት ሸልመናቸው ነበር። በወቅቱ የግቢ መግቢያ ፈተና ስለነበረባቸው ለመሄድ አልቻሉም ነበር። መጅሊስም ለወንድም ኻሊድ ከነ እናቱ የዑምራህ ሽልማት ሰጥቶት ነበር።

እነሆ ወንድማችን ኻሊድ ከወላጅ እናቱ ጋር ሆኖ በአሁኑ በ6ኛ ዙር የሸዕባን ፓኬጅ ተጓዦቻችን ጋር ወደ መከተል ሙከረማህ ካቀኑት የዑምራ ተጓዦቻችን መካከል አንዱ ነው።

የዚህ ዙር ተጓዦች ባለፈ ሐሙስ ወደ መካ አቅንተው ዑምራቸውን ፈፅመው፣ ከዚያም ወደ መዲነተል ሙነወራ በማቅናት ረመዿናቸውን እዛ ጀምረው፤ ዛሬ በአላህ ፈቃድ ድጋሜ በረመዿን ዑምራ እንዲሠሩ ስለተመቻቼ ወደ መከተል ሙከረማህ ያቀኑና የመካ ቆይታቸውን ሲጨርሱ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ይሆናል።
አላህ ይቀበላቸው።

በተከበረው የረመዿን ወር ዑምራህ ማድረግ ለምትፈልጉ የአሽረል አዋኺሩ የተወሰኑ ቦታዎች አሉን።

✅ ከረመዿን 6–16 (ሙሉ ፓኬጅ 225 ሺህ ብር)፣ ወይም
✅ ከረመዿን 16–29 ( የመጀመሪያ ዙሩ ተጠናቋል። ሁለተኛ ዙር ተጨማሪ ፓኬጅ ስላመቻቸን መመዝገብ ትችላላችሁ።)

√ ሙሉ ፓኬጅ 270 ሺህ ብር ነበር፤ አሁን ግን 280 ሺህ ብር ሆኗል፣ ወይም

✅ ከረመዿን 19–29 (ሙሉ ፓኬጅ 270 ሺህ ብር)፣

✅ ከረመዿን 19– ሸዋል 04 (ሙሉ ፓኬጅ 275 ሺህ ብር) አለን።

መመዝገብ የምትፈልጉ ወይም በዋትስአፕ 09 85 222 666 አናግሩን።

ወይም በድረገፃችን www.zadtravelagency.com ላይ አግኙን።

Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 21:00
Tuesday 09:00 - 21:00
Wednesday 09:00 - 21:00
Thursday 09:00 - 21:00
Friday 09:00 - 21:00
Saturday 09:00 - 21:00
Sunday 09:00 - 21:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ZAD Tour & Travel Agent / ዛድ ትራቭል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category