Trekking

Trekking Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Trekking, Eco tour agency, Piasa, Addis Ababa.

28/05/2022
15/05/2022

it is our damEthiopia
19/07/2021

it is our dam
Ethiopia

ባለሐገሩ አስጎብኚ የዘመድ ጥየቃ ፕሮግራም የሀገር ዉስጥ ጉብኝት   /የዘመድ ጥየቃ / መርሀ ግብርየጉዞ አይነት ፡ የዘመድ ጥየቃየሚጎበኟቸዉ ቦታዎች፡  ደ/ብርሃን ፤ አንኮበር ፤ ቁንዲና ሰሪ...
07/07/2021

ባለሐገሩ አስጎብኚ የዘመድ ጥየቃ ፕሮግራም
የሀገር ዉስጥ ጉብኝት /የዘመድ ጥየቃ / መርሀ ግብር
የጉዞ አይነት ፡ የዘመድ ጥየቃ
የሚጎበኟቸዉ ቦታዎች፡ ደ/ብርሃን ፤ አንኮበር ፤ ቁንዲና ሰሪቲ መንደር
የቆይታ ጊዜ ፡ 3 ቀን/ 2 ምሽት
የሚጠቀሙት የትራንስፖርት አይነት ፡ 4 እግር ተሸከርካሪ / ላንድ ክሩዘር/ ወይም ኮስተር ባስ
የተጓዦች ብዛት ፡
ዝርዝር መረጃ /Detailed Tour Package
የመጀመሪያ ቀን/First Day / ፡ መነሻ አዲስ አበባ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል እና እንግዶች የሚያመቻቸዉ ቦታ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዐት ሲሆን ከ 2፡00 ጉዞ በኋላ ደ/ብርሀን ደርሰን ከ 2፡00 -3፡00 ቁርስ ጌትቫ ሆቴል ወይንም ሎካል ሬስቶራንት በልተን ጉዞ ወደ እንቁላል ኮሶ እናደርጋለን ፡፡ እንቁላል ኮሶ በአለም ላይ የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአፍሪካ የድል አባት የሆኑት የንጉሰ ነገስት እምየ ምኒሊክ ዘኢትዮጵያ የተወለዱበት ቦታ ነዉ ፡፡ ከስዐት ወደ ቁንዲ በመንዳት በጣም በሚያምርና ደስ በሚል የመልከአምድር ቦታ የግማሽ ሰአት የእግር ጉዞ አድርገን አዳራችን ቁንዲ ይሆናል ፡፡
ምሽት ቀንዲ ካምፒንግ / overnight camping at Kundi village /

ሁለተኛ ቀን / Second Day / ፡ ቁንዲ - አንኮበር -ደብረብርሀን
ጠዋት ከ ቁንዲ በመነሳት ቁርስ በኋላ የአንኮበር በተመንግስትን እንጎበኛለን ፡፡
አንኮበር በመካከለኛው ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ ነው ፡፡ በአማራ ክልል አንኮበር ወረዳ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው አንኮበር ወደ 2,465 ሜትር (8,100 ጫማ) ከፍታ ላይ በሚገኘው የኢትዮ ደጋማ ምስራቅ አቋራጭ ላይ ይገኛል ፡፡ ከደብረ ብርሃን በስተ ምስራቅ 42 ኪ.ሜ እና ከአዲስ አበባ ሰሜን ምስራቅ 172 ኪ.ሜ ያህል ነው ፡፡
የአንኮበር ቤተ መንግስት 1830 ዓ.ም በንጉስ ሳህለስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራ ሲሆን አጼ ምኒሊክ ከ አጼ ቴዎድሮስ አምልጠዉ ወደ አንኮበር ከመጡ በኋላ በተመንግቱን በማደስ ሸዋን ያስተዳደሩ ሲሆን ንጉሱ አዲስ አበባን ከቆረቆሩ በኋላ በ እንጦጦ እና በ አዲስ አለም ካሰሯቸዉ ቤተ መንግስቶች ጋር ተመሳሳይነት የተላበሰ ነዉ ፡፡
የአንኮበር ቤተ መንግስት ማራኪ በሆነ መልከአምድር ላይ የተሰራ ከመሆኑ በላይ የታላቁ ስምጥ ሸለቆ የሚያልፍባቸዉን የ አፋር ዝቅተኛ ስፍራዎችን እስከ አዋሽ ድረስ መመልከት የሚያስችል እና ከባህር ወለል ጠለል በላይ በ 2870 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ስፍራ ነዉ ፡፡ የእምየ ምኒሊክ ቤተመንግስት አንኮበር ከጎበኘንና ምሳ ከበላን በኋላ ወደ ደብረብርሀን በመሄድ አዳራችንን ደብረብርሀን እናደርጋለን ፡፡


ሶስተኛ ቀን/ Third Day/ ፡ ደብረብርሀን-ሰርቲ መንደር- አዲስአበባ ጠዋት ከ ቁርስ በኋላ ወደ የዘመድ ጥየቃ ጉብኝት የምናድርግበትን የ ሰርቲ መንደርን እንጎበኛለን :: ሰርቲ የአርሶ አደር መንደር ሲሆን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አካካባቢ የሚገኝ ነዋሪዎች አማርኛና ኦሮሚኛ አቀላጥፈዉ የሚናገሩ ናቸዉ ፡፡ የገጠሩን ህይወት ምን እንደሚመስል ከስተማር አልፎ ገብኝዎች ሊያከናዉኑት የሚችሉት እንቅስቃሴዎች ማለትም ፈረስ መጋለበ፤ እርሻ ማረስ፤ ማጨድና መዉቃት ፤ አንጀራ መጋገር ፤ ጌሾ መዉቀጥ፡ እበት መጠፍጠፍ እንዲሁም ወተት መናጥ እና ሌሎችም የመሳሰሉትን እንቅስቃሴዎች በማድረግ የዘመድ ጥየቃ ጉብኝት ከጨረስን በኋላ ጉዟችንን ወደ አዲስ አበባ በማድረግ የመርሀ ግብራችን መጨረሻ ይሆናል ፡፡

ለበለጠ መረጃ 0987868686

  Boat timket/ Epiphany/ procession in Lake Ziway, Ethiopia.
17/01/2021



Boat timket/ Epiphany/ procession in Lake Ziway, Ethiopia.

Address

Piasa
Addis Ababa
2129

Telephone

0911434066

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Trekking posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share