Visit aregoba

Visit aregoba Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit aregoba, Travel Company, adis Ababa, Awash.

aregoba visit
05/12/2025

aregoba visit

የአርጎባ ልማት ማኅበር ምስረታ ፕሮግራም በዱባይ ተካሄደ::በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የአርጎባ ብሔረሰብ ተወላጆችንና ደጋፊዎችን በአንድነት ለማሰባስብና ለማደራጀት የተጠራው ስብሰባ በስ...
04/05/2025

የአርጎባ ልማት ማኅበር ምስረታ ፕሮግራም በዱባይ ተካሄደ::

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የአርጎባ ብሔረሰብ ተወላጆችንና ደጋፊዎችን በአንድነት ለማሰባስብና ለማደራጀት የተጠራው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንሱል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ፣ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማኅበር ም/ሊቀመንበር ወ/ሮ ሕሊና ታደሰ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮሚኒቲ ማኅበር የቦርድ አመራር አባላት፣ በኢትዮጵያ የአርጎባ ልማት ማኅበር ተወካይ አቶ እስማኤል ጠሃ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የብሔረሰቡ ተወላጆችና ደጋፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የልማት ማኅበር ተወካዮች በተገኙበት ምስረታው ተካሂዷል።

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሀገራችን ከ80 በላይ ብሔሮች ያሏት እንደመሆኗ እያንዳንዱ የራሱ ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ማነንት ያለው መሆኑን፣ ሁሉም ቋንቋውና ባህሉን የማሳደግ፣ የመንከባከብና የመጠበቅ መብት በሕገ-መንግሥት በተረጋገጠው መሠረት አርጎባም ይህንን ለማድረግና በሀገር ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን መደራጀቱ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በዱባይ እና ሰሜን ኤምሬቶች የሚገኙ የተለያዩ ብሔር-ብሔረሰቦች አንድነታቸውን የበለጠ አጠንከረውና ተደጋግፈው በሀገራችን የልማት ሥራዎች ላይ ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማኅበር ም/ሊቀመንበር ወ/ሮ ሕሊና በበኩላቸው እንደ ኮሚቲ ማኅበር የተለያዩ ማህበራት በኮሚኒቲው ጥላ ስር ሲሰባሰቡ የመደገፍና የማበረታታት፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ማድረግ ዓላማው እንደሆነ በመግለጽ ለወደፊትም ድጋፉን እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በተጨማሪም በአርጎባ ልማት ማህበር ተወካይና የማህበሩ ቦርድ አባል በአቶ እስማኤል ጠሃ ስለ ማህበሩ ዓላማ፣ ስለ አርጎባ ብሔረሰብ ታሪክ፣ ባህል እና እምነትና ልማድ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል።

𝙫𝙞𝙨𝙞𝙩 𝙖𝙧𝙚𝙜𝙤𝙗𝙖
09/04/2025

𝙫𝙞𝙨𝙞𝙩 𝙖𝙧𝙚𝙜𝙤𝙗𝙖

❤
13/07/2024

ባህላችን ውበታችን ነው
05/05/2024

ባህላችን ውበታችን ነው

26/04/2024

Thanks for being a top engager and making it on to my weekly engagement list! Hayati Mohammed, Selam Selam

 #ቅኝት | "ኮረሚ" - የጥንታዊት አርጎባዎች መንደርን ታሪክን በአግባቡ በመሰነድ ለአለም ባለማስተዋወቃችን ኢትዮጵያ ከኢስላሚክ ቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ገቢ አሳጥቷታል"። ጋዜጠኛና የኢስ...
24/04/2024

#ቅኝት | "ኮረሚ" - የጥንታዊት አርጎባዎች መንደርን ታሪክን በአግባቡ በመሰነድ ለአለም ባለማስተዋወቃችን ኢትዮጵያ ከኢስላሚክ ቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ገቢ አሳጥቷታል"።

ጋዜጠኛና የኢስላሚክ ታሪክ ፀሃፊ ተሾመ ብረሃኑ
****************************************

ከሀረር ከተማ በስተ ደቡብ 8 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው "ኮረሚ" ተብላ በምትጠራው የጥንታዊ የአርጎባዎች መንደር የሸዋል ኢድ በዓል በድምቀት የተከበረ ሲሆን በቦታው የሚገኙ ዘመናትን ያስቆጠሩ ታሪካዊ ቦታዎች ተጎብኝተዋል።

የክልሉ የባህል፣ የቅርስና የቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተወልዳ አብዶሽ ጥንታዊዎቹ የአውሶፊ አውቡርቃ መስጊዶችና አካባቢዎቹ ለአርጎባ ማህበረስብ የስልጣኔ ቀዳሚ ህዝቦች መሆናቸውን የሚያሳይ ታሪካዊ አሻራዎች ናቸው ይላሉ።

በሀረር - ኮረሚ መንደር ከ13ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የሀረር መዲና የነበረችው "ደከር" የምትገኝ መሆኗን ገልፀው የጥንታዊ ኢስላማዊ የግብርናና የስነ ህንጻ ጥበብ ህያው መገኛ እንደነበረች ያስረዳሉ።

ጋዜጠኛና የኢስላሚክ ታሪክ ፀሃፊ አቶ ተሾመ ብረሃኑ እንደሚሉት አርጎቦች በሀረር ታሪክ በሥነ ህንጻ ፣ በልስና ሥራና በሌሎችም ዕደጥበብ ሥራዎች የታወቁ ሲሆኑ ሥራቸው አዲስ አበበ እስከሚገኘው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ቤተመንግሥት እንደሚዘልቅ ይናገራል።

"ጎዜ" እራስን ከጠላት የመከላከያ እና የትምህርት ከተማቸው ፣ "አብዱልረሱል" የባሪያ ንግድ ከተማ ፣ "አልዩ አምባ" የቀረጥ ከተማ ፣ "ኬላ-ኦሲስ ኖራ" አስተዳደራዊ ከተማ ፣ "ጨኖ" የደረቅ ወደብ ከተማቸው ፣ "ጀበርት" አስተዳደራዊ ከተማ ፣ "ኩሊባስ" የመኖሪያ ከተማን ጨምሮ "አህዋጅ" የሸሪፎች/አሽረፎች የመቃብር ቦታዎች እና የትምህርት ማዕከልቻውን በሚገባው ልክ ለአለም ባለማስተዋወቃችን ኢትዮጵያ ከኢስላሚክ ቱሪዝም ታገኝ የነበረውን ገቢ እንድታጣ አድርጓታል ሲሉ ይገልጻሉ።

በቀጣይ እነዚህን ታሪካዊ ቦታዎች ማስተዋወቅ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለዋል።

ስንታየሁ አበራ - ከኮረሚ (የጥንታዊ አርጎባዎች መንደር)

23/04/2024

ባህላችን ውበታችን ነው

20/04/2024

_ባህላዊ _ልብሶች _ጌጣጌጦች(በከፊል እይታ )

የ1445ኛው  የሸዋል ዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ሁለተኛ ቀን ውሎ በሀረሪ ክልል የአርጎቦች መንደር ጉብኝት ተካሔደ። በጉብኝቱ ላይ  የፌደራል እ...
17/04/2024

የ1445ኛው የሸዋል ዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ሁለተኛ ቀን ውሎ በሀረሪ ክልል የአርጎቦች መንደር ጉብኝት ተካሔደ።
በጉብኝቱ ላይ የፌደራል እና የሀረሪ ክልል የስራ ሀላፊዎች የታሪክ ተመራማሪዎች የአርጎባ ጀበርት ይፋት ሱልጣኔት ሱልጣን መሀመድ አሽራዬ ፣ የአርጎባ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሙሳ የአርጎባ ልማት ማህበር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙስጠፋ ሸሁ ፣ የአርጎባ ልዩ ወረዳ አሰሰተዳዳሪ አቶ ባባ አቦ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

Address

Adis Ababa
Awash
115599

Telephone

+251989901010

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit aregoba posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Visit aregoba:

Share

Category