ASKO EVENT and Promotion

ASKO EVENT and Promotion Yesterday is history tomorrow is a mystry TODAY IS A GIFT! Let's make every moment unforgettable. Event planer, organizer and promotor

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡***አዲስ አበባ፤ነሐሴ 11 ቀን 2018ዓ/ም(አዲስ ፖሊስ)፦ፈርዶስ መሃ...
17/08/2026

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 11 ቀን 2018ዓ/ም(አዲስ ፖሊስ)፦ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አካባቢ ጓደኛቸውን ሲደበድቧት የሚያሳይ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ ህብረተሰቡ አስተያየት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከመሰራጨቱ ከወራት በፊት ወንጀሉን የፈፀሙትን ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማጣራቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በወንጀሉ የተጠረጠሩት ሦስት ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በጊዜ ቀጠሮ ታስረው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ልጅቷ ስትደበደብ የሚያሳየው ቪዲዩ መለቀቁ በልጅቷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ቪዲዮውን የለቀቀውን አካል ለማረጋገጥ ፖሊስ ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ ድርጊቱን በማውገዝ ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ያሳየውን መቆርቆር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አድንቋል፡፡
*
Via Addis Ababa Police

በጎፋ ዞን በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተነገረ‼️በዞኑ በሰኔ ወር የወባ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ እንደነበር ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የጎፋ ...
13/08/2026

በጎፋ ዞን በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተነገረ‼️

በዞኑ በሰኔ ወር የወባ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ እንደነበር ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ሣራ አበባዉ ሰፊ ርብርብ ተደርጎ የስርጭት መጠኑን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል ።

ባለፈው ሳምንት 5 ሺህ 194 ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዉ እንደነበር የሚገልፁት ወ/ሮ ሳራ የስርጭት ምጣኔዉ በ16 በመቶ ቀንሶ በዚህ ሳምንት ዉስጥ 4ሺህ 361 ሰዎች የወባ በሽታ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል ።

መምሪያዉ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል ። ከፍተኛ ስርጭት በታየባቸው አምስት ወረዳዎች በተለይም በሁባ ደብረ ፀሀይ እና ዛላ ወረዳዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል ።

በተጨማሪም የኬሚካል ርጭት በየቤቱ መካሄዱ የተገለፀ ሲሆን ከክልሉ ጤና ቢሮ በተገኘ በጀት በቀሪ ቤቶች ላይ የኬሚካል ርጭት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ወ/ሮ ሳራ ገልፀውልናል ።

በጊዜያዊና በቋሚነት ዉሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማዳፈንና የማፋሰስ ስራም በዘመቻ መልክ እየተሰራ ይገኛል ሲሉ አክለዋል።


አትሌት አልማዝ ዮሐንስ : የወርቅ እመቤቲቱ  | በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች በስኬት እየደመቀች የምትገኘው ታዳጊ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ ስሟ በዓለም እየናኘ ነው።በኢትዮጵያ አትሌቲ...
08/08/2026

አትሌት አልማዝ ዮሐንስ : የወርቅ እመቤቲቱ
| በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች በስኬት እየደመቀች የምትገኘው ታዳጊ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ ስሟ በዓለም እየናኘ ነው።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ከሆኑ አዳዲስ ተካኪ ስፖርተኞች መካከል አንዷ የሆነችው አትሌት አልማዝ ዮሐንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ስኬት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች።

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ እና በአህጉራዊ ውድድሮች ሁለት ሜዳሊያዎችን ለሀገሯ ማስገኘት የቻለችው ይህች ታዳጊ አትሌት፣ የስፖርት አፍቃሪዎችን ትኩረት ስባለች።
በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ ከሮ ጫንጮ ቀበሌ የተወለደችው የ19 ዓመቷ አልማዝ ዮሐንስ፣ የስፖርት ጉዞዋን የጀመረችው በአርቤጎና ታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ውስጥ ነበር።

በስፖርቱ ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት፣ የውስጥ ጥንካሬ እና ድፍረት በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ እድገት በማሳየት ወደ ሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ክለብ ተቀላቅላለች። በሀገር ውስጥ በተካሄዱ ውድድሮችም የላቀ ብቃት በማሳየት የክለቧን ስም ማስጠራት ችላለች።

በሀገር ውስጥ ያሳየችውን ድንቅ ብቃት ተከትሎ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የተሸጋገረችው አትሌቷ፣ እ.ኤ.አ. በ2026 በፎሎሪዳ በተካሄደው የ6 ኪሎ ሜትር የሀገር አቋራጭ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን እንድትወክል ተመርጣ አስፈላጊውን ዝግጅት በብቃት ያጠናቀቀች ቢሆንም፣ በቪዛ ምክንያት በውድድሩ ላይ ሳትሳተፍ ቀርታለች።

ይሁን እንጂ በዚህ ሳትበገር ጥንካሬዋን በመቀጠል፣ በ2026 በጋና በተካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3000 ሜትር መሠናክል ውድድር ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችላለች።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበችው ይህ ውጤት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ተስፋ ያለው አዲስ ትውልድ እየተተካ መሆኑን ያሳያል።

Via - Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ጌጡ #ጌጡተመስገን

Congratulations, your excellency! A well-deserved appointment as the first Board-Chair of CGIAR!
31/07/2026

Congratulations, your excellency! A well-deserved appointment as the first Board-Chair of CGIAR!

📢 CGIAR has appointed H.E. Hailemariam Dessalegn Boshe, former Prime Minister of Ethiopia, as the first Chair of the new CGIAR Board. With experience spanning academia, government, international diplomacy and agricultural development, he has dedicated his career to connecting science with better ...

ተጥሎ በረሃብ የሞት አፋፍ ላይ የነበረውን የሁለት ወር ሕፃን ልጅ የፖሊስ አባልዋ የራስዋን ጡት በማጥባት ከሞት ታደገችውበጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ አንዲት እናት ጥላ የጠፋቸውንና  በረሃብ የሞተት...
28/07/2026

ተጥሎ በረሃብ የሞት አፋፍ ላይ የነበረውን የሁለት ወር ሕፃን ልጅ የፖሊስ አባልዋ የራስዋን ጡት በማጥባት ከሞት ታደገችው

በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ አንዲት እናት ጥላ የጠፋቸውንና በረሃብ የሞተት አፋፍ ላይ የደረሰን የሑለት ወር ሕፃን ልጅ የፖሊስ አባልዋ የራስዋን ጡት በማጥባት ከሞት ታደገችው።

የጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች የተጣለና በምግብ እጦት ከሞት አፋፍ የደረሠን ልጅ አይተው ፖሊስ ጣቢያ ይዘው ይመጣሉ። ይሕ ልጅ በምግብ እጦትና በብርድ በመጎዳቱ የሞት አፋፍ ላይ ደርሷል።

ይህንን የተመለከተችው የጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ፖሊስ አባል ረዳት ሣጅን መስከረም ስምኦን የእናትነት አንጀት አላስችል ብልዋት ጡቷን በማጥባት በሞት አፋፍ የነበረውን ልጅ ከሞት ልትታደገው መቻሏን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።ሕፃኑን ሣየው ሆዴ ስፍስፍ አለ የምትለው ረዳት ሳጅን መስከረም ስምኦን ፖሊስነት ሕይወትን መታደግ ነውና በረሐብና በብርድ የተዳከመውን ልጅ ጡቴን በማጥባት ነብስ እንዲዘራ አድርጊያለሁ በማለት ተናግራለች።

የረዳት ሳጅን መስከረም ስምኦን ተግባር ፖሊስነት ከመስዋዕትነት እስከ ሕይወት አድን ተግባር በመሆኑ ምስጋና የተቸራት ሲሆን ከሞት አፋፍ በረዳት ሣጅን መስከረም ስምኦን ጡት ነብስ የዘራው የሑለት ወር ልጆ በአሑኑ ሠዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንዳለ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የቀርሣ ወረዳ ፖሊስ የሴቶች ና ሕፃናት ክፍል ኃላፊ ዋና ሣጅን ነይማ ጀማል ተጥሎ የተገኘ ህፃን ልጅ በረሃብ በመኖር እና በሞት መካከል መሆንኑ በመረዳት ወተት ያጋተውን ጡቷን አውጥታ በማጥባት ህይወቱን መታደጓን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሣል።

ለሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎችም ሆነ ለከተማዋ እንግዶች ደስ የሚል ዜና ነው!በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ በሚገኘው ታዋቂው ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል (South Star International Hotel...
27/07/2026

ለሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎችም ሆነ ለከተማዋ እንግዶች ደስ የሚል ዜና ነው!
በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ በሚገኘው ታዋቂው ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል (South Star International Hotel) አረንጓዴና ማራኪ በሆነው ጋርደን (ግቢ) ውስጥ አዲስ ዘመናዊ የቁርጥ ቤት ተከፈተ።
በተለይ ሆቴሉ ካለው ውብ አየር፣ አረንጓዴ ስፍራና ጥራት ያለው አገልግሎት ጋር ተጣጥሞ የቀረበ ነው!
📌 ጥራት ያለው የሐበሻ ቁርጥና ጥብስ በንጽህና የቀረበበት
ከቤተሰብ፣ ከጓደኛና ከሥራ ባልደረቦች ጋር በተፈጥሮ አየርና በጋርደን ድባብ እየተዝናኑ የሚመገቡበት
📌 ለስብሰባ፣ ለዝግጅት ወይም ለዕረፍት ወደ ሐዋሳ ለሚመጡ እንግዶች ተጨማሪ አማራጭ ይሆናል።
📌 የሐዋሳን ድባብ በጋርደን ውስጥ ከተመረጠ የሀገራችን የቁርጥና ጥብስ ምግብ ጋር አዋህዶ ለመደሰት ለሚፈልጉ አሪፍ ቦታ ነው!

  (HRF) ከ 20.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የተሽከርካሪ ድጋፍ   እና ለፕሮጀክት አስተዳደር ክፍል አስረከበየኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን (HRF) ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ (...
24/07/2026

(HRF) ከ 20.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የተሽከርካሪ ድጋፍ እና ለፕሮጀክት አስተዳደር ክፍል አስረከበ

የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን (HRF) ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ (AFD) ጋር በመተባበር ከ20.6 ሚሊዮን በላይ የሚያወጡ ሁለት ተሽከርካሪዎችን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሞርካ ከተማ ለሚገኘው ማዜ ብሔራዊ ፓርክ እና ለፕሮጀክት አስተዳደር ክፍል አስረክቧል።
የተሽከርካሪ ድጋፉ ማዜ ብሔራዊ ፓርክንና የውሃ ተፋሰሶቹን ለማጠናከር እና ከኢትዮጵያ አርአያ (ሞዴል) የአካባቢ ጥበቃ ሥፍራዎች አንዱ እንዲሆን ለማስቻል HRF እያከናወነው ካለው ተከታታይ ጥረት አንዱ አካል ነው።

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገልገሎ ገልሾ፣ ማዜ ብሔራዊ ፓርክ ባለፉት ዓመታት አስደናቂ መሻሻል ማሳየቱን እና በክልሉ ውስጥ አርአያ(ሞዴል) የአከባቢ ጥበቃ ስፍራ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው፣ ይህ መሻሻል የተገኘው በኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን፣ በመንግስት ተቋማት እና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ባለው ጠንካራ ትብብር እንደሆነ ገልጸዋል።

በHRF የአየር ንብረት ብዝሀ ህይወት ጥበቃ እና የስነ ምህዳር ቱሪዝም ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፣ ፋውንዴሽኑ ወሳኝ የመሠረተ ልማት እና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማቅረብ የፓርኩን የስራ አፈጻጸም አቅም ሲያጠናክር መቆየቱን ገልጸው፣ ፣ ፣ #ኮምፒውተሮችን፣ #ታብሌቶችን እና የጥበቃ ሰራተኞች ስራቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያግዙ ሌሎች ግብዓቶችን በድጋፍ ማካተታቸውን ጠቁመዋል።

በርክክቡ ስነ ስርዓት የማጠቃለያ ንግግራቸው የHRF ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ሶስና ኃይለማርያም፣ #ፋውንዴሽኑ ማዜ ብሔራዊ ፓርክን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት እንደገና አረጋግጠው፣ የተሽከርካሪ ድጋፉ በደቡብ ኢትዮጵያ የአከባቢ ጥበቃ ስራን ለማጠናከር፣ ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ እና ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደርን ለማስፋፋት #ፋውንዴሽኑ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

Via &RomanFoundations page

📢የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት🎯ነገ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-✅ከጠዋቱ 1:00 – 11:00  👉ገ...
24/07/2026

📢የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት🎯
ነገ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-

✅ከጠዋቱ 1:00 – 11:00

👉ገርጅ መብራት ሃይል፣ ጃክሮስ፣ የረር ሆስፒታል፣ ጎሮ፣ ICMC ሆስፒታል፣ እስኩል ኦፍ ቱሞሮ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ መሪ መስጅድ፣ ሳፋሪ እና ፉሪ፣ እና አካባቢው፣

✅ከጠዋቱ 2:00 – 9:30

👉ሆለታ፣ ህዳሴ፣ መናገሻ፣ ቡረዩ ከተማ አስተዳደር፣ ቡራዩ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው፣

✅ከጠዋቱ 2:00 – 6:00

👉ደብረ ብርሃን ከተማ ውሃ አቅርቦት፣ አልዩ አምባ፣ ሃኪም ግዛው ሆስፒታል፣አስራት ወ/ኢየሱስ ካምፓስ እና አካባቢው፣

✅ ከጠዋቱ 2:00 – 12:00

👉መቀሌ ቀበሌ 18፣ ዲያስፖራ ሰፈር፣ ቀዳማይ ወያነ፣ ማጅክ ትምህርትቤት፣ ደብረ ዳሞ፣ አብርሃ ካስት፣ ሃውልቲ ሰማታት፣ DW ቢሮ፣ ፕላኔት ሆቴል እና አካባቢው፣

✅ከጠዋቱ 2:30 – 10:30

👉ሱሉልታ 10 ኪሎ በከፊል፣ ዶሮ እርባታ፣ ቀንብሬ፣ አፍሪካ ልሕቀት ማዕከል፣ጭሮ ከተማ፣ኦዳቡልቱ ዩንቨርሲቲ እና አካባቢው፣

✅ከጠዋቱ 3:00 – 8:00

👉ቤተ መንግስት፣ ቴክስታይል፣ ሐሙሲት ወጪ መስመሮች እንዲሁም ከባህርዳር ቁጥር 1 እና ከወረታ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሃይል የሚያገኙ አካባቢዎች፣

✅እንዲሁም ከሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ ጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ንጋቱ 12፡00 ድረስ:-

👉ከሻሸመኔ ወደ አዳሚ ቱሉ የሚሄደው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

👉 በአሰላ፣ በአዳሚቱሉ፣ በቡታጅራ፣ በወራቤ፣ በቡኢ እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ነባር እና አዳድስ የሲዳማ አርቲስቶች ወደ አርቲ ኢንዱስትሪ ውስጥ ገብተው ተወዳዳሪ የሆኑ ስራዎችን እንዲሰሩ፣ እንዲሁም የሲዳማ ባህል እና ታሪክ በዓለም አደባባይ በአፊኒ ፊልም እንዲታይ ያደ...
18/07/2026

ነባር እና አዳድስ የሲዳማ አርቲስቶች ወደ አርቲ ኢንዱስትሪ ውስጥ ገብተው ተወዳዳሪ የሆኑ ስራዎችን እንዲሰሩ፣ እንዲሁም የሲዳማ ባህል እና ታሪክ በዓለም አደባባይ በአፊኒ ፊልም እንዲታይ ያደረገ ሞገደኛው ባለሙያ፣ ታሪኩ መኮንን/ Zetarian ማነው?

==========================================

በጥበብ ዓለም ውስጥ ስማቸው በገፅ ላይ ደምቆ ሳይጻፍ፣ መልካቸው በካሜራ ፊት ሳይታይ፣ ነገር ግን በስተጀርባ ሆነው ታሪክን የሚቀይሩና የትውልድን ንቃተ-ህሊና የሚያነቁ ጥቂት የላቁ የሙያ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ታዋቂ ለመሆን ሳይሆን አዋቂ ለመሆን የሚተጉ፣ ለዝና ሳይሆን ለዘላቂ አሻራ የሚለፉ የጥበብ አርክቴክቶች ናቸው።

ከእነዚህ ብርቅዬ የጥበብ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ስም ደግሞ፣- ዳይሬክተር፣ ካሜራ ማን፣ ኤዲተር እና ፕሮዲዩሰር ታሪኩ መኮንን (Zetarian) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ታሪኩ መኮንን የኖረበትና እየሰራበት ያለው መርህ "ሀገሬ ምን አደረገችልኝ?" በሚል ጥቅመኝነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ "እኔ ለሀገሬና ለወገኔ ምን አበረከትኩ?" በሚል ዘመን ተሻጋሪና ክቡር በሆነ ሀሳብ የተቃኘ ነው።

ይህ የውስጥ እምነቱና ለሙያው ያለው ታማኝነት ነው ዛሬ ለምናያቸው በርካታ ድንቅ ሙዚቃዎች፣ ልብ አንጠልጣይ ድራማዎችና እውነተኛ ታሪክን የሚተርኩ ፊልሞች መሠራት ምክንያት የሆነው። በጥበብ ስራዎች ውስጥ ትልቅ ዋጋ እየከፈለ፣ ማህበረሰቡ እውቀትና መዝናናትን እንዲያገኝ ሌት ተቀን የሚተጋ የሙያ ሰው ነው።

ታሪኩ (Zetarian) ሙያውን ጠንቅቆ ያወቀ፣ ከፈጠራ ክህሎት ጋር ያዋሃደ ባለሙያ በመሆኑ በተለይ የሲዳማ ማህበረሰብ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባህልና እሴት ከፍ ብሎ እንዲታይ ያደረገው አስተዋፅኦ ማድረግ ችሎአል ። የሲዳማ ህዝብ ያሉት ውብ ባህላዊ ክንዋኔዎች ከሀገር አልፈው በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲታወቁና እውቅና እንዲያገኙ በካሜራው፣ በዳይሬክቲንግ እይታውና በፕሮዳክሽን ስራው ትልቅ ስራ ሰርቷል።

በዚህ ረገድ በተለይ እጅግ አስደናቂና ስኬታማ በሆነው "የአፊኒ ፊልም" (Affini Film) ላይ ያሳየው የላቀ የዳይሬክቲንግ፣ የካሜራና የኤዲቲንግ ጥበብ እርሱ ለሙያው የከፈለውን መስዋዕትነትና ያለውን ጥልቅ አቅም በግልፅ የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው። በሀገር ደረጃ ከተለያዩ ሲትኮሞች እስከ ተከታታይ ድራማዎች፣ አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶች እስከ ትላልቅ ፊልሞች ድረስ ስሙ በጥራትና በጥበብ ልዕልና የሚነሳ "ሞገደኛ" ባለሙያ ነው።

የታሪኩ (Zetarian) ነባር እና አዳዲስ የሲዳማ አርቲስቶች ወደ ጥበብ ኢንዱስትሪው ውስጥ ገብተው ተወዳዳሪና ብቁ ስራዎችን መስራት እንዲችሉ በማገዝ፣ በማማከር፣ በዳይሬክቲንግና በድምፅ ቅንብር (Directing and Mixing) ረገድ ያደረገው ድጋፍ ወደር የለውም።

በአሁኑ ዘመን ለምሳሌ:- አንድ ባለሀብት በአጋጣሚ አንድን ሰው መንገድ ላይ አግንቶ ጋብዞ በማግስቱ ያዉ ግብዣ የተደረገበት ሰዉ ጋባዡን በማህበራዊ ሚዲያ መጥቶ ሲቆለጳጵስና ሲያወደስ ማየት የተለመደ ሆኗል። የሰውየው ማንነትና የሀብቱ ምንጭ በውል ሳይያዉቅ ግብዣ ስለተደረገበት ብቻ ማለት ነዉ።

ነገር ግን ይህ ሙያተኛ እንደዚህ አይነት የውሸት ውዳሴዎችንና አጨብጫቢዎችን የማይፈልግ፣ ከገንዘብ ይልቅ ለሙያው ክብር የሚሰጥ እውነተኛ ባለሙያ እንደሆነ ብዙዎች ስለ እሱ ይመሰክራሉ።

"ሰው በገዛ ቤቱ ያድራል፣ ስራውና አበርክቶቱ ግን በሌላ ሰው ቤት ይወራል" እንደሚባለው፣ ዛሬ እርሱን በቅርብ የማያውቁት እንኳ ስራውን አይተውና አድንቀው እየመሰከሩ ይገኛሉ ። እኔም ከእነሱ አንዱ ነኝ። በተጨማሪም እርሱን እርሱን ለማድነቅና ስራውን ለማውራት የቅርብ ዘመድ መሆን አይጠይቅም፤ የሰራቸው ድንቅ ስራዎች ራሳቸው ጮኸው ይመሰክራሉ።

ወንድማችን ታሪኩ ሆይ! ምናልባት ልፋትህንና በየቀኑ የምትከፍለውን ዋጋ አይቶ ሁሌ የሚያወድስህ "ጉምቱ ዘመድ"፣ የጥቅም አጨብጫቢ ወይም የፌስቡክ ቅጥረኞች በዙሪያህ ላይኖሩ ይችላሉ ። ነገር ግን በመጀመሪያ ሁሉንም የሚያይ እግዚአብሔር፣ በመቀጠልም ያበረከትከውን ውብ የጥበብ ስራዎች የሚያዩና የሚያደንቁ መላው የጥበብ አፍቃሪያን ሁሌም ከጎንህ አሉ ብየ አስባለሁ።

ስለዚህ ይህ የከፈልከው ዋጋና ያስቀመጥከው የጥበብ አሻራ በትውልድ ልብ ውስጥ ለዘላለም ተቀርጾ ይኖራል። በርታ፣ ወደፊት መጓዝህን ቀጥል፤ ጥበብ ሁልጊዜም እውነተኛ ባለቤቷን ታከብራለች።!
👇
/ ገዙቴ ነኝ!








゚viralシ

ሰበር መረጃ‼️በቀድሞው ዲፕሎማ ወይም ከ12+2 ወይም ከ10+3 የተመረቁና ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ኖሯቸው ነገር ግን የደረጃ ስድስት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ...
10/07/2026

ሰበር መረጃ‼️
በቀድሞው ዲፕሎማ ወይም ከ12+2 ወይም ከ10+3 የተመረቁና ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ኖሯቸው ነገር ግን የደረጃ ስድስት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ ተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስችል መመሪያ ሊዘጋጅ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫና የአቻ ግመታ መመሪያ ማሻሻያ ላይ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም የሦስተኛ ዲግሪ የያዙ ተማሪዎች ሚኒስትሩ በሚያወጣው የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው እንደሚሆነም አስፍሯል፡፡

ይህ ማሻሻያ መመሪያ የትምህርት ማስረጃ ሰነድ ማረጋገጫ ሂደቶችን በአስፈላጊነቱ አገልግሎት ለመስጠትና ለማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

የማሻሻያ መመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ማንኛውም የመንግስትና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎች ላይ የሚተገበር ነው፡፡

እንዲሁም በዲግሪ መግቢያ መስፈርት የተቀመጠውን የደረጃ ስድስት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ ተምረው የተመረቁትን፤ ወይም በዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የደረጃ ስድስት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱትን ተመራቂዎች የሚያጠቃልል ነው፡፡

Address

Debub Iz
Awassa
767

Telephone

+251917513153

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ASKO EVENT and Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ASKO EVENT and Promotion:

Shortcuts

Share

Category