Amhara Tourist Attractions የአማራ የቱሪስት መስህቦች

Amhara Tourist Attractions የአማራ የቱሪስት መስህቦች This page is aimed at promoting hidden attractions which are found in Amhara region, so follow us, 👍

ትኩረት ለላሊበላ
27/11/2023

ትኩረት ለላሊበላ

Sankaber to ChennekSankaber, Gich, and Chennek connect across the primary escarpment of the Simien Mountains, and a popu...
14/07/2023

Sankaber to Chennek

Sankaber, Gich, and Chennek connect across the primary escarpment of the Simien Mountains, and a popular trekking option is a 3-night hike from camp to camp. The route across the escarpment has exceptional viewpoints with stunning 360-degree views and lots of wildlife.



   ጣና ሀይቅ ካሉት ደሴቶች ትልቁ በሆነው የደቅ ደሴት ላይ የሚገኝ ገዳም ነው፡፡ የደቅ ደሴት ከባሕር ዳር ከተማ ሰሜናዊ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ሲሆን በጀልባ ከ3-4 ሰዓት ያስኬዳ...
14/07/2023

ጣና ሀይቅ ካሉት ደሴቶች ትልቁ በሆነው የደቅ ደሴት ላይ የሚገኝ ገዳም ነው፡፡ የደቅ ደሴት ከባሕር ዳር ከተማ ሰሜናዊ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ሲሆን በጀልባ ከ3-4 ሰዓት ያስኬዳል፡።

ይህ ደሴት በውስጡ 7 (ሰባት) አድባራትን የያዘ ሲሆን "የሰባት ደብር አገር" በመባል ይታወቃል። እነዚህም ደብሮች በስም፦

1.ዳጋ እሥጢፋኖስ፣
2.ናርጋ ሥላሴ፣
3.ቅድስት አርሴማ፣
4.ኮታ ማርያም፣
5.ዝባድ ኢየሱስ፣
6.ጆጋ ዮሃንስ እና
7.ጋደና ጊዮርጊስ በመባል ይታወቃሉ።

ናርጋ ስላሴ ገዳምን ያሰሩት የአፄ በካፋ ባለቤት እቴጌ ምንትዋብ (1730-1755 ዓ.ም) ናቸው፡፡ ናርጋ ሥላሴ ግድግዳዎች በሥዕሎች ያሸበረቁና የዘመኑን የሥነ-ስዕል ጥበብ አሻራ አጎልተው የሚያሳዩ ናቸው።

hotelNaky hotel - ናኪ ሆቴልናኪ ሆቴል

 / 💚💛❤  ይህ ድንቅ ሰንሰለታማ  የተፈጥሮ ተራራ የሚገኘው ከአዲስአበባ በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ  175 ኪ.ሜ  ርቀት  ነው። አካባቢው የተለያዩ  ሀገር በቀል እፅዋቶች፣ ብርቅዬ እንስ...
14/07/2023

/ 💚💛❤
ይህ ድንቅ ሰንሰለታማ የተፈጥሮ ተራራ የሚገኘው ከአዲስአበባ በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 175 ኪ.ሜ ርቀት ነው። አካባቢው የተለያዩ ሀገር በቀል እፅዋቶች፣ ብርቅዬ እንስሳት እንዲሁም በርካታ አዕዋፋትን አካቶ የሚገኝ ውብ ስፍራ ነው። 📸ጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ


hotel - ናኪ ሆቴልል

የበርካታ ቱሪስት ቀለብ የምትስበው ድንቅ ምድር እንሳሮ
14/07/2023

የበርካታ ቱሪስት ቀለብ የምትስበው ድንቅ ምድር እንሳሮ


  Simen mountain national park
09/07/2023

Simen mountain national park

A family group of geladas sitting on a canyon cliff in Simen Mountains National Park, Ethiopia.

A beautiful scene from  the 4th highest point in Africa , Semien Mountain Amhara region, Ethiopia 🇪🇹Inside Africaa
08/07/2023

A beautiful scene from the 4th highest point in Africa , Semien Mountain Amhara region, Ethiopia 🇪🇹
Inside Africaa

11/01/2023
"የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው። እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።" ዘፍ ፪÷፲፫  በመጽሐፍ ቅዱስ "ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤደን ይወጣ ነበር።" ተብሎ በሁለተኛነት የተጠቀ...
11/01/2023

"የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው። እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።" ዘፍ ፪÷፲፫

በመጽሐፍ ቅዱስ "ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤደን ይወጣ ነበር።" ተብሎ በሁለተኛነት የተጠቀሰው ግዮን ስመ ብዙ፣ ትርጉመ ብዙ፣ ሚስጢር ብዙ ወንዝ አነስተኛ ምንጭ ሆኖ ጉዞውን የሚጀምረው በዚህ ነው።

ሰከላ፥ ግሽ ዓባይ

ይህ ዓባይ ብለን የምንጠራው ግዮን ተፈጥሮን ለሚያደንቁ ውበት፣ ጠበል ነው ብለው ለሚጠጡት መፈወሻ እምነት፣ አርሰው ለሚበሉበት ሕይወት፣ ለሀገራት የዓለምን ፖለቲካ የሚዘውር ፈሳሽ እሳት ነው።

የዓባይ ወንዝን ሁለንተናዊ ፋይዳ ከፍ ለማድረግ፣ በወንዙ ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ወንድማማችነት ለማጎልበት እና የወንዙን ባለቤትነት ለዓለም ለማዘከር ከአምስት ዓመት በፊት የግዮን በዓልን በሰከላ ማክበር ተጀምሯል።

ዘንድሮም የግዮን በዓል ለ፭ኛ ጊዜ ጥር 13 ቀን በድምቀት ይከበራል!
Visit Amhara

10/01/2023

9ኙ የጎንደር ሴቶች የእስክስታ ዓይነቶች



በውዝዋዜ ወቅት ከሚያሳዩት የእስክስታ ትዕይንት አንዱ ጉች ጉች ይባላል። ይህ እስክስታ አንዲት ሴት ጥበበኛና ባለሙያ ከሚያሰኟት ነገሮች ውስጥ አንዱ እንጀራ መጋገር በመሆኑ ይህ ውዝዋዜ ሲጨፈር ሴቷ በእግሯ መዳፍ ቁጢጥ በማለት እየተሽከረከረችና ክብ በመስራት ዙሪያውን በመዞር የሴት ወይዘሮ መሆኗን እና የእንጀራ መጋገር ሙያ እንዳላት የምትገልጽበት የእስክስታ አይነት ነው።

#ዶሮ ውሃ ሲጠጣ

ሁለተኛው የእስክስታ አይነት ዶሮ ውሃ ሲጠጣ ይባላል። ይህ አይነት ውዝዋዜ ዶሮ ውሃ ሊጠጣ ከሚያደርገው የዶሮ ተፈጥሮ የተወሰደ የእንቅስቃሴ አይነት ሲሆን በታዳሚው አዕምሮ ውስጥ እንዲቀረጽ የተፈለገው ዋና ቁም ነገር የሴቷን የዶሮ ወጥ ሙያ ለመግለጽ ነው። ሲጨፈርም ሴቷ የመቀነቷን ጫፍና ጫፍ በመያዝ እጆቿን ወደ ጎን በመዘርጋት ቀስ በቀስ ከወገቧ ዘንበል እያለች ወደ ታች በመውረድ ልክ ዶሮ ውሃ ሊጠጣ ሲል እንደሚያደርገው ተወዛዋዧም አንገቷን ዝቅ ከፍ እያደረገች የምትወዛወዘው ውዝዋዜ አይነት ነው።

#ሰክስክ

ሦስተኛው የእስክስታ አይነት ሰክስክ የሚባለው ሲሆን በዚህ የእስክስታ አይነት ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት የሴቷን አሳ የመስራት ሞያ ነው። አንድ አሞራ ወደ ወንዝ አሳ ለመያዝ ሂዶ ከያዘ በኋላ አንገቱን ዝቅ ያደርግና ከወደ አፉ ቀና በማለት አሳውን ለመዋጥ የሚያደርገውን ትግልና ትዕይንት መሰረት ተደርጎ የተቀዳ የውዝዋዜ አይነት ነው። አጨፋፈሩም የመቀነቷን ጫፍ እና ጫፍ በመያዝ ከአንገቷ ሰበር ከወገቧ ዘንበል በማለት ልክ አሞራ አሳ በማንቁሩ እንደሚያነሳው አንገቷን ወደላይ ቀና በማድረግ በአንገትዋና በትከሻዋ ወደ ላይና ወደ ታች እየወዘወዘች ትጨፍራለች።

#ድስቅ

ጌጣጌጦችን አሳምረው መስራት እንደሚችሉ ለማሳየት ደግሞ ድስቅ የሚባለውን የውዝዋዜ አይነት ይጠቀማሉ። ውዝዋዜው የሚጨፈረው በደረትና በትከሻ ሲሆን በሰርግ እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ በአላቶች ላይ ሴቶች ለመልካቸው ውበት የሚያላብሳቸውን የሞያ እና የእመቤትነት ማዕረግ የሚያጎናጽፋቸውን ጌጣጌጦች በጸጉራቸው፣ በእጃቸው እና በ አንገታቸው አድርገው ይሄዳሉ።
እነዚህን ጌጣጌጦች የሚያዘጋጁዋቸው ራሳቸው መሆናቸውን ለማሳየት ድስቅ የተሰኘውን ውዝዋዜ ይጨፍራሉ። ይህ እስክስታ ሲመታ በደረታቸውና በትከሻቸው በሃይል ስለሚመታ አንገታቸው ላይ ያለው ጌጣጌጥ ዕርስ በእራሱ እየተላተመ ድምጽ ያሰማል። የብዙ ሰዎችን ቀልብም ይገዛል። የሰሯቸው ማጌጫዎች ጥራትና ውበት ይታያል። የሞያ ደረጃቸውን ከፍ አድርጎ ያሳያል።

#ቅቤ መናጥ

አምስተኛው የውዝዋዜ አይነት ቅቤ መናጥ ይባላል። ይህ ውዝዋዜ ሴቷ ስትወዛወዝ በርከክ ብላ የመቀነቷን ጫፍና ጫፍ በእጆቿ በመያዝ እጆቿን ወደፊት እና ወደኋላ እየዘረጋችና እያጠፈች የምትወዛወዘው ሲሆን ሊተላለፍ የተፈለገው ጉረና (ወተት የሚያዝበት እቃ) እየገፋች እና እየናጠች ቅቤ ለማውጣት የሚደረገውን ትዕይንት ለመግለጽ ነው። እንዲሁም የነጠላዋን ጫፍና ጫፍ በትከሻዋ እንዲወርድ አድርጋ በሁለት እጆቿ ጫፍና ጫፉን ከያዘች በኋላ ረጋ ብላ በቀስታ በመነቅነቅ አይነት ትወዛወዛላች። ይህም የወተት መናጫውን ማሰሪያ ገመድ ይዛ ወተቱ እንዳይደፋባት (እንዳይሸፍትባት) ቅቤው እንዲወጣ የመሰብሰብ አይነት ውዝዋዜ ነው።
#እንዝርት

ፈትል፣ ጥልፍና የተለያዩ አልባሳት አስጊጠውና አሳምረው መስራት እንደሚችሉ ለማሳየት ደግሞ እንዝርት የሚባለውን የእስክስታ ትዕይንት ሴቶች ይከውናሉ። የእንዝርት አሿሿርን መሰረት አድርገው በእጆቻቸው ቀሚሳቸውን ከጎንና ከጎን በመለጠጥ ልክ እንደ እንዝርት እየሾሩና እየተሽከረከሩ ይጨፍራሉ። እንዲሁም ቀጭን ፈታይ ባለሙያ ስለመሆናቸው ለመግለጽም ይጠቀሙበታል።
አቀራረቡም ልክ እንዝርት እንደያዙ በማስመሰል በጣቶቻቸው የመቀነታቸውን ጫፍ ይዘው እጃቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የላይኛውን መቀነታቸውን ጫፍ በጣቶቻቸው ጥጥ እንደያዙ በማስመሰል በመፍተል አይነት እንቅስቃሴ ይወዛወዛሉ። ቁጭ ብለው ሲወዛወዙ በ አንደኛው እግራቸው በኩል ያለውን ቀሚሳቸውን ሰብሰብ አድርገው እንዝርት እያሾሩ የሚፈትሉ በማስመሰል ይወዛወዛሉ። እንዝርትና ጥጥ ይዘው እየፈተሉ ሊወዛወዙም ይችላሉ።

#ዋንጫ ልቅለቃ

ሰባተኛው ዋንጫ ልቅለቃ የተባለው የውዝዋዜ አይነት ነው። የሴቷን የወይን አዘገጃጀት የጠጅ አጣጣል የጠላ አጠማመቅና ልዩ ልዩ መጠጥ ማዘጋጀት እንደምትችል እና ባለሙያ መሆኗን ለማሳየት ዋንጫ ልቅለቃ የውዝዋዜ አይነትን ይጠቀማሉ።

ዓባይ ውበትዓባይ እምነትዓባይ ሕይወት፭ኛው የግዮን በዓል እና ዓመታዊው የአቡነ ዘርዓብሩክ የንግሥ በዓል ከታላቁ የዓባይ ወንዝ መነሻ ሰከላ - ከግሽ ዓባይ ሰማይ ስር ጥር 13 ቀን በድምቀት ...
10/01/2023

ዓባይ ውበት

ዓባይ እምነት

ዓባይ ሕይወት

፭ኛው የግዮን በዓል እና ዓመታዊው የአቡነ ዘርዓብሩክ የንግሥ በዓል ከታላቁ የዓባይ ወንዝ መነሻ ሰከላ - ከግሽ ዓባይ ሰማይ ስር ጥር 13 ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡

“ሰከላ ዓባይን ወለደች . . .”

Address

Bahir Dar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251927661747

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Tourist Attractions የአማራ የቱሪስት መስህቦች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara Tourist Attractions የአማራ የቱሪስት መስህቦች:

Share

Category