Alazer yohones

Alazer yohones Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alazer yohones, Tour Agency, Wolayta, Dire Dawa.

ሕይወት አጭር ናት--ሳትቀድማችሁ ቅደሟትበ40 አመቷ ይህቺን የማትሞላ ዓለምና የመከራ ምድርን የለቀቀችው ታዋቂዋ የዓለማችን ቱጃር ሴት የነበረችው ዲዛይነርና ፀሀፊ 《ክሪስዳ-ሮዲሪጌዝ》 በካንሰ...
13/11/2022

ሕይወት አጭር ናት--ሳትቀድማችሁ ቅደሟት
በ40 አመቷ ይህቺን የማትሞላ ዓለምና የመከራ ምድርን የለቀቀችው ታዋቂዋ የዓለማችን ቱጃር ሴት የነበረችው ዲዛይነርና ፀሀፊ 《ክሪስዳ-ሮዲሪጌዝ》 በካንሰር በሽታ ከመሞቷ በፊት ማስታወሻዋ ላይ እንዲህ ብላ ፅፋ ነበር።

🔴✍✍✍…-በአለም ላይ አሉ ከሚባሉ ውድ መኪናዎች ውስጥ አንዱ በእኔ ጋራጅ የተቀመጠው ነው፤ አሁን ግን በዊልቼር ነው የምንቀሳቀሰው።

🔴✍✍✍…-ቤቴ ውስጥ በምርጥ ዲዛይነሮች የተሰሩ ውድ የሆኑ የሚያማምሩ ልብሶችና ጫማዎች አሉኝ፤ ግን አሁን በሆስፒታል በተሰጠኝ ስስ ጨርቅ ነው ገላዬን የሸፈንኩት።

አንብቡት!!!! 🔴✍✍✍…-ባንክ አካውንቴ ላይ እጅግ ከበቂ በላይ ገንዘብ አለኝ፤ ግን እሱን አሁን ልጠቀምበት አልችልም።

🔴✍✍✍…-ቤቴ ፓላስ የሚባል ዓይነት ነው፤ ግን እኔ አሁን ሆስፒታል ውስጥ በምትገኝ ትንሽዬ አልጋ ላይ ነው የተኛሁት።

🔴✍✍✍…-ከአንዱ ባለ-አምስት ኮከብ ሆቴል እንዳሻኝ ወደ አንዱ ባለ-አምስት ኮከብ ሆቴል ስንሸራሸር የነበርኩ ሴትዮ፤ አሁን እዚያው ሆስፒታል ውስጥ ካንዱ የላቦራቶሪ ክፍል ወደ ሌላኛው ላቦራቶሪ ክፍል መመላለስ ግዴታዬ ሆኗል።

🔴✍✍✍…-በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፈሪምልን ብለው እንዳላስጨነቁኝ፤ አሁን ግን የሚያክመኝ ዶክተር እንኳ አንድም ቀን ፊርማዬን ጠይቆኝ አያውቅም።

🔴✍✍✍…-ፀጉሬን የማስውብበት ውድ የተባሉ ሰባት አይነት አልማዞች እና ወርቆች ነበሩኝ፤ አሁን ግን ይኽን ማድረግ አልችልም ምክንያቱም ፀጉር የለኝም።

🔴✍✍✍…-በግል አውሮፕላኔ ዓለም ላይ የፈለኩበት ቦታ ብቻዬን መሄድ እችል ነበር፤ አሁን ግን ለመናፈስ ስፈልግ እንኳ የግድ የሁለት የሰዎች እርዳታ ያስፈልገኛል።

🔴✍✍✍…-በቀን በቀን ብፌ በሚባል ዓይነት የተመረጡ ምግቦችን እመገብ ነበር፤ አሁን ግን በቀን ሁለት ፍሬ ታብሌትና ትንሽ ጠብታ ጨው ማታ ላይ የምወስደው ነው ምግቤ።

🔴✍✍✍…………ይኼ ሁሉ ሀብት እና ድሎት ግን እኔን ከበሽታዬ ሊያድነኝ አልቻለም፤………እውነተኛ ሕይወት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ፣ ለትዕዛዛቱም መገዛት ነው።
ህይወት አጭር ናት፤ ሳትቀድማችሁ ቅደሟት።
═════════❁✿❁ ═════════

13/11/2022
ስሟ ጆይስ ካርሎ ቪንሰንት ይባላል የ 38 ዓመት ወጣት ስትሆን ነዋሪነቷ የነበረው ኢንግሊዝ ውስጥ ለንደን ነው፡፡ትኖር የነበረው አፓርትመንት ተከራይታ ሲሆን የቤቷ የኪራይ ውል በማለቁና ያለባ...
11/11/2022

ስሟ ጆይስ ካርሎ ቪንሰንት ይባላል የ 38 ዓመት ወጣት ስትሆን ነዋሪነቷ የነበረው ኢንግሊዝ ውስጥ ለንደን ነው፡፡

ትኖር የነበረው አፓርትመንት ተከራይታ ሲሆን የቤቷ የኪራይ ውል በማለቁና ያለባትን የኪራይ ውዝፍ ልትከፍል ባለመቻሏ አከራዮቿ በ 2006 ለፓሊስ ያሳውቃሉ ፓሊሶቹም ወደ ቤቷ በመሄድ ሲያንኳኩ በር አይከፈትም ሰብረው ይገባሉ ሰብረው ሲገቡ ግን በህይወት ሳይሆን ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳለች ሞታ ነበር ያገኟት እሷ የሞተችው ግን በ2003 ነበር ፡፡
ሞታ ለ ሶስት ዓመት ምናምን ያለ ጠያቂ በቤቷ ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳለች ቆይታለች ፡፡

ከሞተች ከ 3 ዓመት በኀላም ቀናቸው ያለፈባቸው ምግብና መጠጦች ከፍሪጇ ውስጥ ፓሊሶች አግኝተዋል

ሌላው ብዙዎችን ያሳዘነው ነገር ይሄን ሁሉ ዓመት ሞታ ቤቷ ስትቆይ ማንም የት ነሽ ወዴት ነሽ ያላት አለመኖሩ ነበር ፡፡

በ2011 GC በእውቋ ኢንግሊዛዊት ዳሬክተር ካርሎ ሞርሌ DREAMS OF A LIFE የተሰኘ አሳዛኝ ዶክመንተሪ ተሰርቶላታል፡፡

ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም ግላዊነት ከመንገሱ የተነሳ ሁሉም በየራሱ ይኳትናል እንጂ አጠገቡ ስላለው ጎረቤት አይጨነቅም ፡፡ አብረከው ስለኖርክ ብቻ መጠጋጋትንና ቅርርብን አይፈቅድም ፡፡

አገራችን ውስጥ ምንም ቢሆን ከፋም ለማም ተጣላክም አልተጣላክም እንዴት ነው ወዴት ነው የሚል.. ደሞ ዛሬ ምነው ድምፁ ጠፋ ድምፇ ጠፋ የሚል ጎረቤት ሁሌም ቢሆን ይኖርሃል ....
Dreams of a life ብቸኝነት + መረሳት
#ካነበብኩት

10/11/2022
ጥይቱ ወጥቷል ከእግሬ ውስጥ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እስራኤል ዳንሳ ያስተላለፉት መልዕክት :- "ከትላንት ወዲያ ከዝዋይ በሐይዌይ ወደ አዲስ አበባ እየመጣሁ እያለ ባልታወቁ ሰዎች እግሬ በጥይት ...
10/11/2022

ጥይቱ ወጥቷል ከእግሬ ውስጥ

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እስራኤል ዳንሳ
ያስተላለፉት መልዕክት :-

"ከትላንት ወዲያ ከዝዋይ በሐይዌይ ወደ አዲስ አበባ እየመጣሁ እያለ ባልታወቁ ሰዎች እግሬ በጥይት ተመቷል።

ያን ያክል ብዙ የሚጎዳ አይደለም።

የታሰበው ሌላ ቢሆንም ጌታ ጣልቃ ገብቶ ሁሉ ሰላም ሆኗል።

እግዚአብሔር ከረዳን በቅርቡ ወደምወደው የአገልግሎት ስራ እመለሳለሁ"

ጥይቱ ወጥቷል ከእግሬ ውስጥ ወጥቷል
እቤት ገብቻለው

አርቲስት አበበ ወርቁ ምላሽ ሰጠ! አንቺ ባለጊዜ እባክሽ ተይኝ የሚል አንጀት የሚበላ ግጥም 😭😭እኔም ቂሜን ልርሳ! አርቲስት አበበ ወርቁ እባክሽ እባክሽ ብዙ አታበሳጭኝ ግዜ አገኘሁ ብለሽ ፣...
10/11/2022

አርቲስት አበበ ወርቁ ምላሽ ሰጠ! አንቺ ባለጊዜ እባክሽ ተይኝ የሚል አንጀት የሚበላ ግጥም 😭😭

እኔም ቂሜን ልርሳ!
አርቲስት አበበ ወርቁ

እባክሽ እባክሽ
ብዙ አታበሳጭኝ ግዜ አገኘሁ ብለሽ ፣

ጊዜ የጣለውን ጊዜ ያነሳዋል
ጊዜ ያነሳውንም ጊዜ ይጥለዋል ፣

ይህንን ካወቅሽ ከተረዳሽ ፍቅሬ
ያልነበረ ፀባይ ከየት መጣ ዛሬ ፣

በፍቅራችን ዘመን አብረን የሰራነው
እንደጥፋት አርገሽ ሁሉን ካየሽው ፣

ዛሬም የሰራሽው በጊዜው ያልፍና
ያስተዛዝበናል ፀፀት ታተርፊና ፣

በጊዜ የወደቁ በጊዜ ይነሳሉ
በጊዜ የተነሱም በጊዜ ይወድቃሉ ፣

ጊዜ የጣለው ወድቆ የሚቀር ቢሆን
መች ያልፍልሽ ነበር አስቢ ያለፈውን ፣

አንቺ ባለ ጊዜ እኔ ቀን ጠባቂ
በውድቀትሽ ሰአት ተራዬን ጦር ሰባቂ ፣
እንዲህ አይነት ክፋት
እንዲህ አይነት ጥፋት ፣

ትውልድ እንዳያነሳ
አንቺም በቀል ተይ እኔም ቂሜን ልርሳ!

ሰላሙን ያውርድላችሁ አቦ እንዴት ያሳዝናል እነኚህ ዳያስፓራ ሴቶች ግን ለትዳር ያላቸው ክብር መጣራት አለበት ፣

Rip😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
08/11/2022

Rip😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

በስምምነቱ ምን አገኘን?ሰበር መረጃ ከፕሪቶሪያ በደቡብ አፍሪካ  በተካሄደው የሰላም ውይይት የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም እና ቡድኑ ሙሉ ...
02/11/2022

በስምምነቱ ምን አገኘን?

ሰበር መረጃ ከፕሪቶሪያ

በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሰላም ውይይት የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም እና ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ ስምምነት ላይ ተደረሰ።

በደቡብ አፍሪካ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ዘላቂ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ በስምምነት መቋጨቱን ከውስጥ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ለሁለት አመታት የዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት መቋጫ እንደሚሆን የተገመተ የሰላም ስምንነት ፊርማ በዛሬው እለት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያና በህወሓት ተደራዳሪዎች መፈረሙን ያስታወቁት ምንጮች ፤ ውይይቱ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ፣ የሕግ የበላይነትን ባረጋገጠ እና ለውጭ ጣልቃ ገብነት እድል በማይሰጥ መልኩ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ቁልፍ የስምምነት አጀንዳዎች፦

ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤

ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤

የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤

ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።

የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።

 ‼️👉 ውዱ የጥርኝ ቡና አዘገጃጀት በዚህ መልኩ ነው በመጀመሪያ ጥርኟ ብናውውን ትመገበዋለች ከዚያ ትፈሳዋለች😁 ። ወይም በፎቶው ላይ በምትመለከቱት መልኩ ታስወጣዋለች። ከውስጧ የሚገርም ጣዕ...
31/10/2022

‼️
👉 ውዱ የጥርኝ ቡና አዘገጃጀት በዚህ መልኩ ነው በመጀመሪያ ጥርኟ ብናውውን ትመገበዋለች ከዚያ ትፈሳዋለች😁 ። ወይም በፎቶው ላይ በምትመለከቱት መልኩ ታስወጣዋለች። ከውስጧ የሚገርም ጣዕም😁 ይዞ ይወጣል። በዓለም ላይ ውድ ቡና ሆነ ማለት ነው።
👉 አንድ ስኒ የጥርኝ ቡና እስከ 100 ዶላር ዋጋ አለው። ከመደበኛው ቡና እስከ 60 እጥፍ ማለት ነው። አንድ ኪሎ የጥሪኝ ቡና ቢኖራችሁ 100 ስኒ ቡና ቢወጣው 10ሺ ዶላር ማለት ነው።

"ባሌ፤ አርሲ፤ ሸዋና ጎጃም በእነዚህ አራት ክፍለ ሃገሮች እጅግ የትረፈረፈ የእህል ምርት አየሁ። ሲኒማ ተገብቶ እንደሚታይ ፊልም በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ የተመረተ ምርት ወደ ቀሪ አለም ሲጫ...
30/10/2022

"ባሌ፤ አርሲ፤ ሸዋና ጎጃም በእነዚህ አራት ክፍለ ሃገሮች እጅግ የትረፈረፈ የእህል ምርት አየሁ። ሲኒማ ተገብቶ እንደሚታይ ፊልም በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ የተመረተ ምርት ወደ ቀሪ አለም ሲጫን ቁልጭ ብሎ ተመለከትኩ......የሚመረተው ምርት በታላልቅ ዘመናዊ መሳሪያዎች መሆኑን ተመለከትኩ። የአሁን ገበሬ በበሬ እና በፈረስ እንደሚያርስ አይደለም ትልልቅ ትራክተሮች እዚህም እዚያም በስራ ተጠምደው ትራክተር ሲያርስ በግልጽ ተመለከትኩ።"

የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ፤ 1993/ በቄስ በሊና ሳርካ ገጽ 54

Address

Wolayta
Dire Dawa
ZIPCODE

Telephone

+251912244413

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alazer yohones posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Alazer yohones:

Share

Category