Ahadu Tube

Ahadu Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ahadu Tube, Travel Agency, Durame, Durame.

የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ያስደነገጠው ዲፕሲክ ማን ነው?"ዲፕሴክ" የተሰኘው የኤአይ መተግበሪያ የዓለማችን ተፈላጊው መተግበሪያ ሆኗል   | ከሰሞኑ መሰረቱን ቻይና ያደረገው ዲፕ ሲክ መ...
29/01/2025

የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ያስደነገጠው ዲፕሲክ ማን ነው?

"ዲፕሴክ" የተሰኘው የኤአይ መተግበሪያ የዓለማችን ተፈላጊው መተግበሪያ ሆኗል

| ከሰሞኑ መሰረቱን ቻይና ያደረገው ዲፕ ሲክ መተግበሪያ ወይም አፕ በአፕ ስቶር ላይ ይጫናል።

ይህ መተግበሪያ እንደ ጎግሉ ጀሚኒ፣ እንደ ኦፕን አይ ኩባንያው ቻትጅፒቲ እና ሌሎችም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያች ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት እንዲሰጥ ተብሎ የተዘጋጀ ነው።

የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርገው የሰሩ ቢሆንም ይህ የቻይናው ጀማሪ ኩባንያ ግን በትንሽ ወጪ መስራቱ ተገልጻል።

ዲፕሲክ መተግበሪያ በስድስት ሚሊዮን ዶላር ወጪ መሰራቱ ብቻ ሳይሆን ለተጠቃሚዎች እየሰጠ ያለው አገልግሎት ፈጣን መሆኑ በብዙዎች ተመራጭ መሆን ችሏል ተብሏል።

እንደ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ ዲፕሲክ መተግበሪያ አሁን ላይ በአፕስቶር ላይ ቁጥር አንድ ተፈላጊ ሆኗል።

ይህ መሆኑ እንደ ኦፕን አይ እና ጎግል ኩባንያዎችን ትኩረት ስቧል የተባለ ሲሆን የቴክኖሎጂ ምርቶችን እንዳትጠቀም በአሜሪካ ማዕቀብ ለተጣለባት ቻይና ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆን ተገልጿል።

አዲሱ መተግበሪያ አሁን ላይ ከቻትጅፒቲ እና ጀሚኒ በላይ ተፈላጊው መተግበሪያ ሆኗልም ተብሏል።

ዲፕሲክ መተግበሪያ ለተጠቃሚዎች በውድ ዋጋ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ኩባንያዎች የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ሊያስገድድ እንደሚችልም ተጠቅሷል።

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረተ ልማት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን ከሰሞኑ የ500 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ከኦፕን አይ ኩባንያ ጋር መፈራረሙ ይታወሳል።

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በየጊዜው እየዘመነ እንደሚሄድ እና በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ በሰዎች የሚከወኑ መሰረታዊ ስራዎችን ሳይቀር ይሰራል በሚል ቴክኖሎጂ ቁጥጥር እንዲደረግበት ባለሙያዎች በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል። #አል ዐይን

GRAND OPENING  TOMORROW                JAN 18-2025 🔥
17/01/2025

GRAND OPENING TOMORROW
JAN 18-2025 🔥

🇪🇹 ኢትዮጵያ በ5 ቢሊየን ፓውንድ የተሸለመውን "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ አደረገች!ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁ ኤርፖርት "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ልትገነባ ነው! ከአዲስ አበባ በ25 ...
03/12/2024

🇪🇹 ኢትዮጵያ በ5 ቢሊየን ፓውንድ የተሸለመውን "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ አደረገች!

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁ ኤርፖርት "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ልትገነባ ነው!
ከአዲስ አበባ በ25 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ የወደፊት አየር ማረፊያ በ2029 ሲጠናቀቅ እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት የሚያስተናግድ ትልቅ ተርሚናል እና አራት ማኮብኮቢያዎችን ይይዛል።🇪🇹

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዳር አል ሀንዳሳ አማካሪዎች ጋር በመተባበር የሚመራው ይህ የ5 ቢሊዮን ፓውንድ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ዋና ተዋናይ ለማድረግ ያለመ ነው።
አዲሱ ተቋም እንደ ዱባይ እና ሄትሮው ያሉ አለምአቀፍ አየር ማረፊያዎችን ለመወዳደር ተዘጋጅቷል!🇪🇹

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መጨናነቅ ቢያጋጥመውም "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ይህን ችግር በመቅረፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋል።
ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ የአለምአቀፍ የአቪዬሽን ማዕከል ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው!

#ሜጋ ኤርፖርት ከተማ #ኢትዮጵያ #አቪዬሽን #መሠረተ ልማት #አፍሪካ እየጨመረ ነው።🇪🇹 🇪🇹👌

❤️


Ethiopia is constructing a £5 billion "Mega Airport City," expected to be Africa’s largest airport and one of the busiest worldwide.

The new airport, located near Bishoftu, 25 miles from Addis Ababa, will handle up to 110 million passengers annually upon its completion in 2029. The ambitious project, led by Ethiopian Airlines in collaboration with Dar Al-Handasah Consultants, features a cutting-edge terminal and four runways.

Currently, Addis Ababa's Bole International Airport, situated 2,334 meters above sea level, faces congestion as Ethiopia cements its status as a global aviation hub.

The "Mega Airport City" will not only alleviate this strain but also boost Ethiopia's economy, positioning the country as a major player in international business and tourism. The new facility aims to rival global airports like Dubai and Heathrow.

ዛሬ ማታ 3:00 ላይ ሁላችንም ወደ tiktokMaster Abinet Kebede
08/11/2024

ዛሬ ማታ 3:00 ላይ ሁላችንም ወደ tiktok
Master Abinet Kebede

በፈጣሪ የምታምኑ ሁሉ ጨርሳችሁ እንድታነቡት እንማፀናችኋለን🙏 ሠላም በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ላላችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ: በያላችሁበት የፈጣሪ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እያልን...
26/10/2024

በፈጣሪ የምታምኑ ሁሉ ጨርሳችሁ እንድታነቡት እንማፀናችኋለን🙏

ሠላም በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ላላችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ: በያላችሁበት የፈጣሪ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እያልን: እጅግ የምንወዳት እህታችን ወጣት ረድዔት ዳምጠው አፍላ የወጣትነት ዕድሜዋንና ሕልሟን የጨለማ ድባብ አጠልሽቶባታልና በሕያው በእግዚአብሔር ስም ወገናዊ አጋርነታችሁን እንድታሳዩን እየጠየቅን ወደ ዝርዝር ሀሳቡ ልውሰዳችሁ:-

ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን የምትባል ስትሆን ትውልዷና እድገቷ በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን መዲና በሆነችው #ዱራሜ በተለምዶ አዲስ ከተማ ልዩ ስሙ ሌሊሶ_ቀይመስቀል ሰፈር ነው።

እህታችን ረድዔት በ 10ቀን 2013 ዓ.ም ድንገት የሞተር ሳይክል አደጋ በግራ እግሯ ደርሶባት በዱራሜ ዶ/ቦጋለች ገብሬ አጠቃለይ ሆስፒታል ስትታከም ቆይታ : ጨርሶ ሊሻላት ባለመቻሉ : ሻሸመኔ ፈያ ሆስፒታል ፣ ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል፣ በ ሀዋሳ ያኔት ሆስፒታል ፣ በ ሀዋሳ ፓነስያ ሆስፒታል እና ጥቁር ዓንበሳ ሆስፒታል ተዟዙራ የታከመች ሲሆን በወቅቱ በአንፃራዊነት የተሻላት መስሎ ወደ ቤቷ ብትመለስም እያደር ሕመሟ እየባሰና ጉዳት የደረሰባት እግሯ ላይ የተለየ እድገት በመታየቱ በድጋሚ ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታልና ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈር ተደርጋ ለወራት ሕክምና ብትከታተልም ጉዳዩ ከታሰበውና ከተገመተው በላይ ሆኖ ተገኝቷል። በአደጋው የተጎዳው እግሯም በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ አጥንት ካንሰርነት መቀየሩን የተለያዩ ስፔሻሊስት ዶክተሮች ያሳወቁ ሲሆን በመጨረሻም የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ህክምና ክፍል ዋና ዳይሬክተር #ፕ/ር_ብሩክ_ላምብሶ የወጣቷ ረድዔት ህክምና በሀገር ውስጥ የማይቻል እንደሆነና ሕይወቷን ለመታደግ በአፋጣኝ ወደ ሕንድ ሐገር _ ሆስፒታል ሄዳ መታከም እንዳለባት ሪፈር የፃፉ ሲሆን የተፃፈውንም ደብዳቤ ከታች በምስል አስቀምጠናል።

በዚህ መነሻ የእህታችን ረድዔት ወላጆች በሀገር ውስጥ ህክምና እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው የወጣት ልጃቸውን ሕይወት ለመታደግ ከሚችሉት በላይ ጥረዋል። አሁን ግን ነገሩ ሁሉ ከሚያስቡትና ከሚሸከሙት በላይ ሆኖባቸው ስለመጣ ለህክምናና መሰል ወጪዎች የተጠየቀውን 4,000000 የሚጠጋ ገንዘብ ሊወጡት የማይችሉት ስለሆነባቸው ወላጆችዋ በሚያሳዝን ሁኔታ ከታመመቸው እህታችን በከፋ ልባቸው ተሰብሯልና እጅግ የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን የዚህችን ባለ ተስፋ ወጣትን ሕይወት ለመታደግ ፈጣሪ ከሰጣችሁ ላይ ልባችሁ የፈቀደውን በመቸር የእህታችንን ረድዔት ዳምጠውን የደበዘዘ ተስፋ ዳግም በማለምለም የቆዘመውንም ቤተሰብ ከሐዘን በማስወጣት ኢትዮጵያዊ መልካምነታችሁን እንድትገልፁልን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንማፀናለን 🙏

እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ!!
ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን !!

የረድዔት ዳምጠው ወላጆች ስልክ ቁጥር

የባንክ አካውንት

Nigd bank 1000654819436

Awash bank 013471436377500

Dashin bank 5351755991011

Birhan bank 1030982950414

Abisinya bank 206408677

ለበለጠ መረጃ:-

0931365246 ወ/ሮ ፍቅሬ ሻሜቦ (እናቷ)
0916276346 አቶ ዳምጠው ላንገና (አባቷ)

በማድረግ ለቅን ልቦች መረጃውን ማዳረስ አንዱ የእርዳታ አካል ነውና መረጃውን ለወዳጅ ዘመድ በማድረግ ያጋሩልን🙏

😭   😭😭 ተወዳጁ የEbs የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈተወዳጁ ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን...
14/01/2024

😭 😭

😭 ተወዳጁ የEbs የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ

ተወዳጁ ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከወጣም በኃላ ኑሮ በአሜሪካ የተሰኜ አስተማሪ ፕሮግራም ለኢትዮጵያን ሲያቀርብ የነበረ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነበር

ከውጭ ሀገር ተመልሶም በEbs የእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ዝግጅቶችን በማቅረብ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ የጋዜጠነትን ስነ ምግባር በአግባቡ የተላበሰ በሳል ጋዜጠኛ ነበር

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ በዛሬው እለት ማረፏ ተስምቷል

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር !

ለዘመድ ወዳጅና ለአድናቂወቹ መፅናናትን እንመኛለን

Ahadu tube የናንተው

ሞሪስ ካልካ የታዋቂው አንበሳ ሀውልት ገምቢቀኃሥ ቴያትር አጠገብ የሚገኘው በአለም ዙሪያ ታዋቂው ንድፍ ዝግጅትና ግምባታ ያከናወኑት ታዋቂው በዜግነት ፈረንሳዊ በትውልድ ፖሊሽ የነበሩት በሞሪስ...
31/08/2023

ሞሪስ ካልካ የታዋቂው አንበሳ ሀውልት ገምቢ

ቀኃሥ ቴያትር አጠገብ የሚገኘው በአለም ዙሪያ ታዋቂው ንድፍ ዝግጅትና ግምባታ ያከናወኑት ታዋቂው በዜግነት ፈረንሳዊ በትውልድ ፖሊሽ የነበሩት በሞሪስ ካልካ ነበር።

ሀውልቱ እንዲሰራ ያዘዙት ቀኃሥ ሲሆኑ ትእዛዝ ተቀባዩ የዚያኔ ያዲስ አበባ ከንቲባ ዘውዴ ብላቴን ጌታ ዘውዴ በላይነህ ነበሩ። ብዙ ዘውዴ የተባሉ ወደ አምስት ከንቲባዎች ስለነበሩ እኝህኛውን መግለጽ ያስፈልጋል። ብላቴን ጌታ ዘውዴ የሚታወቁት በቁመታቸው ማጠር ፣ ወፈር ያለ መነጥር ማድረግ ፣ መላጣና እንክብል ራሳቸውና እዚያ ላይ የሚደፏት የእንግሊዝ ቦውለር ቆብ ነበር። በግልጽ ለክብራቸው በሚመጥን ትልቅ መኪና ሲጓዙም እንደ ህጻን ታች ስለሚወርዱ እንዲታዩ ብለው አንገታቸውን ወደ ላይ የሚያንጠራሩት ለኛ ትውልድ አንዱ መዝናኛ ነበር።

የሀውልቱን ትእዛዝ ለማስፈጸም ሲያፈላልጉ ከሁሉ በልጦ የተገኘው ካልካን ኮንትራት ሰጡ። በተመረጠው ቦታ ላይ በሳጠራ ተከልሎና በፖሊስ እየተጠበቀ ከአመት በላይ ፈጅቶ ሀውልቱ በኛ በ1947 ተፈጸመ። ጃንሆይ ሀውልቱን ሊመርቁ ሲሄዱ በሸራ ተሸፍኖ ገመድ ቆርጠው እንደዘመኑ ሀውልቱ ላይ ሻምፓኝ ከተከሰከሰ በኋላ ከንፈራቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ትክ ብለው ካዩ በኋላ ከንቲባ ዘውዴን ለመሆኑ ይህ ምንድን ነው አሏቸው። ከንቲባም ተደናግጠው አንበሳ ነውኮ ጃንሆይ አሉ። ጃንሆይም ለመሆኑ ምን ያህል ተኩፈለበት ብለው ጠየቁ። ከንቲባም ላብ ላብ እያላቸው አንድ ሚሊዮን አሉ። ጃንሆይም ፈገግ ሳይሉ ይህ አንበሲ ባይመስልም የተከፈለበት አንበሳ ያደርገዋል ብለው ባሽሙር ወረፏቸው። ከንቲባም ብዙ ሳይቆዩ ከስራቸው ተባረው ካንድ አመት በላይ ሳይሰሩ ተባረሩ።

ያምበሳው ሀውልቱ ግን ወዲያው ገናና በመሆን በአለም ዙሪያ ታዋቂ በመሆን የጎብኚዎች መስህብ ሆነ። በተለይ በዘመኑ ለአፍሪካ ለነጻነት ይታገሉ የነበሩት መሪዎች የሀውልቱን ምስል የነጻነት ተምሳሌት አድርገውት ነበር። ደርግ ያፈርሰዋል እየተባለ ይፈራ ነበር። ከዚያም በኋላ የመጡት እንደዚሁ። ነገር ግን ሀውልቱ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሎጎ ሆኖ ኖሯል። ገምቢው ሞሪስ ካልካ በ1991 አሜሪካን በጣም ታዋቂ አርቲስት ሆነው አርፈዋል።

ነፍስ ይማር

via ዶ/ር አበበ ኃረገወይን

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው የወንዶች ማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች ************************** በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻም...
27/08/2023

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው የወንዶች ማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች
**************************

በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወንዶች ማራቶን አትሌት ልዑል ገ/ሥላሴ ለሀገራችን የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

በውድድሩ ዩጋንዳዊው አትሌት ቪክቶር ኪፕላጋት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።

03/08/2023

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የክላስተር ቢሮዎች ሽንሸና በማንኛውም ዓይነት መመዘኛ ፍትሃዊነት የጎደለው ነውና አጥብቄ እቃወማለሁ።

Address

Durame
Durame

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahadu Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category