11/04/2026
#ተጋበዙልኝ Family❤️
የትንሳኤ በዓል ልዩ እንግዳ
ወጣቷ አስጎብኚ ሴና ሀ/ማርያም የህክምና ምሩቅ ብትሆንም፣ ብዙዎች የሚመርጡትን መንገድ ሳትከተል የራሷን የአስጎብኚ ተቋም በመመስረት ራሷን ብቻ አልቀየረችም፤ ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥራለች። በተለይ በዚህ ዘመን የስራ እጥረት ሲታይ፣ እሷ ግን ችግርን በእድል ቀይራለች።
🌍 ከቦታ ወደ ቦታ በመጓዝ
🏞️ የአገራችንን ውብ ቦታዎች በማስተዋወቅ
📸 ልምዷን በማህበራዊ ሚዲያ በመካፈል
💼 ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር
ወጣቶች “እኛም እንችላለን” ማለት እንዲጀምሩ አድርጋለች። ለብዙዎች የድፍረት ምሳሌ ሆናለች። ሕልምን ወደ ተግባር መቀየር እንደሚቻል አሳይታለች።
በሀገራችን ያሉ ውብ ቦታዎችን፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ ሀብቶችን ለሌሎች በማስተዋወቅ፣ የጉዞን ትርጉም ከመዝናኛ በላይ መሆኑን በማሳየት ላይ ትገኛለች ።
"ሀኪሟ አስጎብኚ" በሚል የምትታወቀውን ወጣት ሴና ሀ/ማርያም የህይወትና የስራ ልምድ ተሞክሮዎችን በዝርዝር ተካፍለናለች።
👉እንዳያመልጥዎ! ፋሲካን ከእኛ ጋር ያሳልፉ።
📅 መቼ፡ የትንሳኤ ዕለት ከሰዓት
📻 በደቡብ ድምፅ ኤፍ ኤም 100.9 እና በሆሳዕና ኤፍ ኤም 95.3 ይጠብቁን