Hadiya zone culture tourism& sport department

Hadiya zone culture tourism& sport department Hadiya zone culture tourism and sport Dept

የ2013 ዓ.ም ያሆዴ  የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትና ተጋላጭነት ለመከላከል እንዲቻል እንደ ቀድሞ ህዝብ በተሰበሰበበት እንደማይከበር ተገለጸ፡፡የሀዲያ ብሄ...
08/09/2020

የ2013 ዓ.ም ያሆዴ የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትና ተጋላጭነት ለመከላከል እንዲቻል እንደ ቀድሞ ህዝብ በተሰበሰበበት እንደማይከበር ተገለጸ፡፡

የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል አከባበር የዞኑን ባህላዊ እሴቶችን ከማጠናከር አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከመሆኑም ባለፈ ባህላዊ ክዋኔው በቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራ እንደሆነ የገለጹት የዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሲሳይ እዉነቱ የ2013 ዓ.ም የበዓሉ አከባበር ሂደት ህብረተሰቡ ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማይሆን መልኩ ሁሉም በያለበት ሊያከብር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ግን ይህ ታላቅ በዓል ታስቦ የሚውልበትን እና የበዓሉ አከባበር ሂደት አስመልክቶ የዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ከዞን፣ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፍዎች ጋር እንዲሁም ከብሄሩ የባህል ሽማግሌዎች እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በስፋት ወይይት የተደረገበት ሲሆን እንደ ቀድሞ ህዝብ ባልተሰበሰበበት እና የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ባገናዘበ ሁኔታ የክብረ በዓሉን ክዋኔዎች ባካተተ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል።

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሻናፊ ጴጥሮስ በበኩላቸው የብሔሩ ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉም የዞኑ ህብረተሰብ በአንድነት እንዲያከብር በወቅቱ የተጋረጠው የቫይረስ ስርጭት ጤና ስጋት በመሆኑ የሚደረገው የትኛውም የበዓሉ አከባበር ስርዓት ለቫይረሱ ተጋላጭ በማይሆን መንገድ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በዓል ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የዞኑ ተወላጆች ባሉበት አካባቢ ሆነው እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበው ምን አልባትም በአስገዳጅ ሁኔታ የሚምመጡ ከሆነም በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ገብተው ጤናቸው ሳይረጋገጥ ወደ ህብረተሰቡ እንደማይቀላቀሉ አሳስበዋል፡፡

ህብረተሰቡ የበዓሉን አቀባበር በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የሚከታተሉበት ሁኔታ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
ዘገባው የሀድያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።

የጀግናው ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሐውልት ግንባት  የመሰረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ስርዓት ተካሄደነሐሴ 20/2012 ዓ.ም (የሀድያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)መሰረተ ድንጋዩ የተጣለውም በሆ...
26/08/2020

የጀግናው ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሐውልት ግንባት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ስርዓት ተካሄደ

ነሐሴ 20/2012 ዓ.ም (የሀድያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

መሰረተ ድንጋዩ የተጣለውም በሆሳዕና ከተማ ከዚህ ቀደም በጀግናው ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ስም በተሰየመው አደባባይ ነው፡፡

የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ የሀድያ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ አቦ አና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታምራት ግዛው የመሰረተ ድንጋይ የማኖር ስነ-ስርኣቱን አድርገዋል፡፡

የመሰረተ ድንጋይ የማኖር ሥነ-ስርዓት ላይ የዞን እና የከተማ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል፡፡

የግንባታው ዲዛይን ሀገር በቀል በሆነው ኬቭ አርክቴክት አማካሪ ኢንተርፕራዝ በኩል ተሰርቶ የቀረበ ሲሆን የግንባታውን ሂደት ለማከናወን አሸናፊ በሆነው ተቋራጭ ከነገ ጀምሮ ስራው የሚጀመር ይሆናል፡፡ ግንባታውንም ለማጠናቀቅ የ210 ቀናት የስራ ገደብ ተሰጥቶታል፡፡
ምንጭ : የሀድያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ተጀምሯል!!..............የአቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም መጫወቻ ሜዳ ሣር ተከላና ተያያዥ የጥገና ስራዎች በዛሬው እለት ተጀምሯል።ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ  የሆነው የኮሮና ቫይረስ በ...
09/06/2020

ተጀምሯል!!..............
የአቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም መጫወቻ ሜዳ ሣር ተከላና ተያያዥ የጥገና ስራዎች በዛሬው እለት ተጀምሯል።
ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ የሆነው የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲቋረጥ መወሰኑ ይተወሳል:: ወትሮም ቢሆን ከክለቦች ቅሬታ ከፌዴሬሺኑ ማስጠንቀቂያ ሲያስተናግድ የቆየው የአብዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም አምና ከውድድሩ አስቀድሞ የሣር ተከላና የጥገና ሥራ ተጀምሮለት የነበረ ቢሆንም ከነበረው የግዜ መጣበብ የተነሳ ሳይጠናቀቅ የውድድር ጊዜ በመድረሱ የተቋረጠ መሆኑ የሚተወቅ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ይህንን ችግር ለመቅረፍ አስቀድሞ ስራው መጀመሩ ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያ በድህረ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቱሪዝም መስዕብ ተመራጭ ከሚሆኑ ከ7 አገራት ውስጥ አንዷ   ትሆናለች፦ ፎርብስ***************************ኢትዮጵያ  የኮሮና ቫይረስ ወረ...
01/06/2020

ኢትዮጵያ በድህረ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቱሪዝም መስዕብ ተመራጭ ከሚሆኑ ከ7 አገራት ውስጥ አንዷ ትሆናለች፦ ፎርብስ

***************************

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከጠፋ በኋላ በቱሪስት መዳረሻት ከተመረጡ ሰባት አገሮች መካከል አንዷ እንደምትሆን በአሜሪካ ታዋቂ የቢዝነስ መጽሔት የሆነው ፎርብስ ትንበያውን አስቀምጧል፡፡

በአለም የኮቪድ-19 በሽታ ክፉኛ ከጎዳቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል ቱሪዝም አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ሆኖም በድህረ-ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በቱሪዝም ዘርፍ ሰባት የአለም አገራት ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፎርብስ መጽሔት አስነብቧል፡፡

ከእነዚህ ሰባት አገሮች ውስጥም ኢትዮጵያ ባላት የታሪክ፣ የተፈጥሮና የባህል ሀብቷ በግንባር ቀደምትነት የቱሪዝም መዳረሻ ትሆናለች ብሏል፡፡

በተለይ የአውሮፓ ቅኝ ገዢ በጦርነት ያሸነፈች ብቸኛዋ የአፍሪካ አገር፤ የቀድሞ የሰው ልጅ መገኛ እና በጥንታዊ ስልጣኔ በዘርፉ ተመራጭ ከሚያደርጓት ምክንያቶች የተወሰኑት እንደሆኑ መጽሔቱ አትቷል፡፡

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኢራን፣ ማይናማር፣ ጆርጂያ፣ ፊሊፒንስ፣ ስሎቨኒያና ቱኒዚያ በድህረ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተመራጭ የቱሪዝም መዳራሻ ሊሆን እንደሚችሉ መጽሔቱ አመላክቷል፡፡

EBC

ትኩረት የሚሻው ጉዳይ!!.................................የደቡብ ክልል ከአዲስ በአበባ በመቀጠል ሌላኛው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ማዕከል እንዳይሆን ስጋት እንዳለው አስታወቀ...
01/06/2020

ትኩረት የሚሻው ጉዳይ!!.................................

የደቡብ ክልል ከአዲስ በአበባ በመቀጠል ሌላኛው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ማዕከል እንዳይሆን ስጋት እንዳለው አስታወቀ

የክልሎ ጤና ቢሮ እንዳለው በአዲስ አበባ እየተደረገ ባለው የቤት ለቤት አሰሳ የተገኙ የክልሉ ነዋሪዎች ውጤታቸው ሳይደርስ ወደ ክልሉ በመመለሳቸው ስጋት ውስጥ መግባቱን ተናግሯል፡፡

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ አጥናው ካውዛ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በአዲስ አበባ በቀን ስራ ተሰማርተው የነበሩ ስድስት ወጣቶች የጤና ሚኒስቴር ቤት ለቤት ባደረገው አሰሳ ነበር ምርመራ የተደረገላቸው፡፡

ይሁን እንጂ በከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ያመጣውን የስራ መቀዛቀዝ ተከትሎ ስራ በማጣታቸው ውጤታቸው ሳይደርስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በዚህ መሀል ታዲያ ከፍተኛ መዛመት ሳደርስ እንዳልቀረ ስጋት እንዳለው ይናገራሉ፡፡

ወጣቶቹ ውጤታቸው በቫይረሱ መያዛቸውን ስለሚያመለክት በአፋጣኝ ወደ ህክምናው እንዲገቡ ቢፈለጉ መገኘት ስላልቻሉ ጤና ሚኒስቴር በላከልን መረጃ መሰረት ተከታትለን አምስቱን አግኝተናል አንዱ ግን ስልኩን አጥፍቷል ፤የሰጠው መረጃም ስህተት በመሆኑ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል አቶ አጥናው፡፡

በደቡብ ክልል እስካሁን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ቁጥር አሁን ወደ 13 ከፍ ብሏል።

አሁን የተገኙት ሰዎች የጤና ሚኒስቴር የናሙና ምርመራን ሲያደርግ መረጃዎች በትክክል በመመዝገቡ መሆኑን የሚያስረዱት አቶ አቅናው ምርመራ ሳይደረግላቸው ስራ በማጣት ወደ ትውልድ ስፍራቸው የሚመለሱ በርካታ የክልሉ ሰዎች እንዳሉ ያነሳሉ።

ትናንት እንኳን 400 ወጣቶችን አግኝተናል ወደማቆያም አስገብተናል ብለዋል፡፡

በሲዳማ ፤ወላይታ ፤ጉራጊ፤ ስልጤ፤ሀዲያ፤ከንባታን የመሳሰሉ የክልሉ አከባቢዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል
# ምንጭ
👇

የኮቪድ-19 ክትባት!የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ክትባት ወደ 2ተኛው ደረጃ ተሸጋገረ። በቀጣይ ክትባቱን በ10,260 ሰዎች ላይ (ከ70 ዓመት በላይ እና ከ5-12 ዓመት የእድሜ ክልል) በሙከራ ደ...
26/05/2020

የኮቪድ-19 ክትባት!

የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ክትባት ወደ 2ተኛው ደረጃ ተሸጋገረ። በቀጣይ ክትባቱን በ10,260 ሰዎች ላይ (ከ70 ዓመት በላይ እና ከ5-12 ዓመት የእድሜ ክልል) በሙከራ ደረጃ ለመስጠት ታቅዷል።

እስካሁን ክትባቱ ጥሩ ውጤት እያሳየ ነው የተባለ ሲሆን ሳይንቲስቶች አሁን ያለው ሂደት በዚህ ከቀጠለ በጥቂት ወራቶች ውስጥ ክትባቱን በስፋት ለማዘጋጀትና ለማድረስ እንደሚሰራ ተናገርዋል።

የUK መንግስት በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ዋስትና እንደሌለ ተናግሯል ፤ የኮቪድ-19 ክትባትን ለመዘጋጀት ጊዜ ሊውስድ እንደሚችልም ጠቁሟል።

በርካታ ባለሞያዎች ለዚህ ወረርሽኝ ፍቱን ክትባት አግኝቶ እና አምርቶ ለሰዎች ለማዳረስ ከ12-18 ወራት ሊወስድ እንደሚችል እየተናገሩ ነው።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ኮሮና ቫይረስን (ኮቪድ-19) #ይከላከላሉ የተባሉ ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው ነው።

Via= Engda hailu

በ13-09-2012 ዓ.ም ለአምስት (5) ሰዎች ናሙና የተወሰደላቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ቀደም ሲል ፖዘቲቭ የነበረው ግለሰብ ጭምር ሲሆን  ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፡፡ በተጨማ...
22/05/2020

በ13-09-2012 ዓ.ም ለአምስት (5) ሰዎች ናሙና የተወሰደላቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ቀደም ሲል ፖዘቲቭ የነበረው ግለሰብ ጭምር ሲሆን ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፡፡ በተጨማሪም በዛሬው እለት ማለትም በ13/09/2012 ዓ.ም 49 (አርባ ዘጠኝ) በማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩ ተጠርጣሪዎች የቆይታ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁና ምንም ዓይነት የበሽታው ምልክት ያልታየባቸው ሆነው በመገኘቱ አስፈላጊው ትምህርት ተሰጥቷቸው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተሸኝተዋል፡፡
ምንጭ: HZHD

የጨረታ ማስታወቂያበጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ስም በሆሳዕና ከተማ በተሠየመው አደባባይ የኮሎኔሉ ሀውልት ሊገነባ ነው፡፡የሀድያ ዞን አስተዳደርና የሀድያ ልማት ማህበር (ሀልማ) በጀግናው ...
19/05/2020

የጨረታ ማስታወቂያ

በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ስም በሆሳዕና ከተማ በተሠየመው አደባባይ የኮሎኔሉ ሀውልት ሊገነባ ነው፡፡

የሀድያ ዞን አስተዳደርና የሀድያ ልማት ማህበር (ሀልማ) በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ስም ሀውልት ለማስገንባት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ግንባታውን ለማስጀመር #በአዲስ ዘመን ጋዜጣ #ሚያዚያ 28/8/2012 ዓ.ም በወጣው ዕትም ላይ የጨረታ ማስታወቂያው ዝርዝር ቀርቧል፡፡

በዚሁም መሠረት በሀውልት ግንባታ ስራው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተቋራጮች መወዳደር እንድትችሉ ጥቁምታችንን እንሠጣለን፡፡

የሀውልቱን ግንባታ ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት መላው የዞኑ ሕዝብ ከልማት ማህበሩና ከዞኑ አስተዳደር ጎን በመሆን የበኩላችሁን እንድትወጡ ይጠይቃል የዞኑ አስተዳደር፡፡ የዘገበው የሀድያ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

18/05/2020

የሀዲያ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የሀዲይ ነፈራ ዙሪያ አጥር፤ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Bids closing date 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት
Bids opening date 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 4፡30 ሰዓት
Published on Addis Zemen ( ሚያዝያ 27፣ 2012 )
Posted on ሚያዝያ 28፣ 2012
Bid document price Birr 200.00
Bid bond Birr 10,000.00
የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዲያ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የሀዲይ ነፈራ ዙሪያ አጥር፤ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

ደረጃቸው BC/GC-9 የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የኮንስትራክሽን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከዞኑ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ክፍል ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 3ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በዞኑ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ስም ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም እሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው::
ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም እሽጎና የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ እና የቴክኒካል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎና የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ሁለቱንም (ፋይናንሻል እና የቴክኒካል) ፖስታዎችን በሌላ ማጠቃለያ እናት ፖስታ አድርጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የስራውን ዋጋ በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ ለብቻው በየመጠይቁ (ባዶ ቦታዎች) ተሞልቶ፣ ተፈርሞና ታሽጎ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ መጠይቆች (ባዶ ቦታዎች) ላይሞሉ ማህተም ብቻ አድርጎ መመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
ጨረታው በ21ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙባት በዞኑ ግዥ ፋይ/ን/ አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-አዲሱ የተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-555-2304 መጠየቅ ይቻላል፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥ

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ ተፅዕኖ ውስጥ የሚገኘውን የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ በቀጣይ ከገባበት ቀውስ ማገገም የሚችልበት እቅድ ተዘጋጀ፡፡የኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከቱሪ...
17/05/2020

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ ተፅዕኖ ውስጥ የሚገኘውን የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ በቀጣይ ከገባበት ቀውስ ማገገም የሚችልበት እቅድ ተዘጋጀ፡፡
የኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከቱሪዝም ኢትዮጵያና ከሆቴልና አስጎብኝ ማህበራት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ማገገሚያ እቅድ ለዚሁ ተግባር በተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የፀደቀ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ ከክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተደረገውን ውይይት የመሩት የኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው የኮሮና ወረርሽኝ በቀዳሚነት ከሚጎዳቸው ዘርፎች ዋነኛው ቱሪዝም ነው ያሉ ሲሆን ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ፈጣን የማገገሚያ እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ወቅታዊ እቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
የየክልሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የሚመለከታው አካላት ወረርሽኙ የጋረጠውን አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ይህን እቅድ በፍጥነት ማዘጋጀታቸው የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ከየክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ወረርሽኙ ያስከተለባቸው ፈተናዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው ሀገራችን ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ በአዲስ መልክ ተጠናክሮ የሚመለስ የቱሪዝም ዘርፍ ለመፍጠር የተፈጠረውን ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ ልትጠቀምበት ትችላለች ያሉ ሲሆን እቅዱም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፅዋል፡፡
ነገ ለመጓዝ ዛሬን ከቤታችን አንውጣ የሚለውን ዘመቻ በማጠናከር ከኮሮና መልስ ጠንካራ ቱሪዝም ይዘን ወደ አለም አቀፍ ገበያ መመለስ እንችላለን ብለዋል፡፡
በሰነዱ ዝግጅት ላይ የተሳተፉት በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአለም አቀፍ ቱሪዝም ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ደርበው በበኩላቸው ቱሪዝም በባህሪው ከገባበት ችግር በፍጥነት የመውጣት ባህሪ ያለው ኢንዱስትሪ እንደመሆኑ ይህንኑ የሚያግዝ እና በቀላሉ ሊተገበር የሚችል ማገገሚያ እቅድ አስፈላጊ በመሆኑ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
ይህ እቅድ ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እስከ ትልልቅ ባለሀብቶች ድረስ ያለውን የዘርፉ እንቅስቃሴ መልሶ ለማነቃቃት ታስቦ የተዘጋጄ መሆኑን ያብራሩት ደግሞ በእቅድ ዝግጅቱ ላይ ሲሳተፉ የነበሩትና ሰነዱን ለውይይት ያቀረቡት የቱሪዝም ዘርፍ አማካሪው አቶ ይስፋልኝ ሀብቴ ናቸው፡፡ በመጨረሻም አጠቃላይ የማነቃቂያ እቅዱ እንደ የአለም ቱሪዝም ድርጅትና አለም አቀፍ የጉዞና የቱሪዝም ካውንስል (UNWTO, WTTC) ከመሳሰሉ አለም አቀፍ ተቋማቶች የማገገሚያ እቅዶች ጋር ተቀናጅቶ እየተመራ መሆኑን ክብርት ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡
በክልሎችና በፌደራል ተቋማቱ በሚሰሩ ስራዎቹ ዙሪያ ወጥ የሆነ የመረጃ ፍሰት ለመፍጠር እንደሚሰራም ተገልጧል፡፡

የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር በዛሬው ዕለት ከኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ይጠቅማሉ ያላቸውን 58 (ሃምሳ ስምንት) አይነት የባህል መድሃኒቶች ለኢ...
15/05/2020

የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር በዛሬው ዕለት ከኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ይጠቅማሉ ያላቸውን 58 (ሃምሳ ስምንት) አይነት የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስረከበ፡፡
ማህበሩ ለበሽታው ፈውስ ሊሰጡ ይችላሉ ያላቸውንና በመጀመሪያ ዙር ወደ ላብራቶሪ ገብተው ተጨማሪ ፍተሻና ምርምር የሚደረግባቸው 25 (ሃያ አምሥት) አይነት ባህላዊ መድሃኒቶችንም በመለየት በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለኢንስቲትዩቱ አስረክቧል፡፡
ከቀረቡት የባህል መድሃኒቶች ውስጥ በህመሙ ላልተያዙ ሰዎች መከላከያ የሚሆኑ 13 (አሥራ ሦስት) አይነት መድሃኒቶችና በህመሙ ለተያዙ ሰዎች ሊሆኑ የሚችሉ ደግሞ 45 (አርባ አምሥት) አይነት መድሃኒቶች በጥቅሉ 58 (ሃምሳ ስምንት) አይነት መድሃኒቶች ይገኙበታል፡፡
በዚሁ መሰረት መድሃኒቶቹ በመከላከያ መልክ የቀረቡ፣ በተለያዬ መልክ የሚሰጡና ወደ ሆድ የሚገቡ ተብለው የተከፋፈሉ ሲሆን ከዚህ በፊት በጤና ሚኒስቴር በኩል በተሰጠ መመሪያ መመሰረት በዛሬው ዕለት በምድብ 1 ወደ ላብራቶሪ የሚገቡ መድሃኒቶች ኮድ በማህበሩ የተሰጣቸው ሆነው የቀረቡ ስለሆነ ቀጣይ ምርመራ ይደረግባቸዋል ተብሏል፡፡
በርክክቡ ላይ የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እና የባህል ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበርን በመወከል የባህል ሀኪም አቶ ታደሰ ወ/ገብርኤል በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪና የባህላዊና ዘመናዊ መድሃኒቶች ምርምር ዳይሬክተር ለሆኑት ለወ/ሮ ፍሬህይወት ተካ አስረክበዋል፡፡

ምንጭ: MCT

Address

Zone Administration
Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya zone culture tourism& sport department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hadiya zone culture tourism& sport department:

Share