BossYoss Tour and Travel

BossYoss Tour and Travel 🇪🇹Explore Ethiopia with us🇪🇹
Tours | Day Trips | Adventure

Your journey, Our passion

12/08/2026

በወላይታ ህዝብ ዘንድ አራት አይነት ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ያሉ ሲሆን እነዚህም፦

1ኛ - Awaasiya/አዋሲያ
2ኛ - Mahaa/ማሃ
3ኛ - Sigaa/ሲጋ
4ኛ - Cuucaa-Cachchaa/ጩጫ ጫቻ

በመባል ይታወቃሉ።

በነዚህ የዕርቅ ፍልስፍናዎች ውስጥ... ወላይታ የተሰበረ ልብን የሚጠግን ሀገር በቀል ጥበብ እንዳለው ትልቅ ማሳያ ነው።

በርግጥ የሰው ልጆች በአብሮነት በኖሩባቸው ዘመናት ሁሉ፣ አለመግባባቶችና ግጭቶች ተከስተው ማለፋቸው አልቀረም። ነገር ግን በዚህ ረዥም የሕይወት ጉዞ ውስጥ ብልሃት የማይለያቸው የወላይታ አባቶች፣ ለግጭቶችና ለአለመግባባቶች የሚሰጡት ምላሽ ሁልጊዜም የተለየና አስተማሪ ነው። አዋሲያ በሚባለው የእርቅ ስርዓት የሚከወኑ ሁነቶች ደግሞ እጅግ ያስገርማሉ።

የወላይታ ታሪክ አዋቂ፣ ደራሲና ተመራማሪ የሆኑቱ አቶ አዳነ አይዛ ስለ አዋሲያ እንዲህ ይላሉ፦

"አዋሲያ፤ ቀጭኑን የአብሮነት ሰንሰለት ሳይበጥስና ፍቅር ሳይሸረሸር ፍትሕን የማስፈን ነባር ሀገር በቀል የዕርቅ ፍልስፍና ነው።"

ይኼው... ከረዥም ዘመናት በፊት የተዘረጋውና "አዋሲያ" በመባል የሚታወቀው ሀገር በቀል የዕርቅ ሥርዓት ፍትሕን የሚያሰፍነው የማህበረሰቡን ቀጭን የአብሮነት ሰንሰለት ሳይበጥስና በመካከላቸው ያለውን ፍቅር ሳይሸረሽር ነው።

በዚህ ፍልስፍና ውስጥ የሚሰየሙ የሀገር ሽማግሌዎች ምህረት አልባ ብይን ከመስጠት ይልቅ፣ ለዘላቂ ሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ ይሰጣሉ።

" #ከኖራችሁት ዕድሜ፣ #የምትኖሩት ይበልጣል" እያሉ የበዳዩን ገመና በአደባባይ ሳይዘረግፉ፣ የተበዳዩን ልብ አክመውና ጠግነው ዕርቅ የሚያወርዱበት መንገድ ከዘመናዊው የዳኝነት አካሄድ እጅጉን የተለየ ነው።

በአዋሲያ ሥርዓት የተጣሉ ባለትዳሮችን፣ ወላጆችንና ልጆችን አልፎም ወንድማማቾችን ከሚያለያያቸው ይልቅ የሚያስተሳስራቸው ነገር ይበዛል።

ዛሬ ላይ በየማህበረሰቡ ለሚታዩ የትዳር ፍቺዎችና ማህበራዊ ቀውሶች ዋነኛው መፍትሔ ቀላል ዕለታዊ ግጭቶችን ወደ ፍርድ ቤት ከመርታት ይልቅ፣ ጉዳዮችን በዚህ በአዋሲያ ሥርዓት መፍታት ነው።

አዋሲያ የቤተሰብ ጉዳይና ምስጢርን የመጠበቅ መርህ ስላለው፣ የተጣሉ ወገኖች ጉዳይ በአደባባይ እንዳይወጣና ክብራቸው እንዳይነካ ያደርጋል።

ዘመናዊው ሕግና ፍርድ ቤት ጥፋተኛን ይቀጣሉ እንጂ የተሰበረ ልብን አይጠግኑም፤ የሻከረ ግንኙነትንም አያድሱም፤ በመሆኑም ማህበራዊ ቀውሶችን በዘላቂነት ለመፍታትና ፍቅርን ለማስቀጠል እንደ 'አዋሲያ' ያሉ ሀገር በቀል የጥበብ መንገዶችን መከተልና ማልማት የዘመናችን ብልህነት ነው።





🦁World   | ዓለም-አቀፍ የአንበሳ ቀን🦁የዓለም አንበሳ ቀን በየዓመቱ በአውሮፓ አቆጣጠር ነሐሴ10 በዓለም ዙሪያ ይከበራል። ይህ ቀን የአንበሳን ልዩ የተፈጥሮ ሚና፣ የባህል እና የቅርስ ...
10/08/2026

🦁World | ዓለም-አቀፍ የአንበሳ ቀን🦁

የዓለም አንበሳ ቀን በየዓመቱ በአውሮፓ አቆጣጠር ነሐሴ10 በዓለም ዙሪያ ይከበራል። ይህ ቀን የአንበሳን ልዩ የተፈጥሮ ሚና፣ የባህል እና የቅርስ እሴት ለማስታወስ እንዲሁም አንበሶችን ከሚያጋጥሟቸው የመኖሪያ አካባቢ መጥፋት፣ ከሰዎች ጋር ግጭት፣ ሕገወጥ አደን እና የአደን እንስሳት መቀነስ ካሉ ስጋቶች ለመጠበቅ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያገለግል ነው። አንበሳ የዱር አራዊት ንጉሥ ብቻ ሳይሆን፣ የተፈጥሮ ሥርዓት ሚዛን እንዲጠበቅ ጠቃሚ ሚና የሚጫወት እንስሳ ነው። ስለዚህ አንበሳን መጠበቅ የአንበሳን ሕይወት ብቻ ሳይሆን ሰፊውን የተፈጥሮ ሥርዓት እና የወደፊት ትውልድ ተፈጥሯዊ ቅርስ መጠበቅ ነው።

🇪🇹 የኢትዮጵያ አንበሳ🇪🇹

ኢትዮጵያ ከተፈጥሯዊ ሀብቷ ባሻገር ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትርጉም ያላት አገር ናት። ከአንበሳ ጋር በተያያዘም በኢትዮጵያ ታሪክ እና ባህል ውስጥ አንበሳ ማለት #የኃይል፣ #የጀግንነት፣ #የክብር እና #የንጉሣዊነት ምልክት ሆኖ ለረጅም ዘመናት ቆይቷል። በተለይም የይሁዳ አንበሳ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ምልክትነት የተለየ ስፍራ አለው።

በርግጥ በአገራችን ያሉ አንበሶች የታሪክና የባህል ምልክት ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ተፈጥሯዊ ቅርስም ናቸው። እኚሁ አንበሶች... በተለያዩ የአገሪቱ ብሔራዊ ፓርኮችና የዱር አካባቢዎች ይገኛሉ። ከሚገኙባቸው ቦታዎች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል...

(በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ ክልል)፦ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስነው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ ከአባይ ገባር ወንዞች ጋር በተያያዙ ደኖችና ረግረጋማ ሜዳዎች የተከበበ ነው።

እና (በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኦሞ ሸለቆ አካባቢ)፦ ሰፋፊ ያልተነካኩ የዱር አካባቢዎችን የያዙ ፓርኮች ናቸው።

(በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ ከቦንጋ ከተማ አቅራቢያ)፦ ከዝሆኖችና ጎሽ ጋር አንበሶች የሚኖሩበት አካባቢ ነው።

(በአፋር አካባቢ፣ ከአዲስ አበባ ብዙም ያልራቀ)፦ ከኢትዮጵያ ጥንታዊ ብሔራዊ ፓርኮች አንዱ ሲሆን አንበሶች ይገኙበታል።

እንዲሁም ፦ ጥቂት ቁጥር ያላቸው አንበሶች የሚስተዋሉባቸው ቦታዎች ናቸው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእነዚህ ፓርኮች ውስጥ ያሉት አንበሶች ቁጥር በአነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በግጭት፣ በመኖሪያ አካባቢ መመናመንና ውጤታማ ባልሆነ ጥበቃ ምክንያት ቁጥራቸው እየቀነሰ ነው። ስለዚህ ለእነዚህ አንበሶች ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

አሁን ላይ... የኢትዮጵያ አንበሶች በተለያዩ ምክንያቶች ከባድ የሕልውና ስጋቶች ይገጥሟቸዋል። የመኖሪያ አካባቢ መመናመን፣ የዱር እንስሳት መቀነስ፣ ከሰዎችና ከእንስሳት አርቢዎች ጋር የሚፈጠር ግጭት እና ሌሎች የሰው እንቅስቃሴዎች በአንበሶች ላይ ጫና እያሳደሩ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያን አንበሶች መጠበቅ የመንግሥት ወይም የጥበቃ ድርጅቶች ብቻ ኃላፊነት አይደለም፤ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። መኖሪያቸውን መጠበቅ፣ በሰውና በዱር እንስሳት መካከል ሰላማዊ አብሮነትን ማሳደግ እና የኃላፊነት ባለቤትነት ባህልን ማጠናከር አስፈላጊ ነው። አንበሳን ዛሬ መጠበቅ ማለት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ቅርስ ለነገ ትውልድ ማስጠበቅ ማለት ነው።

አንበሶቻችንን እንንከባከብ፤ ተፈጥሯችንን እንጠብቅ!

🦁መልካም ዓለም-አቀፍ የአንበሳ ቀን🇪🇹












06/08/2026

ከዚህ ቀደም ወደ ውቡ #አጆራ #ፏፏቴ ከተደረጉ ጉዟችን የአንደኛው ጸዴ ጉዞ የትውስታ ቪዲዮ 💥

ቀጣይ እሁድም ጉዞ ይኖረናልና ኮሜንት ላይ ባስቀመጥነው detail መሰረት ጻፉልን! ደውሉልን! አብረን ጸዴ ጊዜ እናሳልፍ!




💥የአጆራ ፏፏቴ ጉዞ ~ ወደ ነሐሴ3 ቀኑ ተቀይሯል💥____ይኼን ፖስት ለሌሎችም   አድርጉ!____አጆራ መንታ ፏፏቴ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይተው ከማይጠገቡና ልብ ቀጥ ከሚያደርጉ የተፈጥሮ ውበቶች...
04/08/2026

💥የአጆራ ፏፏቴ ጉዞ ~ ወደ ነሐሴ3 ቀኑ ተቀይሯል💥

____ይኼን ፖስት ለሌሎችም አድርጉ!____

አጆራ መንታ ፏፏቴ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይተው ከማይጠገቡና ልብ ቀጥ ከሚያደርጉ የተፈጥሮ ውበቶች አንዱና በብዙሀኑ እየተጎበኘ ያለ ድንቅ መስህብ ነው!

ነሐሴ 3/2018 ከBossYoss Tour and Travel ጋር ወደዚሁ ድንቅ ፏፏቴ በምናደርገው ግሩም ጉዞ... ለሚገርም ተዝናኖት፣ ለማይረሳ ጊዜና አጆራን ከፍ አድርጎ ለማስተዋወቅ ተዘጋጁ!

ለጉዞው እየመዘገብን ነውና ጻፉልን! ደውሉልን! 😎

የጉዞ ጥቅሉ #የሚያካትተው
🚍 ትራንስፖርት ደርሶመልስ
🙍🏾‍♂️ የአስጎብኚና የፎቶ
🍽 ቁርስና ምሳ
💦 የታሸገ ውሃ
🚧 የመግቢያ ክፍያዎች
👮 የስካውትና የጠባቂ

💵 የጉዞ ጥቅል #ዋጋ ለአንድ ሰው፦ 1150ብር
💵 የጉዞ ጥቅል ዋጋ ለውጭ ዜጋ:- $25

ከተጓዦች የሚጠበቀው
▫የጉዞ ዕለት በተባሉት ሰዓት መገኘት
▫ለተጓዥ የሚሰጥ የጉዞ ኮድ ይዞ መምጣት

#ለመመዝገብ ከታች ያሉ የባንክ አማራጮችን ይጠቀሙ!
👇👇

CBE
1000257737881
Telebirr
+251911535915

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
📲 0911535915
📲 0777555915

📌 የቢሮ አድራሻችን ከታች ባለው Google map ያገኙናል👇
https://maps.app.goo.gl/YQKZbVzRAynwj6TD6
(ወላይታ ሶዶ ከሊጋባ ትራፊክ መብራት 100ሜትር ዝቅ ብሎ ይገኛል...)




03/08/2026

በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት #የአጆራ #ፏፏቴ ጉዞ ወደ ቀጣይ እሁድ (ነሐሴ3) የዞረ ሲሆን ያልተመዘገባችሁ ዕድሉን ተጠቀሙ!
ጻፉልን! ደውሉልን!
🙏

💥ጉዞ ወደ አጆራ ፏፏቴ ~ ከወላይታ ሶዶ💥__ይኼን ፖስት ለሌሎችም   አድርጉ!__አጆራ መንታ ፏፏቴ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይተው ከማይጠገቡና ልብ ቀጥ ከሚያደርጉ የተፈጥሮ ውበቶች አንዱና በብዙሀ...
31/07/2026

💥ጉዞ ወደ አጆራ ፏፏቴ ~ ከወላይታ ሶዶ💥

__ይኼን ፖስት ለሌሎችም አድርጉ!__

አጆራ መንታ ፏፏቴ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይተው ከማይጠገቡና ልብ ቀጥ ከሚያደርጉ የተፈጥሮ ውበቶች አንዱና በብዙሀኑ እየተጎበኘ ያለ ድንቅ መስህብ ነው!

ሐምሌ 26/2018 ከBossYoss Tour and Travel ጋር ወደዚሁ ድንቅ ፏፏቴ በምናደርገው ግሩም ጉዞ... ለሚገርም ተዝናኖት፣ ለማይረሳ ጊዜና አጆራን ከፍ አድርጎ ለማስተዋወቅ ተዘጋጁ!

ለጉዞው እየመዘገብን ነውና ጻፉልን! ደውሉልን! 😎

የጉዞ ጥቅሉ #የሚያካትተው
🚍 ትራንስፖርት ደርሶመልስ
🙍🏾‍♂️ የአስጎብኚና የፎቶ
🍽 ቁርስና ምሳ
💦 የታሸገ ውሃ
🚧 የመግቢያ ክፍያዎች
👮 የስካውትና የጠባቂ

💵 የጉዞ ጥቅል #ዋጋ ለአንድ ሰው፦ 1150ብር
💵 የጉዞ ጥቅል ዋጋ ለውጭ ዜጋ:- $25

ከተጓዦች የሚጠበቀው
▫የጉዞ ዕለት በተባሉት ሰዓት መገኘት
▫ለተጓዥ የሚሰጥ የጉዞ ኮድ ይዞ መምጣት

#ለመመዝገብ ከታች ያሉ የባንክ አማራጮችን ይጠቀሙ!
👇👇

CBE
1000257737881
Telebirr
+251911535915

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
📲 0911535915
📲 0777555915

📌 የቢሮ አድራሻችን ከታች ባለው Google map ያገኙናል👇
https://maps.app.goo.gl/YQKZbVzRAynwj6TD6
(ወላይታ ሶዶ ከሊጋባ ትራፊክ መብራት 100ሜትር ዝቅ ብሎ ይገኛል...)




29/07/2026

እሁድ ሐምሌ 26 ወደ ውቡ የአጆራ መንታ ፏፏቴ ለሚደረገው አይረሴ ጉዞ... ጥቂት ቦታ ስላለን እየመዘገብን ነው!
ጻፉልን! ደውሉልን!
🙌

27/07/2026

💥ጉዞ ወደ አጆራ ~ ከወላይታ ሶዶ💥

እሁድ ሐምሌ 26/2018 መንገዶች ሁሉ ፥ በወላይታም፣ በኢትዮጵያም፣ በምስራቅ አፍሪካም ብቸኛና ታላቅ ኩራት ወደሆነው ወደ ይወስዱናል!

አጆራ ኩራታችን ብቻ ሳይሆን ውስጣችንን የሚያደስ የእግዜር ግሩም ተፈጥሮ ነው! በእውነቱ አጆራ ስላለን በጣም ዕድለኞች ነን! በመሆኑም...

👉 ተማሪዎች
👉 ሰራተኞች
👉 ነጋዴዎች

እና ሌሎቻችሁም... እስከዛሬ አጆራን ያላያችሁም ሆነ ያያችሁ... እሁድ ዕለት ሥራም ትምህርትም የሌለበት offday ስለሆነና እንደዚህ ዓይነት ጉዞ ከስንት አንዴ የምናዘጋጀው በመሆኑ ፤ ከከተማ ግርግር ወጣ ለማለት ተዘጋጁ!

በሚገርም ተዝናኖት አይረሴ ጊዜ እያሳለፍንና እርስበርስ ከመጨዋወቱም ባሻገር በፏፏቴው እየተደመምን ድንቅ የሆነውን #የወላይታ መስህብ ለዓለም እናስተዋውቃለን!

የጉዞ ቀን፦ እሁድ #ሐምሌ 26 - 2018 ዓ.ም
የጉዞ መነሻ ቦታ፦ ወላይታ ሶዶ ቦስዮስ ቢሮ
የጉዞ መነሻ ሰዓት፦ ጧት 12:00

የጉዞ ጥቅሉ #የሚያካትተው
🚍 ትራንስፖርት ደርሶመልስ
🙍🏾‍♂️ የአስጎብኚና የፎቶ
🍽 ቁርስና ምሳ
💦 የታሸገ ውሃ
🚧 የመግቢያ ክፍያዎች
👮 የስካውትና የጠባቂ

💵 የጉዞ ጥቅል #ዋጋ ለአንድ ሰው፦ 1150ብር
💵 የጉዞ ጥቅል ዋጋ ለውጭ ዜጋ:- $25

ከተጓዦች የሚጠበቀው
▫የጉዞ ዕለት በተባሉት ሰዓት መገኘት
▫ለተጓዥ የሚሰጥ የጉዞ ኮድ ይዞ መምጣት

#ለመመዝገብ ከታች ያሉ የባንክ አማራጮችን ይጠቀሙ!
👇👇

CBE
1000257737881
Telebirr
+251911535915

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
📲 0911535915
📲 0777555915

📌 የቢሮ አድራሻችን ወላይታ ሶዶ ከሊጋባ ትራፊክ መብራት 100ሜትር ዝቅ ብሎ ይገኛል...

https://maps.app.goo.gl/YQKZbVzRAynwj6TD6



💥ጉዞ ወደ አጆራ ~ ከወላይታ ሶዶ💥እሁድ ሐምሌ 26/2018 መንገዶች ሁሉ ፥ በወላይታም፣ በኢትዮጵያም፣ በምስራቅ አፍሪካም ብቸኛና ታላቅ ኩራት ወደሆነው ወደ   ይወስዱናል!አጆራ ኩራታችን ብ...
23/07/2026

💥ጉዞ ወደ አጆራ ~ ከወላይታ ሶዶ💥

እሁድ ሐምሌ 26/2018 መንገዶች ሁሉ ፥ በወላይታም፣ በኢትዮጵያም፣ በምስራቅ አፍሪካም ብቸኛና ታላቅ ኩራት ወደሆነው ወደ ይወስዱናል!

አጆራ ኩራታችን ብቻ ሳይሆን ውስጣችንን የሚያደስ የእግዜር ግሩም ተፈጥሮ ነው! በእውነቱ አጆራ ስላለን በጣም ዕድለኞች ነን! በመሆኑም...

👉 ተማሪዎች
👉 ሰራተኞች
👉 ነጋዴዎች

እና ሌሎቻችሁም... እስከዛሬ አጆራን ያላያችሁም ሆነ ያያችሁ... እሁድ ዕለት ሥራም ትምህርትም የሌለበት offday ስለሆነና እንደዚህ ዓይነት ጉዞ ከስንት አንዴ የምናዘጋጀው በመሆኑ ፤ ከከተማ ግርግር ወጣ ለማለት ተዘጋጁ!

በሚገርም ተዝናኖት አይረሴ ጊዜ እያሳለፍንና እርስበርስ ከመጨዋወቱም ባሻገር በፏፏቴው እየተደመምን ድንቅ የሆነውን #የወላይታ መስህብ ለዓለም እናስተዋውቃለን!

የጉዞ ቀን፦ እሁድ #ሐምሌ 26 - 2018 ዓ.ም
የጉዞ መነሻ ቦታ፦ ወላይታ ሶዶ ቦስዮስ ቢሮ
የጉዞ መነሻ ሰዓት፦ ጧት 12:00

የጉዞ ጥቅሉ #የሚያካትተው
🚍 ትራንስፖርት ደርሶመልስ
🙍🏾‍♂️ የአስጎብኚና የፎቶ
🍽 ቁርስና ምሳ
💦 የታሸገ ውሃ
🚧 የመግቢያ ክፍያዎች
👮 የስካውትና የጠባቂ

💵 የጉዞ ጥቅል #ዋጋ ለአንድ ሰው፦ 1150ብር
💵 የጉዞ ጥቅል ዋጋ ለውጭ ዜጋ:- $25

ከተጓዦች የሚጠበቀው
▫የጉዞ ዕለት በተባሉት ሰዓት መገኘት
▫ለተጓዥ የሚሰጥ የጉዞ ኮድ ይዞ መምጣት

#ለመመዝገብ ከታች ያሉ የባንክ አማራጮችን ይጠቀሙ!
👇👇

CBE
1000257737881
Telebirr
+251911535915

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
📲 0911535915
📲 0777555915

📌 የቢሮ አድራሻችን ወላይታ ሶዶ ከሊጋባ ትራፊክ መብራት 100ሜትር ዝቅ ብሎ ይገኛል... ከታች ባለው Google map ያገኙናል👇

https://maps.app.goo.gl/YQKZbVzRAynwj6TD6



  our Beautiful People 💝የናንተው የሕዝብ ድርጅት የሆነው BossYoss Tour and Travel የሚጠቀመው ይኼው የፌስቡክ ፔጃችን በጤናማ የዕድገት ሂደት   | 3000 ተከታይ...
23/07/2026

our Beautiful People 💝

የናንተው የሕዝብ ድርጅት የሆነው BossYoss Tour and Travel የሚጠቀመው ይኼው የፌስቡክ ፔጃችን በጤናማ የዕድገት ሂደት | 3000 ተከታይ በማፍራቱ ፥ ወዳችሁና ፈቅዳችሁ ስለምትከታተሉን በመላው ኢትዮጵያ ያላችሁ ቤተሰቦቻችንን ከልብ እናመሰግናለን 🙌

➡ በቅርቡ 3M
➡ በጣም በቅርቡ 300K
➡ በጣም በጣም በቅርቡ ደግሞ 30k እንገባለን!

Follow የምታደርጉን ከየት ከተማ እንደሆነ በኮሜንት አሳዉቁን!

ደግሞም የናንተው ድርጅት ለሆነው #ለቦስዮስ እንዲህ ቢሆን እንዲህ ቢደረግ የምትሉት አስተያየት ካላችሁም በቀናነት ኮሜንት አድርጉልን!

እናመሰግናችኋለን🙏

Address

BossYoss Street, 100m Below Ligaba Traffic Light
S**o
4620

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BossYoss Tour and Travel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share