በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት : Abeshge woreda culture & tourism office

  • Home
  • Ethiopia
  • Wolkite
  • በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት : Abeshge woreda culture & tourism office

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት : Abeshge woreda culture & tourism office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት : Abeshge woreda culture & tourism office, Tourist Information Center, Abeshge, Wolkite.

03/09/2026
ውጆ (የቅቤ እቁብ)  የጉራጌ  እናቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት ቱባ ባህላዊ እሴት ነው:- ወ/ሮ መሰረት አመርጋነሐሴ 17/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)የጉራጌ እናቶች የመ...
23/08/2026

ውጆ (የቅቤ እቁብ) የጉራጌ እናቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት ቱባ ባህላዊ እሴት ነው:- ወ/ሮ መሰረት አመርጋ

ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የጉራጌ እናቶች የመስቀል በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሏቸውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አጠናክረው መቀጠላቸው ገለፁ።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ በእኖር ወረዳ መቃና ቀበሌ የጉራጌ ባህላዊ እሴት የሆነው የእናቶች የመስቀል ቅድመ ዝህጅት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት ውጆ (የቅቤ እቁብ) የጉራጌ እናቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት ቱባ ባህል ነው።

ይህ እሴት በማህበረሰቡ ዘንድ ከሚታወቁ ቀደምትና ቱባ ባህሎች መካከል አንዱ ሲሆን እናቶች ለመስቀል፣ ለአረፋ፣ ለሰርግም ሆነ ለሌላ ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን ሳይጨናነቁ ለመፍታት ያስችላቸዋል ብለዋል።

በአገራችን በስፋት እየተለመደ ለመጣው በገንዘብ እቁብ የመጣል ባህል መነሻዎቹ እነዚህ ቀዳሚዎቹ የብሔሩ ተወላጅ የሆኑት እናቶች ከብዙ ዓመታት በፊት በአይነት የጀመሩት የወተትና የቅቤ ውጆ እንደሆነ ተናግረዋል።

የጉራጌ ብሔር መገለጫ የሆነው ክትፎ ልዩ ጣዕም እንዲኖረው ከሚያደርጉት ግብአቶች ዋናው በጥራት የተዘጋጀ ቅቤ በመሆኑ እናቶችም ጥራቱን የጠበቀ ንፁህ ቅቤ ከተለያዩ ግብአቶች ጋር በማዋሀድ እንደሚዘጋጁ ተናግረዋል።

በዞኑ በተለያዩ መዋቅሮች የሚኖሩ እናቶች ለመስቀል በዓል የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት በጊዜው ለማጠናቀቅ እያደረጉት ያለው የቅድመ ዝግጅት ሥራ አበረታች መሆኑንም ገልጸዋል።

ውጆ (የቅቤ እቁብ) እናቶች ስለ አኗኗራቸው፣ ስለ ልጆቻቸው አስተዳደግና ስለ አካባቢያቸው ልማት የሚመካከሩበት ማህበራዊ መድረክ ከመሆኑ በተጨማሪ የቅቤ እቁቡ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እናቶች በደስታቸውም ሆነ በችግራቸው ጊዜ እርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህላቸውን ያጠናክራሉ።

ውጆ (የቅቤ እቁብ) በአንድ አካባቢ የሚኖሩ እናቶች ዘር ቀለም፣ እድሜና ሀይማኖት ሳይገድባቸው በአብሮነትና በመተሳሰብ የሚሰበሰቡበት እንደሆነ ተናግረዋል።

እናቶች በየሳምንቱ በውጆ (በቅቤ እቁብ) የሚሰበስቡት ንጽህናውን የተጠበቀና በጥራት የተዘጋጀው ቅቤ ለባለ ተረኛዋ እናት የሚያስረክቡበት እሴት ነው።

ከእያንዳንዳቸው የሚሰበሰበውን የቅቤ መጠን ለመለካት የሚጠቀሙባቸው ባህላዊ ዘዴዎች እንዳሏቸው ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል።
በአውራ ጣትና በአመልካች ጣት መሃከል ቀጭን ወደረ /ከእንሰት ኮባ የሚገኝ ማሰሪያነት በማስቀመጥ ወደረው ቅቤውን ዞሮ በትክክል ሲገጥም ብሽየ እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል፡፡

ለመለኪያነት ከተዘጋጀው ቀጭን ወደረ የቅቤው መጠን ጥቂት ከፍ ካለና በአውራ ጣትና በአመልካች ጣት መሃከል የተያዘው ወደረው ቅቤውን ዞሮ ለመግጠም እጅግ በጣም ትንሽ ክፍተት ካሳየ ደግሞ የዳቀ እንደሚባል ተናግረዋል፡፡

የቅቤው መጠን ለመለኪያነት ከተዘጋጀው ቀጭን ወደረ ሲበልጥና ወደረው ቂቤውን ሙሉ ለሙሉ ዞሮ ለመግጠም ያመልካች ጣት መጠን ያህል ክፍተት ሲኖረው የተከሰ ይባላል፡፡

የቂቤው መጠን ለመለኪያነት ከተዘጋጀው ቀጭን ወደረ ሲበልጥና ወደረው ቂቤውን ሙሉ ለሙሉ ዞሮ ለመግጠም የአውራ ጣት መጠን ያህል ክፍተት ሲኖረው ውርአቴበ ይባላል ፡፡

እናቶች ይህንን ባህላዊ እሴት ጠብቀው ማቆየታቸው በቤተሰብ ደረጃ የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና ከመቀነሱም በላይ፣ ባህሉ ጠብቀው ለተካኪው ትውልድ እንዲተላለፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ወይዘሮ መሰረት አክለውም እነዚህ ባህላዊ እሴቶቻችን በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ ለ

17/08/2026
ወሄም ሳረናሁም፣ወሄም ሳረነምእንኳን ደስ አላችሁ ፣እንኳን ደስ አለን!!የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ በክልሉ ካሉ መዋቅሮ የተሻለ አፈፃም በማስመዝገቡ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ!  ነሀሴ 7/2...
14/08/2026

ወሄም ሳረናሁም፣ወሄም ሳረነም

እንኳን ደስ አላችሁ ፣እንኳን ደስ አለን!!

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ በክልሉ ካሉ መዋቅሮ የተሻለ አፈፃም በማስመዝገቡ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ!

ነሀሴ 7/2018 ዓ•ም(ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ የ2018 ዓ.ም አመታዊ የዕቅድ አፈፀም ጉባኤ በዛሬው እለት በሳጃ ከተማ አካሄዷል።

ቢሮው ባካሄደው አመታዊ ጉባኤ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ በክልሉ ካሉ የዞን መዋቅሮች 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖዋል።

የዞናችን ባህል፣ቋንቋና የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በማበልፀግ በማስተዋወቅ ላይ ከፍተኛ ስራ እየደራ የሚገኘው መምሪያው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሰራቸው ስራዎች እውቅናን አጊንቷል።

እውቅናው መምሪያው በቀጣይ ስራውን በተሻለና በላቀ ሁኔታ ለመስራት የሚያግዘው እንደሆነ ተመላክቷል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ የነበራቸውን የዞኑን የባህል ቡድን፣ አስተባባሪዎችና ሌሎች አመራሮችን እንዲሁም የመምሪያው ባለሞያዎች የወረዳና ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላትን እያመሰገንን ፣በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን።

ተቀናጅተን በመስራት ዞናችንን እናልቃለን!!

11/08/2026
የጉራጌ ዞን ንሟም ቱሪዝም መምሪያ   "ወሔነት ይትዮጵያ ንቅነት" ቢውሪ ቃር  የርሟም የንመ በየ ምስራጀ በሰክቶት በወርቕጤ ቤሮ(ከተማ) ኣትቀንቦት ቀነሰም።ኣምሬ 30/2018 (ወርቕጤ)የጉራ...
06/08/2026

የጉራጌ ዞን ንሟም ቱሪዝም መምሪያ "ወሔነት ይትዮጵያ ንቅነት" ቢውሪ ቃር የርሟም የንመ በየ ምስራጀ በሰክቶት በወርቕጤ ቤሮ(ከተማ) ኣትቀንቦት ቀነሰም።

ኣምሬ 30/2018 (ወርቕጤ)
የጉራጌ ዞን ንሟም ቱሪዝም መምሪያ "ወሔነት ይትዮጵያ ንቅነት" ቢውሪ ቃር ያስራጀን የርሟም የንመ በየ ምስራጀ በወርቕጤ ቤሮ(ከተማ) ኣትቀንቦት ቀነሰም።

በዘንጎትየጉራጌ ዞን ንሟም ቱሪዝም መምሪያ ቡር ዳነ እመዌቸ መሰረት ኣነርጋ ምስራጀዌ በከፈተማቡወ ግዝየ በሕሮተታየባረማሐማ ንመ የትራከሰ ይትሻከትወ፣ ኣት ሐልቅ ይረብርወ ማራ ያይኸኸርቦ፣ ንሞታ፣ ታሪከታም ኣፎታ የጨናቴ ያሰረቡወ ንቅ ሜናው።

ንሞ በትምርት፣ ጡፍም ኣማማ ቦጎት፣ በትሐደሮት፣ ባዠመነ፣ በብኸ ያትኸኸሪ ዝሕ የመሰረ ሜና ያተዌዬ መምሪያዌ ቡችር የሐረ የርሟ ውኸርም የንመ በየ ምስራጀ ሸከተም ባረማም።

በመድረክዌ የዞንዌ ንቅ የሜና ዳነ፣ የወርቕጤ ዩንቨርሲቲ፣ የወርቕጤም ያበሽጌ ወረዳ የሜና ዳነ፣ የገን ባሪቅም እንጉወድ ባዘራ ተረከዎም።

Address

Abeshge
Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት : Abeshge woreda culture & tourism office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share