21/05/2026
ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም
ከ 35 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀድሞ የኢሕድሪ/ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑሊክ/ የኢሠፓ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) ዋና ፀሀፊ የነበሩት ጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም (ሌ/ኮ) ከአገር ወጥተው ወደ ሀገረ ዙምባቡዌ የሄዱበት ዕለት ነው።
ግንቦት 10 ቀን 1983 ዓ.ም ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም በመኖራያ ቤታቸው ለከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው የእራት ግብዣ አደረጉ ፤ ግብዣው ሲጠናቀቅ ፕሬዘዳንቱ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ሁሉንም ተጋባዥ እንግዶች እበራፋቸው ላይ በመሆን አንድ ባንድ እየጨበጡ ሸኙዋቸው።
ግንቦት 12 ቀን 1983 ዓ.ም ፤ ፕሬዘዳንት መንግስቱ መሉውን ቀን የተለያዮ ወረቀቶችን እቢሯቸው ውስጥ ሲቀዳድዱ ዋሉ ፤ ማምሻው ላይ ግን ወደ ዘመቻ መምሪያ በማምራት ለከፍተኛ የጦር አዛዦቻውቸው ንግግር አደረጉ።
ማክሰኛ ግንቦት 13 የፕሬዘዳንቱ ልዮ ረዳት ሻምበል መንግስቱ ፤ብላቴ ማሰልጠኛ ጣቢያ ደርሶ ከዚያም ወደ አስመራ ደርሶ መልስ የሚበቃ ነዳጅ የሞላ አንድ ዳሽ 5 አውሮፓላን እንዲዘጋጅ ትእዛዝ አስተላለፋ።
በዛው እለት ከጠዋቱ ወደ 2 ሰአት ገደማ ፕሬዘዳንቱ ከተመረጡ አጃቢዋች እንደዚሁም ከሶስተኛ ክፍለጦር የመጣና የቅርብ አጃቢያቸው ከነበረው ከሻንበል ደመቀ ባንጃው ጋር በመሆን በኮ/ል ተስፋዬ መሪነት ቦሌ አውሮፓላን ማረፊያ በመድረስ ተዘጋጅታ ትጠብቅ ከነበረችው አውሮፓላን ተሳፈሩ።
©️ አብዮቱና ትዝታዬ (ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ)