Murade Hassen-ሙራድ ሀሰን

Murade Hassen-ሙራድ ሀሰን Welcome to my official page! Follow for updates, news, and more.
(6)

11/04/2026


🪸🪸🪸🪸🪸
አክሱምን የማውቃት በጣም የምንወደው አስተማሪችን ፀጋ-ብርሃን ወ/ጊዮርጊስ ባዘጋጀልን ጉዞ ነው፡፡ ይህን ጉዞ ያደረግነው 60 ምናምን የምንሆን የ2009 ባች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትመህርት ክፍል ተማሪዎች ነን፡፡ ጉዞውን ያደረግነው መጋቢት/ሚያዚ 2011 ነው፡፡ እውነት ለመናገር የትግራይ ህዝብ የዋህ እና ኩሩ ኢትዮጵያዊ፣ እንግዳ አክባሪ መሆኑነ መረዳት ችያለው፡፡ ከተማሪወቹ ውስጥ 5 ሙስሊሞች ነበርን (እኔ፣ አህመድ፣ ቡላላ፣ ፈይሳ እና ሙሃመድ) ፤ ጾመኞች ነን፡፡ በምሽቱ ወጥተን ምግብ ለማሰራት አንድ የማናውቀው የመቀሌ ልጅ እንደ የግል ጠባቂ/ጋርድ ሳንጠይቀው አጅቦን ምግባችንን አሰርተን ካምፓስ ገባን (መቀሌ)፡፡ በቃ ወርቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡

ግን የማንክደው ሃቅ አለ፡፡ በቃ ወንበዴዎች አሉ፤ በተለይ አክሱም፡፡ አክሱም ዓስር ሰላትን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ አንደሌላው ቦታ መስሎኝ ልሰግድ ሳር ቦታ ልብሴን አንጥፌ፣ ሃርሜ ቆምኩኝ ሙሃመድ ቃዲ ሊሰግድ ተከተለኝ፤ ሰላታችንን አሳጥረን ሰገድን፤ ያው ሙሳፊሮች አይደለን፡፡ ከጨረስን በኋላ ቀና እንላለን በሙሉ የዶርሙ ተማሪ ሁሉ እሪሪ እያለ በኮሪደር ዘልቆ ይመለከተናል፡፡ ምንድን ነው ይህ ነገር ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ መስገድ አይቻልም እንዴ እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ፤ ከዛ በፊት ጅምላ ክልከላ እንዳለ አልሰማውም፤ ከመረጃ እርቄአለሁኝ፡፡ የሆነው ሁኖ እንግዳ መሆናችንን አይተው መሰለኝ ማንም ሰው አልጠየቀንም፡፡ አንድ የመውቀው የዩኒቨርስቲው ተማሪ ነበር (ገብረ-ህይዎት) መስገድ አይቻልም፤ ተከልክሎ ነው ብሎ ነገረኝ፡፡ ወገኖቼ፣ አክሱም እንደማንኛውም ከተማ፣ መጠጥ የሚሸጥባት፣ ጭፈራ ቤቶችን የምታስተናግድ፣ ለክርስትና እንኳ በሙሉ እጅ የማይሰጡ አንዳድ አካል ያለባት ከተማ ናት፡፡

እናም መስጅድ መኖሩ እንደምትባለው ቅድስት ከተማም ከሆነች ቅድስነቷ አይጠፋም፡፡ ጀሩሳሌም ውስጥ ያሉትን ቤተ-ክርስቲያኖች እና መስጅዶች ቅርበት፣ ሃገራችን ውስጥ ደጀን ከተማ ውስጥ ያለው የመስጅድ እና የቤተክርስቲያን እርቀት እንዲሁም ራጉኤልን እና አነዋርን እናስብ፡፡ የደጀኑማ ዘይገርም ነው፡፡ የእምነትህን ትእዛዝ ለምን ትፈጽማልህ ተብሎ ግድያ፣ እንግልት፣ ቁርኣንን መቅደድ እኮ የትም አያደርስም፡፡ እምነቱን የሚወድ እና የሚያከብር ሰው ክርስቲያን ይሁን ሙስሊም፣ የሁዳ ይሁንም ዛፍ አምላኪ የሌሎችን ድንበር መጣስ፣ መተናኮል፣ መጋፋት፣ ግፍ መፈጸም አይቀናውመ በቃ ደስ አይለውም፡፡ እምነት እኮ ቀሚስ መልበስ፣ ጺም ማሳደግ፣ ሱሪ ማሰጠር፣ ማተብ ማሰር፣ ነጠላ መልበስ ብቻ አይደለም፡፡ ለምንስ የሌሎችን መብት እንጋፋለን? እምነታችን አዘዘን? እረ ወገኖቼ እኔንም ጨምሮ ልብ የምንገዛበት ጌዜ መች ይሁን? ልብ መግዛት እኮ ያን ያክል ዋጋ አያስከፍልም፡፡ ይህችን ምድር መቼም ወረሾች አየደለንምኮ፡፡

https://t.me/MuradeHassen

05/04/2026

ጫትን የእስልምና አንድ አካል አድርገው የሚቆጥሩት ቂሎች ይገርሙኛል።
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
ትላንት ወንድሜ ወደሚኖርበት ኮምፓውንድ ቦርሳ ይዠ፣ በሳይክል ስገባ የት ነህ? ማን ነህ? ብሎ የጠየቀኝ አካል አልነበረም። እናም ጉዳዬን ጨርሸ በተመሳሳይ በር ልወጣ ስል አያቴ የሚሆኑ ትልቅ ሰው፣ ጥበቃ "ቅድም ጫት ይዘህ ገባህ፤ አሁን ደግሞት ወዴት ነው አሉኝ።" ደሜ ፈላ፤ ትልቅ ሰው ናቸው፤ በቤተሰቦቼም፣ በማህበረሰቡም ትልቅን ቢያጠፋም ቢሆን እንዳከብረው ተኮትኩቸ ነው ያደኩት።

ቀስ ብየ ቀረብኳቸው፤ ጫት ይዠ ስገባ አይተዋል? በምኔ ያስኩት? በፌስታል? ፈትሸው አያስገቡም? "አይ ብዙ ሰው ይዞ ይገባል አሉ።" ሌላው ሰው ኮኬይንም ይዞ ይግባ ምን አገባኝ። ጫት ይዠ ስገባ አይተዋል? ስላቸው "እሱማ አላየሁም አሉ።" ታድያ ውሸት ምን ይሰራል ብየ ከተማሩ ስለ እምነቴም ነገርኳቸው። አብሮ የነበረው ሰውየ ሁሉን ነገር ሰምተዋል ፤ ልጄ ብዙ ሰዎች በቦርሳ ይዘው ስለሚገቡ ነው አለኝ፤ ይዠው የገባውትም፣ ይዡው የወጣው እቃ ይህ ነው ብዬ ላፕቶፔን አሳየዋቸው፤ ይቅርታ እንዲሉ ባልፈልግም ይቅርታ አሉኝ።

✔️የዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ አንድ የአፋር ልጅ ጫትን ይቅም ነበር፤ አንስማማም፤
✔️ ጫት የሙድ እንጅ😂 የየቱኛውም እምነት ዘመድ አይደለም፤
✔️ካሽ ክሮፕ ስለሆነ እንጅ የሚያሳብደውን አፍላ ወጣት ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስት ጫትን እንደ ኮኬይን ይቆጥረው ነበር፤
✔️ ቀሚስ የለበሰ፣ ፂም ያሰደገ ሰው ስታዩ ዓይናችሁ የሚቀላ ግልቦች ልብ ግዙ፤
✔️ጫት የእስልምና አካል አድርገህ የምትቆጥር ሚስኪን ወገኔ፡ አንብብ፣ ጠይቅ በጭፍን አትፍረድ፤
✔️በጣም ከሚያበሳጨኝ ሰው ውስጥ ጫት ቃሚ ከቀዳሚዎቹ ነው፤

05/04/2026

እኛ ሰላም ወዳድ፣ ጭቁን ህዝቦች እንጅ ግጭት ጠማቂ እንዳልሆንን ይታወቅልን።

05/04/2026

ለእናንተም እምነታችሁ አለላችሁ፤ ለእኔም እንዲሁ የራሴ እምነት አለኝ።

22/02/2026

ሚዲያ በአግባቡ ከተጠቀሙበት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ቢታወቅም፣ የፊትና ስብስብም የሚገኘው እዚሁ መንደር ነው። ሸይኽ ያሲን ሙሳ ታላቅ ዓሊም መሆናቸውን የሚያውቃቸው ብቻ ያውቀዋል።

አሏህ እድሚያቸውን በረካ ያድርግላቸው፡ ምንጠቀምባቸውም ያድርገን።
የሳቸውን ትምህርት ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፡ https://t.me/sheih_Yasin_Musa

22/02/2026

የሸይኹን ትምህርት ለመከታተል፡ የቴሌግራም ቻናሉን ይከታተሉ።
https://t.me/sheih_Yasin_Musa

24/12/2025

ኢስላማዊው ፋይናንስ - ከሃይማኖታዊው መርኅ ወደ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አማራጭ!

የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት በከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና በዕዳ ቀውስ ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ከወለድ ነፃ የሆነው የኢስላማዊ ፋይናንስ ሞዴል በዓለም አቀፍ መድረክ አዲስ መነጋገሪያ ሆኗል። ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ ሥርዓቱ ከሙስሊሙ ዓለም አልፎ በምዕራባውያን የኢኮኖሚ ማዕከላት ዘንድ እንደ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ዋስትና እየታየ ይገኛል።

ይህ ግስጋሴ የኢስላማዊ ፋይናንስን መሠረታዊ መርሆዎች ማለትም በወለድ ላይ ሳይሆን በተጨባጭ ንብረት ላይ የተመሰረተ የንግድ ልውውጥን ለዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ መረጋጋት እንደ ቁልፍ መፍትሔ አጉልቶታል። የገበያ ባለሙያዎች እንደሚተነትኑት፣ ኢስላማዊ ፋይናንስ ከተለምዷዊው ባንክ አሰራር በተለየ በትርፍና ኪሳራ መጋራት ላይ መቆሙ ለኢንቨስትመንት መረጋጋት ትልቅ ድርሻ አለው።

ሮይተርስ ሰሞኑን ባወጣው ትንታኔ፣ የኢስላማዊ ቦንድ ወይም ሱኩክ ፍላጎት በአውሮፓ ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልጿል። ይህም የሆነው ባለሀብቶች ከወረቀት ሰነድ ይልቅ በተጨባጭ ፕሮጀክቶች ላይ የተመሰረተ ትርፍን በመምረጣቸው እንደሆነ ይነገራል። በተመሳሳይ ብሉምበርግ የዜና ወኪል ባቀረበው ዘገባ፣ ይህ የፋይናንስ ዘርፍ አሁን ላይ ከዘልማዳዊው የባንክ አገልግሎት ወጥቶ ወደ ካፒታል ገበያ በስፋት እየገባ መሆኑንና ይህም የዓለምን የገንዘብ ሚዛን እየቀየረው መሆኑን አመልክቷል።

ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር፣ የኢስላማዊ ፋይናንስ መርሆዎች ከዓለም አቀፉ የሥነ-ምግባራዊ ኢንቨስትመንት መመዘኛዎች ጋር መጣጣማቸው ዘርፉን ይበልጥ ተመራጭ አድርጎታል። ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ ተግባራትን የሚከለክለው ይህ ሥርዓት፣ አሁን ላይ ወደ ተመራጭ ፋይናንስ እያዘነበለ ይገኛል። አልጀዚራ እና ኢስላሚክ ፋይናንስ ኒውስ እንደዘገቡት፣ በርካታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ከወለድ ነፃ የሆኑ ቦንዶችን በስፋት ማቅረብ ጀምረዋል።

ይህ ለውጥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ እንደሆነ ይተነተናል። በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ኢስላማዊ ፋይናንስን ለተራው ማህበረሰብ ተደራሽ እያደረገው መሆኑ ይታያል። ዘ ፋይናንሺያል ታይምስ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ፣ በደቡብ ምስራቅ እስያ ያሉ የዲጂታል ኢስላማዊ ባንኮች ቁጥር መጨመር ለዘርፉ እድገት ትልቅ ሞተር መሆኑን ጠቁሟል። በአጠቃላይ ኢስላማዊ ፋይናንስ በአሁኑ ሰዓት ከሃይማኖታዊ ክበብ ወጥቶ ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ቋንቋ እየሆነ ነው።

ሥርዓቱ በፍትሃዊ የትርፍ ክፍፍል ላይ መቆሙ የሀብት ክፍፍልን ከማመጣጠኑ ባለፈ፣ ለወደፊቱ የዓለም ኢኮኖሚ መረጋጋት እንደ ዋነኛ መከላከያ እየታየ ይገኛል።

© ሀሩን ሚዲያ

Dear investers Move to paper bag‼️
24/12/2025

Dear investers Move to paper bag‼️

24/12/2025

ስልጣኔ ለራስ የሚበጀውን መምረጥ፡ ለሌሎች በጎ ማሰብ እና ትሁት መሆን ነው።

24/12/2025

Do you know thw greatest gift you can give someone is not your money, not your heart, its your time.

23/12/2025

A new job, new opportunities, and a new environment. May Allah Jalla Jalaluhu bless it all.

22/12/2025

አማኝ ተስፋ ቆርጦ አያውቅም!!!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Murade Hassen-ሙራድ ሀሰን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Murade Hassen-ሙራድ ሀሰን:

Share