Visit Bahir Dar Ethiopia ባህርዳርን ይጎብኙ

Visit Bahir Dar Ethiopia ባህርዳርን ይጎብኙ ባህር ዳርን ይጎብኙ ።

03/05/2026

አብቹ ባህርዳር ገብቷል ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የጎርጎራን ታላቅ ስራ ሙሉ ለማድረግ በሌላኛው የጣና አቅጣጫ፥ በውቧ ባህር ዳር የሚተሳሰሩ ሁለት የአንድ ሐይቅ ዳርቻ ገናና ህልሞችን ለማሳካት በ...
03/05/2026

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የጎርጎራን ታላቅ ስራ ሙሉ ለማድረግ በሌላኛው የጣና አቅጣጫ፥ በውቧ ባህር ዳር የሚተሳሰሩ ሁለት የአንድ ሐይቅ ዳርቻ ገናና ህልሞችን ለማሳካት በገበታ ለሃገር ያለሙትና በግሉ ዘርፍ የታነፁትን ግንባታዎች ጨምሮ: የበርካታ ፕሮጀክቶች ምረቃና ጉብኝት ዝግጅት ላይ ለመታደም እንዲሁም ለማህበረሰባዊ ትስስር አባ ገዳዎች ባህርዳር ገብተዋል::

የባህር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ እና የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ በባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሕውሓቱ ጀነራል የፌዴራል መንግስቱ ላይ ዛቱ፡፡ 🦴🦴🦴ብልጽግናን ለማስወገድ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአደባባይ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ታደሰን እንቅስቃሴ እግር በእግር እንዲከታተሉ ትእዛዝ ...
03/05/2026

የሕውሓቱ ጀነራል የፌዴራል መንግስቱ ላይ ዛቱ፡፡ 🦴🦴🦴
ብልጽግናን ለማስወገድ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአደባባይ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ታደሰን እንቅስቃሴ እግር በእግር እንዲከታተሉ ትእዛዝ የተሰጣቸው እኚህ ጀነራል፤ ሁሉም ነገር አልቋል በቅርቡ ጠብቁን ብለዋል፡፡ ይህ የጀነራሉ ዛቻ የተሰማው ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ህብረት ጦርነት እንዳይፈነዳ እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ነው፡፡

የሕውሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እና ወታደራዊ አዛዦች 4ኪሎ ላይ የሚያሰሙትን ዛቻ ቀጥለውበታል፡፡ ከሰሞኑ የቡድኑ አመራር አዲስአለም ባሌማ ‹‹ለሁሉም ነገር ተዘጋጅተናል፤ ሎጀስቲክ አዘጋጅተናል፤ከፋኖም ከሻብያም ጋር ተጣምረናል›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ ዛሬ ደግሞ ከሕውሓት ወታደራዊ አዛዦች መሀል አንዱ የሆኑት የአርሚ 60 አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ ብልጽግናን ለመጣል ተዘጋጅተናል የሚል ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጠ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ጀነራሉ የህወሓት ልሳን ለሆነው ወይን ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ማንም መጠራጠር የሌለብት ሁሉም ነገር አልቋል” ሲሉ ፉከራ አሰምተዋል፡፡ ጀነራሉ ብዙዎች ተሰውተውለታል ያሉትን በተናጠል ክልላዊ ምርጫ የተመሰረተውን፣ የህወሓት መንግሥት መመለስ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የሁለት ዓመቱን ደም አፋሳሽ ጦርነት መሬት ለማስመለስ ሳይሆን፣ 2.8 ሚሊዮን ህዝብ የመረጠጠውን መንግሥት ለማስመለስ ነው ያሉት ጀነራሉ፤ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰው ሞቷል የሚባለውን አስተባብለው፤ “አንድ ሚሊዮን ሰው ሞቷል የሚለውን ተውት፣ የተገደሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጀነራሉ መስዋእት ከፍለንበታል ያሉትን ህወሓት መራሹን መንግሥት ለመመለስ ሙሉ ዝግጁ አለን ብለዋል፡፡ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረው ውጥረት ማብራሪያ የሰጡት ጀነራሉ፣ “ድጋሜ ከተዋጋን የነብረውን መንግስት ለመመለስ ነው” ይላሉ፡፡

የፕሪቶሪያው ስምምነት ከዚህ በኋካ ዋጋ እንደሌለው የገለጹም ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ወደኋላ የሚመለስን ኃይል የለም ብለዋል፡፡ የፌደራል መንግሥት በስምምነት ሰበብ ትግራይ ከፋፍሏል በማለት የከሰሱ ሲሆን፣ እንደ ጌታቸው ረዳ ያሉ ግለሰቦችንም እንደ ጠላት እንታገላቸዋለን ብለዋል፡፡

ጀነራሉ ትግራይ ከድተዋል ያሏቸውን ኃይሎች ከፌደራል መንግሥት ጎን ተሰልፈው፣ የህወሓት አመራሮችን ለማጥቃት እየተዘጋጁ ነው በማለት ከሰዋል፡፡ በዚህም የህወሓት አመራሮች የጥቃት ኢላማ በመሆናቸው በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳይችሉ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፣ በእነ ደብረጽዮን በኩል ከወዲሁ ደብብቆሽ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

ከባለፈው ጦርነት ተምረናል ያሉት ጀነራሉ፣ ዳግም ውጊያ ከተቀሰቀሰ እንደበፊቱ በቀላሉ እጅ አንስጥም ብለዋል፡፡ የህወሓትን መንግሥት በመመለስ የቤት ሥራችንን ጨርሰናል ያሉት እኚሁ ወታደራዊ አዛዥ፣ ቀጣዩ ጉዞ የትግራይን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ነው ብለዋል፡፡

መሳይ መኮንን ልጆቹ ፋኖን እንዲቀላቀሉ ወሰነ!​ዛሬ አንድ አስደናቂ ዜና ሰማን፤ መሳይ መኮንን በውጭ አገር የሚኖሩ ልጆቹን ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ፋኖን እንዲቀላቀሉ ...
03/05/2026

መሳይ መኮንን ልጆቹ ፋኖን እንዲቀላቀሉ ወሰነ!
​ዛሬ አንድ አስደናቂ ዜና ሰማን፤ መሳይ መኮንን በውጭ አገር የሚኖሩ ልጆቹን ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ፋኖን እንዲቀላቀሉ መወሰኑ ተነግሯል። እርግጥ ነው፣ ይህ ሊሆን የማይችል ህልም ነው። ነገር ግን ይህ ርዕስ አንድ ትልቅ እውነትን ይይዛል፤ መሳይ ለሌላው ልጅ የሚሰብከውን ጦርነት ለራሱ ልጆች ፈጽሞ አይመኘውም።

​የመሳይ መኮንን ህይወት እና ንግግር እጅግ የሚጋጩ ናቸው። እሱና መሰሎቹ በዲያስፖራው የሚሰበሰበውን ገንዘብ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ቅንጡ ኑሮ ሲያውሉ፣ በአገር ውስጥ ያለው ምስኪኑ ገበሬ ግን የእነሱን የቪዲዮ ስብከት ሰምቶ ልጁን ወደ ጦርነት ይልካል። መሳይ ልጆቹን ከጥይትና ከጭስ ርቆ በሰለጠነ መንገድ ሲያሳድግ፣ የአማራን ህጻናት ግን ትምህርት ገበታቸው ላይ ቀርተው በጦር ሜዳ እንዲማገዱ መቀስቀሱ ፍጹም የሞራል ዝቅጠት ነው።

​ዛሬ መሳይ መኮንን ለአማራ ህዝብ ቆሜያለሁ ቢልም፣ ትክክለኛው መለኪያ ግን ለልጁ የሚመኘውን ሰላም ለኢትዮጵያዊው ገበሬ ልጅ መመኘቱ ነበር። ከባህር ማዶ ሆኖ የጦርነት እሳት መቆስቆስ ትርፉ ለደሃው ሞት፣ ለነ መሳይ ደግሞ የዩቲዩብ እይታና የገንዘብ ገቢ ብቻ ነው። ይህ በአገርና በወገን ስም የሚነገድበት የክህደት ጉዞ ሊቆም ይገባል።

አይጥ ምን አማረሽ ቢሏት ሴክስ አለች አሉ፡ ከማን ጋር ቢሉት ከዝሆን ጋር ።😀😀😀
03/05/2026

አይጥ ምን አማረሽ ቢሏት ሴክስ አለች አሉ፡
ከማን ጋር ቢሉት ከዝሆን ጋር ።😀😀😀

መረጃና ጥንቃቄ !የፀጥታ ሀይል ልብስ በመልበስ ዝርፊያ ሲፈፅሙ ተያዙ!በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ ጭብል ለብሰውና የፀጥታ ሀይል ለመምሰል ሚሊተሪ ለብሰው ህዝብን ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰ...
03/05/2026

መረጃና ጥንቃቄ !
የፀጥታ ሀይል ልብስ በመልበስ ዝርፊያ ሲፈፅሙ ተያዙ!

በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ ጭብል ለብሰውና የፀጥታ ሀይል ለመምሰል ሚሊተሪ ለብሰው ህዝብን ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

03/05/2026

ከባህርዳር ምን እንደሰለቸኝ ታውቃላችሁ ለወዳጆቻችን ብር ማሰባሰብ ሲጠይቅ የሰጠውን አካል የባህር ዳር ወርቅ የባህር ዳር ሸበላ የባህር ዳር ቅኑ የዋሁ ምናምን እያሉ እንዳዝማሪ ማሽቃበጥ ኤጭ ።

02/05/2026

ባህርዳሮች ሆይ🤌🤌🤌
ትንሽም ይሆን ትልቅ የሚለግሰውን ግለሰብ እኩል በማየት ትልቁን ሰጪ እንዳዝማሪ የኔ ጨዋ የኔ ለጋሼ የኔ ምስኪን የኔ ዝምተኛ እያሉ ከመካብና ከማሽቃበጥ ይልቅ ስጦታውን እኩል በማመስገን አባት በአካል ቆሞ የውስጥ አንጀቱ በመሰበር እየጠየቀ ነውና ልጁን እናድነው ።
ሙገሳው ሽለላው ቀረርቶውና ቲፎዞነቱ ነገ ይደርሳል።

የጫካው ደርቢ ተጀመረ !  ሳሙኤል ባለድልን ከሃብቴ ወልዴ  ዮሃንስ ንጉሱን ከባየ ቀናዉ  ያፈጠጠዉ የጫካ  ፍልሚያ  አሁን  በይፋ ተጀምሯል ።በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጎንደር ጫካዎች የዘረ...
01/05/2026

የጫካው ደርቢ ተጀመረ !
ሳሙኤል ባለድልን ከሃብቴ ወልዴ ዮሃንስ ንጉሱን ከባየ ቀናዉ ያፈጠጠዉ የጫካ ፍልሚያ አሁን በይፋ ተጀምሯል ።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጎንደር ጫካዎች የዘረፋ ደርቢ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል! ዮሃንስ ንጉሱ እና ሃብቴ ወልዴ በአንድ በኩል ሳሙኤል ባለድል እና ባየ ቀናው በሌላ በኩል ሆነው ያጠቃ ይዝረፍ በሚል የሽፍታ መርህ እርስ በርስ ተናንቀዋል ። ሳሙኤል ባለድል በወያላና በአውርቶ አደር አልመራም በሚል ትዕቢት ሃብቴ ወልዴን ለመቅበር ምሏል። የትላንት የጥፋት ጓደኛሞች ዛሬ ለዘረፋ ግዛት ሲሉ ነጥሮ ለመውጣት መገዳደል ግዴታ ነው እያሉ የጎንደርን ጫካዎች የደም መሬት ለማድረግ ጦርነት ከፍተዋል። ሰላም የራቃቸው እነዚህ ቡድኖች ለህዝብ ደህንነት ሳይሆን ለጫካ ንግስናቸው ሲሉ እርስ በርስ ለመጠፋፋት የጀመሩት ፍልሚያ የውርደታቸው ማሳያ ነዉ ።

ይህ ሁሉ ትያትርና የደም ድግስ ደግሞ ዳይሬክተሩ ዘመነ ካሴ ነው! ዘመነ ከአስመራ ሆቴል ሆኖ የጎንደርን ወጣቶች እርስ በርስ እያታኮሰ ወጥር አለሁልህ እያለ ሃብቴ ወልዴን በቁም ስቅሉን እያሳየው ይገኛል። ዘመነ ራሱ ከአስመራ ህይወት ሳይወጣ እነዚህን የጫካ ስልጣን ናፋቂዎች እንደ ቼዝ ጠጠር እያጋጫቸው መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። የጎንደርን ጫካዎች የሽፍታ መራኮቻ ያደረገው ይህ ሴራ ዘመነ ካሴ በሃብቴ ወልዴ በኩል እያሽከረከረው ያለው የጥፋት ማሽን ነው። በአንድ በኩል ሳሙኤልና ባየ ሃብቴን ሊቀብሩት ሲዝቱ በሌላ በኩል ዘመነ በስልክ በርታ እያለ የሚያሾፍበት ይህ ድራማ የቡድኑን አቅመ-ቢስነትና ሆድ-አደርነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ሰበር! በትግራይ ክልል ኢትዮጵያ ዳርድንበር ጀግናው አየር ሀይላችን በዛሬው ዕለት የተሳካ የድሮን ቅኝት ፈፅመዋል።  የአሸባሪው ህወሓትና ወራሪው ሻዕብያ የጦር ካብፕና የመሳርያ መከማቻ የነ ...
01/05/2026

ሰበር!
በትግራይ ክልል ኢትዮጵያ ዳርድንበር ጀግናው አየር ሀይላችን በዛሬው ዕለት የተሳካ የድሮን ቅኝት ፈፅመዋል።
የአሸባሪው ህወሓትና ወራሪው ሻዕብያ የጦር ካብፕና የመሳርያ መከማቻ የነ ደብረፅዮን ጉድጓድ ሳይቀር በአየር ሀይላችን🇪🇹 ቁጥጥር ስር ተደርገዋል።

ሰማዩም ምድሩም
የኢትዮጵያ 🇪🇹 አየር ሀይላችን ነው!!!

"በአሜሪካ መንግስት ደረጃ ሶስት አሸባሪ የተባለው ፋኖ ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ አንሳተፍም''- የውጭ ዲያስፖራውበአሜሪካ እና በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በአሜሪካ መን...
01/05/2026

"በአሜሪካ መንግስት ደረጃ ሶስት አሸባሪ የተባለው ፋኖ ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ አንሳተፍም''- የውጭ ዲያስፖራው

በአሜሪካ እና በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በአሜሪካ መንግስት ደረጃ ሦስት አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው የፋኖ ታጣቂ ቡድን ስም በሚጠሩ የድጋፍ ሰልፎች ላይ ላለመሳተፍ በስፋት እየተመካከሩ መሆኑ ተሰማ።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ውሳኔ የመጣው በእንዲህ አይነት ሰልፎች ላይ መገኘት የሚያስከትለው የህግ የኢሚግሬሽን እና የደህንነት መዘዝ እጅግ አደገኛ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች በመውጣታቸው ነው።

አውሮፓና አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት እንደገለጹት በስሜት ተገፋፍቶ በሽብር ከተፈረጀ ቡድን ለመደገፍ መሰለፍ ራስን እና ቤተሰብን ማጥፋት ነው በሚል ሰልፉን ማግለል መርጠዋል።

"የአክቲቪስት መሳይ መኮነን የቅርብ ጊዜያት የትግራይ ተቆርቋሪነት ከሕግ ተጠያቂነት አያድነውም" - አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶምበሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተቀስቅሶ በነበረው ጦርነት ወቅት በሳተላይ...
01/05/2026

"የአክቲቪስት መሳይ መኮነን የቅርብ ጊዜያት የትግራይ ተቆርቋሪነት ከሕግ ተጠያቂነት አያድነውም" - አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተቀስቅሶ በነበረው ጦርነት ወቅት በሳተላይት ቴሌቪዥን በሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች በትግራይ ህዝብ ላይ "የዘር ማጥፋት አዋጅ አውጇል" በሚል ክስ የተመሰረተበት ጋዜጠኛና አክቲቪስት መሳይ መኮነን ጉዳዩን የሚመለከት አዲስ የሕግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ።

የህውሀት ታጋይ አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ተቆርቋሪ መስሎ መቅረቡ ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድነው ገልጸዋል።

አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም ለሚዲያ በሰጡት ማብራሪያ መሳይ መኮነን በጦርነቱ ወቅት "ትግሉ በ95 ሚሊዮን እና በ5 ሚሊዮን መካከል ነው" በማለት የሰጠው ንግግር በአንድ ማህበረሰብ ላይ የተቃጣ ቀጥተኛ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ እንደነበር አስታውሰዋል።

እንደ አምባሳደር ፍሰሃ ገለጻ መሳይ መኮነን በሚኖርበት የውጭ ሀገር የተመሰረተበት ክስ በአሁኑ ወቅት የደረሰበትን ደረጃ ለማወቅና ሂደቱን ለማፋጠን አዲስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

ግለሰቡ ሰሞኑን የትግራይ ህዝብ ደጋፊና ተቆርቋሪ መስሎ ለመቅረብ የሚያደርገው የፖለቲካ አቋም ለውጥ፣ ቀደም ሲል ለፈጸመው ድርጊት በሕግ ፊት ከመጠየቅ እንደማያድነው አምባሳደሩ በጥብቅ አሳስበዋል።

የህግ ተጠያቂነት በጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ወይም በጭንብል መቀያየር አይቀየርም ያሉት አምባሳደሩ በወቅቱ የጥላቻ ንግግርን እንደ መሣሪያ በመጠቀም በህዝብ ላይ ጥፋት እንዲታወጅ ያደረጉ አካላት በሙሉ ለፍትህ አደባባይ እንዲቀርቡ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Bahir Dar Ethiopia ባህርዳርን ይጎብኙ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Visit Bahir Dar Ethiopia ባህርዳርን ይጎብኙ:

Share