Keranyo in Jerusalem Tour and Travel

Keranyo in Jerusalem Tour and Travel ቀራንዮ በኢየሩሳሌም አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ከ15 ዓመታት በላይ ቅድስት ሀገር እስራኤልን በማስጎበኘት ዝናን ያተረፈ አናጋፋ ድርጅት ነው፡፡

14/02/2026

⛰️ ቀራንዮ፡ የፍቅር እና የድል ተራራ
ቀራንዮ ስንል ዝም ብሎ ስፍራ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ታሪክ የተቀየረበት፣ መለኮታዊ ፍቅር ለዓለም የተገለጠበት ታላቅ መድረክ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠበት፣ ሞትን በሞቱ የሻረበት የተቀደሰ ቦታ ነው።
📍 የሚገኝበት ቦታ
ቀራንዮ (በላቲን Calvary፣ በግሪክ Golgotha) የሚገኘው በታሪካዊቷ የኢየሩሳሌም ከተማ፣ ከድሮው የከተማው ቅጥር ውጭ በነበረው ኮረብታማ ቦታ ላይ ነው። ዛሬ ላይ ግን ይህ ስፍራ በኢየሩሳሌም በድሮው ከተማ (Old City) ውስጥ በሚገኘው በታላቁ የትንሳኤ ቤተክርስቲያን (Church of the Holy Sepulchre) ውስጥ ይገኛል።
💡 የቀራንዮ ትርጉም
* የራስ ቅል ስፍራ፡ "ጎልጎታ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ትርጉሙ "የራስ ቅል" ማለት ነው። ይህም ቦታው የራስ ቅል ቅርጽ ስላለው ወይም የቀብር ቦታ ስለነበረ የተሰጠው ስም ነው።
* የይቅርታ መፍለቂያ፡ "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" የሚለው ታላቅ ቃል የተሰማው ከዚህ ተራራ ላይ ነው።
🕊️ መንፈሳዊ መልእክት
ቀራንዮ የውድቀት ሳይሆን የድል ምልክት ነው። ዛሬም ድረስ ወደዚህ ስፍራ የሚመለከት ሁሉ የተሰበረ ማንነቱ ይታደሳል፣ ተስፋውም ይለመልማል። የክርስቶስ መስቀል በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ ያፈረሰበት ድልድያችን ነው።

ሁሌም ከኛ ጋር ይጓዙ ቀራንዮ በአኢየሩሳሌም
#ቀራንዮ #ኢየሩሳሌም #መስቀል #ፍቅር #ክርስትና

10/02/2026

❗️ለትንሣኤ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አብረን እንጎብኝ❗️

❤️ ቀራኒዮ በኢየሩሳሌም አስጎብኚ

✝ አድርሻ 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ❤️❤️❤️❤️
ስልክ ቁጥር 0911526425 /+251911436608

10/02/2026
09/02/2026

ጎሎጎታ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም ዘር ሁሉ ሲል ነፍሱን አሳልፎ የሰጠበት፣ ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ የትንሣኤያችን በኩር የሆነበት ቅዱስ ስፍራ! 🕊️
ከእኛ ጋር ይጓዙ ቀራንዮ በኢየሩሳሌም አስጎብኚ
0911526424
0911526425

ሰላም ሰላም የሰላም ዓምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።  ትላንት ሚያዝያ 24 ቀን  2017 ዓ፡ም  የእስራኤል 77 ዓመት የነፃነት ቀን ተጠርቸ ተገኝቸ ነበር።    ክቡር አምባሳደር አቭርሀም ስ...
03/05/2025

ሰላም ሰላም የሰላም ዓምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። ትላንት ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ፡ም የእስራኤል 77 ዓመት የነፃነት ቀን ተጠርቸ ተገኝቸ ነበር። ክቡር አምባሳደር አቭርሀም ስለ ኢትዮጵያና ስለ እስራኤል ግኑኝነት ሲናገሩ ከጥንት ጀምሮ አመታትን ያስቆጠረ ከንግሥት ሳባ እና ከንጉሥ ሰለሞን ጀምሮ እንደነበረ ሲገልፁ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኝ ተመለስኩ። ክቡር አምባሳደር እድሜ ይስጥዎት፣ ሥራዎ ሁሉ የተቃና ይሁን።

May the God of peace be praised. Yesterday, on May 2, 2025, I had the honor of attending the celebration of Israel’s 77th Independence Day.

When the Honorable Ambassador Avraham spoke about the relationship between Ethiopia and Israel tracing it back to the time of the Queen of Sheba and King Solomon I was filled with great joy and deeply moved.

May the Honorable Ambassador be granted a long life, and may all his endeavors be blessed and successful.

02/02/2025

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Abrham Zenebe, Tadu Fishatsion

24/12/2024

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Selam Asefa, Endashaw Getaneh Kassay

10/12/2024

ቀራንዮ በኢየሩሳሌም አስጎብኝና የጉዞ ወኪል በአስተማማኝና በተረጋጋ መንፈስ ከስጋት የፀዳ ጉዞና መንፈሳዊ ጉብኝት ማድረግ ስላለብን የአሁኑን የገና ጉዞ ወደ ትንሳኤ አሸጋግሮታል ። የሰላም ዓምላክ እግዚአብሔር የዚያ ሰው ይበለን።

26/11/2024

በመስተንግዶው እውቅናን ዝናን የተረፈው ቀራንዮ በኢየሩሳሌም አስጎብኝ ድርጅት አሁንም ሥራውን እንደቀጠለ ይገኛል።

22/11/2024

ቀራንዮ በኢየሩሳሌም ቱር ኤንድ ትራቭል እግዚአብሔር ዓምላክ ፈቃዱ ከሆነ ለጉዞ በዝግጅት ላይ ነን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

Address

4kilo Selase Menfesawi Collage 1 Floor
Addis Ababa
NONE

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911526425

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Keranyo in Jerusalem Tour and Travel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category