Visit ኢትዮጵያ

Visit ኢትዮጵያ Get Info about Ethiopian tourism, culture, traditions etc.. know Ethiopia ??

ማሩ ቀመስ ደምቢያ ደብረ ሲና ማርያም ተገኘን !!(ታዴ የማመይ ልጅ )   | ተወዲያ ከውቢቷ ባሕር ዳር እስከ ታሪካዊቷ ጎንደር፤ ከለምለሙ የጎጃም ምድር እስከ ማማው በጌምድር የተዘረጋው የጣ...
30/11/2025

ማሩ ቀመስ ደምቢያ ደብረ ሲና ማርያም ተገኘን !!

(ታዴ የማመይ ልጅ )

| ተወዲያ ከውቢቷ ባሕር ዳር እስከ ታሪካዊቷ ጎንደር፤ ከለምለሙ የጎጃም ምድር እስከ ማማው በጌምድር የተዘረጋው የጣና ሐይቅ ከሕዋ ላይ ሆነው ሲያዩት የሰውን ልጅ ❤️ የልብ ቅርጽ ገፅታ ይዞ ይታየኛል ።

ከዘጌ እስከ ጣና ቂርቆስ፣ ከደልጊ እስከ ሬማ መድኃኒዓለም፣ ከክብራን እስከ ጀበራ ማርያም፣ ከእንጦስ እስከ ማንዳባ፣ ከጉረር እስከ አንጋራ ከቁንዝላ እስከ ጎርጎራ እና ሌሎችም የተንጣለለዉን ሐይቅ ጉማራ ጉዛራና ርብ የተባሉ አፍላጎች ሰርክ ይገብሩለታል ።

ለማንቻዉም በጣና ሃይቅ ወደብ፤ በቤጌምድር መደብ በጎንደር እናት ባሕላዊ፣በቅዱሳን መኖሪያ፣ የበረከት ማደሪያ፣ የእውቀትና የጥበብ መፍለቂያ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ሃብቶች መጠለያ ፣ለዘመነ መሳፍንት ማክተም ምክንያት ከሆኑ ቦታዎች አንዱም ነው፤ ማሩ ቀመስ ደንቢያ ዉስጥ ነኝ ፡፡

መዳረሻዬ ደግሞ ከረጂም ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ በተዘረጋዉ ታሪኳ በዋሻዎቿ የሰው ልጅ ይኖርባት እንደነበር የሚነገርላት ፣ከህገ ልቦና እስከ ህገ ኦሪት፣ ከንጉሰ ነገስት እስከ ወታደራዊ መንግሥት፣ ከጥንታዊው እስከ ዘመናዊው፣ ከተዘመረለት እስካልተዘመረለት ፣የኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ በሚነገርበት፣ ስርዓተ ክህነት እና ስርዓተ መንግሥት የጸናባት ጎርጎራና የ704 ዓመቷ ደብረ ሲና ማርያም ገዳም ናት ፡፡
ከዚያ በፊት ግን ስላለሁበት ለጥ ያለዉ የደምቢያ ምድር ጥቂት ልበል አሁን የምገኝበት ስፍራ በኢትዮጵያ ታሪክ ያላስተናገደው ሁነት የለም ፡፡

አፄ ሱስንዮስ ኢትዮጵያ የሮማን ሐይማኖት እንድትቀበል አዋጅ ያስነገሩት ከዚህ ስፍራ ነዉ።

የአፋሩ ጦረኛው አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ …ግራኝ አህመድ ከርቀት የሰማዉ ገናናው ስሟን አይቶ ለመናገሻነት መረጦ በረሃውን አቋርጦ ለህልሙ መሳካት ከአስር አመት በላይ የተይከራተተላት በመጨረሻም አፈሯን ቀምሷል።

ግራኝ አህመድ መርጦ ጣና ዳርቻ ዋና መዲናውን ለማድረግ እንዳሰበ ሁሉ፤ ፋሺሽት ጥሊያንም ጎርጎራን እና ደንቢያን ዋና መናገሻው ለማድረግ ዳድቶት ነበር አሉ፡፡

ሐማሴኖች ትናንታችን የዘር ሀረጋችን ከዚህ ይመዘዛል ይሉናል ፣ዮዲት ጉዲትም መዲናዋ ለማድረግ መርጣታለች ፣ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ አንጥረኛ እና ጥበበኛ የሆኑት ቋረኛው ንጉስ የመሪነት ጥበብ ስንቃቸውን የቋጠሩት፣ የታላቅነት ራዕይ ህልማቸውን የወጠኑባት ማሩ ቀመስ ደንቢያ ነበር ፡፡

ስፍራው ከአፄ አምደ ፅዮን እስከ ታላቁ ንጉስ ሰርፀ ድንግል፣ ከ አፄ ፋሲል እስከ አፄ ሱስንዮስ ፣ከእንግሊዝ ተስፋፊዎች እስከ የፖርቹጋል አሳሾች ከሮም ቀሳውስት እስከ የግሪክ መልዕክተኞች ፋሺሽት ጣሊያን እስከ ሚሲዮናዊያን ከአፄ ኃይለ ስላሴ እስከ ኮሎኔል መንግስቱ እልፍ ታሪኩን በአጭር ቃላት ገልፀን መጨረስ አያስችልምና ቀጥታ ወደዛሬዋ መዳረሻዬ ላቅና ።

ይህ ሥፍራ በቅዱሳን መኖሪያ፣ የበረከት ማደሪያ፣ የእውቀትና የጥበብ መፍለቂያ ፣ ትናንት ጥበብ የተቀዳበት ፣ ዛሬም የሚቀዳበት ጥበብን የሚሹ ሁሉ የሚረኩበት ስለመሆኑ ሞገሱ ያሳብቃል ።

አሁን የምገኘው ከጎንደር ከተማ በስተምዕራብ 61 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ጣና ሀይቅ ዳር ነዉ ።

በስተምስራቅ የተንጣለለው ሐይቁ በማዕበል ይወዛዋዛል፡፡ ዛፎች ለጌታቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ይመስላሉ፡፡ ጎንበስ ቀና ሲሉ አጀብ ያሰኛሉ፡፡ አበው መነኮሳት ስጋዬን ለመነኩሴ ነብሴንም ለስላሴ ብለው ሳያርፉ ለአገልግሎት ይፋጠናሉ፡፡ ስጋቸውን እያስራቡ ነብሳቸውን ይመግባሉ፡፡ ስለ ዓለም ሀጥያት፣ ስለ ምድር በረከት፣ ስለ ኢትዮጵያ ፅናት፣ ስለ ሕዝቦቿ አንድነት ሳይሰለቹ ይማፀናሉ፡፡

በሃ

ጉራጌ ኢትዮጵያ፦ ውብ ምድር
30/10/2024

ጉራጌ ኢትዮጵያ፦ ውብ ምድር

07/05/2023

Good Morning Ethiopia

Ethiopian Orthodox Tewahido Church!!
09/02/2023

Ethiopian Orthodox Tewahido Church!!

04/02/2023

ውዱ ወገኔ!

- የኢትዮጵያን ስሟን ሲጠራ አንስቶ ልባችን ተንዶ እንደ ነብይ ቆጥረነው ፈጣሪን አሳዝነናል።
- ይህ የሆነው ሀገራችንን አጥብቀን ስለምንወዳት ነውና ፥ ከልክ ባለፈ ላሳደርነው እምነት ፈጣሪያችንን ይቅር በለን ብንለው ይቅርታን ይሰጠናል።
- ፈጣሪ በሺህ አመታት እገዛው ያልተለያት ሀገር ልጆች ነንና እሱ ከኛ ጋር ነው።
- እውነታችንን ካልነጠቅን በሚል የሚደርስብን በደል ነውና ፥ የእውነት አምላክ ከኛ ጋር ነው።
- የእውነት አምላክ ከኛ ጋር ስለሆነም ፥ የአስመሳይ፣ ቀጣፊ ልብን አሳብጦታል።
- ያሳበጠውን ማስተንፈስ የሚችለው አምላክ ከኛ ጋር ነውና ዛሬ እየሆነ ባለው መቆዘም ላይ ሳይሆን ነገ የሚተነፍስ መሆኑን በጭራሽ አንጠራጠር።
- የትዕቢት መንፈስ መተንፈሱም የማይቀር ነውና በንዴት ሳይሆን በአስተውሎት፣ በቆራጥነትና ስለአሸናፊነታችንም በፍፁም እምነት ለነገው የአምላካችን ተግባር የምንመች ሆነን ዛሬ እንገኝ!
- የግፉ ፅዋ ሞልቶ ፈሷልና ፥ ለማይቀረው የፈጣሪያችን ካሳ የታመን እንሁን።
- በእውነት ፣ በልበ ሙሉነት እና በአምላካችን ተመክተን በአንድነት እንቁም!

ማሸነፋችን አይቀሬ ነው !!

#ሼር !

03/02/2023
19/11/2022
Ramadan Mubarak to all Muslim around the world 🌎.
02/04/2022

Ramadan Mubarak to all Muslim around the world 🌎.

Entos Eyesus Monastery_ Lake Tana, Ethiopia.
23/03/2022

Entos Eyesus Monastery_ Lake Tana, Ethiopia.

Religion in Ethiopia. Ethiopian Orthodox Tewahdo Church Meskel celebration
21/03/2022

Religion in Ethiopia. Ethiopian Orthodox Tewahdo Church Meskel celebration

Lake Tana
03/03/2022

Lake Tana

Address

Addis Ababa
00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category