Ethiopian Coffee and Culture

Ethiopian Coffee and Culture I am love travelling.

26/08/2025
16/07/2025
 ? እውነተኛ ታሪክእንደማንኛውም የኢትዮጵያ አርብቶ አደር ልጅ ወይም የኢትዮጲያ ገበረ ልጅ ከብት በማገድ እና ማሽላ በመጠበቅ ወላጆቼን እረዳ ነበር። በአካባቢያችን ዙሪያ ላይ በተከሰቱ ግጭቶ...
12/05/2025

? እውነተኛ ታሪክ
እንደማንኛውም የኢትዮጵያ አርብቶ አደር ልጅ ወይም የኢትዮጲያ ገበረ ልጅ ከብት በማገድ እና ማሽላ በመጠበቅ ወላጆቼን እረዳ ነበር። በአካባቢያችን ዙሪያ ላይ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት 1958 ዓ/ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ፖሊስ ጣቢያ ተቋቋመ። ይህ ነገር ለእኔ እና ለአካባቢው ሰው እንግዳ ነገር ነው። አይተናቸው የማናቅ አዲስ አለባበስ ያላቸው ሰዎች መምጣት የተለየ ትኩረት እንዲሰጥ አደረገኝ። ከብቶችን ሳሰማራ ነገሩ እንግዳ ነገር ስለሆነብኝ ከሪቀት ቀጭ ብዬ የወታደሩን አለባበስ እና ሥራቸውን ለተከታታይ ጊዜ በየቀኑ ከብቶችን ለግጦሽ ሳሰማራ እመለከታለሁ። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ በተቋቋመው ፖሊስ ጣቢያ የሚሰሩ ወታደሮች አብዛኞቹ ያልተማሩ ስለነበር በዚያን ምክንያት ወታደሩ ደሞዝ ስቀበል በእጁ ጣት ላይ ቀለም ተቀብቶለት ፈርሞ ደሞዙን ይቀበል ነበር። ወታደሩ ማንበብ እና መፃፍ መቻል አለበት በእጁ ጣት ላይ ቀለም ተቀብቶለት መፈረም የለበትም ተብሎ ለወታደሩ ከመሀል ሀገር የተዘጋጀ የፊደል ሰራዊት መጽሔት መጣለት።

ወታደሩ የተዘጋጀለትን የፊደል ሰራዊት መጽሔት የያዘውን ፊደል የዛፍ ጥላ ሥር ሆኖ ጮክ ብሎ ይቆጥራል። መንደራችን ፖሊስ ጣቢያው አካባቢ ስለነበር ከብቶችን ሣር ሳስግጥ ይህንን ሄደት ከሩቁ አዳምጥ እና እመለከት ጀመር። ፖሊሶች ፊደል ስቆጥሩ የሚያወጡት ድምፅ እንደ ዜማ ስለማረከኝ ጆሮየን ቀሲሬ እያዳመጥኩ አብሪያቸው ለማዜም እሞክር ተያያዝኩ። ቀስ በቀስ ፈራ ተባ እያልኩ በወታደሮቹ ፊደል ቆጠራ ዜማ ተማሪከ ወደ ወታደሮቹ ጠጋ በማለት እና ከቅርብ እርቀት ሆኘ ፊደል ስቆጥሩ ጆሮየን በመጣል ማዳመጤን ቀጠልኩ። በተደጋጋሚ በቅርብ ሪቀት ሆኘ ስከታተል ያዩኝ ወታደሮች ወደኔ ጠጋ ብሎ ና ከኛ ጋር ፊደል ቁጠር አሉኝ። አማርኛ ስለማልችል የተቆጡኝ መስሎኝ እሮጨ ፈጠር ብዬ ቆምኩ። ከመካከላቸው ኦሮምኛ የሚችሉ ወታደሮች ''ኮቱ እንሶዳትን'' ና አትፍራ ብሎ ጠሩኝ ፈራ ተባ እያልኩ ተጠጋዋቸው። አካባቢው ከቦረና ጋር ስለሚያዋስን ከየቦረና ለኑሮ የመጡ እንድሁም ከአርቦሬ ጋር በጋብቻ የተሳሰሩ ስለነበሩ በመንደሩ ከአርቦሬ ቋንቋ በተጨማሪ ኦሮምኛ ይነገራል። በማቃት ኦሮምኛ ተንተባትበ በመግባት በዛን እለት ፊደል አብሬያቸው መቁጠር ጀመርኩ። የፊደል ሰራዊት ቆጠራውን ለረጅም ቀናት ሳላቋርጥ በየቀኑ እየመጣሁ መቁጠሩን ተያያዝኩ። ቀስ በቀስ ከወታደረቹ ጋር ያለኝ ግንኙነታችን የበለጠ እየጠነከረ ሄደ። ፊደል ለመቁጠር በመጣሁ ጊዜ ሀሉ ሻይ በጋበጣ ኩባያ እና በወፍራሙ የተጋገረ የወታደር ዳቦ ይሰጡኝ ጀመር።

እኔም ልጅ ስለነበርኩ የፊደል ሰራዊቱን ቆጠራውን ከወታደሮቹ ቀዲሜ ጨረስኩ። አማርኛ ባይገባኝም ፍደሎች ተገጣጥሞ ቃላቶችን ማንበብ እንደቻልኩ የሚሰጥ መልክት በወቅቱ መፃፍ እና ማንበብ ከሚችሉ ወታደሮች ከሚሰጡኝ ሞራል ተረዳው።

?
ከፖሊሶች መካከል ወታደር ሙሉጌታ ደምሴ በጊዜ ህደት አስራ አለቃ ቀጥሎም ሃምሳ አለቃ የሆኑ ወታደር ሙሉጌታ ደምሴ ጉብዝናዬን ስለተመለከቱ አንድ ቀን ወደ እኔ ቀረብ ብለው እኛ ወደ ቡስካ ልንቀየር ነው አርቦሬ ላይ ትምህርት ቤት ስለሌለ ለምን ወደ ቡስካ ከኛ ጋር ሄደ የመንግስት አንደኛ ደረጄ ትምህርት ቤት አትማርም አሉኝ።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል

ታሪኩ የተመቻችሁ ከሆነ ክፍል ሁለት እንድቀጥል ከፈለጋችሁ ክፍል ሁለት ይቀጥል በላችሁ በኮመት አስቀምጡ ለሌሎችም ሼር አድርጉ።

ደስ የሚል የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ!

በአንድነት ሆራ ሱራ የተፃፈ እውነተኛ ታሪክ

Andinet Hora

05/05/2025
Ethiopian Coffee and Culture
03/05/2025

Ethiopian Coffee and Culture

31/03/2025

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Coffee and Culture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Coffee and Culture:

Share

Category