ደቡብ ወሎን ይጎብኙ "/Visit South Wollo/"

ደቡብ ወሎን ይጎብኙ "/Visit South Wollo/" የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ
የዞኑን ባህል፣ የቱሪዝምና ስፖርታዊ ሀብቶች ለማስተዋወቅ የተቋቋመ።
South Wollo Zone Culture, Touris

18/09/2026

#ደረሰ ታላቁ በዓል በግሸን
መስቀል፣ ማርያምና ኡራኤል በአንድ ጉዞ

የደቡብ ወሎ ዞን ስፖርት ምክር ቤት 41ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደመስከረም 07/2019 ዓ.ም | ደሴየደቡብ ወሎ ዞን ስፖርት ምክር ቤት 41ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል።ጉባኤው የምክር ቤቱ...
17/09/2026

የደቡብ ወሎ ዞን ስፖርት ምክር ቤት 41ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

መስከረም 07/2019 ዓ.ም | ደሴ

የደቡብ ወሎ ዞን ስፖርት ምክር ቤት 41ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል።

ጉባኤው የምክር ቤቱን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የተገመገመበትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የቀረበበት ነው።

ጉባኤውን በንግግራቸው የከፈቱት የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢና የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮነን፣ ስፖርት የሕዝብን ጤና በማስጠበቅ፣ አምራች ዜጋን በመፍጠርና የወዳጅነትን መንፈስ በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አቅም ያለው መስክ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም መንግሥት የስፖርት ማዘውተሪያዎችንና የሥልጠና ማዕከላትን በማጠናከር እያደረገ ያለውን ጥረት ለማጠናከር ሌሎች አካላትም የድጋፍ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የስፖርት ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢና የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አስያ ኢሳ በበኩላቸው፣ ስፖርት የሰውነት እንቅስቃሴና ውድድር ብቻ ሳይሆን የጤና፣ የወጣቶች አቅም ማጎልበቻና የሰላም መሠረት ሊሆን የሚችል መስክ መሆኑን ገልጸዋል።

ስፖርትን መደገፍ ለአሸናፊዎች ሽልማት ከመስጠት ባለፈ፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን መገንባት፣ የሥልጠና ዕድሎችን መፍጠርና የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግንም የሚያካትት መሆኑን አመልክተዋል።

በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ውጤቶች

በጉባኤው ላይ በቀረበው የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መሠረት፣ ከደቡብ ወሎ ዞን የወጡ ስፖርተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ ሆነዋል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሀገራቸውን መወከል ችለዋል።

በእግር ኳስ ዘርፍ ወረኢሉ እግር ኳስ ክለብ የአማራ ሊግን በማሸነፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ክልሉን መወከል የቻለ ሲሆን፣ በአትሌቲክስ ዘርፍ ደግሞ የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶችን አፍርቷል።

በባህላዊ ስፖርቶች ውድድር ዘርፍም ዞኑ በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ለቀጣይ ዓመት ትኩረት

ያነጋገርናቸው የስፖርት ምክር ቤቱ አባላት፣ ባለፈው ዓመት በስፖርቱ ዘርፍ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት ለመሥራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በጉባኤው መጠናቀቂያም በ2018 በጀት ዓመት ውጤታማ ተግባራትን ላከናወኑ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

ደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ
ደቡብ ወሎን ይጎብኙ! | Visit South Wollo

🏆 የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፤ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጠደሴ፣ መስከረም 6/2019 ዓ.ም. — የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስ...
16/09/2026

🏆 የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፤ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጠ

ደሴ፣ መስከረም 6/2019 ዓ.ም.
— የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ ትውውቅ ፕሮግራም አካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ አስያ ኢሳ፣ የ20 ወረዳዎች የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች እና የእቅድ ዝግጅት ባለሙያዎች፤ የመምሪያው ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ የ2018 ዓ.ም. የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በሪፖርቱ ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በመቀጠልም የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ ቀርቦ የውይይትና የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

የውይይቱ ዋና ትኩረት በ2018 ዓ.ም. የተከናወኑ የባህል፣ የቱሪዝምና የስፖርት ሥራዎችን በመገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችንና ክፍተቶችን በመለየት በ2019 ዓ.ም. የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ነበር።

🏆 የ2018 ዓ.ም. የአፈጻጸም ሽልማት

በ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት መሠረት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ወረዳዎች እውቅናና የገንዘብ ሽልማት ከምስክር ወረቀት ጋር ተሰጥቷል።

🥇 1ኛ ደረጃ — ጃማ ወረዳ
💰 10,000 ብር + የምስክር ወረቀት

🥈 2ኛ ደረጃ — ወረኢሉ ወረዳ
💰 7,000 ብር + የምስክር ወረቀት

🥉 3ኛ ደረጃ — ቃሉ ወረዳ
💰 5,000 ብር + የምስክር ወረቀት

የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ የተካሄደው ውጤታማ የሥራ አፈጻጸምን ለማበረታታት፣ ተሞክሮን ለማጋራትና በወረዳዎች መካከል የሥራ ትጋትን ለማጠናከር በሚያግዝ መልኩ ነው።

በመጨረሻም የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ በተሻለ ቅንጅት፣ ተጠያቂነትና ትጋት ለመፈጸም የጋራ አቅጣጫ ተቀምጦ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

🌟 የ2019 ዓ.ም. መልዕክታችን

“ውጤታማ አፈጻጸምን እናበረታታለን፤ ተሞክሮን እናጋራለን፤ በ2019 ዓ.ም. የተሻለ ውጤት እናስመዘግባለን!”

📸 የመርሃ ግብሩን ፎቶዎች ይመልከቱ፣ ይወዳጁ፣ ያጋሩ፣ አስተያየትዎንም ያስቀምጡ።

ደቡብ ወሎን ይጎብኙ! | Visit South Wollo!

#ባህል #ቱሪዝም #ስፖርት #ዕቅድ #አፈጻጸም #እውቅና #ሽልማት

📢 የ2018 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ፤ የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ ትውውቅ ተካሄደደሴ፣ መሰከረም 6/2019 ዓ.ም. — የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም....
16/09/2026

📢 የ2018 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ፤ የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ ትውውቅ ተካሄደ

ደሴ፣ መሰከረም 6/2019 ዓ.ም.
— የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ ትውውቅ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት አካሄደ።

🌍 የዓለም የቱሪዝም ቀን 2019 ዓ.ም. | World Tourism Day 2026“ቱሪዝምን እንደገና ለመቅረጽ የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት”/“Digital Agenda and A...
15/09/2026

🌍 የዓለም የቱሪዝም ቀን 2019 ዓ.ም. | World Tourism Day 2026

“ቱሪዝምን እንደገና ለመቅረጽ የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት”
/“Digital Agenda and Artificial Intelligence to Redesign Tourism”/

የዓለም የቱሪዝም ቀን መስከረም 17፣ 2019 ዓ.ም. (September 27, 2026) በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል።

በዚህ ዓመት የቱሪዝም ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በማዘመን፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ልማትን ዘላቂና ተጠቃሚ ማድረግ የዘመኑ ዋና ትኩረት ነው።

📢 የጥሪ መልዕክት
ስለሆነም የደቡብ ወሎ ዞን ወረዳና ከተማ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤቶች ይህን ዓለም አቀፍ ቀን በአካባቢያችሁ ባሉ የቱሪዝም ሀብቶችና መዳረሻዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ በተለያዩ የቱሪዝም ማስተዋወቂያና የህዝብ ተሳትፎ መርሃ ግብሮች በድምቀት እንድታከብሩ ጥሪ ይቀርባል።

📸 የአካባቢያችሁን ቱሪዝም መዳረሻዎች በጥራት በማስተዋወቅ
📱 ዲጂታል ሚዲያን በመጠቀም
🤖 AIን ለቱሪዝም ማስተዋወቂያ በመጠቀም
🌿 የተፈጥሮና የባህል ሀብቶችን በመጠበቅ
👥 ማህበረሰቡን በማሳተፍ

የደቡብ ወሎን የቱሪዝም ሀብት በጋራ እናስተዋውቅ!

ደቡብ ወሎን ይጎብኙ! 🌿🏔️📱
Visit South Wollo!

ደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

🌿 መስከረም 21 — ግሸን ደብረ ከርቤን ስትጎበኙ፣ ወንዳች ማርያምንም ይጎብኙ! 🙏 #በመጪው መስከረም 21 የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ግሸን ለምትመጡ ምዕ...
14/09/2026

🌿 መስከረም 21 — ግሸን ደብረ ከርቤን ስትጎበኙ፣ ወንዳች ማርያምንም ይጎብኙ! 🙏

#በመጪው መስከረም 21 የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ግሸን ለምትመጡ ምዕመናንና እንግዶች፦

👉ጉዞዎን በወንዳች ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ያሳምሩ! 🌿⛪
በግሸን ደብረ ከርቤ አካባቢ የምትገኘው ወንዳች ማርያም ከዘመናት በፊት የተመሠረተች ታሪካዊና ቅዱስ ስፍራ ናት። በፊት “ውስጣምባ ማርያም” ተብላ ትጠራ የነበረችው ይህች ቤተ ክርስቲያን፣ ለምዕመናን የጸሎት፣ የምስጋናና የበረከት ስፍራ ናት።

✨ የግሸን በዓል ጉዞዎ በደብረ ከርቤ ብቻ አይቁም!
እስከ ወንዳች ማርያም ይቀጥሉ፤ ታሪኳን ይወቁ፣ ቅዱስ ስፍራዋን ይጎብኙ፣ በጸሎትና በምስጋና ጊዜዎን ያሳልፉ።

🙏መስከረም 21 ግሸን ስትመጡ፣ ወንዳች ማርያምን አትርሱ!

“በግሸን ሲከብሩ፣ ወንዳች ማርያምንም ይሳለሙ!”

📲 ከእኛ ጋር ይቀጥሉ! 🌍❤️
የደቡብ ወሎን ታሪክ፣ ባህል፣ ቅርስና የቱሪዝም ሀብቶች በተሻለ መልኩ እንዲያውቁ እና አብረን እንድናስተዋውቅ፤
👉 ገጻችንን ይከተሉ (Follow)
❤️ ላይክ (Like) ያድርጉ
🔄 ለወዳጅዎ ሸር (Share) ያድርጉ
💬 አስተያየትዎን (Comment) ያካፍሉ
እርስዎ አንድ ላይክና አንድ ሸር ለደቡብ ወሎ ቱሪዝም ትልቅ ድጋፍ ነው! ❤️
🌿 ደቡብ ወሎን ይጎብኙ!
🏛️ ታሪካችንን እንጠብቅ፣ ቅርሳችንን እናስተዋውቅ፣ መዳረሻችንን እናሳድግ!

ደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

Address

Dessie
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደቡብ ወሎን ይጎብኙ "/Visit South Wollo/" posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category