Kedamay Tourism Club

Kedamay Tourism Club Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kedamay Tourism Club, Travel Agency, Addis Ababa.

11/08/2017

☞ ለtelegram ተጠቃሚዎች ብቻ
ስለ ሀገራችን ቱሪዝም : ባህል ስለ ተለያዩ መስዕብ ስፍራዎች እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ አስተማሪ የመረጃዎች ይቀርብበታል፡፡
☞ ይህን በርካታ የቱሪዝም የታሪክ ባለሙያዎች ያሉበትን የtelegram group መቀላቀል ይፈልጋሉ???
እንግዲያውስ ስልኮትን ከዚህ በታች ይፆፋልን ::

03/08/2017

በተጨማሪ መረጃዎችንን
ለመግኘት በቴሌ ግራም(telegram) ቻናላችን ይቀላቀሉን፡፡የቴሌ
ግራም ቻናላችንን ለማግኘት ብለው
ሰርች
ያድርጉ ከዛም join ያድርጉ

ስላነበቡልን ከልብ እናመሰግናለን መልካም ቀን
ተመኘንልዎ❗️

06/09/2016

በግዕዝ አውደ ዓመት ይባላል - ርዕሰ አውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በአማርኛ ደግሞ እንቁጣጣሽ ይባላል፡፡ ዕንቁጣጣሽ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉና ተራ በተራ እንያቸው፡፡ አንደኛው በኖህ እና በልጆቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን፡፡ ሴም፣ ካምና ያፌት ሶስቱ የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ኖህ አህጉራትን ለሶስቱ ልጆች አከፋፍሎ ሲሰጥ ለካም አፍሪካ ደረሰው፡፡ ካም ወደ አፍሪካ የገባው እና መጀመሪያ የረገጠው ኢትዮጵያን ሲሆን ወሩም ምድሪቱ በአደይ አበባ ያሸበረቀችበት የመስከረም ወር ነበር፡፡ በምድሪቱ ውበት በመደመሙና ይህ ዕጣም ለእሱ ስለደረሰው ተደስቶ “ዕንቁ ዕጣ ወጣልኝ” አለ፡፡ እንግዲህ እንቁጣጣሽ ለሚለው ቃል አንዱ የየት መጣ ሀሳብ /Etymology/ እንዲህ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ምድሪቱ በአደይ ፈክታ ሲመለከት “ዕንቁ ዕፅ አወጣሽ” ከሚል ነው እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ የመጣ የሚል ነው፡፡
በዚህኛው አካሄድ “ዕንቁ” ከኦይስተር ቅርፊት /pearl/ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ድቡልቡል፤ ጠንካራ አንጸባራቂ፤ ነጭ ውድ ጌጥ/ ለጌጥነት የሚያገለግል ነገር/ ሲሆን “ዕፅ” ደግሞ በግዕዝ የአማርኛው “ተክል” አቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክሉን መልክ ከዕንቁ ጋር በማነጻጸር የምድሪቱን ውበት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡፡
ሶስተኛው ደግሞ የቀዳማዊ ምኒሊክ እናት ንግስት ሳባ ሰለሞንን ለመጎብኘት በሄደችበት ጊዜ ንጉሱ “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ” ብሎ መስጠቱን መሰረት አድርጎ የሚነሳ ሃሳብ ሲሆን ወሩም ወርሃ መስከረም ነበር፡፡
አዲስ ዘመን ከወቅትና ከመልክአምድራዊ፣ ከባህልና ከኃይማኖት አንጻር
አዲስ ዘመን የሚከበርበት በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛ ወንዞች የሚጎሉበት፣ ገበሬው የክረምቱን ወራት አርሶ ዘርቶ አርሞ ወዘተ… የአዝመራውን አላባ የሚጠብቅበት፣ የጥጋቡ ዘመን የሚመጣበት፣ ብርሃናት ዑደታቸውን ጨርሰው አዲስ የሚጀምሩበት ወዘተ. ሲሆን ሁኔታውን ከወቅቶችና ከመልከአምድራዊ ሁኔታ ጋር አሰናስሎ መመልከት ይቻላል፡፡

01/09/2016

ጳጉሜን- የኢትዮጵያ 13ኛ ወር ፀጋ መገለጫ **************
ጳጉሜ የሚለውን ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ እንደሆነ የኢትዮጵያ የታሪክ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ ቋንቋ ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ደግሞ ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ አውሮፓዎች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ ኢትዮጵያዊያን የወርን ቁጥር ሠላሳ ስናደርግ እነሱ ደግሞ ሠላሳ አንድ ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ሊቃውንቱ ጳጉሜን እንደ ዓመት ማጠቃለያ፣ እንደ ዘመን መፈጸሚያ አድርገው ያስቧታል፡፡ ጳጉሜን በሁለት ዘመናት መካከልም እንደ መሸጋገሪያ የምትታይ፤ ከሌሎች ወሮች በተለየ ቀኖቿ መጠን የሚቀያየሩ ብቸኛ ወር ናት፡፡ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ጳጉሜን ከነሐሴ በሃላ 13ኛ ወር ትባል እንጂ፣ በውስጧ የያዘቻቸው የቀናት ቁጥር በአንድ ሳምንት ካሉ ቀናት ያነሱ ናቸው፡፡ አምስትና ስድስት የምትሆን ወር ናት፡፡ ጳጉሜ 7 ቀናት የምትይዝበት ዓመት እንዳለም ሰምተናል። *********** ጳግሜ ሰባት የምትሆነው በየ600 መቶ አመት አንድ ጊዜ ነው። በየ600 መቶ አመት አንድ ጊዜ እንደምትከሰት ቀደምት አባቶቻችን የቀን አቆጣጠርን ቀመር በቡና ፍሬ አስልተውት በየ600 መቶ አንድ ግዜ ጳግሜ ሰባት እንደምትሆን ደርሰውበታል። ይህም የሚሆነው በየአመቱ የተወሰነ ሰከንድ እየተደመረ ከስድስት መቶ አመት በኋላ ሙሉ አንድ ቀን ይሆናል በሚል ነው።

መጣና በዓመቱኧረ እንደምንሰነበቱ፣ሆያ ሆዬ ሆሆያ ሆዬ ሆእዛ ማዶ ሆ አንድ ብር ሆእዚ ማዶ ሁለት ብር ሆየኔማ ጋሼ ሆ የባንክ ማናጀር..........ክበር በስንዴክበር በጤፍምቀኛህ ይርገፍእን...
17/08/2016

መጣና በዓመቱ
ኧረ እንደምንሰነበቱ፣
ሆያ ሆዬ ሆ
ሆያ ሆዬ ሆ
እዛ ማዶ ሆ አንድ ብር ሆ
እዚ ማዶ ሁለት ብር ሆ
የኔማ ጋሼ ሆ የባንክ ማናጀር
..........
ክበር በስንዴ
ክበር በጤፍ
ምቀኛህ ይርገፍ
እንዲሁ እንዳላችሁ
አይለያችሁ

14/08/2016
14/08/2016
ከ ሀምሌ 22 እስከ ሀምሌ 25 ለአራት ቀናት  ሙሉ ወጪችንን ችላቹ በደብር ማረቆስ እና አካባቢዋ ያሉትን ተፈጥሮዊ  ታሪካዊ እንዲሁም ሀይማኖታዊ  የቱሪስት መስህቦችን  አውቀን እንዲናሳውቅ ...
03/08/2016

ከ ሀምሌ 22 እስከ ሀምሌ 25 ለአራት ቀናት ሙሉ ወጪችንን ችላቹ በደብር ማረቆስ እና አካባቢዋ ያሉትን ተፈጥሮዊ ታሪካዊ እንዲሁም ሀይማኖታዊ የቱሪስት መስህቦችን አውቀን እንዲናሳውቅ ጎብኝተን እንድናስጎበኝ ለጋበዛችሁን ታላቅ ምስጋና በቀዳማይ አገርህን እወቅ ክበብ ስም እናቀረባለን፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kedamay Tourism Club posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kedamay Tourism Club:

Share

Category