Brookan Travel

Brookan Travel Realize your perfect trip to Ethiopia through us.

ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም!🤲መገኛ   ዲማ በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው ዋና መንገድ ከጠልማ ቀበሌ ምስራቅ አቅጣጫ 12 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ይገኛል...
07/08/2026

ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም!🤲

መገኛ

ዲማ በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው ዋና መንገድ ከጠልማ ቀበሌ ምስራቅ አቅጣጫ 12 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ይገኛል።

ስያሜ

የገዳሙ ስያሜ መነሻ ደብረ ድማህ የሚለው ስም ሲሆን ትርጓሜዉም ራስ /ጭንቅላት/ ማለት ነው፡፡ ይህም በቀደመው ጊዜ ዲማ የጎጃም ማዕከል ነበር የሚለውን ለማመላከት ነው። በሌላ በኩል ዲማ ቀይ ማለት ነው።

የተመሰረተበት ዘመን

ዲማ ጊዮርጊስ የተመሰረተው በ1297ዓ.ም የቀድሞ ስማቸው አባ በኪሞስ በኋላ ግን ተከስተ ብርሃን በተባሉ የሃይማኖት አባት አማካኝነት ነው።

የቅርስ ሀብት

የአጼ ይስሃቅ የወርቅ ጫማ፣ የአጼ ዮሐንስ የወርቅ ዘውድና የወርቅ መስቀል፣ የእባብ ቅርፅ ያለዉ የወርቅ ዘንግ፣ በስዕል የተንቆጠቆጡ የብራና መጻሕፍት፣ የንጉሥ ተክለ ኃይማኖት ጦርና ጋሻ፣ የራስ መኮንን ካባ እና ሌሎች በዋጋ የማይተመኑ ውድ ቅርሶች ባለቤት ነው።

አራቱ ጉባኤዎች እና ሴቶች

በዲማ ቅኔን ጨምሮ የአራቱ ጉባኤዎች ትምህርት ይሰጣል። ከወንዶች በተጨማሪ በእማሆይ ህሪት ደባስ መምህርነት ሴቶች ለብቻቸው የቅኔ ትምህርት ይከታተላሉ።

ታዋቂ ኢትዮጵያውያን

ዲማ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ክቡር ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ የተማሩበት እና በመጽሐፋቸው መቸት ያደረጉበት ቦታ ነው፡፡ ታላቁ ሊቅ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ እና ሌሎች በርካታ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን በዲማ ተምረዋል።

ክብረ በዓል

ታህሳስ 8፣ ጥር 18፣ ሚያዝያ 23 በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ዋና የንግሥ በዓል መከበሪያ ቀናት ናቸው።

ምንጭ፦ ፌስቡክ ላይ የተገኘ ነዉ

You will get the full video on our YouTube channel @ብሩካንነን 🙏❤🙏
05/05/2026

You will get the full video on our YouTube channel @ብሩካንነን 🙏❤🙏

Let's take off from Ethiopia today ..... This is Egyptian Coptic church newly built ❤🙏
02/01/2026

Let's take off from Ethiopia today ..... This is Egyptian Coptic church newly built ❤🙏

Pray and sleep 🙏 !
09/12/2025

Pray and sleep 🙏 !

09/11/2025
፩ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።፪ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።፫ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።፬ በሞት ጥላ መካከል እን...
24/10/2025

፩ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
፪ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
፫ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
፬ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
፭ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
፮ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

Ethiopian Spirituality
27/06/2025

Ethiopian Spirituality

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Brookan Travel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Brookan Travel:

Share

Category