Temu tour and travel

Temu tour and travel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Temu tour and travel, Travel Company, Addis Ababa.

Degu yagera sew
23/03/2022

Degu yagera sew

14/06/2021
12/06/2021
03/05/2020

"ጉድ ሊፈላ ነው ዘንድሮ።"
*************************
የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለህ/ሰቡ ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፤ ሆኖም ሠራተኛው የደምወዝ ጥያቄ በውስጡ ያለው ቅሬታ ጎልቶ ተንተከተከ እና ገነፈለ
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ምዘና እናበደረጃ አወሳሰን ትግበራ ለሰራተኛው የተሰጠው ደረጃ ቀደም ሲል ኦፕሬሽን ዘርፍ ለምሳሌ ፋየር ፋይተር 1 ደረጃ 10፣ ፋየር ፋይተር 2 ደረጃ 11 እያለ ለሁሉም ሠራተኞች ደረጃ ወጥቶ ደብዳቤ ደረሳቸው፤ ደሞ ምንም ባልታወቀ መንገድ ለሌላው መ/ቤቶች የደረጃው ክፍያ ሲተገበር ይሄ ተቋም ምንም የለም፤ አሁንም አንድ ሁለት እያለ ወራቶች አለፈ፤ሠራተኛውም ጥያቄ ማንሳት ጀመሩ ፤ ምንም አጥጋቢ እና በውሸት ተስፋ አሁንም አንድ ሁለት እያለ ወራቶች አለፉ፤ ይባስ ብሎ በዚሁ ተቋም ለግማሽ ሰራተኛ ክፍያ እንዲከፈል ተደረገ "ኦፕሬሽን ዘርፋስ?"
ከዛማ የኦፕሬሽን ዘርፍ ሠራተኞች ላይ ጥያቄ ጫረበት ፤ "ለምን ለእኛ አልተከፈለም፤ ምንድነው ችግሩ?" ጥያቄ እና እሮሮ በጣም በዛ፤ ቀደም ብለው የነበሩት ኮሚሽነር አቶ ነሲቡ ያሲን የ6 ወር አፈፃም ላይ ጥቂት አመራሮችን ሰበሰቡን፤ ጥያቄያችንን ጠየቅን፤ አጥጋቢ ምላሽ አላገኘንም "ስቢልሰርቪስ ደረጃውን ዝቅ አድረጎ ላከልን፤ ከንቲባውጋ ደብዳቤ ልከናል እንዲሁም ወደፌደራል ልከናል ትንሽ ታገሱ" አሉን፤ እኔ ምለው እንዴት ደረጃውን አስቀድመዉ ሰጡን ?በማን ኃላፊነት ስቢልሰርቪስ የማያውቀው ደረጃ? እኔ በጣም አዘንኩ፤ ከዛም ኮምሽነሩ አልቆዩም ከሥራ ገበታቸው ተነሱ፤ ሽሽት ይመስላል ፤ ሌላ ኮሚሽነር መጣ፤ ጥያቄያችንን ቀጠልን፤ ስቢልሰርቪስ ሂዱ አሉን ጉዳዩ ከሳቸው በላይ ነው መሰለኝ እኛም ሄድን፤ እዛም ሄደን ጠየቅን ያልተባለ ጉድ የቀረን ነገር የለም ፤ ብዙ ችግር እና ጉድ ያለበት መ/ቤት፤ እኔ አፈርኩ ፤

ጉድ ያስባለውና የተሰራው ስህተት
********************************
1ኛ፦ምዘና እና በደረጃ አወሳሰን ራሱን የቻለ መ/ቤት እያለ ተቋሙ በማያገባው ገብቶ ደረጃ ማውጣቱ ፤

2ኛ፦ በዚህ ምዘና እና በደረጃ አወሳሰን ላይ የነበሩት ኮሚቴዎች ይህንኑ ደረጃ አወሳሰን ትግበራ ለማጥናት ናዝሬት አዳማ ሆቴል VIP ቦታ ተዘጋጅቶላቸው የመንግስትን ገንዘብ ከፍተኛ ወጪ በማድረግ፤ "ኮሚቴዎች የኮሚሽኑ ቢሮዎች አይበቃም ነበር? ለማንኛውም ማስረጃችሁን አዘጋጁ ።"

3ኛ. ስቢልሰርቪስ ህዳር ወር ላይ ወስኖ የላከውን የምዘና እና ደረጃ አወሳሰን እንዲሁም ክፍያ እንዴት እስካሁን ለሠራተኛው ግልፅና ተግባራዊ አልሆነም፤ "የሰው ኃይል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ መልሶትን/ማስረጃዎትን ያዘጋጁ።"

4ኛ. አዲስ የተቀጠሩ ሠራተኞች ከመቀጠራቸው በፊት ማስታወቂያ ላይ ደረጃ X (10) ሲሆን እንዴት ሆኖ የ6 ወር የሙከራ ጊዜ የተሰጣቸው ደብዳቤ ላይ ደረጃ VII (7) ሆነ? "ለዚኛውም የሰው ኃይል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ መልሶትን/ማስረጃዎትን ያዘጋጁ።"

5ኛ. ተቋሙ የሚመራው (የሚተዳደረው) በስቢልሰርቪስ የሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ መሆኑ እየታወቀ እንዴት በየትኛውም ሀገር (ዓለም ውስጥ) ተሰምቶም ታይቶም የማይታወቅ "ፓራ-ሚሊቴሪ" የሚባል ደንብ አምጥታችሁ ሠራተኛውን ታወዛግባላችሁ?

*እነዚህ ብቻ አይደለም ያለው ችግር ፤ በእውነት ጥቂቱን ነው ያነሳውት፤ ሰራተኛውን የሚነካውን ብቻ ነው የዘረዘርኳቸው እሱም ይሄ ብቻ አይለም።

*እንዲህ እንዲህ እያልን ይኸው ዛሬ ላይ ደረስን አሁንም ተስፋ አንቆርጥም፤ የምንጠይቀውም ብዙ ነገሮች አሉ፤

"አዲስ ነገር ካገኘን መረጃውን እንዘግባለን ..

ጥያቄያችን አላለቀም ይቀጥላል።

*ለሠራተኞቻችን የማስተላልፈው መልዕክት የገባነው ቃል-ኪዳን አለ እሱን እያሰብን በተጨማሪም ሥራችን ሰብአዊነት ያለው በመሆኑ ሕብረተሰብን ከምንጊዜውም በላይ በሙያችን ማገልገል አለብን፤ ምክንያቱም እኛ የሕዝብ ሕዝብም የኛ በመሆናቸው፤ አደጋ ሥራ ላይ ቅድሚያ ምናገኘው ሕዝብን ስለሆነ ፤ አብረን ምንሠራው ግዴታ ከሕዝብጋ ስለሆነ፤ አደራችሁን ሞራላችሁ አይሙት፤ በቅርብ ቀን ጥያቄያችን መልስ እናገኛለን በርቱ አደራ እላለሁ ።
የደረስንበትን በቅርብ ቀን ይጠብቁ
like እና share ያርጉ፤ ይሄንን ፔጅ ለጓደኞቿቹ Invite ያርጉ። ሀሳብ አስተያየታቸውን comment ላይ ያስቀምጡ።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251939908001

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Temu tour and travel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category