22/09/2026
በቅርቡ የትግራዩ ጳጳሱ ላይ ስለተሰራጨው ቪዲዮ ሙስሊሞች ሲሳለቁ አየሁኝ
። በቪዲዮው ላይ የታየው ነገር እውነት ከሆነ፣ ዝሙትን መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአት ይለዋል። የእግዚአብሔርም አገልጋይ ከሆነ ኃላፊነቱ የበለጠ ነው። ስለዚህ ኃጢአትን ኃጢአት አይደለም እያልኩ አይደለም።
ግን የእሳቸዉ ኃጢአት በካሜራ ተቀረጸ፤ የእኛስ?
ያልተቀረጸ ኃጢአት ንጽሕና አይደለም።
ሰው ያላየው ኃጢአት ከእግዚአብሔር አልተሰወረም።
እኛ ቪዲዮ ስላልወጣብን ከዚህ ሰው የተሻልን አይደለንም።
ኢየሱስ በዝሙት የተያዘችውን ሴት ወደ እርሱ ሲያመጡ፣ ኃጢአቷን መልካም ነው አላለም። ነገር ግን ድንጋይ ይዘው የቆሙትን፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት በመጀመሪያ ድንጋይ ይወርውርባት” አላቸው። ዮሐንስ 8፥7
ዛሬ እሳቸው ላይ የተነሱትን የሚያፌዙትን እግዚአብሄር ሀጥያት ግንባራቸው ላይ ቢለጥፍ ከቤት የማይወጡ ናቸው ዳሩ ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር ሀጥያት ነው የሰሩት እግዚአብሄር ይቅር ይበለን ለኛ ለፈራጆቹም ለሳቸውም!
ወደ ሚያፌዙት ስንሄድ በቁርአን አስተምህሮ መሰረት እንደዚ አይነት ድርጊት ነብይ የሚያደርግ ነው
#ነብዩ መሀመድ በሐፍሳ ቤት ውስጥ ከባርያው ወይም ከሰራተኛዋ ማርያ ጋር ተኝቶ ነበር።
ሐፍሳ ገብታ አይታው በገዛ ቤቷና አልጋዋ ላይ ዝሙት በመፈፀሙ ፣ ተናደደች።
እርሱም “ ለአይሻ አትናገሪ” እያለ ይለምናት ነበር ።
ከዛ ይሄንን ቁርአን አንቀፅ አወረድኩኝ አለ
ቁርአን 66:1 (ሱራ አት-ተህሪም)
“ነቢይ ሆይ፣ አላህ ያፈቀደልህን ነገር ለምን ትከለክላለህ? ሚስቶችህን ለማስደሰት ትፈልጋለህ? አላህ ምህረት ያደርጋል፣ መሃሪ ነው።
ስለዚ ሙስሊሞች ለናንተ ፅድቅ ነው እንጂ ለፌዝ ሚቀርብ አይደለም !!
የእሳቸዉ ኃጢአት ተቀረጸ፤ ያንተ አልተቀረጸም።
ይህ ግን አንተን ቅዱስ፣ እሱን የማይድን አያደርገውም።
የሰውን ውድቀት መዝናኛ አናድርግ።
ለንስሐው እንጸልይ፤ ለተጎዱትም ሰዎች ፈውስን እንመኝ።
ሰዉ የሚድነዉም የሚቆመዉም በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ነዉ በራስህ ወዳቂ ነህ
በድጋሜ እግዚአብሄር ይቅር ይበለን ምህረቱን ይላክልን እንደ ቸርነቱ እንጂ እንደበደላችን አይቁጠርብን #እፎይ #ኦርቶዶክስ