Fuye Promotion

Fuye Promotion travel with fuye 🌍✈️ 🕋
𝙿𝚛𝚘𝚞𝚍 𝚝𝚘 𝚋𝚎 𝙴𝚝𝚑𝚒𝚘𝚙𝚒𝚊𝚗 🇪🇹 🇰🇪 🇦🇪 🇹🇿 🇸🇨 🇿🇦 🇶🇦 🇴🇲 🇹🇭 🇨🇳 🇮🇩 🇭🇰 🇯🇵
follow my Instagram page

12/12/2025

ታይላንድ ላይ ያለውን Walking Street ታውቁታላቹ?

BookYour !💚 💛❤️🇧🇷🇩🇪🇮🇹🇫🇷🇹🇷🇳🇱🇰🇪🇸🇨🇦🇪🇨🇳🇪🇸🇺🇸+251 911618965..|.. +251 988 13 00 30  Awlo Business Center 3rd Floor Instagram -...
26/08/2025

BookYour !💚 💛❤️
🇧🇷🇩🇪🇮🇹🇫🇷🇹🇷🇳🇱🇰🇪🇸🇨🇦🇪🇨🇳🇪🇸🇺🇸
+251 911618965..|.. +251 988 13 00 30
Awlo Business Center 3rd Floor
Instagram - instagram.com/adpictures_ethio
Facebook - fb.com/Adpicturesethio
Stay tuned our Page



Feel the Moment Forever…

.p.h.iiiii 🔥
23/08/2025

.p.h.iiiii 🔥

አስቀድሞ ክርስቶስን የካደ ሰው ሲሆን፤ ገንዘብም ለማከማቸት ሲልም ብዙ ይተጋ ነበር፡፡በአንድ ወቅት በደማስቆ ከተማ ወዳለው የምሥራቃዊው ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ገባ፡፡ የበዓል ቀን ነ...
23/08/2025

አስቀድሞ ክርስቶስን የካደ ሰው ሲሆን፤ ገንዘብም ለማከማቸት ሲልም ብዙ ይተጋ ነበር፡፡

በአንድ ወቅት በደማስቆ ከተማ ወዳለው የምሥራቃዊው ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ገባ፡፡ የበዓል ቀን ነበርና ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ሳሉ በኋላ በሰማዕትነት ያለፈው ቅዱስ እንጣዎስ ገብቶ ንዋያተ ቅዱሳቱን ሁሉ ማቃጠል ጀመረ፡፡ ቅዱስ መስቀሉንም ሰበረ፡፡
በዚህ ጊዜ በሰማይ ውስጥ የእሳት ፍላፃዎችን ከሃዲዎችን ሲነድፏቸው አየ፡፡ እርሱንም የቀኝ ጎኑን አንዲት ፍላፃ ስትነድፈው ተጨንቆ ላቡ ተንጠፈጠፈ፡፡ በጭንቅ ሀሳብ ውስጥም ሆኖ “የቅዱስ ቴዎድሮስ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አመንኩብህ” አለ፡፡ ከእግዲህም ዳግመኛ ሌላ አምላክ እንዳያመልክም በልቡናው ቃል ገባ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ያሉ ሰዎችም በእርሱ የሆነውን አላወቁም ነበር፡፡ ነገር ግን ጨኸቱንና የሚናገረውን ሰምተው አደነቁ፡፡

እንጣዎስም ኤልያስ ወደሚባል ጳጳስ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገረው፡፡ የክርስትና ጥምቀትንም ያጠምቀው ዘንድ ለመነው፡፡ ጳጳሱም በውኃው ላይ ሲጸልይ የብርሃን ምሰሶ እንደ ቀስተ ደመና ሆኖ ሕዝቡ ሁሉ እያዩት ወረደ፡፡ እንጣዎስም ተጠመቀ፡፡ በተመለከቱት ተአምር አምነውም 10,798 ሰዎች ከእርሱ ጋር አብረው ተጠመቁ፡፡ ቅዱስ እንጣዎስም “እነሆ ይህን እያደነቅሁ ሳለ ራእይን ተመለከትኩ፡፡ ብርሃንን የለበሰች ሴት እጄን ያዘችኝና ወስዳ ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰችኝ፡፡ ወደ መሠዊያውም አቅርባኝ ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ተዘጋጀሁ፡፡ በመሠዊያውም ውስጥ ነጭ በግን አየሁ፡፡ ካህኑም በዕርፈ መስቀል በሠዋው ጊዜ ደሙ በጽዋው ውስጥ ተጨመረ፡፡ ከእርሱም የክርስቶስን ሥጋና ደም በተቀበልኩ ጊዜ ሥጋው ንጹሕ ኅብስት ደሙም ንጹሕ ወይን ሆነ” ብሎ ያየውን ነገራቸው፡፡

በደማስቆ ጎዳና ሲጓዝም አስቀድመው በከሀዲነት የሚያውቁት ሰዎች ያዙትና ወደ ንጉሡ ወሰዱት፡፡ ንጉሡም “በክርስቶስ ማመንህን ተው” አለው፡፡ ቅዱስ እንጣዎስም ፈጽሞ ጌታችንን እንደማይክደው በነገረው ጊዜ ንጉሡ እጅግ በመቆጣት ጥርሶቹ እስኪረግፉ ድረስ አፉን አስደበደበው፤ ደሙም በምድር ላይ ፈሰሰ፡፡ እህል ውኃ ሳያቀምሱት በግንድ ላይ ለሰባት ቀን አሠሩት፡፡ ወደ ውጭ አውጥተውም ዲን፣ ሙጫ፣ ዝፍት፣ ከስብና ሌሎችንም የሚቃጠሉ ነገሮችን ቀላቅለው እሳት አንድደው እንጣዎስን ጨመሩት፡፡ እርሱም በእሳቱ ውስጥ ሆኖ ሲጸልይ ወታደሮቹ አዩት፡፡ እሳቱም ምንም ሳይነካው፣ መልካም መዓዛ ያለው ሽታ ይወጣው ነበርና በመደነቅ ወደ ንጉሡ ወሰዱት፡፡ ንጉሡም “ምትሐት መቼ ተማርክ” አለው፡፡ ቅዱስ እንጣዎስም ንጉሡን “ክብር ምስጋና ይግባውና እኔስ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አሳፍርሃለሁ” አለው፡፡

በዚህም ጊዜ ንጉሡ ቁጣን ተመልቶ የቅዱስ እንጣዎስን ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ቅዱሱም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ሲጸልይ “ከእስጢፋኖስና ከጊዮርጊስ ጋር ታርፍ ዘንድ አገልጋዬ በሰላም ወደኔ ና፡፡” የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ፡፡ ቅዱስ እንጣዎስም ይህንን ድምጽ ከሰማ በኋላ ጸሎቱን ጨርሶ በፍጹም ደስታ ይሰይፉት ዘንድ አንገቱን አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ወታደሮቹም አንገቱን ሰየፉትና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ከሥጋውም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ዳግመኛም የቅዱስ እንጣዎስ ወንድሙ ቅዱስ አክራጥስ ምስክር ሆኖ በዚህች ዕለት ዐርፏል፡፡ ራሳቸውን ለክርስቶስ ፍቅር አሳልፈው የሰጡ ሰማዕታት አብነት ሆነዋቸው ገዳማውያን ዓለምን ንቀው መንነዋል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከታቸው ያድርብናል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

22/08/2025
“ቀድሞ ልጇን ተነሣ፣ አረገ፤ እንደገናም ይህን ዓለም ለማሳለፍ ተመልሶ ይመጣል” እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል። አሁን ደግሞ እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ በማስተ...
22/08/2025

“ቀድሞ ልጇን ተነሣ፣ አረገ፤ እንደገናም ይህን ዓለም ለማሳለፍ ተመልሶ ይመጣል” እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል። አሁን ደግሞ እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን አይደለምን? “ኑ! በእሳት እናቃጥላት” ብለው መጡ፡፡ ከመካከላቸው ታውፍንያ የተባለ አይሁዳዊ ስጋዋን ያለበትን አልጋ ሸንኮር ተራምዶ ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጠውና ተንጠልጥለው ቀሩ። በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በተአምር የተቆረጡ እጆቹን ፈውሳዋለች። በዚያ ጊዜም መልአክ እግዚአብሔር እመቤታችንና ቅዱስ ዮሐንስን ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣቸው ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችን አስከሬን በገነት መኖሩን ነገራቸው።

ሐዋርያትም ዮሐንስ ይህን ክብር አይቶ፣ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ጀምረው በ14ኛው ቀን ጌታችን ስጋዋን ሰጥቷቸው በታላቅ ዝማሬና ውዳሴ በጌቴሴማኒ ቀበሯት። በሶስተኛው ቀን ተነስታ ስታርግ ቅዱስ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል። ያን ጊዜም ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው እርሱ የቀረበት መስሎት በፊት የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ በሀዘን ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው። እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሓዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ፣ ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራችው አዝዛው ለምልክት ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ሐዋርያትም ቅዱስ ቶማስ ስለእመቤታችን ሲጠይቃቸው አጊኝተን ቀበርናት አሉት። እርሱም የያዘውን ያውቃልና “አይደረግም! ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?” አላቸው።

ቅዱስ ጴጥሮስም ተቆጥቶ “አንተ እንጂ፤ ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ። አሁንም አታምንምን?” ብሎ ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ቢሔድ አጣት፤ ደነገጡ፡፡ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች” ብሎ ሰበኗን ሰጣቸው። ለበረከት ቆራርጠው ከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል። በዓመቱ ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን እመቤታችንን መንበር፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፤ ቅዱስ እስጢፋኖስን፤ ገባሬ-ሠናይ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸው የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል። ሐዋርያዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን ታላቅ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት ተርታ አስገብታ ትጾማለች። ከብርሃነ ትንሣኤዋ ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡ ገዳማውያንም በጾምና በጸሎት ይህን በረከት ያገኛሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ካለን ላይ ለተቸገሩ በማካፈል ለነፍሳችን ስንቅን እንያዝ

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቤተ ክርስቲያን “እንቁዎቼ” ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ናት፡፡ ቅድስቷ ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ስትሆን ቅድ...
21/08/2025

ቤተ ክርስቲያን “እንቁዎቼ” ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ናት፡፡

ቅድስቷ ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ስትሆን ቅድስት እንባ መሪና ትባላለች፡፡ “እንባ መሪና” የወንድ ስም ነው የእርሷ ስም “መሪና” ቢሆንም በተለየ ታሪኳ ምክንያት በወንድ ስም ተጠርታለች፡፡

ቅድስት መሪና ገና ልጅ ሳለች እናቷ ማርያም ስለሞተችባት ያሳጋት ደግ አባቷ ነው፡፡ አሥራ አምስት ዓመት ሲሆናትም “ልጄ! እኔ ወደ ገዳም ስለምሔድ አንቺን መልካም ባል ላጋባሽ” አላት፡፡ ቅድስት መሪናም “የራስህን ነፍስ አድነህ እንዴት የእኔን ትተዋታለህ? እኔም እመንናለሁ” አለችው፡፡ አባቷ የተናገረችው ከልቧ እንደሆነ ሲያውቅ “ልጄ! በአካባቢው ያለው ገዳም ሁሉ የወንድ ብቻ ነውና አይሆንም” አላት፡፡ እርሷ ግን “አባቴ! ግዴለህም፣ ስሜን እንደ ወንድ ቀይረህ፣ አለባበሴንም ለውጥ” አለችው፡፡

አባትና ልጅ ሃብት ንብረታቸውን ሸጠው ለነዳያን አካፈሉ፡፡ በፍጹም ልባቸውም መነኑ፡፡ በደረሱበት ገዳም ቅድስት መሪና በወንድ ስም “እንባ መሪና” በሚል ገባች፡፡ ቀጣዩ ሥራዋ እንደ ወንዶች እኩል መስገድ፣ መጾምና መጸለይ ነበር፡፡ ቅድስት መሪና በገዳም ስትኖር ማንም በእርሷ አይፈተንም፤ አያውቋትምና፡፡ እርሷ ግን ወጣት ሴት ሆና በወንዶች ገዳም ጸንታ መቆየቷ መልአካዊ ኃይልንም ይጠይቃል፡፡ በተጋድሎዋ ወንድሞች መነኮሳት ይደነቁባት ነበር፡፡ ጃንደረባ ናት ብለው ስላሰቡ ጺም ባለማውጣቷና በድምጿ መቅጠን አልተጠራጠሩም፡፡ አባቷ ምስጢሩን ያውቃልና ታሞ ከማረፉ በፊት አበ ምኔቱን ጠርቶ “ልጄን ወደ ከተማ እንዳትይልኩብኝ አደራ!” አላቸው፡፡ ያም ሆኖ አንዳንድ መነኮሳት ቅሬታ በማንሳታቸው ወደ ከተማ ተላከች፡፡

በዚህም ቀን ባደሩበት ቤት አንድ ጐረምሳ ገብቶ የአሳዳሪውን ልጅ ከክብር አሳንሷት፣ ወጣቱ መነኩሴ አባ እንባ መሪና ነው በይ ብሏት ሔደ፡፡ ከሦስት ወራት በኋላ የዚያች ዘማ ሴት ጽንስ በታወቀ ጊዜ ለአባቷ “አባ እንባ መሪና እንዲህ አደረገኝ፡፡” አለችው:: አባት መጥቶ እየጮኸ መነኮሳትን ተሳደበ:: አበ ምኔቱ ግራ ተጋብቶ ቢጠይቀው “የአንተ ደቀ መዝሙር እንባ መሪና ልጄን ከክብር አሳነሳት” አለው፡፡ አበ ምኔቱ ቅድስቲቱን ጠርቶ ቁጣና እርግማንን አወረደባት፡፡ ሴት ነኝ ብላ ከመከራከር ይልቅም ተንበርክካ “ማሩኝ ወጣትነት ቢያስተኝ ነው?” አለቻቸው፡፡ ተቆጥተው ዕለቱን እየገፉ ከገዳም አስወጧት፡፡ ከባድ ቀኖናም ጫኑባት፡፡ ከስድስት ወራት በኋላም የእርሷ ልጅ ነው የተባለ ሕፃን አምጥተው ሰጧት፡፡ ይህኛው ግን ከባድ ፈተና ሆነባት፡፡ እንዳታጠባው አካሏ በገድል ደርቁአል::

ለሕፃኑ ከእረኞች ወተት እየለመነች አሳድጋው ወደ ገዳሙ ከከባድ ቀኖና ጋር ተመልሳ በትጋት እያገለገለች ሰላሳ ሰባት ዓመታት አለፉ፡፡ ሕፃኑም አድጐ ደግ መናኝ ወጣው፡፡ በመጨረሻ ቅድስት መሪና ታማ ዐረፈች፡፡ ሊገንዟት ሲቀርቡ ሴት ናት፡፡ እጅግ ደንግጠው አበ ምኔቱን ጠሩት፡፡ በዙሪያዋ ከበው እንባቸውን አፈሰሱ፡፡ ሥጋዋን በክብር ገንዘው፣ በአጐበር ጋርደው፣ በራሳቸው ተሸክመው “ስለ ቅድስት መሪና ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን?” ሲሉ ዋሉ:: ድንገት ግን ከተባረከ ሥጋዋ “ይቅር ይበለን” የሚል ድምጽን ሰምተው ደስ ብሏቸው ቀበሯት፡፡ ገዳማውያን ዓለምን ጥለዋት ቢሔዱም በምናኔ የሚገጥማቸው መከራም የበረታ ነው፡፡ ነገር ግን በጸሎትና በትጋት ያልፉታል፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡      

ካለን ላይ ለተቸገሩ በማካፈል ለነፍሳችን ስንቅን እንያዝ

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለ ታላቅ አባትእግዚአብሔር ለትልቅ ስራ ያጨው እስራኤልን ከ215 ዓመታት ባርነትና ከ430 ዘመን ስደት በኋላ መርቶ ሀገራቸው ያስገባ ታላቁ ነቢይ ነው፡፡ 40 ቀ...
20/08/2025

ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለ ታላቅ አባት

እግዚአብሔር ለትልቅ ስራ ያጨው እስራኤልን ከ215 ዓመታት ባርነትና ከ430 ዘመን ስደት በኋላ መርቶ ሀገራቸው ያስገባ ታላቁ ነቢይ ነው፡፡ 40 ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረ ድንቅ አባትም ነው፡፡ የአምስት ዓመት ሕጻን ሳለ በሁሉም ዘንድ እጅግ የሚፈራውን ፈርኦንን በጥፊ መታው፡፡ ለንጉሳቸው ትልቅ ቦታ በሚሰጡት ግብጻውያን ዘንድ ድርጊቱ ሕጻን ቢሆንም የሚያስገድል ነበር፡፡ ይሁንና ከውሃ አጊኝታ ልጇ አድርጋ የምታሳድገው የፈርኦን ልጅ ቴርሙት ሕጻን ስለ ሆነ ክፉና ደጉን አይለይም፣ እሳት እንኳ በፊቱ ቢቀመጥ አንስቶ ይበላል ብላ ተከራከረች፡፡ እንደተባለውም የጋለ ፍም ከፊቱ ሲቀመጥ አንስቶ በመጉረሱ ምላሱ ኮልታፋ ቢሆንም ነፍሱ ግን ከሞት ተርፋለች፡፡  ከ12 የያእቆብ ልጆች የእስራኤል ነገዶች አንዱ ከሆነው ከሌዊ ወገን የሚወለደው ሊቀ ነቢያት ሙሴ የስሙ ትርጓሜ “ከውሃ የተገኘ” ማለት ነው፡፡ 

ቅዱስ ዻውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ በምዕራፍ 11÷24 እንዳለው “በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና” አንድ ግብጻዊ እስራኤላዊ ወገኑን ሲመታ ቢያየው ገድሎ አሸዋ ውስጥ ቀበረው፡፡ በፈርኦን ቤተ መንግስት ቢያድግም ወገኖቹ እስራኤልን አልረሳም፡፡ እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው የወገኖቹን ታሪክና ማንነቱን ትነግረው ነበርና 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ፡፡ በግብጻዊው ላይ ያደረገው ነገር እንደተሰማ ሲያውቅም ወደ ምድያም ሸሸ:: በምድያምም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ፣ ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ልጆች አፈራ:: በ80 ዓመቱ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው፡፡ ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው፡፡

አንደበቱ ኮልታፋ ቢሆንም ወንድሙ አሮን በንግግር እያገዘው ግብጻውያንን በዘጠኝ መቅሰፍትና በአስረኛ “ሞተ በኩር” መትቶ እስራኤላውያንን ነጻ አውጥቷል፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ውስጥም ትልቁን የመሪነት ሚና የተወጣ ሲሆን፣ ባሕር ከፍሎ በደረቅ ያሻገራቸው፣ ለህዝቡ መና ከደመና ያወረደ፣ አለት ከፍሎ ውሃ ያፈለቀ፣ ሌቱን በብርሃን ምሰሶ ቀኑን በሰባት ደመናት ጋርዶ የመራቸው፣ ጠላቶቻቸውን የደመሰሰላቸው እግዚአብሔር መሳሪያው እንዲሆን የመረጠው ታላቅ አባት ነው፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳው እስራኤላውያን ነጻ ስላወጣቸው አላከበሩትም፤ ይልቁንም ደግመው ደጋግመው አስከፍተውታል፡፡ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ “አሰርቱ ትዕዛዛትን” ይዞ ከተራራው ሲወርድ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አሳዝነው ጠበቁት፡፡

ወንድሙ አሮንን አስገድደው ጣኦት አሰርተው ሲያመልኩ፣ ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ በደስታም ሲጨፍሩ ነው ያገኛቸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር “እነርሱን ላጥፋቸውና በሌላ ታላቅ ሕዝብ ዘንድ ልሹምህ” ሲለውም፣ “እነርሱን ከምታጠፋቸው እኔን ከጻፍከኝ ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለ ታላቅ አባት ነው፡፡ በጽላቱ ጣኦቱን መትቶት ሲሰበርም በድጋሚ ጽላቱን በእጁ ሰርቶ አምጥቶ በእግዚአብሔር ጣቶች 10ቱ ትዕዛዛት ተጽፈዋል፡፡ በረከቱ ትደርብንና በየትኛውም ምቾት ውስጥ ብንሆን፣ ክብራችን ከፍ ቢልም ወገንንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አለመርሳት ከአባታችን ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ እንማራለን፡፡ ለዚህ ነው ባለን አቅም ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና የምንለው፡፡       

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲ...
19/08/2025

ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ

ቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲማሮስ “በራማ ሰማይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡” ይለናል፡፡ ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 6÷3 ላይም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሏል፡፡

ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም “በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚህ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በኾነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ” በማለት አስተምሯል፡፡ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ “ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ በሚበርቅ፣ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ” ይላል፡፡

በ720 ዓ.ዓ ዐሥሩ ነገደ እስራኤል ሲማረኩ ጦቢት የተባለ ጻድቅ ሰው ዐብሮ ተማርኳል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ይህን ጦቢትን የተራዳ መልአክም ነው፡፡ በመጽሐፈ ጦቢት 2÷14 እንደተጻፈው ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ኩስ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “በጐነትህ ምጽዋትህ ያዳነህ ወዴት ነው?” በማለት ስትናገረው ዐዝኖ ሞትን ተመኘ፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም አይኑን ሲፈውሰው፣ በላይዋ ላይ ያደረ ጋኔን ባሎቿን ይገድልባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ያደረባትን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፡፡   

የመላዕክት ተራዳኢነት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ስፍራ አለው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም ከዚህ በኋላ ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ ብሏቸው ተሰውሯል፡፡ ጦቢት 12÷15፡፡ ፈታሔ ማኀፀን ወሰፋድል። መወለድ መንፈሳዊ። ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል። የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ በእግዚአብሔር ስለተሾመ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ቅዱስ ሩፋኤል በዚያ አይታጣም፡፡ በተለይ በባላገር ያሉ ሴቶች በምጥ ጊዜ ሁሉ መልክአ ሩፋኤል በአንገታቸው ያነግታሉ፣ ይጸልያሉ፣ የተጸለየበትንም ጸበል ይጠጣሉ፤ በፍጥነትም ይወልዳሉ። በየወሩ በ13 ቀን መታሰቢያ በዓሉ የሚከበር ሲሆን ጳጉሜ 3 ደግሞ ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በረከትና ረድኤቱ አይለየን፤ ምልጃው ይጠብቀን፡፡ ገዳማውያንም ይህን ተራዳኢነቱን በመታመን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fuye Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Fuye Promotion:

Share

Category