08/02/2026
#ወሎ ወሎ እኮ ነው
#ጓሳ
#መንዝ
ይንን ቦታ የሚገኘው ወሎ ሰው ተቀባይ ህዝብ ባለበት
እስልምናን ክርስትናን በአንድ አክብረው ተከባብረው አንድነትን ፍቅርን ለአለም ማሳየት የቻሉ የአንድነት እና የመተሳሰብ ተምሳሊት ከሆነችው ወሎ ውስጥ ነው።
ወሎ እንደ ዛሬው ሳይሆን ክፍለሀገር ተብሎ በሚጠራበት እና ወሰኑም ቀይ ባህር በነበረበት ዘመን ትንንሺ ሀይቆች ከሚባሉት አሁን የለማውን ለጎን እና ሀይቅ እስጢፋኖስ፣ አሸጌን ጨምሮ በወሎ ክፍለሀገር የሚገኙ ሚስጥርን እና ውበትን በአንድ ሰንደው የያዙ እና የእሮሀን ስልጣኔ(ላሊበላን) ለአይምሮ የሚከብድ የስነ ህንፃ ስልጣኔን ለአለም ያስደመሙ እና በሀገረ መንግስት ምስረታ እና ወራሪን መመከት የቻሉ የዋግ ጀግኖች የእህል ክምር እንደተራራ ጎልቶ የሚታይበት እራያ እራዩማ የውበት መፌለቂያነቱን ለብቻው የያዘ የሚመሥል ሀገር
የባቲ ገበያና የሰንበቴን ተወዳጅ ገበያን የያዘ አሰብን እንደ ሀገር ተቀንሶበት በትግስት ነገ ሌላ ቀን ነው ይመጣል ሰው ከእናቱ ቤት አይቀርም ለግዜው ነው ብሎ የትእግስት እና የአስተዋይነትን ጥግ ማሳየት ለሚያውቀው ለዎሎ ወገኔ እማ ከዚህም ላቅ ያለ ልማት ያሻዋል።
ለማንኛውም እደግመዋለሁ የአሰብ ባለቤት ለሆነ ህዝብ ለጎ ሀያቅ ላያስገርም ይችላል።
ቢሆንም ግን ይህ ስፍራ በአለው ሁኔታ ለደሴ ከተማም በቅርብ እርቀት ስለሚገኝ መልማቱ ለቱሪዝሙ ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል እና ማመስገን ወደድኩ።
ምስጋናማ ይገባል።
በተጨማሪም
ይህ የገበታ ለሀገር የመንዝ ጓሳን እና የሰሜን ተራሮችን እና መሠል መዳረሻዎችን መመልከት ቢቻል ጥሩ ነበር
በእርግጥ መንዝ ጓሳ መንገዱን መሥራት ያስፈልጋል ግን የጓሳ ጥብቅ ስፍራ ለማህበረሰቡ ካሉት ሀብቶች ሁሉ አብዝቶ ይወደዋል በጎብኝወችም እጅግ ተመራጭ ነው
ታዲያማ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የመንዝ ጓሳን እና አንኮበር ቤተመንግስትን ቢመለከትልን አብዝተን ለማመስገን እንወዳለን
ክብረት ይስጥልን።