Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ

Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ This page promotes and offers History ,Culture, Religion, Architecture, Wildlife, Scenic and other Interesting things in . Love and peace �

We consult, arrange and conduct your next trip! Contact us for your domestic travel arrangements.

12/04/2026
ኢትዮጵያ በድጋሚ የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ሳይንሳዊ ግኝት አስተናግዳለች።2.6 ሚሊዮን ዓመታት  አዲስ የሰው ዘር ቅሪተ አካል በአፋር ክልል ተገኘ::ኔቸር የሳይንስ መፅሄት በዛሬው ዕትም...
21/01/2026

ኢትዮጵያ በድጋሚ የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ሳይንሳዊ ግኝት አስተናግዳለች።
2.6 ሚሊዮን ዓመታት አዲስ የሰው ዘር ቅሪተ አካል በአፋር ክልል ተገኘ::
ኔቸር የሳይንስ መፅሄት በዛሬው ዕትም ይፋ ሆኗል::
ጥር 13/2018ዓ.ም

በአፋር ክልል በሚገኘው ሚሌ-ሎጊያ መካነ ቅርስ፣ ከዚህ ቀደም ተገኝቶ የማይታወቅና "ፓራንትሮፐስ" (Paranthropus) የተሰኘ የ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያለው የቅድመ ሰው ዘር ቅሪተ አካል ተገኝቷል።

🔎 ግኝቱን የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

👉 አዲስ ግኝት፦ ይህ የቅድመ ሰው ዘር ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ከተገኙት ዝርያዎች የተለየና አዲስ መሆኑን ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።

👉 የጥናት ቡድኑ፦ ግኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ዝነኛ በሆኑት ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ (ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ) በሚመራ ቡድን የተገኘ ነው።

👉 የኢትዮጵያ ኩራት፦ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደገለጹት፥ ግኝቱ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ዳግም ያረጋገጠ ነው።

👉 የተለየ ባህሪ፦ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ እንዳሉት፥ ይህ "ፓራንትሮፐስ" የተሰኘው ዝርያ አካባቢን የመላመድ ከፍተኛ ችሎታ የነበረው በመሆኑ በተለያዩ አካባቢዎች ይኖር እንደነበር በጥናቱ ተረጋግጧል።

👉 ፋይዳው፦ ይህ ግኝት ለሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት እና ለዲፕሎማሲ እንቅስቃሴያችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ወጣት ተመራማሪዎችን በዘርፉ ለማፍራት ትልቅ መነሳሳት ይፈጥራል ተብሏል።

#ኢትዮጵያ #አፋር #ቅርስ #የሰውዘርመገኛ

 : Where Time Whispers and Colors Breathe!Step into Dire Dawa—Ethiopia’s eastern gateway where history, trade, and soul ...
16/01/2026

: Where Time Whispers and Colors Breathe!

Step into Dire Dawa—Ethiopia’s eastern gateway where history, trade, and soul collide. Wander through vibrant markets alive with spice-scented air, touch the legacy of the iconic railway, sip coffee brewed with ancestral pride, and taste flavors born of crossroads culture. Just beyond the city, the Rift Valley unfolds in dramatic beauty, making Dire Dawa not just a destination, but a feeling—warm, timeless, and unforgettable.



Visit Ethiopia, Exotic Ethiopian Adventures
via Dawit Argaw Mekonen

Exciting news! 🎉 Gifaataa, the unique New Year celebration of the Wolaita people, has been inscribed on UNESCO’s Intangi...
10/12/2025

Exciting news! 🎉

Gifaataa, the unique New Year celebration of the Wolaita people, has been inscribed on UNESCO’s Intangible Cultural Heritage list.

The recognition was announced at the 20th Session of the Intergovernmental Committee for the Safeguarding of the Intangible Cultural Heritage, underway in New Delhi, India.

Congratulations to all!

መልካም የመስቀል በአል ወዳጆቼ!!በሀገራችን የተለያዬ ቦታ የምትኖሩ ወዳጆች  በሙሉ መልካም ጊፋታ ፣ ያሆዴ ፣ መስቀላ ፣ ጎፋ ማስቃላ ዮ ፣ ማሽቃሮ ፣ ጋሪ ዎሮ ፣ ቡዶ ኬሶ ፣ ባላ ካዳቤ ፣...
27/09/2025

መልካም የመስቀል በአል ወዳጆቼ!!

በሀገራችን የተለያዬ ቦታ የምትኖሩ ወዳጆች በሙሉ መልካም ጊፋታ ፣ ያሆዴ ፣ መስቀላ ፣ ጎፋ ማስቃላ ዮ ፣ ማሽቃሮ ፣ ጋሪ ዎሮ ፣ ቡዶ ኬሶ ፣ ባላ ካዳቤ ፣ ሄቦ ፣ መሳላ ... ይሁንላችሁ !!

#መስቀል #ሳባ #ኦርቶዶክስ

  እና  #ኢትዮጵያ (ምርጥ ትንታኔ)🦃🦃🦃🦃🦃🦃🦃🦃🦃መስከረም ወር ላይ የሚከሰቱ እንግዶች ሳይሆኑ አመቱን ሙሉ አብረውን የሚቆዩ ፣ በተፈጥሮ ሂደት የላባቸው ቀለም የሚቀየር ቤተኛ አእዋፋት ስለ...
24/09/2025

እና #ኢትዮጵያ (ምርጥ ትንታኔ)
🦃🦃🦃🦃🦃🦃🦃🦃🦃

መስከረም ወር ላይ የሚከሰቱ እንግዶች ሳይሆኑ አመቱን ሙሉ አብረውን የሚቆዩ ፣ በተፈጥሮ ሂደት የላባቸው ቀለም የሚቀየር ቤተኛ አእዋፋት ስለመሆናቸዉ ምን ያክል ያዉቃሉ!? የመስቀል ወፍ በኢትዮጵያ ብርቅዬ ናቸዉ !?
የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ ቀጠሮ እንዳላቸዉ ....ምን አገናኛቸዉ ??

የመስቀል ወፍ ለወራት ጠፍቶ ቆይቶ አዲስ ዓመት ሲገባ በተለይ ደግሞ መስከረም ሲጋመስ እንደሚከሰት በብዙዎች ዘንድ ይታመናል።

በአባባልም አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ ጠፍቶ ቆይቶ ድንገት ሲከሰት ' ምነው የመስቀል ወፍ ሆንክ' ይባላል። ይህም ለረጅም ጊዜ ሳይታዩ ወይም ጠፍቶ ቆይቶ መታየትን ለማመልከት ማህበረሰቡ የሚጠቀምበት አባባል ነው።
አእዋፋትን በቅርበት የሚያጠኑት አቶ ይልማ ደለለኝ ግን "እነዚህ የመስቀል ወፍ ተብለው የሚታወቁት አእዋፋት እንደሚባሉት ለረጅም ጊዜ ተሰውረው ቆይተው በመስቀል ሰሞን የሚከሰቱ ሳይሆኑ ዘወትር አብረውን የሚኖሩ ናቸው" ይላሉ።

በኢትዮጵያ በመስቀል ወፍ ስም የሚታወቀው አንድ አይነት ዝርያ ያለው ወፍ ብቻ ሳይሆን ቁጥራቸው ከአራት በላይ የሆኑ የተለያዩ ዝርያ ያለቸው አእዋፋት እንደሆኑ ይናገራሉ። ለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ቁራ በሚል የሚጠሩ አእዋፋት ቢኖሩም በውስጣቸው የተለያዩ ዝርያዎች እንዳሉት ሁሉ የመስቀል ወፍ ውስጥም የተለያዩ የወፍ አይነቶች መኖራቸውን ነው። ከእነዚህ የመስቀል ወፎች መካከልም አዘውትረን የምናያቸው በቅርብ የምናውቃቸው ትንንሽዬዎቹና ድንቢጥ ተብለው የሚታወቁት አእዋፋትም በመስቀል ወፍነት ከሚጠሩት ውስጥ ይካተታሉ።

እንደየቋንቋውና እንደየአካባቢው እነዚህ ወፎች የየራሳቸው ስያሜና መጠሪያ ሊኖራቸው እንደሚችል የሚጠቅሱት አቶ ይልማ የመስቀል ወፍ የሚለው ግን በርካታ አይነት ወፎች በውስጡ አካትተዋል ይላሉ። በእንግሊዝኛው እነዚህ አዕዋፋት ኢንዲጎ በርድስ፣ ዋይዳ፣ ቢሾፕ ወይም ዊዶ
በርድ ተብለው እንደሚታወቁ በእነዚህ ውስጥም የተለያዩ ዝርያዎች መኖራቸውን ያስረዳሉ።


እነዚህ የመስቀል ወፍ ተብለው የሚጠሩት አእዋፋት በስፋት ታይተው በበርካቶች ዓይን ውስጥ የሚገቡት የክረምቱ ወራት አብቅቶ የበጋው ወቅት በሚጀምርበት ጊዜ ነው። አእዋፋቱ በአብዛኛው ዘር በል በመሆናቸው በዚህ ወቅት ደግሞ የሚደርሱ ሰብሎች በስፋት የሚገኙበትና ወፎቹም የሚራቡበት አመቺ ወቅት በመሆኑ በስፋት እንደሚታዩ አቶ ይልማ ይናገራሉ።

እነዚህ አእዋፋት ባሕሪያቸው ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ ወቅቶችንና የአየር ሁኔታዎችን እየተከተሉ የሚሰደዱ በመሆናቸው በሌሎች ሃገራት ውስጥም ይገኛሉ።
አቶ ይልማ እንደሚሉት የተለያዩ አእዋፋት በተለያዩ ወቅቶች በተለይ ከሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ወደ አፍሪካ የሚመጡ ሲሆን በሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዚያው የሚሄዱም አሉ። ወደ ኢትዮጵያ ወቅቶችን ጠብቀው የተለያዩ ወፎች ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከስካንዴኔቪያን ሃገራት፣ ከምስራቅ አውሮፓ ሃገራት እንዲሁም ከሩሲያ የሚመጡ
እንዳሉና እነዚህም በስደተኛ ወፍነት በባለሙያዎች እንደሚታወቁ ይገልጻሉ።

የመስቀል ወፍ ተብለው የሚታወቁት አብዛኞቹ ግን በኢትዮጵያ ውስጥና በዙሪያዋ ባሉ ሃገራት ውስጥም እንደሚገኙ ይነገራል። ስለዚህ አእዋፋቱ ከኢትዮጵያ ባሻገር በኬንያ፣ በኡጋንዳና በታንዛንያ ውስጥ እንደሚገኙ ይጠቅሳሉ።


አቶ ይልማ እንደሚሉት በልምድ እንደምንለው የመስቀል ወፍ ለረጅም ጊዜ ጠፍተው ቆይተው በመስቀል ወቅት የሚከሰቱ እንዳልሆኑና በዙሪያችን አብረውን
የሚኖሩ ናቸው። አእዋፋቱ አዲስ የሚሆኑብን አብረውን በዙሪያችን በሚቆዩበት ጊዜ የሚኖራቸው ገጽታ በመስከረም ወር ላይ በተፈጥሯዊ ሂደት ቀለማቸው ተለውጦ አይነ ግቡ ስለሚሆኑ የዚያ ወቅት አዲስ ክስተት እንደሆኑ ስለሚታሰብ ነው። "ለዚህም የአዕዋፋቱን ተፈጥሮ መረዳት ያስፈልጋል" የሚሉት አቶ ይልማ እነዚህ ወፎች ላይ ይህ ተፈጥሯዊ ለውጥ የሚታየው በዋናነት በመስከረም ወር ላይ የሚራቡበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ከመስቀል በዓል ጋር ተቀራራቢ በመሆኑ የተለየ ገጽታን ተላብሰው እንዲታዩ ያደርጋቸዋል።


በመስከረም ወር ላይ እንስት አእዋፋቱ እንቁላል ለመጣል የሚዘጋጁበት በመሆኑ ተባዕቱ ለእሱና ለተጣማሪው እንዲሁም ለሚፈለፈሉት አእዋፋት የሚያስፈልገውን ምግብና መጠለያን በሚያገኝበት ቦታ ላይ አንድ የተወሰነ
አካባቢን ከልሎ ይይዛል። የመራቢያ ጊዜ በመሆኑ ወንዱ ይህንን በሚያደርግበት ወቅት የላባው መጠን ይረዝማል ቀለሙም ይቀየራል። ቀለሙ ደማቅና ውብ ስለሚሆን የሰዎችን አይን በመሳብ እንደ አዲስ ወፍ ሊታይ ይችላል ይላሉ አቶ ይልማ። ይህ ቀለምም ከሩቅ የሚታይ እንደሚሆን የሚናገሩት ባለሙያው በተለይ ፀሐይ
በሚያገኘው ጊዜ በማንጸባረቅ ትኩረት የመሳብ አቅም አለው። በተጨማሪም ለውጡ የሚከሰተው በመራቢያ ጊዜ በመሆኑ እንስት ወፎችን ለመሳብና ለማማለል ከመጥቀሙ በተጨማሪ በአንጸባራቂ ውበቱ በቀላሉ ስለሚታይ፣ እንዲሁም በዚህ ላይ ዝማሬን ስለሚጨምር ሌሎች አእዋፋት የእርሱን አካባቢ እንዲርቁ ያስችለዋል።

እንግዲህ ይህ የአእዋፋቱ ሥነ አካላዊ ለውጥ ነው በሌለው ጊዜ በአካባቢያችን ይኖሩ የነበሩትን እነዚህን አእዋፋት ለረጅም ጊዜ ጠፍተው በመስቀል ወቅት ብቅ ያሉ እንዲመስሉ ያደረጋቸው ይላሉ አእዋፋቱን በቅርበት የሚያጠኑት አቶ ይልማ ደለለኝ። ባለሙያው እንደሚሉት "በአካባቢያችን ያሉትን አእዋፋት በቅርበት የመከታተል
ልምድ ስለሌለንና ክረምቱ አልፎ መስከረም አጋማሽ ላይ አእዋፋቱ ላባቸው በቀለማት አሸብርቆ በቀላሉ አይናችን ውስጥ ሲገቡ በዙሪያችን የነበሩት ወፎች ሳይሆኑ ጊዜ እየጠበቁ ብቅ የሚሉ ይመስሉናል።"

ቀለማቸውና ዝማሬያቸው ከአዲስ ዓመትና ከመስከረም የፀሐይ ወቅት ጋር ተዳምሮ ከሚፈጠረው መልካም ስሜት ጋር የሁሉንም ቀልብ ስለሚስቡ ሁሉም ይመለከታቸዋል ሁሉም አዲስ ወፍ የመስቀል ወቅትን ጠብቆ እንደመጣ
ይታመናል።የመስቀል ወፍ ብለን የምንጠራቸው አእዋፋት ከሌሎች ለየት የሚሉት ተባዕቶቹ በጣም ደማቅ ቀለም ሲኖራቸው፣ ሴቷ ግን ቡኒ ወይም ወደ ግራጫ የሚያደላ
ቀለም ነው ያላት፤ በመራቢያ ወቅት ወንዱ ከበርካታ እንስት አእዋፋት ጋር የመሆን ባሕሪ እንዳለውም አቶ ይልማ ይጠቅሳሉ።

ስለዚህ የአእዋፋት አጥኚ የሆኑት አቶ ይልማ ደለለኝ እንደሚሉት የመስቀል ወፎች ለረጅም ጊዜ ሳይታዩ ቆይተው መስከረም ወር ላይ የሚከሰቱ ዓመታዊ እንግዶች ሳይሆኑ አብረውን ቆይተው በተፈጥሮ ሂደት የላባቸው ቀለም የሚቀየር ቤተኛ አእዋፋት ናቸው ማለት ነው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ
#


Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Taban Gatkuoth, Getacher Man
24/09/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Taban Gatkuoth, Getacher Man

ጠፍቶ የነበረዉ የ ጅማ ፤ ኢትዮጵያ
19/05/2025

ጠፍቶ የነበረዉ የ
ጅማ ፤ ኢትዮጵያ

 #አድዋ - የጥቁር ህዘቦች ድል!! አድዋ - ከምኒልክ ለመላው ጥቁር ህዝቦች የተሰጠ የአሸናፊነት ገፀበረከት!እኔነት" ሳይሆን "እኛነት" ያሸነፈበት፤ የመደማመጥ ውጤት ጎልቶ የታየበት፤ የአባ...
28/02/2025

#አድዋ - የጥቁር ህዘቦች ድል!!

አድዋ - ከምኒልክ ለመላው ጥቁር ህዝቦች የተሰጠ የአሸናፊነት ገፀበረከት!

እኔነት" ሳይሆን "እኛነት" ያሸነፈበት፤ የመደማመጥ ውጤት ጎልቶ የታየበት፤ የአባቶቻችን ጀግንነት፤ የእናቶቻችን ጥበብ ሁሌም የሚዘከርበት ድንቅ በአል!

አድዋ - ግዑዝ ብቻ አይደለም በተራራና ሐውልት ብቻ የሚወከል፤ ይልቁንም አድዋ መንፈስ ነው በትውልድ ቅብብሎሽ የልቦና ውቅር ላይ የታተመ!!

እንኳን ለ129ኛዉ የአድዋ መታሰቢያ በአል አደረሳችሁ!!

#

🇪🇹 እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹''ሔር ኢሴ'' የኢሳ ባህላዊ የፍትህ ስርዓት በዩኔስኮ የአለም ማይዳሰስ የባህል ቅርስነት ተመዝግቧል። ይህ ቅርስ በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ ውስጥ ባሉት ...
06/12/2024

🇪🇹 እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹

''ሔር ኢሴ'' የኢሳ ባህላዊ የፍትህ ስርዓት በዩኔስኮ የአለም ማይዳሰስ የባህል ቅርስነት ተመዝግቧል።

ይህ ቅርስ በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ ውስጥ ባሉት ኢሳዎች ዘንድ ተከብሮ የኖረና ከትውልድ ትውልድ ተጠብቆ ሲተላለፍ የቆየ ባህላዊ የፍትህ ስርዓት ነው።

ይህ ስርዓት ተጠብቆ እንዲቆይ እና ዛሬ ለአለም ቅርስነት እውቅና እንዲበቃ ያደረጉት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል!

ሰላማዊት ካሳ - የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር

🇪🇹


እንኳን ደስ አለን!  የአኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ ተመዘገበ፡፡በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የ...
09/08/2024

እንኳን ደስ አለን!

የአኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ ተመዘገበ፡፡

በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአረኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሶስት መስፈርቶችን በማሟላት የዓለም ቅርስ ሆነ ተመዝግቧል::

Address

Haile Selassie Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ:

Share

Category