Vacation Ethiopia Tour & Car Rent

Vacation Ethiopia Tour & Car Rent We are committed to provide quality and reliable service! We happily help you best wherever you want to fly or drive with us!

05/06/2024

ክፍት የስራ ቦታ:
* ልምድ ያላት/ያለው ትኬት agent እንፈልጋለን
ብዛት: 2 (ሁለት)
ደሞዝ: በስምምነት

14/05/2024

ኮድ 3 ቪትዝ መኪኖችን ለድርጅት እንፈልጋለን
የስራ ቦታ: አዲስ አበባ
ቆይታ: ለአንድ አመት

Vacation Ethiopia Tours and Car Rent wishes for you!
10/09/2021

Vacation Ethiopia Tours and Car Rent wishes for you!

በኬንያ አስደናቂ የጉብኝት ፓኬጅ ድርጅታችን ቫኬሽን አስጎብኚ አሁን ደሞ በኬንያ ያዘጋጀው የጉብኛት ፐሮግራም በዓይነቱ የተለየና ወጣ ያለ የህይወት ተሞክሮ የሚሰጥ ነው፡፡ በናሽናል ጂኦግራፊ ...
02/09/2021

በኬንያ አስደናቂ የጉብኝት ፓኬጅ

ድርጅታችን ቫኬሽን አስጎብኚ አሁን ደሞ በኬንያ ያዘጋጀው የጉብኛት ፐሮግራም በዓይነቱ የተለየና ወጣ ያለ የህይወት ተሞክሮ የሚሰጥ ነው፡፡ በናሽናል ጂኦግራፊ ስናይ የተደነቅንባቸውን የዱር እንስሳቶችን (አንበሳ ፤ ነብር ፤ አቦ ሸማኔ ፤ ጅብ ፤ ዝሆን ፤ ቀጭኔ ፤ ጎሽ ፤ አውራሪስ ፤ አጋዘን ፤ ሚዳቆ ፤ ዝንጀሮዎች እና ሌሎች) እንስሳቶችን በተፈጥሮዋዊ ቦታቸው በአካል ተገኛተን የምንጎበኛበት አጋጣሚ ነው፡፡

ኬንያ ለተቀረው ዓለም ፀጋዋን አቅርባ የምታስጎበኛቸውን አምቦሰሊ ብሄራዊ ፓርክ ፤ ኔቫሺ ሐይቅ ፤ ናኩሩ ሐይቅ ብሄራዊ ፓርክ እና ማራ ፓርክ ባአካባቢው የሚኖሩትን ተወዳጆቹ ማሳይ ጎሳዎችን ይህ የጉብኛት ፐሮግራም ውስጥ ተካትተዋል፡፡

ይህ የጉብኛት ፕሮግራም የተዘጋጀው ለጉብኛት አመቺ በሆነበት ጊዜ ነው፡፡ እንስሳቶቹ በብዛት በአንድ ቦታ ተከማችተው የሚገኙበትና አስደናቂውን ስፍር ቁጥር የሌለውን የእንስሳት ፍልሰት ፤ በዛም አጋጣሚ የአዳኛ ታዳኛ ትዕይንት የሚታይበት ወርቃማ ወቅት ነው፡፡

ጉብኛቶ ደህንነቶንና ምቾቶን በሚጠብቁ ላንድክሩዘር መኪኖችና ልምድ ባላቸው የሀገሬው አስጎብኚውች ያታገዛል፡፡

በሚቆዩባቸው ሰባት (7) ቀናቶች ሁሉ በምዳራዊ ገነት ስፍራዎች በተገነቡ ሎጆች ውስጥ ከነሙሉ የምግብ አገልግሎት ጋት ተሠናድቶ ይጠብቆታል፡፡
ድርጅታችን ሁሉንም ነገር ጠቅልሎ ይሰራሎታል እርሶ ብቻ ሻንጣዎትን አዘጋጅተው በቀኑና ሰዓቱ ቦሌ አዲስ አበባ ኤርፖረት መገኘት ብቻ ነው፡፡ ፈጥነው ይመዝገቡ!

 የጉብኛቱ ቀን መነሻ ከአዲስ አበባ መስከረም 28

 የጓብኚዎች ቁጥር ብዛት "10"

ፍላጎቱ ያላችሁ ደንበኞቻችን በስልክ ቁጥራችን ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ

 ስልክ፡ 0983 359696
 አድራሻችን፡ ሀያሁለት ሌክስ ፕላዛ 2ኛ ፎቅ / ቢሮ ቁጥር 204

ቫኬሽን አስጎብኚና የመኪና ኪራይ
አንገደብም ፤ አለምን ሁሉ እናያለን!

24/12/2020

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን
ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ) የተሸከርካሪዉን የመጫን አቅም(የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣ ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡
ተገጣጥመው ወደ ሀገር የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 1300 ከሆነ 75.67%ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ1800 በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሸከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው ያገለገሉ(USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡
የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ እንደ ተሽከርካሪው አይነት ወደ ሀገር የሚገቡ የተሸከርካሪዎች ላይ እስከ አራት ዓይነት የቀረጥና ታክስ ዓይነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከአምራች ድርጅቶች ውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ደግሞ በተጨማሪነት የዊዝሆልዲንግ ታክስ ይሰበሰባል፡፡ የቀረጥና ታክስ ማስከፈያ መሠረት(Tax base) የሚሆነው የእቃው ዋጋ(CIF) እና በቅድም ተከተል የሚሰላው የቀረጥ ወይም ታክስ መጠን (የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ) ድምር ይሆናል፡፡
የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ ለምሳሌ ሁሉም ዓይነት ታክስ በሚመለከተው በቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በምሳሌነት እንመልከት፡፡
የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 400,000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1300 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ሲገባ:-
በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 400,000 X 30%(ከፍተኛው መጣኔ) = 120,000 ይሆናል፡፡
ቀጥሎ ኤክሳይዝ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (400,000 + 120,000) 5%= 26,000 ብር ይሆናል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000) 15% = 81,900 ብር ይሆናል፡፡
በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000 +81,900)10%= 86,190 ብር ይሆናል፡፡
ተሽከራካሪው በመደበኛ አስመጪ(ከአምራች ድርጅት ውጪ…) የሚመጣ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 400,000 X 3%= 12,000 ብር ይሆናል፡፡
በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት
120,000 + 26,000 + 81,900 + 86,190 + 12,000= 326,090 ብር ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው መሠረት በማድረግ የተለያየ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል፡፡
Source: Ministry of Revenues

Address

Haile G/silassie Street, Lex Plaza Bldg, 2nd Floor, Office # 204B
Addis Abeba

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Vacation Ethiopia Tour & Car Rent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Vacation Ethiopia Tour & Car Rent:

Share

Category