25/05/2025
የሙያ ፈቃድ መንጠቅ ...?
በአንዳንድ ሚዲያዎች እየተናፈስ
ያለዉ የመንግስት አቋም ሳይሆን የግለሰቦች ስሜታዊ ምላሽ ይመስለኛል...!
-የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የደሞዝ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን የጤና ስርዓቱ እንዲሻሻልም ጭምር ነዉ፤
-ሊሰጥ የሚገባዉ ምላሽ የሙያ ፈቃድ ለመንጠቅ መዛት መሆን የለበትም !!!
-ደሞዝ ባይጭመር እንኳ ከደሞዛቸዉ የሚቆረጠውን የስራ ግብር ማሻሻል አይቻልም...?
-ለጤና ባለሙያዎች ደሞዝ መጨሙር ባይቻል እንኳ ተመጣጣኝ የነዳጅ ወጪ እንዲሸፍኑ አድረጎ የትራንስፖርት ሰርቪፕስ ማቅረብ አይቻልም ...?
-ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በመነጋገር ለቤት ግንባታ የሚሆን ቦታ በነፃ በማዘጋጀት፣ ከባንኮች ጋር በዝቅተኛ የወለድ መጠን ብድር በማዘጋጀት የመኖሪያ ቤት ችግራቸውን መፍታት አይቻልም ?
-የጤና ስርዓቱን በጥናት አስደግፎ ማሻሻል፣ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና ቤተሰቦቻቸው በነፃ ህክምና የሚያገኙበትን ስርዓት መዘርጋት አይቻልም?
-የጤና ባለሙያዎች በደሞዝ ጭማሪ አሳበዉ ወደ ዉጪ አገራት ለመኮብለል የተዘጋጁ በሚመስል መልኩ ችግሩን አቅሎ ማየትና ማናናቅ ተገቢ አይመስለኝም፤ ይቅርና ዛሬ ዓለም ዝብርቅርቋ ወጥቶ የሰዉ ዘር መደበቂያ ተብላ የምትወሰደዉ አሜሪካ ሳትቀር ጥቁርን ከነጭ ለይታ ዉጡ ግቡ ማለት በጀመረችበት ወቅት የመኖር ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል ልዩ የፖለቲካ ችግር ካልኖረ በስተቀር ኢትዮጵያ ሀገሩን ለቆ ለመኮብለል የሚፈልግ የጤና ባለሙያ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ...!!!
-የሙያ ፈቃዳቸውን መንጠቅ ይቻላል፤ ግን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የታክሲ ሾፌር፣ የሽንኩርት ነጋዴ፣ወዘተ... መሆን፣ወይም በገበያ ላይ የሞላውን የውሸት ዲግሪና ከዚያም በላይ የትምህርት ማስረጃ ሸምተዉ በሌላ የስራ ዘርፍ ሊሰማሩ እንደሚችሉም ማስተዋል ጥሩ ነዉ፤
እነዚህን የጤና ባለሙያዎች በማስተማር የእያንዳንዱ ጤና ባለሙያ ቤተሰብ የከፈለውን መስዋዕትነት፣
እንዲሁም ይህች ድሃ ሀገር የጤና ባለሙያዎቹን ለማስተማር ኢንቨስት ያደረገችውን ከፍተኛ ወጪ ከግምት በማስገባት ከጤና ባለሙያዎች ጋር በተናጠል እልህ በመጋባት ሳይሆን ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት አንፃር በማየት መንግስት መጣኝና ተገቢ ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታል ብዬ አምናለሁ !!!
የጋሞ የሀገር ሽማግሌ፦