Amhara Tourism Attractions

Amhara Tourism Attractions Tourism sites are disclosed here

የውጭ አገር ቱሪስቶች ወደ ድንቅ ምድር የሚያደርጉት ጉዞ እየጨመረ ነው። More and more international tourists are coming to explore the 𝗟𝗮𝗻𝗱 𝗼𝗳 𝗘𝘁𝗵...
26/11/2025

የውጭ አገር ቱሪስቶች ወደ ድንቅ ምድር የሚያደርጉት ጉዞ እየጨመረ ነው።

More and more international tourists are coming to explore the 𝗟𝗮𝗻𝗱 𝗼𝗳 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮𝗻 𝘄𝗼𝗻𝗱𝗲𝗿𝘀, 𝗔𝗠𝗛𝗔𝗥𝗔.

Come and experience the 𝑳𝒂𝒏𝒅 𝒐𝒇 𝑬𝒕𝒉𝒊𝒐𝒑𝒊𝒂𝒏 𝒘𝒐𝒏𝒅𝒆𝒓𝒔. Visit Amhara

የደብረ ሲና ማርያም አንድነት ገዳም ህዳር 21/ 2018 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል ።ደብረ ሲና ማርያም አንድነት ገዳም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ የምትገኝ ሲሆን ጥንታዊው ...
25/11/2025

የደብረ ሲና ማርያም አንድነት ገዳም ህዳር 21/ 2018 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል ።
ደብረ ሲና ማርያም አንድነት ገዳም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ የምትገኝ ሲሆን ጥንታዊው የአሰራር ጥበቧ፣ በድንቅ የግድግዳ ስዕሏ እና በውስጧ ለዘመናት የተከማቹ ውድ ቅርሶቿ በጎብኝዎች የምትመረጥ ያደርጓታል፡፡።
በገዳሙ ጎብኝዎች በተለያዩ ጊዚያት የሚሄዱ ቢሆንም ህዳር 21 በድምቀት በሚከበረው ዓመታዊ ንግስ በዓል ላይ መገኘት ደግሞ ልዩ ያደርገዋል፡፡

የጊምባ እረኛ ታሪክ           ✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍ከደሴ ተነስተው በገራዶ አድረገው ደሴ ዙሪያ ወረዳን አቋርጠው ሲጓዙ የለጋምቦ ወረዳን  ሶስት ፈርጅ  እናገኛለን  ፡፡ ሜዳውን ተጉ...
22/11/2025

የጊምባ እረኛ ታሪክ
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ከደሴ ተነስተው በገራዶ አድረገው ደሴ ዙሪያ ወረዳን አቋርጠው ሲጓዙ የለጋምቦ ወረዳን ሶስት ፈርጅ እናገኛለን ፡፡ ሜዳውን ተጉዞ ቁልቁለቱን ወረድ እንዳልን የሰኞ ገበያ ገመገም ዙሪያሽ ሰፈር ይታያል ወዳውኑም ሰኞ ገበያን እናገኛለን ፡፡ አውላላውን መንገድ ይዘው በግራና በቀኝ እየታለፍ ሲኬሄድ ደግሞ በስተቀኝ በኩል ለአይን የሚያታክት የጊምባ ሜዳ ላይ ብዛት ያላቸው በጎች ሳር ሲግጡ ማየት የተለመደ ነው፡፡አለፍ እንደተባለም ቱሉ አውሊያ ከተማ እና መቅደላ አምባ ዩኒቭርስቲ ደምቀው ይታያሉ ፡፡ ወረድ ስንልም አይን የሚያማልለው የጭሮሜዳ አረንጎዴ መስክን ያገኛሉ ፡፡
የለጋምቦ ወረዳም ካሏት አያሌ እምቅ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶች መካከል የጊምባ እርኛ ታሪክ አንዱ ነው፡፡ የጊምባ ሜዳን ጨምሮ ቀርመሜ ፣ እብራሂም አገር ፣ ካባ ፣ አዩቤት ፣ ቡክዳ ፣ ጭሮ ፣ ሰኞ ገበያና ከረጊምባ የሚሰኙትን አካባቢዎች ጠቅልሎ ለመጥራት የሚያገለግል የወል መጠሪያ ነው፡፡
የነዚህ አካባቢ ነዋሪዎች ዋነኛ መተዳደሪያቸው የእርሻ ስራ ቢሆንም ከዚህ ጎን ለጎን በስፋት የበግ እርባታ ስራም ያከናውናሉ ፡፡ ተፈጥሮ አመቻችቶ በዘረጋው የተንጣለለው ሜዳ ላይ እጂግ በርካታ ቁጥር ያላቸው በጎች ለግጦሽ የሚሰማሩ ሲሆን ሜዳውን እኩል ለሁለት ከፍሎ የሚያልፈው የጊምባ ወንዝ በአረጓደው ስጋጃ መሃል እንደኩል ጥርት ብሎ ዝግ ባለ አኳኋን ሲፈስ ባማረ ነጭ ነጠላ ላይ ያረፈ ጥለት ይመስላል፡፡
በዚህ ሁኔታ በሜዳው ላይ የሚታዩት ብዛት ያላቸው በጎች ከሚውሉበት ሠፊ ሜዳ ወደ ቤታቸው ለመወሰድ ሲፈልጉ እረኛው ትሪ- ትሪ- በማለት ሲናገር የተቀላቀሉት በጎች ወደ ጠራው እረኛ በመለየት ለየብቻቸው ይወጣሉ ፡፡ ምንም እንኳን አያሌ በጎች በአንድ እረኛ ቢጠበቁም አንድ በግ ከመካከል ቢጠፋ ሳይቆጠርና ብዙ ማስታወስ ሳያሥፈልገው የጠፋው በግ ወንድ ወይም ሴት ወይም ነጭ ወይም ጥቁር መሆኑን ወዳውኑ ይታወቃል ፡፡ በዚህ መንገድ ካልተገኘ ቀሪዎቹን በጎች ወደ ቤቱ ይወስድና ከማዶ ማዶ ተጠራርቶ በመጠየቅ ካለበት ቦታ እንዳድርለት ይደረጋል፡፡
በመጣራት የሚያደርገው ጥሪም የሚሄደው ማታላይ ነው ፡፡ ከዚህ ሌላ እረኞችን ልዩ የሚያደርጋቸው ከበጎቹ ወተት የሚያልቡበት ሁኔታ ነው፡፡ ወልዳ ከምታጠባ በግ ከጥቁር ዋልካ ጭቃ የሚዘጋጅ እንስራ መሰል እቃ በጮጮ ይታለብና ‹ድራ››ከሚለው ከሜዳ መካከል ከሚገኙ ድንጋያማ ቦታ መሬቱን በመቆፈር በጮጮ የተሞላው የበግ ወተት ይቀበራል ፡፡ ይህ የተቀበረ ወተት በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደእርጎነት ይቀየራል፡፡ ካልሆነም ጮጮውን በእጃቸው በመወዝወዝ ቅቤ እንድወጣው ያደርጋሉ ፡፡ ይህም ለእረኞች ምግብነት ይውላል፡፡ የተቀበረበት ቦታም እንዳይጠፋ የድንጋይ ምልክት ያደርጋል፡፡ ይህ ስፍራ አሁንም ድረስ እርጎ መደበቂያ በመባል ይታወቃል፡፡
የጊምባ እረኛ ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ታሪካዊ ሁኔታዎችን በመግጠምና በዜማ በማዋዛት የሚናገሩ ሲሆን ከነዚህ ስንኞች መካከልም ትንቢታዊ ይዘት የነበራቸውም ነበሩም ይባላል፡፡
ይህ ከላይ የገለጽነው የበጎች እረኝነት ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ ታሪካዊ ፍርስራሽ ስራ ቢያሸልብም የጊምባ እረኛ ‹‹እንዲህ ይል ነበር›› ወይም‹‹ የጊምባ እረኛ ትንቢት ነው-››
የሚባልላቸው በርካታ ስነ -ግጥሞችና ሰነ ቃሎች አዘል አባባሎችይገኛሉ፡፡
ለምሳሌም በጊምባ ማእከላዊ ስፍራ ላይ በመቆርቆር ዛሬ ፈጣን እድገት የምታሳየውና የመቅደላ አምባ ዩኒቭርስቲ መቀመጫ የሆነቸው ቱሉ አውሊ ከተማ አስመልክቶ አንድ የተባለ ነገር ነበር፡፡
‹‹ አህያ መጣች ተጭና ላም
ቱሉ አውሊያ ላይ ያለችው አለም
የዛሬም አይደል የዘላለም›› ብለው እንደ ነበር እድሜ ጠገብ የአካባቢው ሽማገሌዎች ይናገራሉ፡፡
የጊምባ እረኛ ለንፋስ መከላከያ የሚክቡት የድንጋይ ካብ ውስጥ ሆነው ቆሎ አቸውን ከበሉ በኋላ ‹‹እልዎ›› በሚባል ጫዎታ መሰል ዜማ ውስጥ በግጥም የተዋቡ ነገሮችን ይናገራሉ
እረኞች ከተናገሯቸው ከሚባሉት መካከልም በሁለተኛው ፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ድርማዊ ቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት ኃይለ ስላሴ ከሃገር የመውጣታቸውን ጉዳይ አስመልክቶ እንዲህ ብለው ነበር፡፡
‹‹አህያ መጣች ተጭናሻሽ
ሃይለ ስላሴ አጥብቀሕ ሽሽ››፡፡
በሌላም በኩል የአጼዩሃንስ መተማ ላይ መውደቅ አስመልክተው
‹‹በመተማ በኩል ይዘልቃል ወጠጤ
ትበላለች ንጉስ ትበላለች አጤ፡፡›› ብለው ነበር፡፡
በፋሽስት ወረራ አገራቸውን ከድተው ለጣሊያን ያደሩ ወገኖች እንዱህ ብለዋል ነበር፡፡
‹‹አህያ መጣች ተጭና ምስር
ባንዳ ተደበቅ በየድንጋይ ስር
ይህ የጊምባ እረኞች ታሪክ ራሱን የቻለ ወጥ ታሪካዊና ማህበራዊ እሴት ያለውንና ሰፊ ጥናት ቢደገፍ የተሻለ ሥራ መስራት ይቻላል እያልን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት በታሪኩና በእረኞቹ ሁለንተናዊ ሁኔታ በማጥናት በኩል የየራሳቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል እንላለን፡፡
መረጀ ጥንቅር ተውፊቅ ጌቶ

በ ላሊበላ ይህ ታየ
07/09/2025

በ ላሊበላ ይህ ታየ

ሶለል - ራያ
22/08/2025

ሶለል - ራያ

ሻደይ ፣አሸንድየ እና ሶለል ደርሷል
24/07/2025

ሻደይ ፣አሸንድየ እና ሶለል ደርሷል

በደሴ ከተማ Diamond Luxury የተሠኘ ሆቴል ተመርቋል።ሆቴሉ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎችን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በቱሪዝም ዘርፉ የጎላ ድርሻ ይጫወታል።
20/07/2025

በደሴ ከተማ Diamond Luxury የተሠኘ ሆቴል ተመርቋል።
ሆቴሉ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎችን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በቱሪዝም ዘርፉ የጎላ ድርሻ ይጫወታል።

የወል ተራራ‼      የወል አረጀ አሉ የወል ምን ያረጃል ፤      ሠባት አሜሪካ ባንድ ቀን ይፈጃል ።     የወል ተራራ ከባህር ጠለል በላይ 3960 ሜትር ከፍታ ያለው ከወሎ መዲና ከሆነ...
29/06/2025

የወል ተራራ‼

የወል አረጀ አሉ የወል ምን ያረጃል ፤
ሠባት አሜሪካ ባንድ ቀን ይፈጃል ።
የወል ተራራ ከባህር ጠለል በላይ 3960 ሜትር ከፍታ ያለው ከወሎ መዲና ከሆነችዉ ደሴ ከተማ ወደ ምዕራብ ወሎ አቅጣጫ በገራዶ በኩል ስንሄድ በደሴ ዙሪያ ወረዳ በጉጉፍቱ 036 ቀበሌ የሚገኘው ሲሆን እንዲሁም ተራራዉን የወረኢሉ ወረዳዉ ደኙ 014 ቀበሌ የሚጋራዉ ነው ለሁለቱም ወረዳዎች እንደ ድንበር ሁኖ ያገለግላል ።

ከደሴ 40 ኪሎ ሜትር ከምትርቀዉ ጉጉፍቱ ከተማ በግምት አንድ ኪሎ ሜትር ወደ ካቤ መስመር በሚያስኬደዉ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ተራራው በምዕራብ ወሎ ዉስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ቦታዎች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ በዚሁ አካባቢ የሚገኙትን አብዛሀኛዎቹን አካባቢዎች ከየወል ተራራ ላይ ሁኖ ከአልብኮ ምልስ እስከ ወረኢሉ እና ለገሂዳ እንዲሁም ለጋምቦ ድረስ እና በእነዚህ ዉስጥ ያሉ ሌሎች ትንንሽ መንደሮችና ከተሞችን ማየት ይቻላል እንዲሁም በማታ አዲስ አበባ ከተማን ማየት ይቻላል ።

ስለ ተራራው በስሱ ይህን ካልኳችሁ ተራራው ብዙ ግልጋሎት እና ታሪክ ያለው ነው አንድ ሁለቱን ልንገራችሁ ተራራው አናት ላይ እንደ ዛሬው ተንቀሳቃሽ ስልክ ሳይመጣ ለምዕራብ ወሎ የቤት ስልክ ማቀባበያ ( ማይክሮዌቭ ) ተራራው ጫፍ ላዬ በመግጠም ሲያገለግል የነበረ እና አሁንም እያገለገለ ያለ ነው እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚደርጉ የተለያዩ የተለያዩ እንቅስቃሴወች እያደረገ ሲሆን በታሪክ እንዲሁ በ 1940 ዎቹ አካባቢ አንዲት ሠባት አሜሪካውያን የያዘች አውሮፕላን ጉም ሸፍኖት ተገልብጣ ሠባቱም አሜሪካውያን ወዳው ሂወታቸው ሲያልፍ በዚህ የተነሳ

የወል አረጀ አሉ የወል ምን ያረጃል ፤
ሠባት አሜሪካ ባንድ ቀን ይፈጃል ። ተብሎ ተገጥሟል ።

እንዲሁም በአካባቢዉ ከፍተኛ የበግ እና ወተት ተዋፅዖ ምርት ያለ ሲሆን ለጉብኝት ብትመጡ ጉጉፍቱ ላይ እኔ ነኝ ያለ እርጎ ጠጥታችሁ ጦስኝ የበላ በግ ጥብስ በልታችሁ ትመለሣላችሁ ።
#ኢትዮጲስ
Wasu Mohammed - Mereja

ሎጎ ሀይቅ
25/06/2025

ሎጎ ሀይቅ

የጉና እጅግ ልዩ ተፈጥሯዊ ውበት!
02/06/2025

የጉና እጅግ ልዩ ተፈጥሯዊ ውበት!

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የቅድስት ፃድቃኔ ማርያም  አመታዊ ክብረ በዓል ይህን ይመስላል
29/05/2025

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የቅድስት ፃድቃኔ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል ይህን ይመስላል

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Tourism Attractions posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category