Riverland Hotel

Riverland Hotel Riverland Hotel is a three star hotel found in Bahir Dar, Ethiopia.

ʺ ደብረ ታቦር እልል ትላለች፤ አጅባር በደስታ ትዋጣለች"ጥንታዊቷ ከተማ በእልልታ ትዋጣለች፣ አምላክን እያመሰገነች እልል ትላለች፣ ጎዳናዎቿ ይባረካሉ፣ ነጫጭ በለበሱ ምዕመናን ይመላሉ፣ ጎበዛ...
31/01/2023

ʺ ደብረ ታቦር እልል ትላለች፤ አጅባር በደስታ ትዋጣለች"

ጥንታዊቷ ከተማ በእልልታ ትዋጣለች፣ አምላክን እያመሰገነች እልል ትላለች፣ ጎዳናዎቿ ይባረካሉ፣ ነጫጭ በለበሱ ምዕመናን ይመላሉ፣ ጎበዛዝቱ ትጥቃቸውን አሳምረው በኩራት ይወጣሉ፣ በአስፈሪ ግርማ ይረማመዳሉ፣ ወይዛዝርቱ ኢትዮጵያዊነት በበዛበት ውበት ተውበው ልብን በሚያስደነግጥ ደም ግባት ይታያሉ፣ አጅባር በደስታ ትዋጣለች፣ በምስጋና ትመላለች፣ በእልልታና በዝማሬ ከፍ ከፍ ትላለች፣ ፈረሳቸውን በሸለሙ ጀግኖች ትከበባለች፡፡

ዓይኖች ጥንታዊቷን ከተማ ያያሉ፣ ጀሮዎች ወደ ጥንታዊቷ ከተማ ያዘነብላሉ፣ እግሮች ወደ ጥንታዊቷ ከተማ ይጓዛሉ፣ በታቦር ተራራ የተሰየመችው፣ የነገሥታቱን፣ የመኳንንቱን፣ የመሳፍንቱን ቀልብ የሳበችው፣ለሊቃውንቱ፣ ለዲያቆናቱ፣ ለዘማሪያኑና ለአንባቢያኑ ማረፊያ የኾነችው ከተማ በአራቱም ንፍቅ በሚመጡ እንግዶች ትደምቃለች፡፡

ሊቃውንቱ ምድራዊ የማይመስለውን፣ ሰማያዊ የሚመስለውን፣ በምድርም በሰማይም የተወደደውን ምስጋና ያቀርባሉ፣ ያለድካም አምላካቸውን ያመሰግናሉ፣ ለምድር ሰላሙን እና በረከቱን ይለምናሉ፣ ዲያቆናቱ በትሕትና ለተልዕኮ ይፋጠናሉ፣ ለአበው ሊቃውንት እጅ እየነሱ ይታዘዛሉ፣ ነጫጭ የለበሱ ምዕመናን እልል እያሉ ወደ ቤተመቅደስ ይጓዛሉ፣ለጌታ ክብር የተገባውን መባ እየያዙ ይገሰግሳሉ፣ እጅ እየነሱ በአጸዱ ሥር ይሰባሰባሉ፡፡

ኃያላኑ ስለ ሀገር ፍቅር፣ ስለ ሠንደቅ ክብር መክረውባታል፣ በብልሃትና በጥበብ ሀገር መርተውባታል፣ የሀገር አንድነትን አጽንተውባታል፣ የኢትዮጵያዊነትን ልክ፣ የጀግንነትን ዳር አሳይተውባታል፡፡ ጎበዛዝቱ በተራራዎቹና በሸንተረሮቹ ተመላልሰውባታል፣ በሜዳው በፈረሶቻቸው ሽምጥ ጋልበውባታል፣አንደኛው ከሌላኛው ልቆ ለመገኘት ተፎካክረውባታል፡፡

የእግዚዓብሔር መልዐክ የሚመራቸው ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፤ አምላካቸውን በልባቸው ይጠብቁታል። አብዝተው ያመሰግኑታል። በፍቅር ይገዙለታል። እርሱም አብዝቶ ይወዳቸዋል። ይጠብቃቸዋል። ቄስ ወንድማሆም እና ቄስ ዘ ጊዮርጊስ ይሰኛሉ፡፡ እነዚህ ካህናትም አምላካቸውን የሚፈሩ፣ ሃይማኖታቸውን የሚያከብሩ ደጋጎች ነበሩ፡፡ ለታሪክ ተመርጠዋል፣ ደብር ይደብሩ፣ ቤተ እግዚዓብሔርን ያከብሩ ዘንድ ታጭተዋል፡፡ ለእነዚህ የተመረጡ ወንድማማቾች የእግዚዓብሔር መላዕክ ሁለት ፅላት ሰጣቸው፡፡ ፅላተ ጽዮንና ፅላተ ማርያምን። ከሸዋ መንዝ ተነስተው ታቦተ ማርያምን እና ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ስሜን በጌምድር አቀኑ፡፡ የእግዚዓብሔር መላዕክ በመንገዳቸው ኹሉ ይጠብቃቸውና ይመራቸው ነበር። ረጅሙን መንገድ ተጉዘው ደብረ ታቦርም ደረሱ፡፡

በዚያ ዘመን አጼ ሰይፈአርድ ነግሠው ኢትዮጵያን ያሥተዳድሩ ነበር፡፡ የመንበረ ንግሥት ቅድስት ልጅቱ ማርያም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት ተጠሪ ዲያቆን በልአንተ ተመስገን እንደነገሩኝ አጼ ሰይፈአርድ በኢየሱስ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ነበሩ፡፡ እኒያ ደጋግ ሰዎችም ደግሞ ደብረ ታቦር መጥተው በአንድ ሥፍራ ተቀምጠዋል፡፡ አፄ ሰይፈ አርድም ዓይናቸውን ባማተሩ ጊዜ በአንድ ሥፍራ ጭስ ሲጨስ ይመለከታሉ፡፡ ይህም ጭስ ከአንድ ሥፍራ በተደጋጋሚ ሲጨስ ተመለከቱ፡፡ የጦር አበጋዛቸውንም ጭስ የሚጨስበትን አካባቢ አስሶ ይመጣ ዘንድ አዘዙት፡፡

የጦር አበጋዛቸውም ጭስ ወደ ሚጨስበት ስፍራ ባቀና ጊዜ እኒያን ወንድማማቾች ካህናት አገኛቸው፡፡ ሰላምታ ሰጥቶም ጠየቃቸው፣ ካህናቱም ለታቦታቱ ማረፊያ የሚኾን ቤተ መቅደስ ማነጽ እንደሚሹ ነገሩት፡፡ እርሱም ያሰቡት ይሳካ ዘንድ ፈቀደላቸው፡፡ አምላካቸው ይፈቅድ ዘንድ ተማጸኑ፡፡ አምላክም ራዕይ አሳያቸው፣ ቤተ መቅደስ የሚያንጹበትን ሥፍራ አመላከታቸው፡፡ ለታቦተ ማርያም ቤተ መቅደስ አንጸው ቅዳሴ ቤቱን አከበሩ፡፡ ታቦተ ጽዮን የምታርፍበት ቤተ መቅደስ የሚያንጹበት ሥፍራም ፈለጉ፡፡ ለአንድ ዓመት ከአራት ወራትም ቆዩ፡፡

ካህናቱ ራዕይ አዩ፡፡ ለታቦተ ጽዮን መጀመሪያ መጥተው ካረፉባት ሥፍራ ቤተ መቅደስ ይታነጽ ዘንድ ተመለከቱ፡፡ ያንንም አደረጉ፡፡ የአብያተ መቅደሱ አሠራር በአንድ ዓመት ከአራት ወራት ስለሚለያዩ ለአብያተ ክርስቲያናቱ ስያሜ እናውጣ በተባለ ጊዜ የሀገሬው ሰው ቀድማ የተሠራችውን እናቲቱ ማርያም፣ ቆይታ የተሠራችውንም ልጅቱ ማርያም እንበላቸው አሉ፡፡ ተባሉም፤ ያ ስምም እነኾ ዛሬ ድረስ ዘልቋል፡፡ ስሙም ለአብያተ ክርስቲያናቱ ስያሜ ይኾን ዘንድ ወጣ እንጂ በሃይማኖት አስተምህሮስ ልጅቱና እናቲቱ የሚባል የለም ይላሉ አበው፡፡

እኒህ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክን እየነገሩ፣ ሃይማኖትን እያስተማሩ የሚኖሩ ናቸው፡፡ ከጊዜ በኋላ በራዕይ በተሠራችውና በጥበብ በታነጸችው በመንበረ ንግሥት ቅድስት ልጅቱ ማርያም ቤተክርስቲያን ታቦተ መርቆሬዎስ ገባ፡፡ የሰማዓቱ መርቆሬዎስ ታቦት በዚያች ደብር በመግባቱ በዓለ መርቆሬዎስ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይታሰብባታል፡፡ በወረኃ ጥር በሃያ አምስተኛው ቀን ደብረ ታቦር በበዓለ መርቆሬዎስ ትደምቃለች፡፡ ከፍ ከፍም ትላለች፤ የሊቃውንት እና የምዕመናን ዝማሬ ከፍ ብሎ ይሰማባታል፣ የጎበዛዝቱ ግርማ ይከባታል፣ የወይዛዝርቱ ደም ግብዓት ያስጌጣታል፡፡

የደብረ ልዑላን መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የአራቱ ጉባዔያት መምህር መምህራን በጽሃ ዓለሙ በዓለ መርቆሬዎስ በደብረ ታቦር በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይከበራል ብለዋል፡፡ ሊቃውንት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ሲያደርሱ፣ ምዕመናን በፈረስ ያስቡታል፣ ታቦቱን ያጅቡታል፣ ያመሰግኑታል፡፡

ፈረስ አበው ጋማውን ጭራ እያደረጉ ይዋቡበታል፣ ጭራውን ማሲንቆ እያሠሩ አዝማሪዎች አምላካቸውን ያመሰግኑበታል፣ ነገሥታቱን ያደንቁበታል፣ ደስታቸውን ይገልጹበታል፣ የአዘነውንም ያጽናኑበታል፡፡ ፈረስ ከጠጠር ጋር እህል ሲሰጠው እህሉን መርጦ ይመገባል፣ ሰውም በሕይዎት ሲኖር ከበርካታ መጥፎ ነገሮች መልካሙን እያወጡ መሥራት እንደሚገባ ያመላክታልም ነው የሚሉት የኔታ፡፡

የመርቆሬዎስ ታቦት ከመንበሩ በወጣ ጊዜ፤ ከየአቅጣጫው የመጡ ፈረሰኞች ፈረሶቻቸውን ሦስት ጊዜ ያሰግዳሉ፤ ምስጋናም ያቀርባሉ፣ የቅዱስ መርቆሬዎስ ፈረሰኞች ይባላሉ፣ ከቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ለመሳተፍ ታቦቱን በፈረስ ያጅባሉ፡፡ ፈረሱን ወደ ታቦቱ ሳያሰግዱ አይጋልቡም፣ ከሰገዱ በኋላ ነው የሚያጅቡት ነው ያሉኝ፡፡ ለታቦቱ ማሰገዱ ከአባቶች የቆዬና ሃይማኖታዊ ክብር በመኾኑ ሳይቀንስ መቀጠል አለበት ይላሉ የኔታ በጽሃ፡፡

በዓለ መርቆሬዎስ በደረሰ ጊዜ መንበረ ንግሥት ልጀቷ ማርያም ቤተክርስቲያን በሊቃውንት ትመላለች፣ አጸዷ ሥር ምዕመናኑ ይሰባሰባሉ፡፡ ታቦቱ ከመንበሩ ሲወጣ እልልታው ይደምቃል፣ ምስጋናው ያይላል፣ ፈረሰኞች ያጅቡታል፣ በታላቅ ክብር ወደ ታሪካዊ አጅባር ሜዳ ይወርዳል፤ በማደሪያውም ያርፋል፡፡ አጅባር በሊቃውንት እንደተመላች፣ በመልካሙ ማዕዛ እንደታወደች፣ በምዕመኑ እንደታጀበች ታድራለች፡፡

በነጋም ጊዜ ፈረሰኞቹ ታቦታቸውን በክብር ያጅቡ ዘንድ ይሰባሰባሉ፣ አምሳለ እርግብ የመሰሉ ምዕመናን ነጫጭ ለብሰው፣ ጎዳናዎችን ሞልተው ወደ አጅባር ሜዳ ይጓዛሉ፤ በአጅባር ሜዳ ጀግኖቹ በፈረሶቻቸው ተቀምጠው ሽምጥ ይጋልባሉ፣ አጅባር በጀግኖቹ ትጨነቃለች፣ ምድር በደስታ ትዋጣለች፣ መልካሙን ነገር ታያለች፡፡ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአለቃ ገብረሃና የባሕል ጥናት ዳይሬክተርና የታሪክ መምህሩ መሠረት ወርቁ በአጅባር ሜዳ ነገሥታቱ፣ መኳንንቱ፣ መሳፍንቱ እና የጦር አበጋዞች የፈረስ ጉግስ የሚያዩበት፣ የሚጫወቱበት፣ ሽምጥና የፈረስ ላይ ውጊያ ልምምድ የሚያደርጉበት ጥንታዊ ታሪክ ያለው ነው ይሉታል፡፡

በበዓለ መርቆሬዎስ በቀደመው ዘመን ፈረሰኞች ያደርጉት የነበረው አኹንም ይደረጋል፣ በጦር መትቶ ራሱን በጦር ይከላከላል፣ መትቶ ከጠላት ራሱን ያርቃል፣ ጀግኖች አባቶች በጦር ሜዳ ያደርጉት የነበረውን የጦር ስልት በአጅባር ያሳያሉ፡፡ ጀግኖች የጦር ልብሳቸውን ይለብሳሉ፣ ጋሻና ጦራቸውን ይይዛሉ፣ ፈረሳቸውን ሸልመው በአጅባር ሰማይ ሥር እንደ አሻቸው ይኾናሉ፡፡ አጅባር በሰው ተጨንቃ ትውላለች፣ ሰዓቱ በደረሰም ጊዜ ታቦተ መርቆሪዎስ በታላቅ አጀብ ወደ መንበሩ ይመለሳል፡፡

ደጋጎቹ ደግሰዋል፣ አዳራሹን አሳምረዋል፣ ስሞት አፈር ስኾን እያሉ ማብላትና ማጠጣት ያውቁበታል፡፡ እንግዳ ያቀማጥላሉ፣ ሂዱ ጥንታዊቷ ከተማ ደግሳለች፣ እጆቿን ዘርግታ ትቀበላችኋለች፤ ሂዱ ሃይማኖትን፣ ጀግንነትን፣ እሴትን፣ አንድነትን፣ ባሕልን እና ኢትዮጵያዊነትን ከአጅባር ሰማይ ስር ተመልከቱ፡፡

ተፃፈ በታርቆ ክንዴ
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም

"የአዊ ሕዝብ ከ1932 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ የምንጊዜም ጀግኖች አርበኞችን ገድል ከፈረሰኞች ጋር በመዘከር ብሔራዊ ውለታውን እየተወጣ ይገኛል።" አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል መንግሥት...
31/01/2023

"የአዊ ሕዝብ ከ1932 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ የምንጊዜም ጀግኖች አርበኞችን ገድል ከፈረሰኞች ጋር በመዘከር ብሔራዊ ውለታውን እየተወጣ ይገኛል።"

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
******
የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 83ኛ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልእክት ያስተላለፉት አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ወርሃ ጥር በአማራ ክልል፤ የኢትዮጵያውያንን አይነተ ብዙ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ እሴቶችን ከፍ በማድረግ ለቱሪዝም መስህብነት የተጠቀምንበት ወር ሁኖ ቀጥሏል ብለዋል።

ከጥር 21 - 23 በተለያዩ የባሕል፣ የፓናልና ጥናታዊ ጽሐፍ
ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው የአገው ፈረሸኞች ማኅበር በዓል ከ1932 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ የምንጊዜም ጀግኖች አርበኞችን ገድል ከፈረሰኞች ጋር በመዘከር ብሔራዊ ውለታውን እየተወጣ እንደሚገኝም ኃላፊው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

በዓሉ ፈረሶች ለአገው ሕዝብ ሃገሩን ከጠላት ለመከላከል የአርበኞች የጀግንነት ክንዶች ሁነው ማገልገላቸው የሚታወስበት ከመሆኑ በተጨማሪ በሰላም ጊዜም ለማጓጓዣ፣ ለሰርግ፣ ለሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ ለለቅሶ ስርዓት፣ ለእርሻ አገልግሎት በመስጠትም ፈረሶች ለአገው ሕዝብ ልዩ መሆናቸው የሚዘከርበት እንደሆነ ነው አቶ ግዛቸው የተናገሩት።

የአገው ፈረሰኞች በዓል ለየት ያለ እና አንዱ የክልላችንና የሃገራችን የቱሪስት መስህብ ማዕከል እየሆነ የመጣ የወርሃ ጥር ዋና ትዕይንት መሆኑን ያነሱት ኃላፊው በፈረሰኛ ማኅበር የተደራጁ 62 ሺ በላይ አባላት፣ ከ 52 ሺ በላይ ፈረሶች እንዲሁም በነገው ዕለት በሚካሄደው የፈረስ ጉግስ ልዩ ትዕይንት ብቻ 4 ሺ ፈረሶችና ፈረሰኞችን እንደሚያሰልፍ አቶ ግዛቸው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

የፈረሰኛ ማኅበሩ አባላትን ቁጥርም 150 ሺ ለማድረስ ማኅበሩ እየሠራ እንደሚገኝ ታውቋል።

ፈረስ ለአገው ሕዝብም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያዊ ከጀግና ሜዳይ ባለቤትነት እስከ ሥርዓተ ቀብር የማይለይ ከሕይወታችን በእጅጉ የተቆራኘ አገልግሎት ያለው እንስሳ እንደመሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለመላው የአማራ ክልል ሕዝብ አንዱ የመስህብ ማዕከል በማድረግ መላው ዓለም የሚጠራበት ሃብታችን ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል ያሉት አቶ ግዛቸው የአገው ፈረሰኞች በዓልን ዘንድሮ ለ 83ኛ ጊዜ ስናከብር የቀደምት አርበኞች ጀግኖች አባቶቻችንን ገድል ብቻ ሳይሆን ዛሬም በመስዋእትነታቸው ሃገር ያቆሙ የዘመናችን ጀግኖችን በመዘከር ጭምር ነው ብለዋል።

በዓሉን ለየት ባለ የፈረስ ጉግስ ውድድር ትዕይንትና ሌሎች የባሕል ዝግጅቶች ማክበራችን የአካባቢውን ማኅበረሰብ ታሪክ፣ ባህልና ልዩ ልዩ በጎ እሴቶችን ከፍ አድርጎ በማሳየት የቱሪዝም ሃብት ልማታችን ማሳለጫ ለማድረግ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው በዓሉ የሕዝብን አንድነት የበለጠ የምናሰፋበት፤ ባሕልና ሌሎች እሴቶቻችንን ለመላው ዓለም የምናስተዋውቅበት እንዲሁም በጋራ ጉዳዮች ላይ የምንመክርበት እንደሆነም ገልጸዋል።

ይህንን በዓል ስናከብር የሕዝባችንን የሃገረ መንግሥት ግንባታ አስተዋጽኦና ነባር እሴቶች በማስተዋወቅ እንዲሁም ሃገራችንን በልዩ ገጽ በማሳየት በዓሉን ለየት ያለ የምድራችን ገጽታ እንዲሆን ለማድረግ ነውም ብለዋል።

መላው የክልላችን ሕዝብ ይህንን በዓል በእንጂባራ ከተማ ለማክበር ከሃገር ውጭም ሆነ ከውስጥ ለሚመጡ እንግዶች የተሻለ እንክብካቤ በማድረግና ለጎብኝዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር እንግዶቻችን የባሕል አምባሳደሮቻችን እንዲሆኑ ሁሉም የበኩልን አስተዋጽኦ እንዲወጣም ኃላፊው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
አማራ ኮሙኒኬሽን






ጥምቀትን፥ የፊልም ቀረፃችሁን በባህር ዳር፣ ቆይታችሁን እኛ ጋር ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን።መልካም ጊዜሚለን ኃይሉእንግዳሰው ሃብቴ(ቴዲ) #ጎንደር    #ኦርቶዶክስ  #ተዋሕዶ  #ቤተክርስቲያ...
21/01/2023

ጥምቀትን፥ የፊልም ቀረፃችሁን በባህር ዳር፣ ቆይታችሁን እኛ ጋር ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን።

መልካም ጊዜ

ሚለን ኃይሉ
እንግዳሰው ሃብቴ(ቴዲ)

#ጎንደር #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን

#ጥምቀት
#አባይ #ጣና



ሪቨርላንድ ሆቴል

በመላው ዓለም ለምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀት አደረሳችሁ!!! መልካም በዓል!!!  #ጎንደር    #ኦርቶ...
18/01/2023

በመላው ዓለም ለምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀት አደረሳችሁ!!!

መልካም በዓል!!!

#ጎንደር #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን

#ጥምቀት
#አባይ #ጣና

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!!!ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ (የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል)“ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዓቢየ...
06/01/2023

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!!!

ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ (የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል)

“ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዓቢየ ወለአለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ”

በድንቁርናና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ፍጹም እውቀት ተሰጣቸው፤ ሞት ባመጣው ምስል ሞትን በመምሰል ለነበሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍስ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው፤ በኃጢአት ለነበሩ ስርየት፤ በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተሰጣቸው ኢሳ.ም 9፣2

መልካም በዓል!!!

ከእናንተ ከውድ ደንበኞቻችን ጋር ይሄው አንድ ዓመት ሆነን!!!ለሆቴላችን ደንበኞች፣ ሰራተኞች እና ወዳጆች በሙሉ ለአንደኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችን እንኳን አደረሳችሁ!🌼🌼🌼እንጉሮጎባሽ!!!ውድ...
26/09/2022

ከእናንተ ከውድ ደንበኞቻችን ጋር ይሄው አንድ ዓመት ሆነን!!!

ለሆቴላችን ደንበኞች፣ ሰራተኞች እና ወዳጆች በሙሉ ለአንደኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችን እንኳን አደረሳችሁ!
🌼🌼🌼
እንጉሮጎባሽ!!!
ውድ የሃገራችን ሰዎች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!🌼🌼🌼

"መስከረም በአበባው ሠርግ በጭብጨባው ይታወቃል” ይላሉ አበው። አንድም መስከረም ርዕሰ ዓውደ ዓመት፣ የዘመን መለወጫ በመሆኑ ወርኃ አደይ ወወርኃ ጽጌ ተብሏል። እናም ኢትዮጵያውያን በርዕሰ በዓልነት ታላቅ ማዕዘን ላይ ያስቀመጡት ወርኃ መስከረም፣ ኃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን አቅፏል። ከነዚህም ውስጥ ከዕንቁጣጣሽ በዓል ቀጥሎ በሠፊው የሚታወቀው በዓለ መስቀል ነው።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በዓለ መስቀል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የተሰቀለበት መስቀል በአይሁድ ከተቀበረበት ሥፍራ መገኘቱን ማስታወሻ በዓል ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ መስከረም ፲፯ ቀን ይህንን በዓል በአደባባይ በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች።

ልክ የዛሬ ዓመት ሥራ የጀመረው ሆቴላችን ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች እንዲሁም በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለመጣችሁ እንግዶች እንኳን አደረሳችሁ ይላል።
መልካም የደመራ በዓል።
እኛም በዓሉን እንዲህ ከወገናችን ጋር አሳልፈናል።🌼🌼🌼


እንቁጣጣሽ!!! 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻ያማረ፣ ፍክት ያለ፣ ደስስስ የሚል አዲስ ዓመት ይሁንልን።🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻  #እንቁጣጣሽ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
10/09/2022

እንቁጣጣሽ!!! 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ያማረ፣ ፍክት ያለ፣ ደስስስ የሚል አዲስ ዓመት ይሁንልን።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

#እንቁጣጣሽ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

Master Room "> RIVERLAND HOTELA best placefind our moreRIVERLAND HOTEL "> RIVERLAND HOTELA best placefind our moreBed Room "> RIVERLAND HOTELA best placefind our more Welcome to Riverland Hotel Bahir Dar, Ethiopia READ ABOUT US OUR ROOMS DISCOVER NEWS UPDATE From: $20.00 / Night Single Bed 25m2 City...

እናታችሁን ማን ብላችሁ ትጠራላችሁ?"እናቴ እንጨት ተሸክማ ነው ያስተማረችኝ"💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤የእናትነት ውለታ እንዲህ ሲገለፅ ደስስስ ይላል። እናትን የሰጠኸን ...
16/07/2022

እናታችሁን ማን ብላችሁ ትጠራላችሁ?

"እናቴ እንጨት ተሸክማ ነው ያስተማረችኝ"
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
የእናትነት ውለታ እንዲህ ሲገለፅ ደስስስ ይላል። እናትን የሰጠኸን ፈጣሪ ስምህ የተመሰገነ ይሁን።
የዛሬው ተመራቂ " እናቴ እንጨት ተሸክማ ነው ያስተማረችኝ" 😍ብሏል። ልብ ይነካል😭
ክብር እኛን ለማሳደግ እንቅልፋቸውን አጥተው ረሃብቨ ብርድ፣ ፀሐይ ወዘተ ሳይበግራቸው ሁላችንንም አሁን ያለንበት ደረጃ ላደረሱን!

ሆቴላችን ለተመራቂዎቹ እና ለአስመራቂ እናቶች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል።

እናትነትን እናክብር!!!
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
#እናቴ

Master Room "> RIVERLAND HOTELA best placefind our moreRIVERLAND HOTEL "> RIVERLAND HOTELA best placefind our moreBed Room "> RIVERLAND HOTELA best placefind our more Welcome to Riverland Hotel Bahir Dar, Ethiopia READ ABOUT US OUR ROOMS DISCOVER NEWS UPDATE From: $20.00 / Night Single Bed 25m2 City...

ከጋሽ   ጋር በ #ሪቨርላንድ ሆቴል።ጥሩ ጊዜን በሆቴላችን ያሳልፉ።አድራሻ:- ባህር ዳር፣ ከአባይ ድልድይ 200ሜ ርቀት ወደ ጎንደር መውጫ
07/06/2022

ከጋሽ ጋር በ #ሪቨርላንድ ሆቴል።

ጥሩ ጊዜን በሆቴላችን ያሳልፉ።
አድራሻ:- ባህር ዳር፣ ከአባይ ድልድይ 200ሜ ርቀት ወደ ጎንደር መውጫ

Master Room "> RIVERLAND HOTELA best placefind our moreRIVERLAND HOTEL "> RIVERLAND HOTELA best placefind our moreBed Room "> RIVERLAND HOTELA best placefind our more Welcome to Riverland Hotel Bahir Dar, Ethiopia READ ABOUT US OUR ROOMS DISCOVER NEWS UPDATE From: $20.00 / Night Single Bed 25m2 City...

መልካም የትንሳኤ በአል።
24/04/2022

መልካም የትንሳኤ በአል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Riverland Hotel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Riverland Hotel:

Share

Category