Inside Gojjam

Inside Gojjam Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Inside Gojjam, Tourist Information Center, Gojjam, Bahir Dar.

ባህርዳርን የፈተኗት "ጎጠኞቹ" በቃችሁ ይባሉ!!ያለፉት አመታት ባህርዳር ላይ የነበረው ትግል ከተማዋ ከተፈጥሯዊ ወዟ ውጪ ሰርቶ የሚለውጣት መሪ አላገኘችም የሚል ነበር። የባህርዳርን የትናንት...
11/07/2026

ባህርዳርን የፈተኗት "ጎጠኞቹ" በቃችሁ ይባሉ!!

ያለፉት አመታት ባህርዳር ላይ የነበረው ትግል ከተማዋ ከተፈጥሯዊ ወዟ ውጪ ሰርቶ የሚለውጣት መሪ አላገኘችም የሚል ነበር። የባህርዳርን የትናንትና የዛሬ ለውጦች ለማየት በትነሹ አይንን መግለጥ በቂ ነው። ከተማዋ በሶስት አመታት ውስጥ መሰረታዊ ወደሚባል ከፍታ ተሻግራለች። ይህ ከፍታ ያለፈበት ሂደት በዛሬ ውጤቱ ብቻ የሚለካ አይደለም። ይልቁንም ደም የተከፈለበት ውጤት ነው። ይህንን ዘርዘር አድርጎ ማየት ይገባል።

ከጥይት ድምፅ መናኸሪያነት ወደምቹ ከተማነት

ከተማዋ እንደሌላው የክልሉ አካባቢ ሁሉ የሰላም እጦት ወላፈኑ የገረፋት ነበረች። የክልሉ የፖለቲካና ኢኮኖሚ የስበት ማዕከል በመሆኗ ምክንያትም ተደጋጋሚ ሰላሟን የማደፍረስ ሙከራዎች ነበሩ። የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ከመሰረቱ ቀይሯል። በ12:00 ሰዓት ሰው አልባ ይሆኑ የነበሩት የባህርዳር አስፓልቶች ዛሬ ሌሊቱን ሙሉ ሰው ይንቀሳቀስባቸዋል። የሌሊት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰላት ነው። ይህ እንዲሆን ብዙ ዋጋ ተከፍሏል።

በፖለቲካ ሸፍጥ የተሸፈነው ውምብድና

በከተማዋ ውስጥ ሰርጎ ገብቶ የለየለት ውምብድና ላይ የተሰማራ ሀይል ሰውን እያገተ፣ እየዘረፈና እየገደለ በራሱ የፕሮፖጋንዳ ክንፍ በኩል ደግሞ ከተማዋን መንግስት አልባ ለማስመሰል ጥሯል። እንዲህ ያለውን የተደባለቀ ሴራ ለመቁረጥ ብዙ ርቀት ተሂዶ እንዲመክን ተደርጓል። የባህርዳር መሪዎች እንዲህ ያለውን ርምጃ በመውሰዳቸው ሊመሰገኑ ይገባል።

የማይካዱ እውነቶች

👉የከተማ ልማትን ከዲሽ ቦይና ኮብል ድርደራ እሳቤ አውጥቶ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ አድርጓል። በዚህም በርካታ ደረጃቸው የተጠበቀ የአስፓልት መንገዶችና ማስዋቢያዎች ተገንብተዋል።
👉የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ አዳዲስ ባሶችን ከመግዛት እስከስምሪት ቁጥጥርና ማስተካከያ ድረስ ተሰርቷል።
👉የግለሰብና የቡድን ጥያቄ ያላቸውና በተጓተተ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ይሰቃዩ የነበሩትን እያደመጡ፣ እየመዘኑና እየወሰኑ ችግሩን ለመፍታት ተሰርቷል።
👉የክፍለ ከተማና የመምሪያ ተቋማት ላይ ከፍተኛ መሻሻል መጥቷል።
👉የመንግስት ሰራተኞች ቤት መስሪያ ቦታ የመስጠት ሂደት፣ የኢንቨስትመንት መፋጠን፣ ወደልማት ያልገቡ ፕሮጀክቶች ርምጃ፣ ድለላን ከመንግስት መዋቅር የማራቅ ጅምሮች....እነዚህ ከበጣም ጥቂቶች ናቸው።

እነ ካልበላን እናፍስሰው ቡድን

የባህርዳር ከተማ ዋነኛ ጋንግሪኖች የሷን ወተት እየጠጡ የጠገቡ ቁንጣናሞች ናቸው። የከተማው አመራር ሊወቀስ የሚችልበት አንዱ ችግር እነዚህን ግለሰቦች ተሸክሞ መቀጠሉ ነው። ከመንደራቸው አሻግረው መመልከት የማይችሉ ደካሞች የከተማዋን አመራር በተለይም ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን በሐሰት እየወነጀሉ ለማድከም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ ነው። በአስተባባሪ አመራርና በካቢኔ ውስጥ ተቀምጠው ውሳኔዎችን እነአያሌው መንበርን ለመሰሉ በጎጥ ለተከራዩአቸው ግለሰቦች የሚሸጡ ከሀዲዎች የከተማ አስተዳደሩ ፈተና ናቸው። እዚህ አካባቢ በክልሉም ሆነ በከተማው ላይ የሚስተዋል አጉል የማባበል አካሄዶች መታረም አለባቸው። እነዚህ ግለሰቦች የከተማውም የክልሉም ስጋት ናቸው። ከአማራነት የአንድነት ቅንፍ ወጥተው አይናቸውን በጎጥ ፎጣ የሸፈኑ ሰነፎች ከአሜሪካ እስከ ኡጋንዳ ከእስራኤል እስከ አውስትራሊያ በተዘረጋ የክፋት ገመዳቸው የባህርዳርን አመራር ለመጥለፍ ደጋግመው ሞክረዋል። ሆኖም እየታወቀ በመቻል ለማለፍ ተሞክሯል። ይህ ግን እዚህ በላይ እንዲጓዝ መፍቀድ ተገቢ አይደለም። ተቆራርጦ ከመዋቅሩ እየነቀሉ መጣል ይገባል።

ለመታሰር ትኬት ቆርጦ ከአሜሪካ የተመለሰው ሰሜ ባላገር(ያሬድ ሹመቴ)ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ሐምሌ 7 ቀን 1994 ዓ.ም. ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ባምቢስ ድልድይ አካባቢ መኪና ሲ...
16/06/2026

ለመታሰር ትኬት ቆርጦ ከአሜሪካ የተመለሰው
ሰሜ ባላገር
(ያሬድ ሹመቴ)

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ሐምሌ 7 ቀን 1994 ዓ.ም. ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ባምቢስ ድልድይ አካባቢ መኪና ሲያሽከረክር አደጋ ደርሶ ነበር።

በአደጋው ወቅት አብሮት የነበረውና የታወቀው የግጥምና ዜማ ደራሲ ግሩም ተስፋዬ ሕይወቱ አለፈ።

"በቸልተኝነት መኪና በማሽከርከር የሰው ነፍስ እንዲጠፋ አድርገሃል" የሚል ክስ ተመሰረተበት።

ፍርድ ቤቱ የሰማኸኝ በለውን መከላከያ ምስክሮች ከሰማ በኋላ፣ በቸልተኝነት የሰው ሕይወት በማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ አድርጎት በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አሰናበተው።

የገንዘብ ቅጣቱን እንዲከፍል ከተደረገ በኋላ በነፃ ቢሰናበትም ዓቃቤ ሕግ "ቅጣቱ እጅግ የቀለለ ነው፣ አደጋው ሆን ተብሎ የተደረገ ነው" በሚል የቅጣት ማሻሻያ ይግባኝ ጠየቀበት።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት መዝገቡን እንደገና መርምሮ የቀድሞውን የገንዘብ ቅጣት በመሻር፣ በድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ላይ የ 5 ዓመት ጽኑ እስራት ፈረደበት።

የእስር ውሳኔው ከመተላለፉ አስቀድሞ ሰማኸኝ በለው ለሥራና ለሙዚቃ ዝግጅት ወደ አሜሪካ አገር ሄዶ ነበር። ፍርዱን የሰማውም አሜሪካ እያለ ነበር።

"የፖለቲካ አሻጥር ተሰርቶብኝ ነው የተጠየቅኩት እንጂ ጓደኛዬ ሞቶ እኔ በመትረፌ ምክንያት ብቻ ልጠየቅ አይገባም" ብሎ ቢያምን፤ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈበትን እና እሱ የማያምንበትን የእስር ፍርድ ተቃውሞ አሜሪካ መቅረት የሚችልበት ዕድል ቢኖረውም፣ "የጓደኛዬ ደም እያሳደደኝ በሰው አገር በስደት መኖር አልፈልግም፤ ፍርዴን ጨርሼ በነፃነት መኖር አለብኝ" በሚል የሕሊና ውሳኔ በራሱ ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ወሰነ።

ሰሜ ሳይውል ሳያድር የአውሮፕላን ትኬቱን ቆርጦ ወደ አገር ቤት እንደተመለሰ በቀጥታ ወደ ተፈረደበት እስር በፈቃዱ ገባ።

ይሁን እንጂ ሙሉውን 5 ዓመት አልታሰረም።

በእስር ቤት ውስጥ በነበረው እጅግ መልካም ሥነ-ምግባር ፤ ኪነጥበብ ክፍል ውስጥ ለሰጠው ከፍተኛ አገልግሎት፣ እና እስረኞችን የሙዚቃ ትምህርት ሰጥቶ በማስመረቅ ባበረከተው ቀና አስተዋጽዖ የይቅርታ ዕድል አግኝቶ ከ 2 ዓመት ከስድስት ወር እስራት በኋላ በነፃ ተለቋል።

እንዲህ ያለ ሞራል የነበረው ተወዳጅ ከያኒ ነው ያጣነው።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው
ነፍስህ በሰላም ትረፍ

18/06/2025

የባህርዳር ከተማ በተለየ እድገት ላይ ናት። ይህ እንዲሆን የደከሙ ሁሉ ምስጋና ይግባቸው። 24/7 የሚሰሩላትና የሚመሯት ጀግኖች እንዳሏት ታይቷል። ከተማዋ ከነበራት የተለየ ተፈጥሮ ላይ ድንቅ ስራ ተጨምሮላታል። ባለዘምባባዋ ንግስት🌴🌴🌴

18/06/2025

ከተማዋ❤ ውቢቷ ባህርዳር 🌴🌴🌴

18/06/2025

የባህር ዳር ከተማ አዲስ ገፅታ። ከተማዋ ከውበቷ ላይ ውበት ደርባለች

ዳሞት አይፈራም ሞት!!
25/07/2024

ዳሞት አይፈራም ሞት!!

ተቀማጥለሽ አድገሽ ጎጃም ላይምኔን ልስጥሽ ከፍቅር በላይ
25/07/2024

ተቀማጥለሽ አድገሽ ጎጃም ላይ
ምኔን ልስጥሽ ከፍቅር በላይ

ባህርዳር-ጎጃም- አማራ
25/07/2024

ባህርዳር-ጎጃም- አማራ

My city Bahirdar- gojjam
23/07/2024

My city Bahirdar- gojjam

Abay-  The desert, monkeys show, river, challenge , view ... what a beautiful nature. what agiven resource . Gojjam.
14/12/2022

Abay- The desert, monkeys show, river, challenge , view ... what a beautiful nature. what agiven resource . Gojjam.

Address

Gojjam
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Inside Gojjam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share