Narga tour Ethiopia

Narga tour Ethiopia Narga Ethiopia Tour (NET ) is a well organized private tour campany providing tour, car rental and many other related services throught Ethiopia .
(1)

በስቅለተ ዓርብ የክርስቶስን መስቀል በልዩ ሁኔታ እናከብራለን፤ ለሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት እንገልጻለንwww.nargatour.comWww.nargahotel.netበዐብይ ጾም ወቅት በእለተ አ...
27/09/2025

በስቅለተ ዓርብ የክርስቶስን መስቀል በልዩ ሁኔታ እናከብራለን፤ ለሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት እንገልጻለን
www.nargatour.com
Www.nargahotel.net

በዐብይ ጾም ወቅት በእለተ አርብ እለት የክርስቶስ ሕማም በማስታወስ የመስቀል መንገድ ጸሎት ይደረጋል

ቤተ ክርስቲያን

በስቅለተ ዓርብ የክርስቶስን መስቀል በልዩ ሁኔታ እናከብራለን፤ ለሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት እንገልጻለን

በመሰቀል ላይ የተሰቀለውንና የቆሰለውን ክርስቶስ ማስታወስ በስቃይ ውስጥ ለሚገኙ እና ተስፋ በሌለው ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሰዎች ትልቅ ተስፋና ማጽናኛ ነው።

በሥቅለተ ዓርብ ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ለይ ተሰቅሎ መሞቱን እናስባለን፣ በዚህ ዕለት እኛ ካቶሊኮች መስቀልን በልዩ ሁኔታ የምናከብረው፣ አከባበሩም የሚፈጸመው በሚከተለው ዓይነት ነው።

- ትልቅ መስቀል የወይን ጠጅ ቀለም ባለው ጨርቅ ተሸፍኖ ካህኑ ከፍ አድርጎ ተሸክሞት ወደ ቤተክርስቲያን ይገባል።

- ካህኑ መሸፈኛ ጨርቁን እያነሳ ሶስት ጊዜ “እነሆ ዓለምን የሚያድን ጌታ የተሰቀለበት የእንጨት መስቀል” እያለ ይዘምራል፤እንዲህ እየዘመረ ቤተክርስቲያኑን አቋርጦ ያልፋል።

- ምዕመናኑ ደግሞ በጉልበታቸው ተንበርክከው «ኑ ለእርሱ እንስገድለት» እያሉ ይመልሳሉ።

- መሸፈኛ ጨርቁ ሙሉ በሙሉ ከተነሳ በኋላ ምዕመናኑ አንድ በአንድ ወደፊት እየመጡ በመስቀሉ አጠገብ በመንበረከክ፤ በእጃቸዉ በመንካት ወይም በመሳም መስቀሉን ይሳለማሉ።

አንዳንድ ሰዎች ምናልባት መስቀሉን እንዲህ ባለ ሁኔታ በማክበራችን የእንጨት መስቀልን በመንበርከክና በመሳምም ጭምር ታመልካላችሁ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፣ ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች በአክብሮት እንዲህ እያልን እንመልሳለን። “እኛ ካቶሊኮች የእንጨት መስቀልን አናመልከም፤ እኛ የምናመልከው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ መካከል የሚኖረውንና ህያው የሆነውን ክርስቶስን ነው፣ ስለሆነም “ኑ ለእንጨት መስቀል እንስገድለት” አንልም፡ ይልቁንም “ ለርሱ (ለክርስቶስ) እንስገድለት” ነው የምንለው፤ በመካከላችን ለሚገኘው ለክርስቶስ እንስገድለት ማለታችን ነው፣ መስቀል ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ ለእኛ ያሳየውን ትልቅ ፍቅር ያስታውሰናል። ልባችንንና አእምሮአችንን ወደዚህ ሀሳብ ያነሳሳናል፣ ክርስቶስን በልባችንና በአእምሮአችን በመያዝ ለእርሱ ሰግደን እሱን እናመልካለን እንጂ እፊት ለፊታችን የሚታየውን መስቀሉ የተሠራበትን የሞተ እንጨት አይደለም፣ በየዕለት ሕይወታችን የሚሆኑ ነገሮች እዚህ ላይ ማሰብ እንችላለን፡ ለምሳሌ አንዲት ሙሽሪት በድንገተኛ አደጋ የሞተባትን የባሉዋን ፎቶ ልትስም ትችላለች፤ ታድያ በዚህ ሰዓት ይህች ሴት የምትስመውና የምትወደዉ ፎቶው የታተመበት ወረቀትን ሳይሆን ያንን ውድ ባሉዋን ነው፤ ፎቶው ያንን ወድ ባሏን እንድታስተውስ እንድትስመውና እንድትወደው የሚረዳት መሣሪያ ብቻ ነው።

ሰዎች የተሰቃየውንና የተሰቀለውን የክርስቶስን አካል ምስል በመስቀል ላይ የሚያኖሩት

መልካም መሰቀል 2018

 #እንቁጣጣሽ 2018ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የ...
09/09/2025

#እንቁጣጣሽ 2018
ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

#ሁለተኛው የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ
በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ
በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን
ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

#አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን
መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብራቸውና ከሚያዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጅ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። እንደ ዕፅዋት ሁሉ ሰው በመስከረም ላይ በተስፋ ስሜት ይለመልማል። ከቅዱስ ዮሐንስ ዋዜማ ጀምሮ በየቤቱ ጨፌና ቄጠማ ይጐዘጐዛል። አበባ በሥርዓት እየተዘጋጀ በየቦታው ይቀመጣል። በተለይም ልጆች አዳዲስ ልብሳቸውን ለብሰው በደስታ ይፈነድቃሉ።

ዝናሙን ዝናመ ምሕረት፣ እህሉን እህለ በረከት ያድርግልን፣ ሰላም ይስጠን። አሜን።

መልካም በዓል አንቁጣጣሽ ! 2018

መንኮሳቱ ይጣራሉ!  | በ1313 ዓ.ም. የተመሠረተው የሴቶች እንጦስ ኢየሱስ ገዳምአምና የጣና ሐይቅ በመሙላቱ ምክንያት በተፈጠረ ከፍተኛ ማዕበል በደሴቱ (በገዳሙ) ዳርቻ የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ...
22/07/2025

መንኮሳቱ ይጣራሉ!

| በ1313 ዓ.ም. የተመሠረተው የሴቶች እንጦስ ኢየሱስ ገዳም

አምና የጣና ሐይቅ በመሙላቱ ምክንያት በተፈጠረ ከፍተኛ ማዕበል በደሴቱ (በገዳሙ) ዳርቻ የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ እፅዋትን እየነቀለ ጥሏቸው ነበር

ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ነው። ርዝመቱ 84 ኪ.ሜ.፣ ስፋቱ 65 ኪ.ሜ ሲሆን በአጠቃላይ 3,600 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል።

በአጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች አሉት። ከእነዚህ መካከል አንዱ የእንጦስ ደሴት ነው።

እንጦስ ኢየሱስ አንድነት ገዳም ከሰፊው የጣና ሀይቅ ውስጥ እንጦስ በተባለች ትንሽ ደሴት ውስጥ የሚገኝ የሴቶች ገዳም ነው፡፡

ገዳሙ ከባህር ዳር ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በ4 ኪሎ ሜትር ርቀት (ከ45 ደቂቃ የጀልባ ጉዞ) በኋላ ይገኛል፡፡

ከእንጦስ ሲደርሱ ትይዩ የክብራን ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ይመለከታሉ፡፡

የእንጦስ ኢየሱስ አንድነት ገዳም በ1314 ዓ.ም ከሰባቱ ክዋከብት አንዱ በሆኑት አቡነ ዘዮሐንስ እንደተመሰረት ይነገራል፡፡

በጣና ሐይቅ ዙሪያዋን በተከበበች በአንዲት አነስተኛ ደሴት ላይ የተመሰረተው ታሪካዊው ገዳም በውስጡ ከያዛቸው ውድ ቅርሶች በተጨማሪ በበርካታ አዕዋፍት እና በልዩ ልዩ ሀገር በቀል እፅዋት የተሸፈነ በመሆኑ በቦታው መገኘት ልዩ መንፈሳዊ እርካታን ያጎናጽፋል፡፡

የገዳሙ አስተዳዳሪ እማሆይ ወ/ሥላሴ ገ/ሚካኤል
እንደተናገሩት " በገዳሙ 30 የሚሆኑ ሴት መነኮሳት የሚኖሩበት ሲሆን በዚህ ዓመት የጣና ሐይቅ በመሙላቱ ምክንያት በተፈጠረ ከፍተኛ ማዕበል በደሴቱ (በገዳሙ ዳርቻ) የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ እፅዋትን እየነቀለ እያጣላቸው እና ገዳሙ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው"።

ከእንጦስ በተጨማሪ ዳጋ እስጢፋኖስ፣ ክብራን ገብርኤል እና ሌሎችም ጣና ውስጥ የሚገኙ ገዳማት በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡

***

እንጦስ ደሴት ላይ በ1313 ዓ.ም. በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን ገዳም ተመስርቷል። ገዳሙን የመሰረቱት ደግሞ አቡነ ዘዮሐንስ ይባላሉ።

*አቡነ ዘዮሐንስ "ከሰባቱ ከዋክብት" ደቀ መዛሙርት አንዱ ናቸው።

*ሰባቱ ከዋክብት የሚባሉት አኩስም አቅራቢያ የሚገኘው የደብረ በንኮል ገዳም መሥራች አቡነ መድኅነ እግዚእ ደቀ መዛሙርት ናቸው።

ገዳሟን የመታደግ ልዩ ልዩ እየተሰሩ ናቸው

4261117957233018
የአባይባንክ

1000406999231
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ይደዉሉልን
0913362024

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

ኢትዮጵያ የአለም ቅርስ በማስመዝገብ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች  leads in Africa with its UNESCO World Heritage Sites, preserving treasures reflec...
22/07/2025

ኢትዮጵያ የአለም ቅርስ በማስመዝገብ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች

leads in Africa with its UNESCO World Heritage Sites, preserving treasures reflecting our rich history, inspiring generations. These sites are invaluable sources of life, with outstanding universal value, narrate our world’s remarkable history.
www.nargatour.com

www.nargatour.com
12/06/2025

www.nargatour.com

4315 likes, 71 comments. Check out Abay Go (ጎንደሬው)’s post.

Address

H9PF+RQM, Belay Zeleke Road, Bahir Dar3. 4 Km
Bahir Dar
H9PF+RQM,BELAYZELEKERD,BAHIRDAR3.4KM

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Narga tour Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category