Erkab Tour & Travel

Erkab Tour & Travel ✧ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጉዞ ትኬት
✧ የመኪና ኪራይ
✧ የሆቴል Reservation
"መንገድዎን ያቅኑ ፤ ጫናዎን ያቅሉ!"

16/05/2026
09/05/2026

ዛሬ ደስታ ነው🙏

.eth Visit AmharaTicketmaster***እርካብ የጉዞ ወኪል0920425320
06/05/2026

.eth
Visit Amhara
Ticketmaster
***
እርካብ የጉዞ ወኪል
0920425320

ቀዳም ስዑር+++በመስቀሉ ሰላምን አደረገ!  0920425320
11/04/2026

ቀዳም ስዑር
+++
በመስቀሉ ሰላምን አደረገ!

0920425320

"ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን፥ ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።" (ሮሜ 6:5)***  0920425320
10/04/2026

"ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን፥ ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።" (ሮሜ 6:5)
***

0920425320

ኢትዮጵያ ለትራንዚት መንገደኞች የ7 ቀን ነፃ የቪዛ አገልግሎት ልትፈቅድ ነው ++++++++++++++++++++የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ቱሪዝምን ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሻሻል ...
06/04/2026

ኢትዮጵያ ለትራንዚት መንገደኞች የ7 ቀን ነፃ የቪዛ አገልግሎት ልትፈቅድ ነው
++++++++++++++++++++
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ቱሪዝምን ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሻሻል ለትራንዚት መንገደኞች እስከ ሰባት ቀናት የሚቆይ ነፃ የቪዛ አገልግሎት በቅርቡ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን ገለጸ።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው የቪዛ ማሻሻያ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል።
ይህ ማሻሻያ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አልፈው የሚሄዱ መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ ሰባት ቀናት ያለምንም የቪዛ ክፍያ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም በዓመት በአውሮፕላን ማረፊያው በኩል የሚያልፉ ከ15 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ወደ ሀገር ውስጥ በመሳብ የቱሪዝም ዘርፉን አሁን ካለበት በእጥፍ ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።
ማሻሻያው መንገደኞች በአውሮፕላን ማረፊያ ረጅም ሰዓታት ከማሳለፍ ይልቅ አዲስ አበባንና ሌሎች የበረራ አማራጭ ያለባቸውን የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲጎበኙ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።
ይህ አሠራር በቢሾፍቱ እየተገነባ ካለው ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያን ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
የ’ስቶፕ ኦቨር’ ቱሪዝምን ውጤታማ ለማድረግ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅንጅት ለመሥራት ስምምነት ማድረጋቸውን አቶ ስለሺ አስታውሰዋል።

ሰሙነ ሕማማት***እርካብ የጉዞ ወኪል09204253200911730234
05/04/2026

ሰሙነ ሕማማት
***
እርካብ የጉዞ ወኪል
0920425320
0911730234

https://youtu.be/9lWlFQ5UFno?t=200
30/03/2026

https://youtu.be/9lWlFQ5UFno?t=200

#በነገራችንላይ የ"በነገራችን ላይ" ዝግጅታችን ድንበሮችን አቋርጦ ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ደርሷል! ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ከተከበሩት የታሪክ ምሁ....

29/03/2026

የኔዘርላንዱ ልዑል በርንሃርድ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከጎበኙ በኋላ ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በኮክፒት ውስጥ ሆነው የተነሱት ፎቶግራፍ ፤
ጥር 22 ቀን 1961 ዓ.ም

Prince Bernhard of the Netherlands, after visiting the Lalibela rock-hewn churches, photographed from the cockpit of an Ethiopian Airlines plane; January 30, 1969.

Ethiopian Airlines



youtube.com/

ባሕር ዳር የውብ ዳር***@እርካብ የጉዞ ወኪልትኬትዎን እኛ ጋር ይቁረጡ!09204253200911730234
26/03/2026

ባሕር ዳር የውብ ዳር
***
@እርካብ የጉዞ ወኪል
ትኬትዎን እኛ ጋር ይቁረጡ!
0920425320
0911730234

20/03/2026

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የገበያ ዕድል ፈጠረ

| በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተጠበቀ የገበያ ዕድል ይዞ መጥቷል። በእስራኤል፣ አሜሪካ እና ኢራን መካከል ያለው ግጭት በባህረ ሰላጤው አገራት የአየር ትራንስፖርት ላይ መስተጓጎል በመፍጠሩ፣ በርካታ የደቡብ አፍሪካ መንገደኞች አዲስ አበባን እንደ ዋነኛ የመሸጋገሪያ (Hub) ማዕከል መጠቀም ጀምረዋል።

የኢንዱስትሪ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የሚደረጉ የቦታ ማስያዝ (Bookings) መጠኖች የ110\% ድንገተኛ ጭማሪ አሳይተዋል። የFlight Centre South Africa የሥራ ኃላፊ ሱ ጋሬት እንደገለጹት፤ ይህ ለውጥ የመጣው በተለመዱት የበረራ መስመሮች ላይ በተፈጠሩ ስረዛዎችና የአየር ክልል ገደቦች ምክንያት ነው።

የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ አየር መንገዱ አሁን ካለው ቀውስ በፊትም ቢሆን በቁልፍ የጉዞ መስመሮች ላይ የበላይነቱን እያጠናከረ ቆይቷል፦

* ወደ ሕንድ፦ በ2025 በጆሃንስበርግ-ሙምባይ መስመር በአዲስ አበባ በኩል ከ69,000 በላይ መንገደኞችን በማጓጓዝ ቀዳሚው ምርጫ ሆኗል።

* ወደ ብሪታንያ፦ በደቡብ አፍሪካ እና በእንግሊዝ መካከል ባለው መስመር ኤምሬትስን በ39,000 መንገደኞች በመብለጥ ትልቁ ቀጥተኛ ያልሆነ አጓጓዥ ለመሆን በቅቷል።

* ወደ አሜሪካ፦ በደቡብ አፍሪካ እና በአሜሪካ መካከል በሚደረግ ጉዞ ከዩናይትድ እና ከዴልታ በመቀጠል በሦስተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ጠንካራ ተወዳዳሪነቱን አስመስክሯል።

ይህ ወቅታዊ ክስተት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ስትራቴጂካዊ ተመራጭነት ይበልጥ እያሳደገው ይገኛል ያለው ካፒታል ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

#ጌጡ

Address

St Goerge
Bahir Dar

Telephone

+251920425320

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Erkab Tour & Travel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Erkab Tour & Travel:

Share