Tankwa Tours & Travel Agency

Tankwa Tours & Travel Agency Looking for the vacation experience of a life time? Welcome to Ethiopia. P.O. Box: 2021 Bahir Dar, Ethiopia.

Tankwa Tours & Travel Agency is your option for responsible and nature friendly tour operator in Ethiopia. We are always available and serve you excellent tour experience as you wished in your mind. Address:
Addis Abeba, wereda 10 sub-city Gulelie, and Bahir Dar at Lake Tana ferry boat authority. For all tour information and bookings please call or email us at:
M: +251 (0) -9

11-76-49-33
+251(0) -918-01-64-66
+251(0) -947-05-80-80
Experience Eco-Friendly and Sustainable Community Tourism in Ethiopia!

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው  በስላም አደረሳችሁ!መልካም በአል!HAPPY EASTER!
20/04/2025

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በስላም አደረሳችሁ!

መልካም በአል!
HAPPY EASTER!

ዒድ ሙባረክ!
29/03/2025

ዒድ ሙባረክ!

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ !ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎትየሁሉም ምርጫ!
01/03/2025

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ !
ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት
የሁሉም ምርጫ!

Did you know that World Cancer Day is celebrated worldwide?International Cancer Day has been celebrated by the Union for...
04/02/2025

Did you know that World Cancer Day is celebrated worldwide?

International Cancer Day has been celebrated by the Union for International Cancer Control since 2000 to raise awareness about cancer.

Tankwa Tours and Travels is supporting what it can because it believes that health is the most important thing. This special day not only reminds us of the importance of health care, healthy living, and supporting people with cancer, but also raises awareness that early screenings, understanding symptoms, nutrition, and an active lifestyle are key principles to staying cancer-free.

Cancer, like any health problem, is curable if detected early, prevented, and treated properly. Achieving this requires individual, community, and national commitment.

According to studies, breast cancer is the most common type of cancer in Ethiopia, and the prevalence of all types of cancer is 15.2 to 26 percent, and cancer affecting women is said to be 29.3 to 37 percent. Studies show that breast cancer is increasing in Ethiopia.

Experts recommend timely check-ups, proper nutrition, and exercise to build a healthy lifestyle; control our contact with textiles and chemical substances; and avoid dangerous situations to protect our health.

As much as we enjoy when we visit tourist destinations, the satisfaction we visit patients at the hospital is the same, and a small gift to the patients. Support the health institutions as much as we can. Tomorrow is where we will be served if we are sick. Visiting patients who are bedridden from health facilities is a wonderful, educational, and transformative activity. Let's work together to create a healthy world with a better age!

If you need domestic and international flight bookings and other services, we can be reached at our global call center phone numbers at +251942777770 or by switching the last number from 1-5. Also call us at +25191176493.

Let's create healthy and productive world through cooperation!

Tankwa Tours and Travels

The choice for all!

Join us via our social media channels at
Instagram https://instagram.com/tankwa_travels
Facebook https://.facebook.com/travelinethiopia
X https://x.com/TankwaTours
LinkedIn https://.linkedin.com/in/tankwatours
Tiktok https://tiktok.com/
YouTube https://www.youtube.com/
telegram https://t.me/tankwatravels

ዓለም አቀፍ የካንሰር ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ እንደሆነ ያውቃሉ? አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በአለም አቀፍ ካንሰርን ለመቆጣጠር በተቋቋመው ማህበር ( Union for Internat...
04/02/2025

ዓለም አቀፍ የካንሰር ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ እንደሆነ ያውቃሉ?

አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በአለም አቀፍ ካንሰርን ለመቆጣጠር በተቋቋመው ማህበር ( Union for International Cancer Control) እ.ኤ.አ 2000 ጀምሮ ስለካንሰር ግንዛቤን ለማስጭበጥ በማሰብ የሚከበር በዓል ሲሆን ቀድሞ ለመከላከል፣ ሕመሙን ቀድሞ ለማወቅ እንዲሁም ለማከም ያካተቱ ሂደቶች በዓለም አቀፈፍ እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለካንሰር ግንዛቤ የሚጨበጥበት በዓል ነው።

ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት፣ ጤና ከሁሉም በላይ መሆኑን በማመኑ የሚችለውን እየደገፈ ይገኛል። ይህ ልዩ ቀን የጤና እንክብካቤ፣ ጤናማ ኑሮ እና በካንሰር የተያዙትን ሰዎች የመደገፍ አስፈላጊነት ከማስታወሱም በላይ ቅድመ ምርመራዎች ማድረግ፣ ምልክቶችን ማገናዘብ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ንቁ የኑሮ ዘይቤ ከካንሰር ነጻ ሆኖ ለመቆየት ቁልፍ መርሆዎች መሆናቸውን ግንዛቤ ያስጨብጣል።

ካንሰር እንደ ማንኛውም የጤና ችግር፣ በጊዜው ማወቅ፣ መከላከል እና ትክክለኛ ህክምና ሲያገኝ ሊታከም የሚችል በሽታ ነው። ይህንን ለማሳካት የግለሰብ፣ የማህበረሰብ እና በአገር ደረጃ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።

እንደጥናቶች ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የጡት ካንሰር በጣም የተለመደ የካንሰር አይነት ሲሆን ስርጭቱ ከሁሉም የካንሰር አይነቶች ከ15.2 እስከ 26 በመቶ እና ሴቶችን የሚያጠቃ ካንሰር 29.3-37 በመቶ እንደሚደርስ ይነገራል።

ምርመራዎችን በጊዜው ማድረግ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጤና ኑሮን ለመገንባት፣ ከጨርቃ ጨርቅ እና ከኬሚካላዊ ንጥረ ነገሮች ጋር ያለንን ግንኙነት በመቆጣጠር አደገኛ ሁኔታዎችን በማስወገድ ጤናችንን መጠበቅ እንደሚቻል ባለሙያዎች ይመክራሉ።

የጉብኝት መዳረሻዎችን ስንጎበኝ የምንደሰተውን ያክል በየጤና ተቋማቱ ታመው አልጋ ላይ የተኙትን የምንችለውን በመውሰድ ይማራችሁ ስንላቸው የምናገኘው እርካታ ወደር የለውም። የጤና ተቋማትንም ለህሙማን የሚሰጡትን አገልግሎት በምንችለው እንደግፍ፤ ነገ እኛም ከታምን የምንገለገልበት ነውና። ከጤና ተቋማት ተኝተው የሚገኙ ህሙማንን መጎብኘት በነብስ በስጋ የሚያስደስት፣ የሚያስተምር እና የሚለውጥ ተግባር ነው።

የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጉዙ ትኬት ለመቁረጥ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶቻችንን ለመጠቀም ካስፈለገዎ በዓለማቀፍ የጥሪ ማዕከል ስልክ ቁጥሮቻችን በ0942777770 ወይም የመጨረሻውን ቁጥር ማለትም ዜሮን ከ1-5 በመቀያየር ያገኙናል። በተጨማሪም 0911764933 ይደውሉልን፡፡

በትብብር የጤናማ እና ምርታማ ዓለምን እንፍጠር!

ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት

የሁሉም ምርጫ !

የማህበራዊ ሚድያ ገጾቻችንን ለመቀላቀል ታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ።

Instagram https://instagram.com/tankwa_travels
Facebook https://.facebook.com/travelinethiopia
X https://x.com/TankwaTours
LinkedIn https://.linkedin.com/in/tankwatours
Tiktok https://tiktok.com/
YouTube https://www.youtube.com/
Telegram https://t.me/tankwatravels

እንኳን ለአገው ፈረሰኞች በዓል አደሳረሳችሁ!85 ተኛው የአገው ፈረሰኞች ቀን በነገው ለት በእንጅባራ ከተማ ይከበራል፡፡ የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የአገው ፈረሰኞች ቀንን የአገው አባቶች ከሌሎ...
30/01/2025

እንኳን ለአገው ፈረሰኞች በዓል አደሳረሳችሁ!

85 ተኛው የአገው ፈረሰኞች ቀን በነገው ለት በእንጅባራ ከተማ ይከበራል፡፡ የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የአገው ፈረሰኞች ቀንን የአገው አባቶች ከሌሎች አባት አርበኞች ጋር በመተባበር የጣልያንን ወራሪ ጦር ዓድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለመዘከር በየዓመቱ ጥር 23 በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚከበር በዓል ነው፡፡ ማኅበሩ በ1932 ዓ.ም ከ30 በማይበልጡ አባላት የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ59 ሺህ በላይ አባላት አሉት፡፡ ማህበሩ አባቶች የተጣላን የሚያስታረቁበት፣ የተቀማን ሲያስመልሱበት፣ ሌባን ሲያጠፉበት ከቆዩ በኋላ አባላቶቹን እያሰፋ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን አገው ፈረሰኞች በዓል በድምቀት እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸውን የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
የአገው ፈረሰኞች በዓል ታሪክ፣ ባሕል እና እሴት የሚገለጽበት ታላቅ እና ደማቅ በዓል ነው። በበዓሉ በርካታ ፈረሰኞች እና እንግዶች ይታደማሉ።በበዓሉ ከፈረስ ትዕይንት ባለፈ የአገው ሕዝብ የአመጋገብ ሥርዓት፣ አለባበስ፣ ባሕል፣ ማንነት የሚገለጥበት እንዲሁም የአገው ሕዝብ የእንግዳ ተቀባይነት የሚገለጥበት ነው ። የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ የአገው ፈረሰኞች በዓል በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሠራ መኾኑንም ቀደም ብሎ ያስታወቀ ሲሆን። በዓለም ቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መሥፈርቶችን አሟልቶ እንዲሄድ ለማድረግ ቢሮው ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ጨምሮ ገልጿል።
በበዓሉ ጎብኝዎች በስፋት እንዲገኙ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሠራ ሲሆን የአገው ፈረሰኞች በዓል ለክልሉ የቱሪዝም ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ቢሮው ገልጸዋል። በዓሉ የጥንት ይዘቱን እና ታሪኩን ጠብቆ እንዲከበር እናም ለትውልድ እንዲሸጋገር የመጠበቅ፣ የማልማት እና የመንከባከብ ኀላፊነት አለብን ሲል ቢሮው ገልጿል። (ምንጭ ቢቢሲ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮ)
በድጋሚ እንኳን ለአገው ፈረሰኞች በዓል አደስረሳችሁ እያልን በአሉን ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም በዓል እንላለን!

የአውሮፕላን በረራ ትኬት ለመቁረጥ ወይም ሌሎች አገልግሎቶቻችን ለመጠቀም ካስፈለገዎ በዓለማቀፍ የጥሪ ማዕከል ስልክ ቁጥሮቻችን በ0942777770 ወይም የመጨረሻውን ቁጥር ማለትም ዜሮን ከ1-5 በመቀያየር ያገኙናል። በተጨማሪም 0911764933 ይደውሉልን፡፡

ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት
የሁሉም ምርጫ !

በሶሻል ሚዲያ ገጾቻችንን ይቀላቀሉን

Instagram https://instagram.com/tankwa_travels
Facebook https://.facebook.com/travelinethiopia
X https://x.com/TankwaTours
LinkedIn https://.linkedin.com/in/tankwatours
Tiktok https://tiktok.com/
You Tube https://www.youtube.com/
telegram https://t.me/tankwatravels
official website https://tankwatravels.com

Visit Amhara Zehabesha BBC

አስገራሚው ብዙዎች የማያውቁት የባህር ዳር ክብረ በዓል              "ጥርን በባህር ዳር"ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት ጥርን በባህር ዳር ዝግጅት በባሕር ዳር ከተማ እንዲሳተፉ እ...
25/01/2025

አስገራሚው ብዙዎች የማያውቁት የባህር ዳር ክብረ በዓል
"ጥርን በባህር ዳር"

ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት ጥርን በባህር ዳር ዝግጅት በባሕር ዳር ከተማ እንዲሳተፉ እየጋበዝን ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎችም ሆነ ከውጭ ሀገራት ወደ ባህርዳር በመምጣት ይህንን ፕሮግራም መታደም ለምትፈልጉ የአውሮፕላን በረራ ትኬትዎን ጨምሮ ጥቅል የጉብኝት አገለግሎቶችን ያዘጋጀን በመሆኑ አሁኑኑ ወደጥሪ ማዕከል ስልክ ቁጥሮቻችን 0911764933 እንዲሁም በ0942777770 ወይም የመጨረሻውን ቁጥር ማለትም ዜሮን ከ1 - 5 በመቀያየር በመደወል ይህን ማራኪ ዝግጅት እንዲታደሙ ጋብዘነዎታል፡፡

https://youtu.be/NcveQj1Ef7U

አስገራሚው ብዙዎች የማያውቁት የባህር ዳር ክብረ በዓል
"ጥርን በባህር ዳር"

ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት ጥርን በባህር ዳር ዝግጅት በባሕር ዳር ከተማ እንዲሳተፉ እየጋበዝን ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎችም ሆነ ከውጭ ሀገራት ወደ ባህርዳር በመምጣት ይህንን ፕሮግራም መታደም ለምትፈልጉ የአውሮፕላን በረራ ትኬትዎን ጨምሮ ጥቅል የጉብኝት አገለግሎቶችን ያዘጋጀን በመሆኑ አሁኑኑ ወደጥሪ ማዕከል ስልክ ቁጥሮቻችን 0911764933 እንዲሁም በ0942777770 ወይም የመጨረሻውን ቁጥር ማለትም ዜሮን ከ1 - 5 በመቀያየር በመደወል ይህን ማራኪ ዝግጅት እንዲታደሙ ጋብዘነዎታል፡፡

https://youtu.be/NcveQj1Ef7U

Join us via Telegram
https://t.me/tankwatravels

ኢትዮጵያ ታይተው የማይጠገቡ የበርካታ ቅርሶች፣ ታሪኮችና መስህቦች ባለቤት ናት። ባህር ዳር ከተማ ደግሞ በጣና ኃይቅ ዳርቻ፣ አባይን ተንተርሳ የተመሰረተች፣ በዙሪዋ የሚገኙ የተፈጥሮ...

እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! ከየትኛውም ወደ የትኛውም የሃገራችን ክፍል ወይም በዓለም አቀፍ በረራ ለመብረር እቅድ ይዘው  ከሆነ በበዓል ወቅት የሀገር ውስጥ የአውሮፕላ...
18/01/2025

እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

ከየትኛውም ወደ የትኛውም የሃገራችን ክፍል ወይም በዓለም አቀፍ በረራ ለመብረር እቅድ ይዘው ከሆነ በበዓል ወቅት የሀገር ውስጥ የአውሮፕላን በረራ ትኬቶች ቀድመው የሚሞሉ በመሆኑ ከተጨማሪ ወጭና መጉላላት ራስዎን እንዲያድኑ ከታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት ጋር ትኬትዎን ቀድመው እንዲቆርጡ አስቀድመን እንመክራለን።

ክፍያዎን በሞባይል ባንኪንግ ወይም በቴሌብር ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ ባንክ መክፈል እስከቻሉ ድረስ በአሉበት ቦታ ሆነው ሥራዎን እየሠሩ ሌሎች ተጨማሪ ወጭዎን ሳያወጡ ከበረራዎ ከአንድ ሳምንት በፊት ቀድመው ትኬትዎን በመቁረጥ ከአላስፈላጊ ተጨማሪ ወጭና መጉላላት ራስዎን ያድኑ!

ለበረራ መረጃ ወይም ትኬት ለመቁረጥ በዓለማቀፍ የጥሪ ማዕከል ስልክ ቁጥሮቻችን በ0942777770 ወይም የመጨረሻውን ቁጥር ማለትም ዜሮን ከ1-5 በመቀያየር ያገኙናል። በተጨማሪም 0911764933 ይደውሉልን፡፡

ታንኳ አስጎብኝና የጉዞ አገልግሎት
የሁሉም ምርጫ !

17/01/2025

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በአብ ስም፣ በወልድ ስም፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም፤አንድ አምላክ አሜን።

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም ወዳጆች እንኳን ለብርሐነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን በተወለደ በ30 ዘመኑ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ5531 ዓ.ም በዘመነ ሉቃስ ጥር 11 ቀን ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት ተጠመቀ። ፍት.ነገ አን.19፤ ድስቅ፣ 29 ፤ ሉቃ. 3፣23
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚያስተምርበት ጊዜ ቃሉን የሰሙትን ሰዎች ያጠምቃቸው ነበር። "በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ። የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።” ማር 1፥3 ይህ ጥምቀት በእርሱ የተጀመረ መንፈሳዊ ተግባር አልነበረም።

1. የብሉይ ኪዳን አባቶች በዓላቸውን ከማክበራቸው በፊት በውሃ በመረጨት በመነከርና በመጥለቅ ይነጹ ነበር። የዝግጅቱ ዕቃዎችንም በውሃ ማንጻት አለባቸው ከርኩሰት መንጻት በዚህ ነበርና። ዘሌ 6፥27
2. ኢዮብና ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቀው ተፈውሰዋል። 2ነገ 5፥8
3. ለ 38 ዓመት አልጋ ቁራኛ የነበረው ሰው እንደመሰከረው በሰሊሆም ቤተሳይዳ ውኃ ሰዎች እየተጠመቁ ፈውስ ያገኙ እንደነበረ እርሱ ግን ወደ ውኃው የሚወስደው በማጣቱ በዚያ እንዳለ
ለጌታ መንገሩ ሌላው ማስረጃ ነው። ዮሐ 5፥2
ስለሆነም በውኃ ተጠምቆ ፈውስ ማግኘት አስቀድሞም የነበረ ነው።

ጥምቀት ምንድነዉ?
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ብዙ ሊቃውንት እንደሚስማሙበት ጥምቀት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ውሃ ውስጥ መዘፈቅ" የሚል ትርጉም አለው። ይህ ነጠላ ትርጉሙ ሲሆን ምሥጢራዊ ትርጉሙ ደግሞ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ ተጠምቆ ስመ ክርስትናን መቀበል" ነው። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማናዊ ጥምቀት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከእምነት አንጻር ሲታይ ሞታችን፣ መቀበሪያችን፣ ትንሣኤያችን በመሆኑ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ህብረት የሚፈጥርልን ምሥጢር ነው።
"ከክርስቶስ ጋራ አንድ ትኾኑ ዘንድ የተጠመቃችኹ ዅሉ ክርስቶስን ለብሳችዃልና።
አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም ዅላችኹ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችኹና" ገላ 3፥27
ጥምቀት በመረጨት ወይም በማፍሰስ የሚፈጸም ሰይሆን ሰውነት በሙሉ በማጥለም በሥላሴ ስም 3 ጊዜ ብቅ ጥልም በማለት የሚፈጸም ምሥጢር ነው።

የጥምቀት ምሳሌ
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
1. ግዝረት
2. የእስራኤል ቀይ ባሕርን ማቋረጥ
3. አብርሃም ባሕረ ዮረዳኖስን ተሻግሮ ለመልከጼደቅ ጽዋዕ በረከት ሕብስት አኮቴት ማቅረቡ
4. የኖሕ መርከብ

ከጥምቀት ለክርስቲያኖች ምን ይገኝበታል
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
1. ጽድቅ ይገኝበታል። "ያመነ የተጠመቀ ይድናል።" ማር 16፥16
2. እንደገና እንወለድበታለን። ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የምንወለድበት ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ የሚፈጸመውም በውሃና በመንፈስ ነው። ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም። "ከውሃና ከመንፈስ ልትወለዱ ግድ አላችኹ" ዮሐ 3፥3 እንዲል። በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ዉሉድ የሚያሰኝ ነው።
3. የኃጢአት ሥርየት ይገኝበታል። "ኃጢአታችሁ ይሠረይ ዘንድ ንስሐ ግቡ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስም ተጠመቁ።" ሐዋ 2፥3
4. ክርስቶስን እንመስልበታለን። አርዓያ ሆኖ ያሳየንን በመፈጸም በሥራ እንመስለዋለን። "ከክርስቶስ ጋራ አንድ ትኾኑ ዘንድ የተጠመቃችኹ ዅሉ ክርስቶስን ለብሳችዃልና።" ገላ 3፥27። "ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋራ አንድ እንኾን ዘንድ የተጠመቅን ዅላችን ከሞቱ ጋራ አንድ እንኾን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን፧" ሮሜ 6፥3
5. አድስ ሕይወት ይገኝበታል። "እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በዐዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ፥ከሞቱ ጋራ አንድ እንኾን ዘንድ በጥምቀት ከርሱ ጋራ ተቀበርን። ሮሜ 6፥4

የጌታችን ጥምቀት
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
"ወሀሎ ዮሐንስ ያጠምቅ በገዳም" ዮሐንስ በምድረ በዳ ያስተምር ነበር። ወይሰብክ ጥምቀተ ለንስሐ ወይትኃደግ ሎሙ ኃጢአቶሙ" ኃጢአታቸው ሊሠረይላቸው የንስሐ ጥምቀትን ያስተምር ነበር።
"ወአሜሃ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ እምገሊላ ውስተ ዮርዳኖስ ከመ ይጠመቅ እም ዮሐንስ" ማር 1፥9። በዚያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ከገሊላ ክፍል ከናዝሬት ወደ ዮርዳኖስ መጣ። "ወአጥመቆ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ" ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቀው። በመጠመቁ ጸጋ ሊያገኝበት አልነበረም ለጥምቀት ክብር ሊሰጥ እንጅ። "ወመጽአ ቃል እምሰማይ ዘይብል አንተ ውእቱ ወልድዬ ዘአፈቅር ወኪያከ ሠመርኩ።"፤"ደስታዬን የማይብህ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ" የሚል ድምጽ ከወደ ሰማይ ተሰማ። ጌታችን ሲጠመቅ የባሕርይ አባቱ አብ "ዝንቱ ውእቱ ወልድዬ" ብሎ ሲመሰክር "መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ከራሱ ላይ በመቀመጥ" አንድነቱ ሦስትነቱ ተገለጸ።

ጌታችን ለምን ተጠመቀ?
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
1. ዲያብሎስ በዮርዳኖስ ወንዝ ደብቆት የነበረውን የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ።
2. በጥምቀት ዳግም ልደት እንዳለን ለማጠየቅ አርአያ ሊሆነን።
3. ትሕትናን ለማስተማር። በአገልጋዩ በዮሐንስ መጠመቁ ትሕትናን ሊያስተምረን ነው።
4. አንድነቱንና ሦስትነቱን ለመግለጽ ("ሰማያት ተከፈቱ" ለሚለው አነጋገር መልስ ሊሰጥ)
5. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ። በዮርዳኖስ ወንዝ እንደሚጠመቅ ትንቢት ተነግሮ ነበርና። መዝ 113፥3

ጥምቀት ሦስት አይነት ሲሆን አንደኛው በደም ጥምቀት ነው። ኢአማንያን ወደ ማመን በሚመለሱበት ጊዜ ለሚስጥረ ጥምቀት
ሳይደርሱ ለምን ወደ ክርስትና ገባችሁ ብለው
አሕዛብና ክፉዎች ቢገድሏቸውና ስሙን መስክረው ስለስሙ ቢሞቱ የፈሰሰው ደማቸው ጥምቀት ይሆንላቸዋል። (ለምሳሌ ፍያታዊ ዘየማን) ሁለተኛው በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ሲሆን እግዚአብሔር ለመረጣቸውና ለፈቀደላቸው እንደ ሐዋርያት ጥምቀት አይነት ነው። ሐዋ 2፥3 ሦስተኛው ደግሞ ጌታችን የተጠመቀውና አርዓያ የሆነልንና እኛ የምንጠመቀው የውሃ ጥምቀት ነው።
ጥምቀት ሦስት ወገን ነው። አንደኛ የአይሁድ ሁለተኛ የዮሐንስ ሦስተኛ የጌታ ጥምቀት ናቸው።

ታቦታቱ ወደ ባሕር መውረድ
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ይህ በዓል በሚከበርበት ጊዜ ዋዜማው "ከተራ" ይባላል። ከተራ ማለት መገደብ ማለት ነው። በዚህ ቀን ታቦታት ከየቤተክርስቲያናቸው ወጥተው በወንዝ ዳር ወይም በሰው ሰራሽ የውሃ ግድብ በዳስ በድንኳን ያድራሉ። ታቦታቱ ወጥተው ውሃ ወዳለበት መሄዳቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአገልጋዩ በዮሐንስ ዕጅ ሊጠመቅ በወደደ ጊዜ ሁለቱም በአድነት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በመውረዳቸው ነው። ቤተክርስቲያን ይህንን ዓቢይ ምስጢርና ሥርዓት ተከትላ ታቦታቱን ከመንበራቸው አውጥታ፤ የውሃ ምንጭ፤ ወዳለበት ወንዝ በመውረድ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥርዓት በዓሉን ታከብራለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም ታቦታቱን አጅበው አብረው በመውረድ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ እያከበሩ የበረክቱ ተሳታፊ ይሆናሉ።

♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
ወንድሞች ሆይ!!! ሁል ጊዜ በሊቃውንት፤ በአባቶችና በካህናት የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር እየተቀበልን፤ ሕጉንና መመሪያውን መጠበቅ ፥ ትዕዛዙንም መፈጸም አለብን። "ኦሆ በልዎ ለእግዚአብሔር" እግዚአብሔርን እሽ እንበለው። ሃይማኖታችንን ከመልካም ምግባር ጋር ይዘን በንስሐ ጥምቀት ታጥበን ከኃጢአት ሁሉ ንጹሐን በመሆን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን (በዕለተ ዓርብ ከጌታችን ቀኝ ጎኑ በፈሰሰው ማየ ህይወት (የህይወት ውሃ) ወይም ማየ ገቦ (የጎን ውሃ) ተጠምቀን፤ ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች በመባል ወደ ገነት፤ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንድንገባ የእርሱ ፈቃድ ይሁንልን። የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ፥ የትጉሃን መላዕክት፣ የቅዱሳን፣ የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በረከትና ረድኤት ሁልጊዜ አይለየን።
ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ስዓት አሜን።

14/01/2025

Timket Celebration is coming up!

Dive into the vibrant and sacred celebration of Timket, Ethiopia's grand Epiphany festival. This immersive video takes you on a journey through breathtaking processions, the spiritual significance of the Tabot (a replica of the Ark of the Covenant), and the rich cultural traditions of Ethiopia.

Feel the atmosphere come alive with ethereal chanting and mesmerizing sounds reminiscent of ancient rituals, paired with stunning visuals of priests, worshippers, and vibrant community festivities.

Experience the best of Timket with Tankwa Tours, your trusted guide to Ethiopia’s heritage. From participating in the sacred rituals to enjoying traditional dances, local feasts, and scenic landscapes, we ensure your journey is both spiritual and unforgettable.

🌍 Book Your Experience Today: tankwatravels.com
✨ Follow Us: on Facebook Instagram Tiktok links are on profile
🎥 Don’t miss the chance to witness one of the world’s most breathtaking festivals—subscribe now and join the celebration!
Call us now at
+251911764933
+251942777770
+251942777771
+251942777772
+251942777773
+251942777774
+251942777775

የታንኳ አስጎብኝ እና የጉዞ አገልግሎት ቅናሽ መከታተያ ኩፖን ቁጥር አለዎት?  ካለዎትስ ስለጠቀሜታው ያውቃሉ?
10/01/2025

የታንኳ አስጎብኝ እና የጉዞ አገልግሎት ቅናሽ መከታተያ ኩፖን ቁጥር አለዎት? ካለዎትስ ስለጠቀሜታው ያውቃሉ?

YES IT IS! CHOOSE BAHIR DAR FOR YOUR NEXT ADVENTURE!
27/08/2022

YES IT IS! CHOOSE BAHIR DAR FOR YOUR NEXT ADVENTURE!

ውቢቷ ባሕር ዳር

📸 HAM HAM

Address

Bahar Dar
Bahir Dar
POBOX2021

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tankwa Tours & Travel Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tankwa Tours & Travel Agency:

Share

Category

Our Story

TANKWA Tours & Travel Agency has been operating in tour operation, boat and car rental services since 2013. We’re your option for responsible and nature friendly tour operator in Ethiopia and are always available and serve you excellent tour experience as you wished in your mind.

Our company is well equipped with modern, well maintained latest fleets, camping and cooking equipment which enable us to offer quality tour services and competitive price that meets the expectations of our customers. Address: Main office is in Bahir Dar, protection house, ground floor, office No: _ 14 and satellites in Addis Ababa and Mekele.

Our working process: Step 1, Send us your request, using our contact form that you will find on this page. Step 2, We Send you our suggested itinerary and quote that befits your interest. Step 3, Send us your confirmation with a request for a booking and a down payment; upon receiving the booking confirmation from our end, and complete the rest of the payment due.Step 4, commence your travel and acquire the services you are entitled to and go back home after completing your tour. Step 5, you write reviews about us on one of travel website like trip advisor or social medias like face book. For all tour information and bookings please call or email us at: