Amhara Culture Tourism & Sport Bureau

Amhara Culture Tourism & Sport Bureau Government organization

‎የጎንደር አብያተ መንግስታትንና በዙሪያው የሚገኙ ቅርሶችን ለማስተዳደር የሰው ሀይል መዋቅር ጥናት ለውይይት ቀረበ።‎‎የጎንደር ከተማ ዓለም አቀፍ ቅርስ የሆነው የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስታ...
27/05/2026

‎የጎንደር አብያተ መንግስታትንና በዙሪያው የሚገኙ ቅርሶችን ለማስተዳደር የሰው ሀይል መዋቅር ጥናት ለውይይት ቀረበ።

‎የጎንደር ከተማ ዓለም አቀፍ ቅርስ የሆነው የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስታት ቅጥር ግቢ አጠቃላይ ጥገና በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ተነሳሽነት ከተጠገነ በኋላ ለተፈጠረው ምቹ የጉብኝት አውድ እና የቱሪዝም መዳረሻውን የሚመጥን መዋቅር በማስፈለጉ ቅርሱን የማስተዳደር አቅም የሚፈጥር የሰው ሃይል ጥናት ለውይይት ቀርቧል።
‎በአብክመ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ፣ አማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲና በጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በኩል የተዘጋጀው ይህ ጥናት ከብርት ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ፣ የባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ማሪያሟ ካሳሁንና ከአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ከአብክመ ገንዘብና ፕላንና ልማት ቢሮ ፣በተከማው ውስጥ የሚገኙ የባህልና የቱሪዘም ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችና በላድርሻ አካላት በተገኙበት መድረክ የመዋቅር ጥናቱን ማቅረብ ተችሏል ።

‎በጎንደር ከተማ ውስጥና አካባቢው የሚገኙ የአብያተ መንግታትና ልዩ ልዩ ቅረሶችን በዘላቂነት ለማሰተዳደር የገቢ ምንጭ ለማሰደግና ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል አደረጃጀት መፈጠር እንዳለበት በጥናቱም ከ96 ላይ የሰው ኃይል እንደሚያስፍልግ ቀርቧል።

‎ክብርት ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ ለቀረቡ ጥያቄዎች እና ሃሰቡች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የሰው ሃይሉ አደረጃጀት ቅርሶቻቸን በዘላቂት ለመጠበቅና ለመንከባከብ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም ቅርሶችን በማስተዋወቅ የቱሪስት ፍሰቱን ለማሳደግ የኢኮኖሚ ፋይዳቸውን በማሳደግ የሚጫወተው ሚና ጉልህ መሆኑን ክብርት ም/ከንቲባዋ ጠቁመዋል።

‎የጎንደር ከተማ የባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ማሪያም ካሳሁን ተነሳሽነቱን ወስዶ ጥናቱን በማስጠናት ተግባራዊ እንዲሆን የክልሉን የባህልና ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ እንዲሁም አመራሩን የሚያደርገው ድጋፍ ካመሰገኑ በኋላ ጥናቱ ዳብሮ በሥራ ላይ እንዲውል እንደ መምሪያ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አሳስበዋል።
‎የመዋቅር ጥናቱም የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተትና በማዳበር የጋራ አመራር ተሰጥቶበት በቀጣይ ወደ ተግባራዊነት እንደሚገባ ተጠቁሟል ።።

ለመላው የስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን  ለ 1447ኛው  ኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ! ኢድ-ሙባረክየአማራ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ።
27/05/2026

ለመላው የስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1447ኛው ኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!

ኢድ-ሙባረክ

የአማራ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ።

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ በዜሮ ዓመትና በስራ ልምድ!
25/05/2026

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ በዜሮ ዓመትና በስራ ልምድ!

23/05/2026

በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የጀልባ አደጋ ይመለከታል!
በጣና ሀይቅ ላይ በሰሞኑ ስለተከሰተው የዓሣ ማስገሪያ ጀልባዎች አደጋ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ገጾች ገጾች የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ። ተቋማችን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በቦታው ከነበሩ አካላት መረጃዎችን በማጣራት የሚከተለውን እውነታ ለህዝብ ማሳወቅ ይፈልጋል።
አደጋው ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ በሀይቁ ላይ በተፈጠረ ከፍተኛ ሞገድ ምክንያት ሁለት የዓሣ ማስገሪያ ጀልባዎች ላይ የተከሰተ የመስጠም አደጋ ነው።
በወቅቱም በአካባቢው የነበሩ ሌሎች ዓሣ አጥማጆች ባደረጉት ፈጣን እና የተቀናጀ ጥረት፣ ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ የነፍስ አድን ስራ ተከናውኗል። ይሁን እንጂ እስካሁን ባለን የተረጋገጠ መረጃ መሰረት በአደጋው የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን በታላቅ ሀዘን እንገልጻለን።
ህብረተሰቡ እና የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች ትክክለኛውን መረጃ ከመንግስት አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ብቻ እንዲወስዱ እና ያልተጣሩ የሀሰት ወሬዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

የደረጃ እድገት የቅጥር ማስታወቂያ
22/05/2026

የደረጃ እድገት የቅጥር ማስታወቂያ

ተፈጥሯዊ ውበትን የተላበሰው የዘንገና ሀይቅ- አዊ ብሄረሰብ ዞን!
20/05/2026

ተፈጥሯዊ ውበትን የተላበሰው የዘንገና ሀይቅ- አዊ ብሄረሰብ ዞን!

ውብና ማራኪው የሀርዲቦ ሀይቅ- ደቡብ ወሎ ዞን!
20/05/2026

ውብና ማራኪው የሀርዲቦ ሀይቅ- ደቡብ ወሎ ዞን!

ጉብኝት በመቅደላ አምባ-ደቡብ ወሎ ዞን !መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ነው፡፡
19/05/2026

ጉብኝት በመቅደላ አምባ-ደቡብ ወሎ ዞን !
መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ነው፡፡

ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም-ጣና ሀይቅ
18/05/2026

ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም-ጣና ሀይቅ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ በራራውን አደረገ: ለቱሪዝም እድገቱ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።ግንቦት 08/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ከዓመታት በኋላ የመጀመሪያ ...
16/05/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ በራራውን አደረገ: ለቱሪዝም እድገቱ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።

ግንቦት 08/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓመታት በኋላ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ አድርጓል።

ከዓመታት በኋላ ወደ ደብረ ማርቆስ በረራ ያደረገችው አውሮፕላን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎችን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ይዛ ደብረ ማርቆስ ደርሳለች።

እንግዶቹ ደብረ ማርቆስ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው። የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለዓመታት የሕዝብ ጥያቄ ነበር። ግንባታው የሕዝብ ጥያቄን የመለሰ ነው።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Culture Tourism & Sport Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share