Zagol Ethiopia Tours

Call Directions Website Contact the business

Zagol Ethiopia Tours Zagol Ethiopia Tours is one of the best travel company in Ethiopia, and also well license travel agen

16/10/2026

The eight wonders of the world, churches of king lalibela.

Discover the extraordinary rock-hewn churches of Lalibela, a UNESCO World Heritage Site and one of Ethiopia’s most remarkable historical treasures. Explore the magnificent 12th-century churches carved from solid rock, admire their incredible architecture, experience the deep spiritual traditions of Ethiopian Orthodox Christianity, and discover the rich history and living culture of this sacred destination with Zagol Ethiopia Tours.

03/10/2026

እንኳን ለሰማዕታቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሀዊ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ: ቅዱስ ጊዮርጊስ ለሀገራችን ሰላም ፍቅር ይላክልን መልካም በዓል

Happy holiday of St George

Today is the annual feast day of st George Church it is colorful celebrated in the new African Jerusalem lalibela Ethiopia.

Blessing for our country Ethiopia !!!!

01/10/2026

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓል አደረሰን አደረሳችሁ

Meskerem 21 – Kidist Maryam (ቅድስት ማርያም) is a special monthly feast dedicated to the Virgin Mary in the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. The 21st day of every Ethiopian month is traditionally dedicated to St. Mary.

27/09/2026

I got over 1,000 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

27/09/2026

እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሰን አደረሳችሁ 2019

Meskel Celebration in Ethiopia
Meskel, meaning “Cross” in Amharic, is one of Ethiopia’s most important religious and cultural celebrations. It commemorates the discovery of the True Cross on which Jesus Christ was crucified, according to Ethiopian Orthodox tradition.
The celebration is famous for the Demera bonfire, decorated with flowers and a cross. People gather to sing, dance, pray, and celebrate together. The festival is especially beautiful in Addis Ababa and Lalibela.

22/09/2026

Upcoming holiday in the city of African Jerusalem

🇪🇹 Meskel Festival – Finding of the True Cross
Meskel is one of Ethiopia’s most colorful religious and cultural celebrations, held every year on September 27 (or September 28 in leap years). It commemorates the discovery of the True Cross (Meskel) by Empress Helena.

The celebration is famous for the Demera, a large bonfire decorated with flowers and surrounded by thousands of people singing, dancing, and praying. The main celebrations take place in Addis Ababa, as well as in many towns and villages across Ethiopia.

Experience Meskel with Zagol Ethiopia Tours — discover Ethiopia’s faith, history, culture, and traditions.

19/09/2026

I got over 100 reactions on one of my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

17/09/2026

👇ለሚመለከተው ሁሉ👇
የቱሪዝም ዘርፍ አስጎብኚዎች ያስመጧቸው 42 ዘመናዊ የቱሪዝም ተሽከርካሪዎች ለሦስት ዓመታት ሳይረከቡ መቆየታቸውን ተከትሎ አቤቱታ ቀረበ
በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ አስጎብኚዎች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር ያስመጧቸው ዘመናዊ የቱሪዝም ተሽከርካሪዎች ከሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለረጅም ጊዜ ሳይረከቡ መቆየታቸውን በመግለጽ፣ ጉዳዩ እንዲፈታ ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ አቀረቡ።

አቤቱታ አቅራቢዎቹ እንደገለጹት፣ ተሽከርካሪዎቹ ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ለሦስት ዓመታት ያህል ቆመው ይገኛሉ። በዚህም ተሽከርካሪዎቹ በአንድ ቦታ ቆመው በመበላሸት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው፣ ችግሩ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያዘጋጀው ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ተሽከርካሪዎቹ በሊዝ ፋይናንሲንግ ሂደት እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፣ በኋላም የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔን ተከትሎ ቀረጥና ታክስ ተከፍሎባቸው እንዲገቡ ተፈቅዷል።

በዚህ መሠረት 43 የስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎች ለ15 የአስጎብኚ ድርጅቶች እንዲገዙ ተደርጎ ጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ተከፍሎባቸው ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ሪፖርቱ ያብራራል።
ሆኖም ተሽከርካሪዎቹ ለተጠቃሚዎቹ ሳይረከቡ መቆየታቸውን ተከትሎ፣ ባለሀብቶቹ ጉዳዩ በአግባቡ እንዲታይና መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የባንኩ ውስጥ ኦዲት ክፍል የሊዝ ፋይናንሲንግ ሂደቱን መርምሮ ሂደቱ የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ ፖሊሲና ፕሮሲጀር መከተሉን ለቦርዱ ሪፖርት ማቅረቡን የባንኩ ሰነድ ያስረዳል።

ጥያቄ
ተሽከርካሪዎቹ ከሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለረጅም ጊዜ ሳይረከቡ መቆየታቸው በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ኢንቨስት ባደረጉ አስጎብኚዎች ላይ የሚያስከትለው ጫና ከፍተኛ ነው።

ስለሆነም ጉዳዩ በሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፣ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት በጥልቀት ታይቶ፣ ለተጎዱት አስጎብኚዎች ግልጽና ፈጣን መፍትሔ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።
ለሚመለከተው ሁሉ እንዲደርስ በአክብሮት እናቀርባለን።
✍️ (ዘ-ሐበሻ)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) Visit Amhara ተጓዡ ጋዜጠኛ /ሄኖክ ስዩም/ Ethiopia Land of Origins ጉርሻ page Mengistu Gobezie Sileshi Girma Amhara Culture Tourism & Sport Bureau Selamawit Kassa Global Tourism Forum Henoke Seyuome Hagere Biniyam-Bini Hailu

16/09/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ አስጎብኚዎች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር ወደ ሀገር ያስገቧቸው 42 ዘመናዊ የቱሪዝም ተሽከርካሪዎች ርክክብ ሳይፈጸም አዲስ አበባ ውስጥ ለረጅም ጊዜ መቆማቸውን በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቤቱታ አቀረቡ።

አቤቱታ አቅራቢዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት እና ዘ-ሐበሻ በተመለከተው ግልጽ ደብዳቤ እንዳስታወቁት፣ ተሽከርካሪዎቹ ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ያለ ምንም አሳማኝ ምክንያት ለ3 ዓመታት ያህል ቆመዋል። ባለሀብቶቹ የልማት ባንክ እና የሚመለከታቸው የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን በተደጋጋሚ ሲጠይቁ "በቅርቡ ትረከባላችሁ"፣ "ቆዩ" እንዲሁም "እኔ ምንም ማድረግ አልችልም" የሚሉ ምላሾችን ብቻ እያገኙ ለከፍተኛ ግራ መጋባት መጋለጣቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም መኪኖቹ በአንድ ቦታ ቆመው በመበላሸት ላይ ስለሚገኙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጣልቃ ገብተው ተሽከርካሪዎቹን እንዲረከቡ ትብብር እንዲያደርጉላቸው ተማጽነዋል።

በሌላ በኩል ጉዳዩን አስመልክቶ ግንቦት 2017 ዓ.ም የተዘጋጀው ዘ-ሐበሻ የተመለከተው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አጭር የዳሰሳ ሪፖርት የችግሩን መነሻ ያብራራል። ባንኩ 15 ለሚሆኑ የአስጎብኚ ድርጅት ደንበኞች ለማስጎብኘት አገልግሎት የሚውሉ ስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎችን በካፒታል እቃ ኪራይ (ሊዝ ፋይናንሲንግ) ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የብድር ጥያቄ አጽድቆላቸው የ20 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽመው ነበር። ነገር ግን አዲሱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ፣ ተሽከርካሪዎቹን ከቀረጥ ነፃ ማስገባት እንደማይቻል የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቆ ሂደቱ ተስተጓጉሎ ነበር።

ደንበኞቹ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይላቸው ባቀረቡት አቤቱታ እና የቱሪዝም ሚኒስቴር በጻፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ መሰረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር በሰኔ 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው አዲስ ውሳኔ ተሽከርካሪዎቹ የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶላቸው ቀረጥና ታክስ ተከፍሎባቸው እንዲገቡ መፍቀዱን የባንኩ ሰነድ ያስረዳል። በዚህም መሰረት ለእነዚህ 15 ደንበኞች 43 ስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎች ከ'RED Sea Automotive FZCO' (በሞኤንኮ በኩል) ግዥ ተፈጽሞላቸው፣ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ተከፍሎባቸው ሀገር ውስጥ ሊገቡ ችለዋል።

ይሁን እንጂ ተሽከርካሪዎቹ ሀገር ውስጥ ገብተውም ለደንበኞቹ እስካሁን አልተላለፉም። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሪፖርት የርክክቡን መቆም በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ያብራራል፦

1ኛ. ተሽከርካሪዎቹ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ባንኩ ለደንበኞች ለማስረከብ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት የዳይሬክተሮች ቦርድ ርክክቡ እንዲቆም መመሪያ አስተላልፏል።
2ኛ. ቦርዱ በሰጠው መመሪያ መሰረት የሊዝ ፋይናንሲንግ አሰጣጥ ሂደቱ በውስጥ ኦዲት ክፍል እንዲጣራ ተደርጓል።
3ኛ. የውስጥ ኦዲት ክፍሉም የእያንዳንዱን ደንበኛ የሊዝ አፈቃቀድ ሂደት መርምሮ፣ አጠቃላይ ሂደቱ ፍጹም የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ ፖሊሲ እና ፕሮሲጀር የተከተለ እንደነበር በማረጋገጥ ለቦርዱ ሪፖርት አቅርቧል።

ይህ የኦዲት ማረጋገጫ ቢቀርብም፣ የደንበኞቹ ተሽከርካሪዎች አሁንም ሳይተላለፉ በመቆማቸው ባለሀብቶቹ ጉዳያቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል እልባት እንዲያገኝ አቤቱታ ለማቅረብ ተገደዋል።

Address

Bole
81 ADDISABABA,

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zagol Ethiopia Tours posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zagol Ethiopia Tours:

Shortcuts

Share

Category