07/08/2025
የካፋ ዘመን መለወጫ ”መሽቀሮ“
CHRIST is = Number 77
77 የሚለውን ቁጥር በተደረገዉ አጭር ዳሰሳ ጥናት በስነ ቁጥር ጥናት (Numerology) In certain numerological systems based on the English alphabet, the number 77 is associated with Jesus Christ. CHRIST is C = 3, H = 8, R = 18, I = 9, S = 19, T = 20, which added together equal 77.
በዓለማችን ላይ በተለያዩ ንፍቀ ክበቦች የሚገኙ ሀገራት እንደ ባህላቸው የየራሳቸው አዲስ ዓመት ሰይመው ያከብራሉ፡፡ በዓለም በስፋት ከሚታወቀው የአዲስ ዓመቱ ለውጥ ኃይማኖታዊ (Religious) ልምምድን ፣ የጨረቃን ዑደት (Lunar calendar) ወይም ጨረቃንና ጸሃይን (Luni Solar) በጥምረት፤ የወቅቶች ፍርርቅን (Seasonal Change) ፣ ወይም ደግሞ የእርሻ ጊዜን (Agriculture activity season) መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ ቻይና፣ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ህንድ፣ ኮምቦዲያ፣ አይሁድ፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ታይላንድ፣ ቬትናም፣ ኔፓል፣ ባንግለዲሽ፣ ሶሪያ ፣ኢራን፣ ኢራቅ፣ ቱርክ፣ ኒውዝላንድ እና ማዳካስካር አዲስ ዓመታቸውን በድምቀት በማክበር ይታወቃሉ፡፡ በህንድ በአብዛኛዎቹ ክፍላተ ግዛቶች እንደየባህሉ የተለያየ አዲስ ዓመት ቀን አሏቸው፡፡ እንዲሁም የእስልምና እምነት ተከታዮች የእስልምና ቀን መቁጠሪያ ( Islamic Calander - Hijri) በመባል የሚታወቅ በየዓመቱ የሚቀያየር አዲስ ዓመት አለ፡፡
እንደ ህንድ እኛም ሀገር በየዓመቱ የሚከበረውን የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላን ጨምሮ በወርሃ መስከረም የዘመን መለወጫን እና የመስቀል በዓልን ተደርቦ የሚከበረባቸው የወላይታ ”ጊፋታ“/ “ማስቃላ” ፣ የዳወሮና፣ ጋሞ “ማስቃላ”፣ የካምባታ “መሳላ” ፣ የየም “ሄቦ”፣ የጉራጌ “መስቀር “፣ የኦሮሞ “ጉባ” ወይም “መስቀላ” እና የካፈቾ እና ሻኬቾ “መሽቀሮ” በየዓመቱ የሚናፈቁ ባህላዊ የማይዳሱ ቅርሶቻችን ሆነው መጥተዋል፡፡ በቀድሞው ደቡብ ክልል በነበርኩባቸው የስራ ጊዜያቶች የብዙዎቹን ብሔረሰቦች ባህላዊ አከባበር ስነ ስርዓት ታድሜ እንደተረዳሁት ክብረ በዓሎቹ ያነገቡት ድንቅ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እሴቶች ለበሽታዎቻቸን ፈውስ ፣ ጥበብ እና ለማንነት የሚሰጡት ድምቀት ልብን በሃሴት ይሞላል፡፡ የኢትዮጵያውነት ልዩ ልዩ ህብር ለሚረዳ ደግሞ ባህላዊ ውበቱ በፍቅር ያሳስባል (ጠብቆ ይነበብ)፡፡
በካፋ ህዝብ አዲስ ዓመት ማብሰሪያ በር ላይ ሆኜ ዛሬ ብዙም ስላልተነገረለት ታሪካዊው የካፋ መሽቀሮ አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ እንኳን አደረሳችሁ ልላችሁ ደግሞም ኖሬ ያየሁትን አንብቤ የተረዳሁትን አስደናቂ ታሪኮች ላጋራችሁ ወደድኩ፡፡
እንኳን ለካፊቾ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!
የካፋ ዘመን መለወጫ ”መሽቀሮ“ በመባልም ይታወቃል፡፡ የካፋ ዘመን ለውጥ የክረምት ወቅትን ተከትሎ ይታደሳል፡፡
ስለ ካፋ አዲስ ዓመት በWerner J. Lange የተባለው የታሪክ ተመራማሪ Dilaects of Divine ‘’ Kinship’’ in the Kafa Highlands በተሰኘው የምርምር መጽሃፉ እስከ 13ኛው መቶ ክፍለዘመን የካፋ ሰርወ መንግስት ከዚያም በኋላ በነበረው የማንጆና ማቶ ስርወ መንግስት ስር፣ ከ1390 እስክ 1897 ድረስ ደግሞ በምንጆ ስርወ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚከበር ባህላዊና መንግስታዊ ክብረ በዓል እንደነበር ተጽፏል፡፡
ላንጌ የመሽቀሮ በዓል ከአስራ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ አስራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለዘመን የካፋ ብሔራዊ በዓል እንደነበር አረጋግጦ ጽፏል፡፡ የመሽቀሮ በዓል አከባበር ንጉሳዊ ስርኣተ መንግስቱ በቀዳሚነት እየመራዉ የሚከበር ህዝባዊ በዓልም ነበር፡፡
ወደ ካፋ አዲሱ ዓመት ታሪካዊ አመጣጥ ስንመጣ ልክ እንደብዙዎቹ የአዲስ ዓመታት ብያኔዎች የወቅቶች ፍርርቅና እምነትን ተከትሎ እንደተወሰነ ስምምነት አለ፡፡ ሃምሌ ወር በካፋ ክረምቱ አይሎ ከፍተኛውን ፍሰት የሚይዝበት ወር ነው፡፡
በዚህ ጊዜ ካፋ የሚገኙ ትልልቆቹ ጅረቶች አንደ ጎደፎ (ጎጀብ) ፣ ጉማ፣ ጉሚ፣ሻርማ፣ ወሺ፣ በቆ፣ እና ባሮ ሞልተው ይሰለጥናሉ፣ አፈሩን አጥበው አፈር ይመስላሉ፣ እሰከአፋቸው ሞልተው ከተራራ አናት እየተንፎለፎሉ ፏፏቴ እየሆኑ ለጥ ያለ መሬት ላይ በዝምታ ይፈሳሉ፡፡ ምንጮች በየቦታው ይፈልቃሉ፡፡ እናም በካፋ ጊዜው ከፍተኛ የዝናብ ፍሰት እና ጎርፍ የሚበረታበት እንደመሆኑ ለገበሬው ዘር የሚዘራበት እና አረም የሚያርምመበት ወቅት ይሆንለታል፡፡ በክረምት የእርሻ መሬቶች በጠል ዝናብ ይረካሉ፡፡
የካፋ ህዝብ ህይወቱ የተመሰረተው በግብርና ስራ ላይ በመሆኑ በክረምት ገበሬዎች ማሳዎቻችውን በዕጽዋት አዝርዕትና አትክልት በአረንጓዴ የሚሸፈኑበት ወቅት ነው፡፡ እናም ክረምቱን ተከትሎ ባተዘጋጀው መሬት ላይ ከሃምሌ አምስት ጀምሮ መዘራት ይጀምራል፡፡
የካፋ ህዝብ የመሽቀሮ አዲስ ዓመት ከገበሬው የእርሻ ስራ ጋር የተያያዙም እንደሆነ በባህሉ ላይ የተደረጉት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በካፋ ማህበረሰብ አዲስ ዓመት መለያው ከመዝራት፣ ከእድገት እና ከመኸር ዑደት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል፡፡
የአዲስ ዓመት አቆጣጠር ከገበሬው የእርሻ አመራረት ባህል እና ልማድ ከክርስትና ኃይማኖት ልምምዶች ጋር ተያይዞ ከሃምሌ አንድ ጀምሮ 77 ቀናትን ተቆጥረው ሰባ ሰባት፣ ሰባ፣ ስልሳ፣ አምሳ፣ አርባ እያለ ሰባ ሰባቱ ቀን ሲያበቃ ማለትም መስከረም 12/13 የካፋ ዘመን መለወጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
እንግዲህ የአዲስ ዓመት ጊዜ ቆጣሪ (Countdown timer) 77 ቀናቶች ልክ መስከረም 12/13 ሲጠናቀቅ ገበሬው የማረስ ስራዎቹን አቁሞ እርፍ የሚነቅልበት ነው፡፡
ከ1390 ዓ.ም ወደዲህ የካፋ አዲስ ዓመት በየዓመቱ እየተከበረ እንደዘለቀ ከ1896 የሰርወ መንግስቱ መውደቅ በኋላ ትውልዱ አንደባህል እያከበረው የዘለቀው ባህላዊ የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡ አንድ ትልቅ አባት እንዳጋሩኝ ከሆነ በጷግሜን 5/6 መሆን ምክንያት 77ኛው ቀን እንዳይናጋ በካፋ ብሔር አቆጣጠር መስከረም 12 እና 13 ሁለቱ ቀን እንደ አንድ ቀን ወይም እንደ ሰባ ሰባተኛው ቀን ተደርጎ መቆጠሩን ነግረውኛል፡፡
ለምን? የሚል ጥያቄ አንስቼላቸው እንዳብራሩልኝ እዚህ ላይ ሰባ ሰባት ቀናት የተቆጠሩበት ምክንያት ከባህላዊ እምነት ጋር ግንኙነት እንዳለው አወጉኝ፡፡ የሃምሌ መጀመሪያ ላይ አንድ ተብሎ ቢጀመርም የቀኑ መቋጫ ሰባ ሰባተኛው ቀን ከቁጥር ሁሉ ገዳም እድል ያለው ቁጥር ነው አሉኝ፡፡
በዚህ ቀን ምድርንና ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ብዙ በረከትን ፣ እድልን እና ሰላምን አድሶ ለሰው ልጆች የሚለቅበት ቀን ሰለሆነ ነው የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ ዕለት የተደረገው አሉኝ፡፡
77 የሚለውን ቁጥር ባደረግሁት አጭር ዳሰሳ ጥናት በስነ ቁጥር ጥናት (Numerology) In certain numerological systems based on the English alphabet, the number 77 is associated with Jesus Christ. CHRIST is C = 3, H = 8, R = 18, I = 9, S = 19, T = 20, which added together equal 77.
አሸናፊ ⏳ አርሜ 🔶, [6/1/2025 8:20 PM]
77 has deep connections to the spiritual world, and with that comes the ability to reinvent yourself!) ተብሎ ተተርጉሞ አገኘሁት፡፡
ከዚህ ጋር ስላለው ተያያዥነት አርግጠኛ ባልሆንም የእኚህ አባት ያወጉኝ ታሪክ ምናልባት በካፋ ህዝብ ቀደምት አኗኗር ባህልና ዘይቤ የሂሳብ ዕውቀቶች ምን ያህል ርቀት ይወስደን ይሆን? የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ያስገድደኛል ፡፡ ጥናት ይፈልጋል፡፡
በካፋ ስርወ መንግስት ዘመናቶች አዲሱ ዓመት ከመከበሩ በፊት የተለያዩ ኩነቶች ይከናዋናሉ፡፡ ከነዚህም መኻከል አንዱ ንጉሱ( ማዕከላዊ መንግስት እና) የሚመሩት ሚክሬቾ (የአሁኑ የሚኒስትሮች ምክርቤት ወይም የክልል ካቢኔ ተወካዮችአምሳያ) እንዲሁም የወራፎ (የዞን፣ወረዳ፣አውራጃ፣ ክፍለሃገር) አካባቢ ገዥዎች (Local governments) ተወካዮች የሚገኙበት ዓመታዊ የስራ አመራር ግምግማ ነው፡፡ ለግምገማው ቅድመ ዝግጅት ለመስክ ምልከታ ንጉሱ በተለያዩ ጊዜያቶች ወደ እያንዳንዱ አካባቢ በአካል በመውረድ ያለውን ተጨባጭ አፈጻጸም ይመለከታሉ፡፡ ጎደ ቡሾ በመባል የሚታወቀው የመረጃ እና ጸጥታ ሃላፊም በራሱ መስመር አስፈላጊውን ቅድመ ስለላ በማድረግ የራሱን ምልከታ እና አስተያየት ለንጉሱ ያቀርባል፡፡ ማዳላት የሚባል ነገር ነውር ነው፡፡ በሃቅና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት ጥረቶች ሁሉ ይደረጋሉ፡፡ በዚህም የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ መሪዎች ይሸለማሉ፣ ደካማ አፈጻጸም ያመጡ መሪዎችም ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ይደረጋል፡፡ አዲሱ ዓመት ሹም ሽር ተደርጎ በአዲስ ኃይልና አመራር ዝግጅት ይደረጋል፡፡ ሁለተኛው ነገስታቶቹ ለበዓሉ አከባበር ድምቀት ቀደም ብሎ ለእስረኞች ምህረት ይሰጣሉ፡፡ሶስተኛው ገራሚ ትዕይንት በዋዜማው የሚደረግ የቀደሙ ነገስታቶችና አርበኞች በዋዜማው የሚደረገው መታሰቢያ ስነስርዓት ነው፡፡
አሁን ቦንጋ ከሚገኝበት በ60 ኪ.ሜ ርቀት ጠሎ ልዩ መጠሪያው ሾሾ ሞጎ ተብሎ በሚጠራው የነገስታት መካነ መቃብር (Kings Sanctuary) ቦታ ላይ ላረፉት 18 የቀደሙ ነገስታቶች እና አርበኞችን መታሰቢያ በማኖር ይጀመራል፡፡ ዝግጅቱ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ስርአቶች ያኔ በሰማያዊ፣ ነጭ ፣ እና ቀይ አልባሳት በተዋቡ በጦር፣ ጋሻና ጎራዴ በታጠቁ ፈረሰኞችና ሰረገላዎች አጀብ ይደምቃል፡፡ (አሁን የሀገር መሪዎችና ታላላቅ ሰዎችን ለማክበር በፓሬድ ግራውንድ ላይ እንደሚደረጉ ፌስቲቫሎች ማለት ነው)፡፡
ይህ የዋዜማው ክንውን በተደረገ ማግስት አዲሱ ዓመት እንዲከበር ይበሰራል፡፡ በሚቀጥለው ቀን ማለዳ ጸሃይ በምትወጣበት ሰዓት አካባቢ ከንጉሱ መቀመጫ ቦታ በሁሉም የካፋ ግዛት አዲሱ ዓመት መግባቱን የሚገልጹ የንጉሱን የመልካም አዲስ ዓመት ምኞት መልዕክቶች ይተላለፋሉ፡፡ እንዴት የሚለው ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ስርወ መንግስቱ መልዕክቶችን በድምጽ የሚያስተላልፉበት ከአንድ እስከ ሁለት ኪ.ሜ ርዝመት ባላችው ቦታዎች ላይ በተቀመጡ ከቀረሮ ቀይም ዋንዛ ተሰርስረው የሚሰሩ ሆኮ በመባል የሚታወቅ ቴክኖሎጂ!! ሶስት ጊዜ ተደብድቦ (Ringing) የሰውዬው ስም እየተጠራ መልዕክቱን ለሚቀጥለው ሰው ያስተላልፋል፡፡ በቅብብሎሽ ለሰሚው ይተላለፋል፡፡ የተራራ አናት ላይ ስለሚቀመጡ ድምጹ ያለንም ግርዶሽ በቀላሉ ያስኬዱታል፡፡ የካፋ ግዛት በ12 ቀለበት የተቀጣጠለ በአማካይ በሁለት ኪ.ሜ በተቀመጡ ጣቢያዎች (ሆኮ) ከ1000 እስከ 2000 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የመገናኛ ኔትውርክ እንዳለው ይህም ከወራሪ ለመከላከል ግብር ለማሰብሰብ ወረርሸሽኝ ሲመጣ ለማሳወቅ ይጠቀሙት ነበር፡፡ እናም በዚህ የመገናኛ ዘዴ በግማሽ ቀን ውስጥ በሁሉም የካፋ ግዛት አካባቢዎች ይዳረሳል፡፡ ህዝቡም ዘመኑ በይፋ እንደተለውጠ ያውቃል፡፡ ዛሬም ድረስ የተለመዱት የድግስ ስነ ሰርዓቶች ይከናወናሉ፡፡
የመሽቀሮ በዓል በኢትዮጵያ የማይዳሰሱ ተብለው ከተለዩ ሀገራዊ ቅርሶች መኻከል በየዓመቱ የመስቀልንና ዓዲስ ዓመት ተደርቦ የሚከበርበት ታላቅ ባህላዊ ውርስ ነው፡፡ በካፋ ተወላጆች ዘንድ መሽቀሮ የሚናፈቅ የበዓላት አውራ ነው፡፡ በተለያዩ ቦታ የሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች በዕለቱ ከያሉበት ተሰብስበው ቤተሰብን የሚጎበኙበት በልዩ ልዩ ማህበራዊ ክንዋኔዎች፣ ስነ ስርዓቶችና ፌስቲቫሎች በድምቀት ሲከበር ቀልብን ይስባል፡፡
የካፋ አዲስ ዓመት ሲወርድ ሲወራረድ ዛሬ ያለነው ትውልድ ደርሶ መከበሩን ቀጥሏል፡፡ በማሽቀሮ ህዝቡ በህብረት ይዘፍናል፣ ይጨፍራል፣ ግጥም ይገጥማል፣ ይሸልላል፡፡ ባህላዊ መሪዎች ትርኢት ያሳያሉ፡፡ በማሽቀሮ በህዝቡ ዘንድ ፈጣሪውን በመፍራት እና በማክበር የሚተሳሰብበት ፣ የፍቅርና የወዳጅነት መንፈስ የሚጎለበትበት ጊዜ ነው፡፡ በማሽቀሮ የተለያዩ የቤተሰብ አባላት ይገናኛሉ፣ ዘመድ ዘመዱን ይጎበኛል፣ በጋብቻ የተዛመዱ ቤተሰቦች ይጠያየቃሉ፡፡
ማሽቀሮ በካፋ ህዝብ ዘንድ ህዝባዊ የሆኑ ታሪኮች የሚወሱበት፣ ባህል የሚከበርበት የአዲስ ዓመት መለያ ብቻ ሳይሆን የክርስትና እምነት መለያ ከሆነው የመስቀል በዓል ጋር ተሰናስሎ የሚከበር ድንቅ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣የፍቅር፣ የልማት፣ የአብሮነት፣ የተስፋ፣ የጽናት፣ አርበኝነት፣ እምነት መግለጫ ነው፡፡
ከቡና መገኛዋ ካፋ ምድር በመንፈስ ሆኜ እንኳን ለካፋ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ስላችሁ አዲሱ ዓመት ለሀገራችን የሰላም፣ የልማት፣ የፍቅርንና ፍጹም የምንረጋጋበት ዓመት እንዲሆንልን ከልብ ከመመኘት ጭምር ነው!!!
ስላም ሁኑ ኃመተኃማ
አሸናፊ ⏳ አርሜ 🔶
Visit_Bonga_visit_Bonga