Amhara Tourism Attractions

Amhara Tourism Attractions Tourism sites are disclosed here

ሻደይ ፣አሸንድየ እና ሶለል ደርሷል
24/07/2025

ሻደይ ፣አሸንድየ እና ሶለል ደርሷል

በደሴ ከተማ Diamond Luxury የተሠኘ ሆቴል ተመርቋል።ሆቴሉ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎችን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በቱሪዝም ዘርፉ የጎላ ድርሻ ይጫወታል።
20/07/2025

በደሴ ከተማ Diamond Luxury የተሠኘ ሆቴል ተመርቋል።
ሆቴሉ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎችን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በቱሪዝም ዘርፉ የጎላ ድርሻ ይጫወታል።

የወል ተራራ‼      የወል አረጀ አሉ የወል ምን ያረጃል ፤      ሠባት አሜሪካ ባንድ ቀን ይፈጃል ።     የወል ተራራ ከባህር ጠለል በላይ 3960 ሜትር ከፍታ ያለው ከወሎ መዲና ከሆነ...
29/06/2025

የወል ተራራ‼

የወል አረጀ አሉ የወል ምን ያረጃል ፤
ሠባት አሜሪካ ባንድ ቀን ይፈጃል ።
የወል ተራራ ከባህር ጠለል በላይ 3960 ሜትር ከፍታ ያለው ከወሎ መዲና ከሆነችዉ ደሴ ከተማ ወደ ምዕራብ ወሎ አቅጣጫ በገራዶ በኩል ስንሄድ በደሴ ዙሪያ ወረዳ በጉጉፍቱ 036 ቀበሌ የሚገኘው ሲሆን እንዲሁም ተራራዉን የወረኢሉ ወረዳዉ ደኙ 014 ቀበሌ የሚጋራዉ ነው ለሁለቱም ወረዳዎች እንደ ድንበር ሁኖ ያገለግላል ።

ከደሴ 40 ኪሎ ሜትር ከምትርቀዉ ጉጉፍቱ ከተማ በግምት አንድ ኪሎ ሜትር ወደ ካቤ መስመር በሚያስኬደዉ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ተራራው በምዕራብ ወሎ ዉስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ቦታዎች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ በዚሁ አካባቢ የሚገኙትን አብዛሀኛዎቹን አካባቢዎች ከየወል ተራራ ላይ ሁኖ ከአልብኮ ምልስ እስከ ወረኢሉ እና ለገሂዳ እንዲሁም ለጋምቦ ድረስ እና በእነዚህ ዉስጥ ያሉ ሌሎች ትንንሽ መንደሮችና ከተሞችን ማየት ይቻላል እንዲሁም በማታ አዲስ አበባ ከተማን ማየት ይቻላል ።

ስለ ተራራው በስሱ ይህን ካልኳችሁ ተራራው ብዙ ግልጋሎት እና ታሪክ ያለው ነው አንድ ሁለቱን ልንገራችሁ ተራራው አናት ላይ እንደ ዛሬው ተንቀሳቃሽ ስልክ ሳይመጣ ለምዕራብ ወሎ የቤት ስልክ ማቀባበያ ( ማይክሮዌቭ ) ተራራው ጫፍ ላዬ በመግጠም ሲያገለግል የነበረ እና አሁንም እያገለገለ ያለ ነው እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚደርጉ የተለያዩ የተለያዩ እንቅስቃሴወች እያደረገ ሲሆን በታሪክ እንዲሁ በ 1940 ዎቹ አካባቢ አንዲት ሠባት አሜሪካውያን የያዘች አውሮፕላን ጉም ሸፍኖት ተገልብጣ ሠባቱም አሜሪካውያን ወዳው ሂወታቸው ሲያልፍ በዚህ የተነሳ

የወል አረጀ አሉ የወል ምን ያረጃል ፤
ሠባት አሜሪካ ባንድ ቀን ይፈጃል ። ተብሎ ተገጥሟል ።

እንዲሁም በአካባቢዉ ከፍተኛ የበግ እና ወተት ተዋፅዖ ምርት ያለ ሲሆን ለጉብኝት ብትመጡ ጉጉፍቱ ላይ እኔ ነኝ ያለ እርጎ ጠጥታችሁ ጦስኝ የበላ በግ ጥብስ በልታችሁ ትመለሣላችሁ ።
#ኢትዮጲስ
Wasu Mohammed - Mereja

ሎጎ ሀይቅ
25/06/2025

ሎጎ ሀይቅ

የጉና እጅግ ልዩ ተፈጥሯዊ ውበት!
02/06/2025

የጉና እጅግ ልዩ ተፈጥሯዊ ውበት!

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የቅድስት ፃድቃኔ ማርያም  አመታዊ ክብረ በዓል ይህን ይመስላል
29/05/2025

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የቅድስት ፃድቃኔ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል ይህን ይመስላል

የላሊበላ መንገድ ውብ ገፅታ
29/05/2025

የላሊበላ መንገድ ውብ ገፅታ

ተድባበ ማርያም! ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ገዳም ከክርስቶስ ልደት በፊት በዘመነ ብሉይ በቀዳማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በ982 ዓመተ ዓለም ተመሠረተች፡፡በኢትዮጵያ መስዋዕት ...
10/05/2025

ተድባበ ማርያም!

ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ገዳም ከክርስቶስ ልደት በፊት በዘመነ ብሉይ በቀዳማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በ982 ዓመተ ዓለም ተመሠረተች፡፡

በኢትዮጵያ መስዋዕት ኦሪት ከተሰዋባቸዉ አክሱም ጽዮን፣ መርጦ ለማሪያም እና ጣና ቂርቆስ ጋርም ትመደባለች፡፡ በአመሠራረትም ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ ሁለተኛዋ ባለታሪክ ደብር ናት፡፡

ገዳሟ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአማራ ሣይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ሰሜናዊ ምሥራቅ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይም ትገኛለች፡፡

በተድባበ ማርያም ከ300 በላይ የብራና መጽሐፍት፣ ገድሎች፣ ስዕሎች፣ የነገሥታት ዘውዶች፣ ወንበር እና አልባሳት፣ የአጼ ገላውዲዎስን ጨምሮ የነገሥታት አጽም፣ የጥንት ነገሥታት የጦር መሳሪያዎች ይገኛሉ፡፡

የበግ ምስል እና የተቆለመለመ የበግ ቀንድ ያለበት መስቀልም ይገኛል፡፡ መስቀሉ የሚያንፀባርቅ ሲኾን ከምን አይነት ማዕድን እንደተሰራ አይታወቅም፡፡

አጼ ካሌብ ከደቡብ አረቢያ ዘመቻ ሲመለሱ በስለት የሰጡት ጋሻ በቦታው እንደሚገኝ መዛግብት ይናገራሉ፡፡

ከአንድ ሺህ ያላነሱ በአክሱም ዘመነ መንግሥት የተጻፉ የብራና ጥንታዊ መጽሐፍት ይገኛሉ፡፡

በአረበኛ እና በግዕዝ የተጻፉ መጻሕፍት፣ ወንጌል ዘወርቅ እየተባለ የሚጠራ ትልቅ የወርቅ ጉብጉብታ ያለበት የወንጌል መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሉቃስ እንዳሳላት የሚነገርላት የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕለ አድኖ፣ ባለ ሦስት ተከፋች የገበታ ስዕል እና ጥንታዊ ሥነ ጥበባዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡

በተድባበ ማርያም በርካታ ጥንታዊ የእጅ እና የመጾር መስቀል እና ሌሎች በርካታ ቅርሶች እንደሚገኙም መረጃዎች ይናገራሉ፡፡

እነዚህ ቅርሶች በሙሉ በአመት አንድ ጊዜ በግንቦት 1 ቀን ወጥተው ለእይታ ይቀርባሉ።

08/05/2025
የአማራ ክልል ፕሬዝደንት በአዊ ባህል አልባሳት ደምቀው ታይተዋል። ባህልን ማነቃቃት ተገቢ ነው።
08/05/2025

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት በአዊ ባህል አልባሳት ደምቀው ታይተዋል። ባህልን ማነቃቃት ተገቢ ነው።

የኮምቦልቻ ከተማ የኮሪደር ልማት እየተሳለጠ ይገኛል።
04/05/2025

የኮምቦልቻ ከተማ የኮሪደር ልማት እየተሳለጠ ይገኛል።

Address

Debra Markos

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Tourism Attractions posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category