24/10/2021
ኢ ፓስፖርት ምንድን ነው? ማይክሮ ችፕ የተቀበረለትን ፓስፖርት ሰምተዋል???
ኢ ፓስፖርት Electronic Passport በሌላ ስሙ Biometric Passport ይጠራል። ይህ አይነት ፓስፖርት መደበኛ ፓስፖርት የያዘውን ነገር በሙሉ ከመያዙም በላይ ማይክሮ ቺፕ Microprocessor Chip የተገጠመለት ነው። በዚች በተገጠመችም አነስተኛ ቺፕ አማካኝነት ዳታ ከዳታ ቤዝ ማውጣት እዲቻል ያስችላል። ይህም ቲክኖሎጂ ስራን ያቀላጥፋል፤ በፓስፖርት ላይ ያለውን ማጭበርበር እና ወንጀል የቀንሳል ተብሎ ይታመናል።
ለምሳሌ፦ አንድ eVisa ያዘዘ(Order ያረገ) ሰው ፓስፖርቱ ብቻ በመያዝ የኮንፊርሜሽን ስሊፕ ወረቀት መያዝ ሳያስፈልገው ፓስፖርቱን በስካነር ስካን በማስደረግ በ ኢቪዛ ያለውን ፍቃድ (ያዘዘውን ኢቪዛ) ማሳየት ይችላል ማለት ነው።
ባዮሜትሪክ ፓስፖርት (ኢ-ፓስፖርት) በፎቶ እንደሚታየው ከታች በኩል የማይክሮ ቺፕ ምልክት (PASSPORT ከሚለው ስር) ስላላቸው በቀላሉ መለየት ይችላሉ።
በሚቀጥሉት ፖስቶች ላይ ስለ Schengen Visa፣ ስለ USA ቪዛ እና ዜግነት እንዴት እንደሚገኝ እንጽፋለን። ስለዚህ LIKE, SHARE እና Follow አድርገው ይቆዩን።