11/02/2026
(ኡሾ)
ማለት ማየት ማለት ሲሆን የሙሽሪት ዘመዶች ከጋብቻ በኋላ ልጅቷን በአካል ማየትና ድንግልናዋን ለማረጋገጥ ሴቶች ተመልምለው ወደ ልጅ አባት ቤት የሚከድቡት ሥርዓት ነው። እነዚህ ከቤተሰብ የመጡ ሴቶች ሙሽራውን ወደ አንድ ለየት ባለ ቦታ ጠርተው የልጅቷን አጠቃላይ ሁኔታ ይጠይቃሉ። በጌዴኦ በሔር ጋብቻ ቅቤ የምትጠጣው ድንግል ብቻ ናት። ድንግል ካልሆነችና ቅቤ ከጠጣች ሀጢአት ነው ተብሎ ይታመናል። በዚህን ጊዜ ሙሽራው ስለ ድንግልናዋ ሲጠየቅ እሷን ጠይቋት እኔ አላውቅም በማለት መልስ ይሰጣል። ምክንያቱም ሙሽሪት ስለሁኔታው በራሷ ድንግል ነኝ ብላ ለመናገር ስለምትፊራ ዝም ትላለች። ያም ሆነ ይህ ባሏ(ሙሽራው) ተደጋግሞ ተጠይቆ መልስ ሳይመልስላቸው Uushsho ከመጡ ሴቶች መካከል ወደ አንዷ ሄዶ ይቀመጣል። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላ ልጅቷ ድንግል ስለመሆንዋ በይፋ ለመጡት ሴቶች ይገልጽላችዋል። ስለ ድንግልናዋ ከሙሽራው አንደበት በመነገሩ ደስ ይላችዋል። ከሙሽራው አንደበት መልስ የሚጠባበቁትና የሚጨነቁላትም #ክብሯ፤ #ሞገሷ ድንግልናዋ የመኖሩ ጉዳይ በመሆኑ እሷም ወላጆችዋን እንዳኮራች ዘመድ አዝማድዋ ይደሰታል። ጥሩ ፀባይ ያላት ልጅ መሆንዋ ይረጋገጥላታል። ወላጆችዋ በጥሩ ሁኔታ እንዳሳደጓትና ምስጋና እንደሚገባቸው ይወራላታል። ከዚያም ተሰብስበው የመጡ ሴቶች መልሱን ለሙሽሪት ቤተሰቦች ተመልሰው ያበስራሉ። በዚያም ደስታና ፈንጠዚያ ይሆናል። ሴቶችዬ ይህን እየሰማችው ከማንም ጋር አትከሰከሱ እሺ ይህ የስሜት ጉዳይ ሳይሆን የክብር ጉዳይ ነው።
ከኡሾ ሥርዓት የሚቀጥለው (ሃፋ) ሥርዓት ነው...
#ይቀጥላል...✍️
MULUNEH