እናስተዋውቅዎ

እናስተዋውቅዎ ይህ በAbaaya Wudi'a Foof FB አካውንት ላይ የተከፈተው እናስተዋውቅዎ የ FB ገጽ በህጋዊ መንገድ የተቋቋሙ የግልና የመንግስት ድርጅቶችን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ ባህላዊና ዘመናዊ ዝግጅቶችን በክነጥበባዊ ከሽኖ ያስተዋውቃል።

  ዳኤ ሁሉሽም ወደተግባር : ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር የዲላ ከተማ የአስፓልት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አበባየሁ ታደሴ (ዶ/ር) አሳሰቡዲላ፡ግንቦት፣25/201...
02/06/2026


ዳኤ ሁሉሽም ወደተግባር : ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

የዲላ ከተማ የአስፓልት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አበባየሁ ታደሴ (ዶ/ር) አሳሰቡ

ዲላ፡ግንቦት፣25/2018ዓ.ም (ጌዴኦ ቴሌቪዥን)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ ከተማ አስተዳደር የታቀዱ የአስፋልት እና የኮሪደር ልማት ግንባታ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሴ (ዶ/ር) አሳሰቡ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዲላ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን የገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ልዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይም ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይ አበባየሁ ታደሴ (ዶ/ር) እንደገለጹት እስካሁን ባለው ሂደት በተቋራጩ በኩል የተደረገው ቅድመ ዝግጅትና ለአስፋልት ግንባታ የሚውል የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት አፈጻጸም መልካም የሚባል እንደሆነ አንስተዋል።

በከተማዋ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የዲላን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለሕዝቡ ያላቸው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ መሆኑን ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

በመሆኑም እነዚህ የልማት ሥራዎች በሚቀጥሉት ጊዜያት በፍጥነትና በጥራት መከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ለዚህም ከክልሉ ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ጋር በጋራ በመሥራት ግንባታዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አብድሳ ኩፎ በበኩላቸው የአስፋልትና የኮሪደር ልማት ሥራዎቹ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ተቋማቸው የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

ኢንተርፕራይዙ የተጣለበትን የማማከር፣የቅርብ ክትትልና የቁጥጥር ሥራ በትጋት እንደሚወጣ ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።

የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቶቹ ያለምንም መስተጓጎል በተቀመጠላቸው የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቁ አስፈላጊውን የቅርብ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ከንቲባው አረጋግጠዋል።

አርሰናል 1 - 0 ፒኤስጂ የመጀመሪያ አጋማሽ... ግንቦት 22፣ 2018 (እናስተዋውቅዎ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል ፒኤስጂን 1 ለ 0 እየመራ አጠ...
30/05/2026

አርሰናል 1 - 0 ፒኤስጂ የመጀመሪያ አጋማሽ...

ግንቦት 22፣ 2018 (እናስተዋውቅዎ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል ፒኤስጂን 1 ለ 0 እየመራ አጠናቅቋል።

The Big Club PSG # 1🙏
30/05/2026

The Big Club PSG # 1🙏

🚨 IT'S THE BIG DAY! 😍PSG face Arsenal today in the Champions League final to try to achieve a historic DOUBLE! 🇫🇷🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿...
30/05/2026

🚨 IT'S THE BIG DAY! 😍

PSG face Arsenal today in the Champions League final to try to achieve a historic DOUBLE! 🇫🇷🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿🤩

PSG can make history this Saturday May 30! ❤️💙

Dilla University Hosts Doctoral Research Defense ===========*************===========May 20, 2018 E.C (Let us promote)  T...
28/05/2026

Dilla University Hosts Doctoral Research Defense
===========*************===========

May 20, 2018 E.C (Let us promote)

The College of Agriculture and Natural Resources at Dilla University held a doctoral research defense for Tigistu Gezahagn, a lecturer in the Department of Natural Resource Management. The event took place at the university’s Nebaru campus seminar hall, in the presence of internal and external examiners, advisors, faculty members, family, and other stakeholders.

The dissertation, titled “Potential of Indigenous Agroforestry Practice to Climate Change Adaptation and Livelihood Diversification in the Gedeo Zone, Southern Ethiopia Rift Valley Escarpment,” was evaluated by a panel that included Dr. Firezer Alemu, Director of Academic Programs, and Dr. Samson Hailemariam, Dean of the College of Agriculture and Natural Resources, alongside other faculty representatives.

During the defense, it was highlighted that the study scientifically examined traditional agroforestry systems and conservation practices passed down through generations in the Gedeo Zone. The research demonstrated how indigenous knowledge can be harnessed to address challenges such as population growth, human pressure, and climate change, and identified future directions for sustainable resource management.

Evaluators emphasized that the dissertation offers valuable contributions to climate resilience and livelihood diversification and reflects the growing environmental awareness among younger generations.

The ceremony concluded with the candidate's gowning, marking a significant academic achievement for Tigistu Gezahagn and a proud moment for all

"አሪቲ" (Artemisia) በኢትዮጵያ በስፋት የሚገኝና በባህላዊ ሕክምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ተክል ነው። በሳይንሳዊ ስሙ Artemisia afra በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ጠንካራ መዓዛና...
28/05/2026

"አሪቲ" (Artemisia) በኢትዮጵያ በስፋት የሚገኝና በባህላዊ ሕክምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ተክል ነው።

በሳይንሳዊ ስሙ Artemisia afra በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ጠንካራ መዓዛና መራራ ጣዕም አለው።

የአርቲ ምንነትና ጥቅሞች፦

👉 የጤና ጥቅሞች

* ለጉንፋንና ለሳል፦ አሪቲን በሙቅ ውሃ በመዘፍዘፍ ትንፋሹን መታጠን ወይም በትንሹ መጠጣት ለጉንፋን፣ ለሳልና ለሳይነስ መፍትሔ እንደሆነ ይታመናል።

* ለሆድ ህመም፦ የሆድ መቆራረጥንና የምግብ አለመፈጨት ችግርን ለማስታገስ ይረዳል።

* ወባን ለመከላከል፦ አሪቲ በውስጡ "አርቴሚሲኒን" (Artemisinin) የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው፣ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለማከም በሚዘጋጁ ዘመናዊ መድኃኒቶች ውስጥ እንደ ዋና ግብዓት ያገለግላል።

* ተባይን ለመከላከል፦ ጠንካራ ሽታ ስላለው ቁንጫን፣ ትንኝንና ሌሎች ነፍሳትን ለማራቅ በቤት ውስጥ ይነሰነሳል።

👉 የአመራረት ዘዴ

* ተስማሚ አካባቢ፦ አሪቲ በማንኛውም የአየር ንብረት (ከቆላ እስከ ደጋ) በቀላሉ ሊበቅል ይችላል።

* አተካከል፦ ብዙውን ጊዜ ከግንዱ በመቁረጥ (Cutting) በቀላሉ መትከል ይቻላል። አንዴ ከጸደቀ ብዙ ውሃና እንክብካቤ አይጠይቅም።

* አሰባሰብ፦ ቅጠሎቹና ቀንበጦቹ በማንኛውም ጊዜ ተቀጥፈው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለረጅም ጊዜ እንዲቆይም ጥላ ባለበት ቦታ አድርቆ ማከማቸት ይቻላል።

👉 ማወቅ ያለብዎት ጥንቃቄ

* አሪቲ በጣም መራራና ኃይለኛ በመሆኑ በብዛት መጠጣት የለበትም።

* በተለይ ለነፍሰ ጡር እናቶችና ለሚያጠቡ ሴቶች ከመውሰዳቸው በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

ጠቃሚ ምክር፦ አሪቲን በከብቶች በረት ዙሪያ መትከል የእንስሳቱን በረት ከነፍሳትና ከመጥፎ ሽታ ለመከላከል ይረዳል።

VIa AD

 #ማንችስተር-ዩናይትድ-ይችላል!ማንችስተር ዩናይትድ በ6.6 ቢሊዮን ዶላር የዓለማችን ሁለተኛው ውድ ክለብ ሆነ ​  I የእንግሊዙ ታላቅ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ በ6.6 ቢሊዮን ዶላር ግምት...
27/05/2026

#ማንችስተር-ዩናይትድ-ይችላል!
ማንችስተር ዩናይትድ በ6.6 ቢሊዮን ዶላር የዓለማችን ሁለተኛው ውድ ክለብ ሆነ

​ I የእንግሊዙ ታላቅ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ በ6.6 ቢሊዮን ዶላር ግምት በዓለማችን ላይ ካሉ የእግር ኳስ ክለቦች በክብርና በገበያ ዋጋው ሁለተኛው ውድ ክለብ መሆኑን ይፋዊ መረጃዎች አመልክተዋል። ክለቡ ባለፈው የውድድር ዓመት 834 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን፣ ይህም ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውጪ በነበረበት ወቅት ጭምር ያስመዘገበው በመሆኑ ክለቡ አሁንም በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ትልቅ የፋይናንስ መዋቅርና የደጋፊ መሠረት እንዳለው ማረጋገጫ ሆኗል።

​በታዋቂው ፎርብስ (Forbes) መጽሔት ይፋዊ መረጃ መሠረት፣ ስፔኑ ሪያል ማድሪድ በ6.75 ቢሊዮን ዶላር አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በ6.6 ቢሊዮን ዶላር በቅርብ ርቀት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ክለቡ በአውሮፓ መድረክ ላይ የሚጠበቀውን ያህል ውጤታማ ባልሆነባቸው ዓመታትም እንኳ፣ ከማስታወቂያ፣ ከስፖንሰርሺፕ እና ከስታዲየም ገቢዎች ያገኘው ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት በገበያ ላይ ያለውን ዋጋ ሊያሳድግለት ችሏል። በተለይም በቅርቡ ሰር ጂም ራትክሊፍ በክለቡ ላይ ያደረጉት ከፊል ባለቤትነት ኢንቨስትመንትና የተጀመሩት አዳዲስ የአወቃቀር ለውጦች ለክለቡ የንግድ ዋጋ መነቃቃት ተጨማሪ ጉልበት መሆናቸው በዘርፉ ባለሙያዎች ተገልጿል።

ምርጫው 8 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በምርጫ ካርድዎ የሀገርዎን መጻኢ ዕድል ለመወሰን ዝግጁ ነዎት?በድምፅዎ ዴሞክራሲን በማፅናት በብልፅግና ጉዟችን ላይ ጉልህ አሻ...
24/05/2026

ምርጫው 8 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በምርጫ ካርድዎ የሀገርዎን መጻኢ ዕድል ለመወሰን ዝግጁ ነዎት?

በድምፅዎ ዴሞክራሲን በማፅናት በብልፅግና ጉዟችን ላይ ጉልህ አሻራዎን ያሳርፉ!

የህይወት ሂሳብ፡ ለጥላቻ ጊዜ የለንም!ብዙ ጊዜ "ህይወት አጭር ናት" ስንል እንሰማለን እኛም እንናገራለን ነገር ግን ይህች አጭር የተባለች ህይወት እንዴት እያለፈች እንደሆነ ቆም ብለን የምና...
18/05/2026

የህይወት ሂሳብ፡ ለጥላቻ ጊዜ የለንም!
ብዙ ጊዜ "ህይወት አጭር ናት" ስንል እንሰማለን እኛም እንናገራለን ነገር ግን ይህች አጭር የተባለች ህይወት እንዴት እያለፈች እንደሆነ ቆም ብለን የምናስተውል ስንቶቻችን ነን? የሚገርመው ግን፣ህይወት አጭር መሆኗን እያወቅን፣እንደ ዘላለም ነዋሪ በመመካት ጊዜያችንን ባልባሌ ነገር ስናባክነው፣በክፋትና በጭቅጭቅ ስንወጠር ማየቴ ነው።እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ፤ህይወት አጭር ስለሆነች ነው ችላ ብለን በከንቱ ማሳለፍ ያለብን ወይስ አጭር ስለሆነች ነው በእያንዳንዱ ደቂቃ ቁምነገር መሥራት ያለብን? እንደ እኔ እምነት፣ ህይወት እጅግ አጭር ስለሆነች እያንዳንዷን ሰከንድ በፍቅር፣ በይቅርታ፣ በመተሳሰብና በመረዳዳት ልናሳልፋት ይገባል። ምክንያቱም ነገን ለመኖር ዋስትና የለንም፤ ለጥላቻና ለቂም የምናባክነው ትርፍ ጊዜም የለንም።የህይወትን ሂሳብ እስኪ በዝርዝር እንመልከተው። ሺህ ዓመት የምንኖር ብንሆን ኖሮ፣ አንድ መቶ ዓመት ብናባክን "ዘጠኝ መቶው ይበቃኛል" ልንል እንችል ነበር። መቶ ዓመት እንኳን በርግጠኝነት የምንኖር ብንሆን፣ሰላሳውን ዓመት በከንቱ ብናሳልፈው "ሰባው ይበቃኛል" ልንል እንችል ይሆናል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው።
በአሁኑ ዘመን "ኖረ" ተብሎ የሚነገርለት ሰው ቢበዛ 70 ዓመት ነው። ይህንን 70 ዓመት ደግሞ በዝርዝር ስናየው ያስደነግጣል፦
✅ ከ70ው ዓመት ግማሹን (35 ዓመቱን) የምናሳልፈው በእንቅልፍ ነው። ቀሪው 35 ዓመት ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
✅ ከዚህ ላይ ቢያንስ 10 ዓመቱን ለልጅነት አለማወቅና ለጨዋታ ቀንሱት፤ ቀሪው 25 ዓመት ነው።
✅ ከ50 ዓመት በኋላ ያለውን የድካምና የሽበት 20 ዓመት ቀንሱት፤ የቀረችን የወጣትነትና የጥንካሬ ጊዜ 5 ዓመት ብቻ ናት!
አስቡት! ይህች አምስት ዓመት ደግሞ ለሻወር፣ ለሽንት ቤት፣ምግብ ለመብላት፣ መንገድ ላይ በትራፊክ ለምናሳልፈው ሰዓትና ለተለያዩ ትናንሽ ጉዳዮች ስትከፋፈል፣ በእውነት ለቁምነገር የምትሆን ምን ያክል ጊዜ አለችን? ህይወታችን እንዴት ያለች እጅግ አጭርና የምትፈጥን ናት!ታዲያ በዚህች ቅጽበት በምትጠፋ ህይወት ውስጥ ለምን እንቀናናለን? ለምንስ እንተላለፋለን? ጥላቻ፣ ቂም፣ ወሬና ክፋት ለዚህች አጭር ህይወት ይገባታልን? በፍጹም!
ስለዚህ ወገኖቼ፣ዛሬ ቆም ብለን እናስብ ፍቅር፣ሰላም፣ አንድነትና መደራረግ ከምንም በላይ ትልቅ ነገሮች ናቸው። እኔ ከዛሬ ጀምሮ ማንንም ላለማስከፋት፣ በሰው ልብ ላይ ጠባሳ ላለማሳረፍ ቃል እገባለሁ።ከዛሬ በፊት በንግግሬም ይሁን በድርጊቴ ያስቀየምኳችሁ፣ ልባችሁን የሰበርኩባችሁ ካላችሁ፣ እባካችሁ በፈጣሪ ስም ይቅርታ እንድታደርጉልኝ እማጸናለሁ።
ሕይወት ብድር ናት፤ ነገ ተመላሽ ነን። ዛሬ ላይ ስንኖር ግን ክፉን በደግነት፣ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ እያሸነፍን እንኑር።በመጨረሻም ከእኛ በኋላ የሚቀረው የሰራነው መልካም ስራና የዘራነው የፍቅር ዘር ብቻ ነው።

በፍቅር እንኑር! ምክንያቱም ጊዜ የለንም!

Address

Dilla

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እናስተዋውቅዎ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share